የስውሩ መንግሥት ዘመንተኞቹ በለገጣፎ።

እንኳን ደህና መጡልኝ።

የስውሩ መንግሥት
ዘመንተኞቹ በለገጣፎ።

ምንም እንኳን በለስም ባታፈራ፣ በወይን ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፣
 የወይራ ሥራ ቢጓል እርሾችም መብልን ባይሰጡ
በጎችም ከበረት ቢጠፉ ላሞችም በጋጥ ውስጥ ባይገኙ
 እኔ ግን እግዚአብሄር ደስ ይለኛል፤
በመዳህኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ።
ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯ ቁጥር ፲፰

የተባረከ አሜን ለተባረከ ትውልድ!
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ።

የለውጡ ስውር ውጋት!

·       መነሻ። 
አቶ ንጉሱ ጥላሁንና አቶ አዲሱ አረጋ በለገጣፎ ጉብኝት አደረጉ


እኔም ያልኩት እኮ ይኸው ነው። አጃን ነው የወቅቱ መሪ ነው ያልኩት። የመንፈስ ጠላፊዎቹ እነሱ ናቸው። ከዚህም ላለፈ ጉዳይ ቢያስኬድ ይቻላል። ቀድሞ መገፋት ያለበት ተገፍትሯል። ጠርጣሬ እንደሆነ አፈር ሆኗል እንደ ወጣ ቀርቷል። ሌላም ቀጣይ ይኖራል። ባለቤት የሌለው ህዝብ እዬሸኙ ዝም። 

የሆነ ሆኖ ዛሬ ፋና እንደዘገበው „ጃ“ ሲቀር „አ“ እና „ን“ ተገኝተው ጉብኝት አድርገዋል ይላል ፋና ከሰቆቃው ውቅያኖስ ጨላልፎ። ይህን ነገር እጅግ በቀደመ ሁኔታ ተቸክችኳል። አድማጭ የለም እንጂ።


የህፃናት የሰቆቃ ዕንባ የናፈቀው፤ የእናቶች የማህጸን ደም ዕንባ  ለሚያሰኘው ይህ እርካታ ነው። ጉዳዩ እና ዓላማው በዚህ መከራ ውስጥ በዚህ ጨለማ ውስጥ መከራን እዬመነዘሩ ፌስታ ነውና። የኢትዮጵያ የመፍትሄ ቁልፍ ያለው ከዚህ የጭካኔ የአራዊትነት ውስጥ ነው ልብ ከተገኜ።

ያ ጎንደር የአማራ ተጋድሎ ያን ያህል መስዋዕትንት የከፈለው ለአቶ ንጉሡ ጥላሁን አጤነት ነው። ለሳቸው ዘመናይነት ሲባል ከ80ሺህ ያለነሰ ጎንደር ሜዳ ላይ አሁንም ፈሶ ኤሉሄ ይላል። ለገጣፎ ላይ መሰሉ ተከውኗል። መሳ ለመሳ ነው በጣምራነት በቀሉ የተከወነው። 
                                            ፍቅር እስከ መቃብር!

የለብ ለብ ጉዞው ቀርቶ ከውስጥ ሆኖ ነገሮችን በርጋታ ማዬት ያስፈልጋል። ማናው አሁን መሪው? ማነው ሥልጣን ያለው? ማነው የመወሰን ሥልጣን ያለው? በማን እና በምን ሽፋን? ልብ ይጠይቃል።

የንጉሱ ጥላሁን እና አዲሱ አረጋ ምስል ውጤት
          ፍሬ ነገሩ ያለው ከዚህ ላይ ነው።

ቅንጅቱ ትክክለኛ ነው የዛሬው ማለቴ ነው እንዲህ አደባባይ ላይ ጎላ ብሎ መውጣቱ። የናፈቃቸውን አግኝተዋል አጤዎቹ። የተገባም ነው። እንዲህ ወጣ ብሎ አገር እያዬ ጸሐይ እዬሞቀ እኛው ነን ብሎ ደረትን ነፋፍቶ መኮፈስ ሆነ መከሸን የተገባ ነው። መፍትሄም አፍለቂ ከተሆነ ይታያል ...  ስለምን ጄኒራላቸው እንደቀረ ግን አልገብቶም። እሱም ቢኖር የበለጠ የጎሸው ይጠራ ነበር። የሃይል አሰላለፉም ይነጥር ነበር

