አዝነን አዝነን እኛም ገርጥተን ሀዘን ሆነን አረፍነው።

አዝነን አዝነን እኛም ገርጥተን
 ሀዘን ሆነን አረፍነው።
„አቤቱ ለምን ርቀህ ቆምክ?“ ምዕራፍ ቁጥር፲፩
ከሥርጉተ©ሥላሴ
 Sergute©Selassie
 21.02.2019
ከእመ ሲዊዘርላንድ።

የnegusu tilahun ምስል ውጤት

ግራጫማ መንፈስ ዘመነ ጃዋርውያን እንዲህ አና ብሎ ሲያውጅ አዝንን አዝነን እኛም የጠለሸ ግርጫማ ሀዘን ሆነን አረፍነው ደማችንም ማቅ ለባሽ። ይህ የሆነው ደግሞ ከሐምሌው ዝምታ በኋዋላ የሆነ ነው። ከዚያ በኋዋላ የሚሆነው ሁሉ ብልጭ ድርግም በሚል ናዳና ፈገግታ የዋጀው ነበር።

በዛ የዕቀባ፤ የእግዳ ሰሞናት እንጨርሰዋለን ያሉት ነፍስን በፈጣሪ ጥበብ መትረፉ ሌላ ጥርስ አስነክሶ ሌላ ድቅድቅ ትዕይንት ቤተ መንግሥት አካባቢ ያው አፋኙ ቡድን ፈጠረ። አታስታውሱም ውዴቼ አንድ ዓለም አቀፍ የሴቶች ጉባኤ ላይ አኮ የቀድሞዋ ደልዳለ እመቤት ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ ነበር ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት። ስለምን ይህ ሊሆን ቻለ ብዬ ሁሉ ጽፌያለሁኝ በወቅቱ … ተወራራሽነት ያላቸው ሰፊ ምልክቶች ነበሩ።

ከልቤ ሳዳምጠው በነበረው ጭብጥም ወስኜ የአብይ ዲታ መንፈስ ተጠለፈ ብዬ ጣፍኩኝ። መጣፍ ብቻ አይደለም ሁኔታውን በተደሞ አስቤበትም እንዲያው ለአንድ ዕውቅ የሰብዕዊ መብት ተሟጋች ደውዬ ተናገርኩኝ። በሳምንቱ እሱ እራሱ ኢትዮጵያ መግባቱን ሰማሁኝ።

እኔ ኢትዮጵያ ለመግባት ስለመወሰኑ ምንም ዕውቅት አልነበረኝም፤ ግን መተንፈሻ ያጣው፤ ሚስጢር እንዳያወጣ ማዕቀብ የተጠለት ነፍስ እንዳለ ለሚያውቃቸው አካላት ሹክ እንዲል እና ሁኔታውን በወፍ በር እንዲከተተሉት ነበር ምኞቴ። ምክንያቱም „አክ“ ወሬ በሚል ስጋቱ ብን እንዲል ቅኖች ደግሞ ያን ጥርጣሬ ይታገሉት ስለነበር። የሆነው ግን ያ ዕውነት ነበር። ሁለት ነገር ነበር የተከሰተው።

አንደኛው ውስጥን መርዞ ማሳጣት ነበር። ያ ሳይሳካ ሲቀር ማዕቀብ መጣል። ይህ ድብልቅ ዝንቅ ገጠመኝ ባለቤት ሳያገኝ የተዘለለ ጉዳይ ነበር። ብራና ላይ እንኳን ለማዋል የደፈረ የለም። እኔ እንዲያውም ወደ አገር በሚገቡት ላይ ትንሽ አደብ ይኑራችሁ። እባካችሁ እንዳናጣችሁ እስከማለት ሁሉ ደርሼ ነበር። በሃሳብ ልትለይ ትችላለህ ጥቃቱን ግን አትፈልግም የወገንህን። ስለሆነም ጉዞው በቁጠባም ይሁን ብዬም ነበር። ሰሚ ግን የለም።

መሄዱ ብቻ አይደለም ክፋቱ ቢያንስ ይህም ሊኖር ይችላል ብሎ መጠርጠር አለመቻሉ ነበር መከራው። የመጀመሪያውን እርምጃ „ሹክሽኩታ“ ሹክ ሲል ሀሰት የሚል ማስተባበያ ተጻፈ። „ሹክሹክታም“ ሀሰት አይደለም እውነት ነው ብሎ አተመበት። በተለያዬ ሁኔታም እኔም በግል አጣራሁኝ። የሆነው የቡና ፖለቲካ ነበር።

