? የመጨረሻው ዳርቻ የት ነው?!
እንኳን ደህና መጡልኝ። ? የመጨረሻው ዳርቻ የት ነው?! „አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ?“ መዝሙረ ዳዊት ፳፩ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 22.02.2019 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ። አሁን አንድ ዜና ሰማሁኝ። ዶር ለማ መገርሳ የለገጣፋው መፈናቀል እንዲቆም ማዘዛቸውናን እና ከህዝቡ ጋር ለመነጋገር መፍቀዳቸውን። እንግዲህ ነፍሰ ጃውርውያን አቶ ንጉሹ ጥላሁን እና አቶ አዲሱ አረጋ አነ ሰውር ሐዋርያቱ ከጎበኙ በኋዋላ የተሰጠ ተስፋ መሆኑ ነው። ዜናው ዕውነት ከሆነ መልካም ነው። እኔ ግን መጨረሻው ፍርጥርጥ ብሎ መታወቅ አለበት ባይ ነኝ። ብልጥ የኦሮሞ አክቲቢስቶች ቀስ ብሎ መከወን ነበር እያሉን ነው። ይህ ማለት ሙሉ ለሙሉ መደላደል ከተረጋገጠ በሆዋላ እንደማለት ነው። ያን ጊዜ 5ቱ የኦሮሞ ድርጅቶች መግለጫ ሲያወጡ ያሉትን ነው የደገሙት አሁን መሆን አልነበረበትም ብለውን ነበር። መቻል እኮ መቻል ከተሰጠው ባለመክሊት ብቻ ነው የሚገኘው … እውነት ደግሞ ቀን አይቀጠርለትም ለውጡን እንመራለሁ የሚለው ቲም ለማ ኢትዮጵያዊ ለውጥ ወይንስ የኦሮሞ ኢንፓዬር ለመገንባት ነው እዬተጓዘ ያለው? ይህ በፈጣጣው በግልጥ መንገድ ሊገለጥ ይገባል። ልክ ያጣ ነገር እኮ ነው እዬታየ ያለው። ቲም ጃዋር እኮ ስለመምራቱ ምንም አያጠራጥርም። ራስ እግሩ እኮ ህዝብ የሚያሸብር እና ስጋትን ያዘመተ ድርጊት ነው እዬተፈጸመ ያለው። ፋታ ጠፋ እኮ? ለዛውም ጉድጓዱን ህወሃትን አስቀምጦ። የሚገርመው አገር ጠቅልለው የገቡት የቆረበ ሰው ይመስል አፋቸውን ዘግተው በተረታው መስመር የተሰጣቸውን ብቻ እዬከወኑ ይገኛሉ። ድንቅ ያለኝ ደግሞ ስንት ጊዜ በሚበላው የኮሚሽን አባልነቱኝ እሰዬው ብ...