አቶ ንጉሡ ጥላሁን ጎበዝ ናቸው። ኮስታራነታቸውን እና ድፈረታቸውን እውድላቸወለሁኝ። ጉብዝናቸው ግን ለራሳቸው ኢጎ ብቻ ነው። የአገር መሪ መሆን ይፈልጋሉ።  ኢጓም ናቸው። ለአገር መሪነት ግን ኢትዮጵያ አያድርግባት ነው የምለው። ለአገር መሪነት ግልጽነት ወሳኝ ነውና። እሳቸው ደግሞ እንደ እባብ መሬት ለመሬት ሄጅ ናቸው። ለውጡን እጁን ጠምዝዘው ከሥራቸው ወሽቀውታል። አሁን ለውጡ የስሞታ መናህሪያ ሆኗል። 

አቅም የለም አሁን በጎውን ዜና እራሱ እኔ ለመስማት። ያ ሁሉ ድካም፤ ያ ሁሉ ፈቅዶ መከራን ለመቀበል ለ ኦነጋውያን ትፍስህት ሳይሆን ለኢትዮጵውያን ትፍስህት ነበር። ባክኖ እንዲቀር አደረጉት ሌላ ማንም ሳይሆን አቶ ንጉሹ ጥላሁን ናቸው። አሁን በአዳዲስ ገብርዲን እና ከረባት የሚጆበኑበት ሥልጣን በነፍስ ወከፍ ሁሉም ዋጋ ከፍሎበታል። ተሰደንም አፈር ድሜ ግጠንበታል። ድምጽ አልባዎቹ የ ኢትዮጵያ እናቶች ዕንባ እንዲቆም። 

ሰው ቢሆን ስንት ደም የፈሰሰበት ለውጥ በመሰሪ ኢጎ እንዲህ አገርን ከሚያተራምሱ ኢትዮጵያን ከዚህ የሰውር የእባባ ጉዞ እጃቸውን ቢያወጡ መልካም በሆነ ነበር። ግን ጥሟቸዋል። ቀጥለውበታል።

አማራ ደግሞ የ27 ዓመት ሙሉ የሳጅን በረከት ስምዖን ነቀርሳዊ ሸክም ዘመን አልበቃ ብሎ አሁን ደግሞ በአዲስ የውስጥ አርበኛ ፍዳውን ይከፍላል። የሚነገደው በሥሙ ነው። የእኔ አይደለህም ብሎ ደፍሮ ወጥቶ መሞገት ይገባዋል - አማራ ልቡ ከሰጠው። እሳቸው ጃዋርውያን ናቸውና።
                                       ለግል ኢጎ የተሰጠ በረከት!

በዘመነ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሲከውን እንደነበረው ነው አሁንም ፊት ለፊት ሌላ በስውር ሌላ እንዲህ ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ የሚኮነው። ለዚህም ነው ህዝብ ባለቤት አለኝ ብሎ እንዳይናገር እዬተገፋ የሚገኘው። ቅጥ መጠኑ ጠፍቶ መልካም እና መልካም ያልሆኑ ነገሮችን ለመለዬት እንዳይችል እያንጨቧረቁት የሚገኙት እነሱው ናቸው የአቶ ንጉሱ ጥላሁን ቲም። 
  
እጅግ በጣም ጹሑፎች በዚህ ዙሪያ ጽፌያለሁኝ። በቅርቡ እንኳን ይህን አበክሬ ገልጫለሁኝ። „አክራሪ ብሄርተኛ“ ብቻ ነው የሚባለው ለዛ የጀርባ አጥንት ማነው ብሎ ተንታኙም፤ ፖለቲከኛውም፤ ጋዜጠኛውም ሂዶበት አያውቅም።