ከዚህ ቀጥሎ ያለው እገዳው ደግሞ ጭራሹን ባሊህ ያልተባለ ጉዳይ ነበር። በዛ ሰሞን የነበሩ መላ ቅጥ ያጡ የዜና ቅንብሮች እራሱ የተዘቀዘቁ ነበሩ። በአንድም በሌላም ቤተ መንግሥት አካባቢ የሆነ ነገር እንደነበር ፍንትው አድርጎ የሚሳይ ተደሞ ነበር። እናም ሥርጉትሻ ትዝብቷን ትኮልም ነበር - በተከታታይ። ከዛ እዬተረሳ እዬተረሳ ጉዳዩ ባለቤት አልባ ሆኖ አከተመ። ሁለም ከፊቱ ላይ መድፍ ሲተኮስ ብቻ ነውና እና የሚባንነው።

ሌላው ቀርቶ ጠ/ሚር አብይ አህመድ በአለሙ የሰብዕዊ መብት አስከባሪ ጉባኤ ላይ እንዲናገሩ የተገኘው ዕድል እንዲታጠፍ ሲደረግ የጠረጠረ አልነበረም። ውጭ ሲወጡ በኦዴፓ ሰዎች ጥበቃ ሥር መሆናቸውም የሚያስተውለው የለም።

ፍትልክ የምትል ነገር ብትኖር ብዙ ነገር ይደረመሳል። በዝምታ ውስጥ ያለ የጨለመበት ጨረቃ ነው ገመናው። አሁን ጊዜውን እዬጠበቀ ውልብልቢቱን ሲያሳይ አብይ ከዳን በሚል ሌላ ወግ ተተከ። አብይ ወዶ አይደለም። ተይዟል ተጠርንፎ። ለዚህም ነበር እኮ ትዳሩን ስደት ያቆዬው፤ ያ ብልህነት ዛሬ ላይ ሰርቶ እንዴት ባለ ጥበብ ይህን ዘመን እስከ ቤተሰቡ ከሳት መንጋ አውጥቶ ሊሻገር እንደሚችል ፈጣሪ ይወቀው። ድንግለዬም ትርዳው።  

ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ ያ ቅን ታታሪ የሰብዕዊ መብት ተሟጋች የነገርኩትን አለመነበትም ነበርና እሱም አብሮ ተደመረ። እኔም አትደመር ሳይሆን ፍንጩን ለምታውቃቸው የውጭ ዜጎች ሹክ በል ነበር። መተንፈሻ ለሌለው ድምጽ መሆን ይገባ ነበር። የጽድቅ መንገድም ነው - ላወቀበት። ቢያንስ መጠርጠር እንዴት ያቅታል? የምታውቀው ጠረን ሲበረዝ እንዴት አይገባም?

ያ ወዳጄ አገር ከገባ በኋዋላ በአንድም በሌላም ቅሬታውን ሲገልጽ አዳምጣለሁኝ። ቅሬታው ግን የአብይ ካቢኔ ያቃተው ነገር አለ ነው የሚለን። እኔ መረጃውን በሰጠሁት አቅጣጫ አልተጋም። ምን አልባት ፖለቲካ ውስጥ ስላልሰራ ሊሆን ይችል ይሆናል ኢንትሪጉ ፍንትው ብሎ ሊታየው ያልቻለው።

የአብይ መንፈስ ከሀምሌ የቡና ፖለቲካ በኋዋላ ትእዛዝ የሚሰጠው ሌላ ስውር አካል እንዳለ እኔ ይረዳኛል። በጽኑም አምናለሁኝ። በተሰጠው ልክ ነው የሚንቀሳቀሰው። ለቀቅ ሲያደርጉት ዕውነተኛውን ዘና ያለ ብሩህ መንፈስ ስናይ ጠበቅ ሲያደርጉት ደግሞ የተሳቀቀውን መንፈስ እናስተውላለን። እውነቱ ይኽ ነው። አብይ መንፈሱ ሊሰራ ያሰበው፤ የተለመው ለኢትዮጵያ ይህ አይደለም፤ አልነበረምም። ፈጽሞ።