ይልቅ ኤስቢኤስ በጥበብ መጠይቁ በልሃ ልበልሃ ብሎት ነበር። መቼም የታዬው ነገር እንዳለም ይገባኛል ያ ብልህ ጋዜጠኛ አቶ ካሳሁን። ጋዜጠኛ አንጀት ጉበቱን አውጥቶ ግራ ቀኙን ዝርግፍግፍ አድርጎ መጪውን ጊዜ ማመላከት ካልቻለ እሱም ታዳሚ ሆኖ ብቻ ነው የሚያርፈው … 

አቶ ንጉሡ ጥላሁን በብአዴን ጉባኤ ያሰቡትን ያህል ባያሳኩም ከጉባኤ መልስ ግን ሸርሽረው ሸርሽረው የልባቸውን አድርሰዋል። አሁን ግዳጃቸውን ሲፈጽሙ ደግሞ አናት ሆነዋል።

እነ ዶር አንባቸው መኮነን ደግሞ ተወርዋሪ አጃቢ። ይልቅ ሰሞኑን አይታክቴ ተንሳፋፊው ሚ/ር ኦፌኮን አሸኮኮ አድርጎ ደግሞ የአማራ ሙሁራን የፈረደበትን ባህርዳር ላይ ንግግር እንዲደረገልት ሲያደርግ ደግሞ አይቻለሁኝ። 

ዶር አንባቸው ቢበቃው ምን አለ? እንደ አከበርነው እንደ ሳሳንለት አርፎ ቢቀመጥ። ልጠለው ትንሽ ነው የቀረኝ። አይበቃም ወይ ጅልነቱ?! አማራውንም ምን አለ ተወት ቢያደርገው? ይህን አፍዝ አደንዝዛቸውን ስብከት ቢያቆሙትስ … ሌላ ቦታ እኮ አትሞከረም አንድም  የአማራ ሊሂቅ ኦሮምያ ላይ ሄዶ ገለጣ እንዲሰጥ ... እእ?!የተከለከለ መንገድ ነው።

ወደ ቀደመው ስመለስ ለዚህ ሁሉ የቅልበሳ የመንፈስ ሂደት ያን ዲታ የፍቅር የመታመን መንፈስ ለመዝረፍ ግንዱ ዋርካው ግን አቶ ንጉሡ ጥላሁን ናቸው እሳቸውን በአገር ውስጥ ብቻ አድርጎ መመልከትም ስህተት ይመስለኛል። ሊንካቸው ክንዳም ነውና።

 የደህነነት ሰው ለመሆንም የሚችሉ ናቸው። ሃሳባቸውን ለማውጣት በራስ ጊዜ ኤዲት እዬተደረገ ተመጥኖ ነው የሚነገረው… አቶ ጃዋር መሃመድ ልኩን፤ የሚመጥነው ግራጫማ ተፈጥሮውን አግኝቷል። አሁን ገብያው ደርቷል በለውጡ ስኬት ላይ ማላታይን …
  
አንድ ነገር አዳምጥኩኝ ... ከሰሞናቱ ጠ/ሚር አብይ አህመድ መቼ እንደሆን አላውቀውም እንጂ ሥልጣኔን እንደምለቅ ነው ማለታቸውን  … ድሮስ እባብን በኪስ ይዞ ይህ ሳይታለም የተፈታ ነው። አሁን እኮ ጭንቅላቱ ውስጥ በሚገባ መቅጃ ተገጥሞለታል - ለውጡ። እሳቸው ሁልጊዜም የሚፈለጉት መንገድ ለመጥረግ ብቻ ነው።

ይብቃኝ ከዚህ በላይ አቅም የለኝም ለመጻፍ እራሱ … ያቅለሸልሻል። ለገጣፎ አራስን በግሪደር እያሳረስክ ባህርዳር ላይ የወጣት ሊቃናት ስበሰባ?! 
የአቶ ንጉሱ የትዕይንት ጠቀራ!

አዝነን አዝነን እኛም ገርጥተን ሀዘን ሆነን አረፍነው።

ዳግማዊ አባኮስትር አቶ ንጉሱ የማን ናቸው?

እውነት እራቀች!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።