በአጭር ጊዜ ውስጥ ገኖ ሲወጣ ነገሩ ሁሉ የራሱ ወደ እግር የእግሩ ወደራስ ሆነ ኢትዮጵያን አጥበቀው በሚጠሏት ነፍሶች። ሚስጢሩ ይህ ነው። እንደሰው የአብይ መንፈስ ግድፈት ቢኖርበትም ነገር ግን ህዝብን ኢትዮጵያን የሚያስከፋ አንዳችም ነገር ይፈጽማል የሚል ጥርጣሬ ከቶውንም የለኝም። ፈጣሪም ይከፋብኛልና።

የአብይ መንፈስ ቅን ነው። የአብይ መንፈስ ታዛዥ ነው። የአብይ መንፈስ ንጹህ ነው። ንጽህናው፤ ቅንነቱ፤ የበዛ ሰው አማኝነቱ ደግሞ ልክም ደንበርም የለውም። ብዙዎች የሚሉት ነግረናችሁ ነበር የሚሉም አለ ጭንብል የለበሰ አስመሳይ ነውም ይላሉ። አዝናለሁ እኔ ስለ እነሱ።

አብይ አንድ ነፍስ ነው ያለው። ያን ነፍሱ ከተመረጠባት መጋቢት 24 ቀን 2010 ጀምሮ እንቅልፍ የተኛበት ሰዓት እራሱ ከቁጥር የሚገባ አይደለም። እንዲህ የታተረ መሪ ሙሴ  በዕድሜዬ አላዬሁም። ደከመኝ የማይል። ግን እሱ በዚህ ሲገነባ ሌላው በዛ ይንደዋል፤ ያነደዋል፤ ይደረምሰዋል።

ይህ ነፍስ በሁለት ቀን እስከ 11 ስብሰባ የሚያደርግ ከብረት ቁርጥራጭ የተሰራ ፍጥረት ነው። ህሊናውም፤ መንፈሱም ሰብዕናውም ሰውኛ እንጂ አውሬኛ አይደለም። ፈጽሞ!
መንፈሱ ግን በታሰረ በማዕቀብ በተያዘ፤ በቅደመ ሁኔታ በተቀፈደደ ሁኔታ ነው እዬሠራ ያለው። አሳሪዎቹ ቀላል አይደሉም። ይህን ደግሞ የሚያውቅለት የለም። ገልጦም እስከ ወዲኛው አይናገረውም። ከእኛ በመፈጠሩ ብቻ ነው ይህ ሁሉ መከራ እዬደረሰበት ያለው እንጂ እስካንዳንብያ ተፈጥሮ ቢሆኖ ኖሮ ወይንም ጀርመን ተፈጥሮ ቢሆን ኖሮ ምንኛ መልካም በሆነ ነበር።

ኢትዮጵያዊነትን ማጉላቱ፤ አባቶቻችን ማለቱ ለዬትኛውም የፖለቲካ ሊሂቅ አይመችም። ይህ እውነት ነው። የፕ/መራራ "የቡዳ ፖለቲካ" እኮ ይኸው ነው። የሊሂቃኑን የሴራ ልክ ያሳያል የሳቸው ቅኔ። እሳቸው እራሱ „ለማ ፊቱ ኦሮሞ ይመስላል“ ሲሉን የቡዳ ፖለቲካን እያመሳጠሩልን ነው።

ጃዋርውያን በቀላውያን ህዝቃላውያን እራሳቸውን መሪ አድርገው ያሰቀመጡ ሰዎች ናቸው። ይህን ጥሶ የወጣ፤ ሁሉም ያለው፤ አብዛኛው የሚወደው፤ አብዛኛው እምነቱን የጣለበት፤ አብዛኛው ተስፋ ያደረገው መሪ ለዛውም ወጣት ሲወጣ ሁሉም ራድ ነው የያዘው። ያልደነገጠ አልነበረም። ያልተሸበረ አልነበረም። ያላበደ አልነበረም። ሲዊዘርላንድ ጄኔባ ድረስ መጥተው ትኩረት ለማግኘት ስብሰባ ተቀምጠዋል። የሚይዙትን የሚጨብጡትን ነው ያሳጣቸው። የዛ ጥምዝ እና ጥምልልም ጉድ ነው አሁን መከራ እያመረተ ስጋትን እያጫጫነ ተስፋ ማጣትን እያቀና የሚገኘው።

ቀድሞ ነገር አቶ ንጉሱ ጥላሁን የጠ/ሚር ቢሮ አንደበት ሲሆኑ እንኳን ልብ ያለው ሰው የለውም። አንዲት ቀን በቃላቸው ኢትዮጵያ ብለው አያውቁም „አገሪቱ“ ነው የሚሉት። አሁን ከመሼ ለዛውም ሥማቸውን ሳይሆን „ጠ/ሚሩ“ ሲሉ ሰምቻለሁኝ። እሳቸው ሲናገሩ የተጨነ ስሜት ይሰማኛል።

ወደ 4 ጊዜ አማራ ክልል ጠ/ሚር አብይ አህመድ ተገኝተዋል። እሳቸው አብረው የተነሱበት አንደም ፎቶ አይገኝም። የመጀመሪያው ለማስተዋወቅ በጨረፍታ ከመታየታቸው በስተቀር። የሚዲያ ሳቦታጅም ነበረበት ጉዞው እራሱ።


አቶ ንጉሡ ጥላሁን እጅግ ነው የሚጠዬፉት የአብይን ጠ/ሚር መሆን። ወዳጃቸው አቶ አዲሱ አረጋ ናቸው የልብና የምር። አሁን ማዕከላዊ አመራር አባ ገዳ ጃዋር መሃመድ እና ከአባ ገዳ አቶ በቀለ ገርባ በሚሰጠው ትእዛዝ ሁሉም እዬሆነ ነው።

የጃዋር መሃመድ ምስል ውጤት


በነገራችን ላይ አሁን አይደለም ስሜን አሜሪካ እያሉ ነበር ሁሉም ነገር የተደራጀው። ኦሮምያ ላይ እና ፌድራል ላይ ሳንክ በቅሏለኝ። አማራ ክልል ላይ ደግሞ ዳግሚያ ትንሳኤውን የእነ አቶ ጋዱ አንዳርጋቸው ቡድን ስሜን አሜሪካ ስንብቾ ነው።

የጎንደርን መከራ የወያኔ ሃርነት ችግር የፈጠረው ብቻ አይደለም እዛው ብአዴን ውስጥ በተሟላ ሁኔታ የተቀነባበረ እና የተደራጀ ነው። ለዚህ ነው የአቶ ንጉሡ ጥላሁን ወዳጅ የሚመራው OMN ስለ ቅምናት ጉዳይ አጀንዳው የሆነው። የሚገርመው እና የሚደንቀው የብአዴን አንደበት እኮ የህውሃት ቧንቧ የሆኑት አቶ አሰማህኝ አስረስ ነው የሾሙት አቶ ንጉሡ ጥላሁን።


ሌሎቹም አዲሶቹ የበታች አካላት አይነኩም ባይ ወታዳራዊ ትእዛዝ ሰጪዎች ናቸው አዲሶቹ ንጉሳዊ ምልምሎች። ጥቂት ነፍሶች ብአዴን ላይ ቢኖሩም እነሱም ከመርዝ ብክለት ካመለጡ ነው። አንድ አንድ እያደረጉ ጊዜ እዬጠበቁ ይጨርሷቸዋል።

 አሁን ሰው የብአዴን መሪዎች አቶ ደመቀ ሞኮነን እና ዶር ገዱ አንዳርጋቸው ይመስላቸዋል። አይደለም። የብአዴን አራጊ ፈጣሪ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ናቸው። እሳቸው ናቸው ሊቀ ጳጳስ። ለዚህም ነው እኮ ኤርትራ ላይ እሳቸው ተደራዳሪ ሆነው የሄዱት። ህዝቡ ተፈርቶ እኮ ነው እንጂ ተከድኖ የሚንተከተከው ሃቅ ይህ ነው።   

ኦሮምያ ላይም ቀንጣ ነፍሶች ቅኖች ሊኖሩ ይችላሉ። ነገር ግን ሙለው በዛ አብይ እና ለማን አትንኩ ብሎ በተነሳው ጽኑ መንፈስ ውስጥ ሁሉም አለ ማለት አይቻልም። የዛ ጦሱ ደግሞ የስሜን አሜሪካው ጉዞ ነበር። ለራስ ተሰማ ናደው ሴረኞች ያን ጊዜ ክፍት ሆነላቸው። የቆሞስ ስመኛው በቀለም ህልፈት ከዚህ ጋር የሚታይ ነው። ገለባ ገለባውን ሳይሆን ምርት ምርቱን ማድመጥ ይገባል።

የቡራዩ እና የአዲስ አባባ መከራ እኮ እዛው ተቀምጠው ነው ጠ/ሚር አብይ አህመድ የተከወነው። የሻሸመኔውም እንዲሁ። የ አዲስ አባባውም እንዲሁ። ለሚዲያ እንዲበቃ ሁሉ አልተደረገም። ያ ደግሞ የመርዶ ስጦታው አልገባውም እንጂ ግንቦት 7 አገር ገባ ነው የእልሁ ቁልፍ። የአሁኑ የለገጣፎ ደግሞ የኢሳት ጋዜጠኞች አገር ገቡ ነው። ታቅዶ እኮ ነው የሚከወነው። ታልሞ እኮ ነው የሚሠራው።

እንደሰው ሰው ስለምን ከሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚ/ር በነበሩበት ጊዜ ዶር አብይ አህመድ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተነሱ ብሎ ማሰብ አይፈልግም። እሳቸው አባ ቅንዬ የሚፈለጉት ሁልጊዜ መንገድ እንዲለደሉ ብቻ ነው። መንገድ ከደለደሉ፤ ካስተካከሉ ካሳመሩ በኋዋላ አይፈለጉም።

አቶ ካሳሁን ጎፌ ከዶች ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደ ነገሩን የኦሮምያ ጽ/ቤትን እንዴት አድርገው ባጭር ጊዜ ውስጥ ከአንድ ተራ ኮንደምንዬም ቤት ወደ ቱሪስት መናህሪያ እንደቀዬሱት አስርገጥው ነግረውናል። በተጨማሪም የጽ/ቤቱን ሠራተኞች በሙሉ እንዴት ወደ አንድ ወጥ ቤተሰባዊነት እንደቀዬሩትም አብራርተውልናል።

አሁን የጠ/ሚር ቢሮም በአዲስ መልክ ነው ያደራጁት። አውሮፓ ነው የሚመስለው መሰብበሰቢያ አዳራሹ ጠረኑ እና አርቱ ሁሉ። ጥረታቸውን፤ ክህሎታቸውን ለማቅናት የማይሰስቱ፤ ፈጠራቸው ጥበባቸው ለሌለው ለመስጠት የማይሰስቱ የጠራ እና ሳቢ እና ማራኪ ብሩህ ህሊና ያላቸው ሰው ናችው። ይህም መሰናዶ ለቀጣዩ ባለተራ ነው። መንገዳቸው ተስፋ መናህሪያ እንዲሆን ነው። የጠ/ሚር አብይ አህመድ መስመር እና ምህንድስናም አለበት። ዲዛይነርም ናቸው።

ነገር ግን ከእኛ ተፈጠሩ ሐሤት እንዳይኖረን ከተረገምነው፤ እሳቸው ካለጊዜያቸው እንደ ቀደምቶች ተፈጠሩ እናም አሳራቸው በረከተ። የአብይ ዘመን መጥቆር - መክሰል ስላለበት በደቦ እዬተሠራበት ነው። የሳቸውን አቅም አንጥሮ ያወጣው ዘመን ሁሉንም ህመምተኛ፤ ሁሉንም አድመኛ አደረገው።

ትልቁ ተልዕኳቸው ቤተሳባዊነት ነው። ይህን ማክሰል ተፈለገ። ሆነም። ለራሳቸው ብቻ በሚያስቡ ሰዎች መሃከል ለህዝብ መቆርቆር እብደት ነው። መስሏቸው ነው እንጂ ፍርድና ዳኝነት የመዳህኒዓለም ስለሆነ ፍርዱን ይሰጥበታል። 

ዕንባም ሰውኛ አይደልም መልሱ እዮርኛ ነው። የእሱ ፍርድ የመጣ ዕለት ወዮ ነው! ለነገሩ ከሚሊዮን በላይ ህዝብ ከመፈናቀል በላይ ምንስ ማዕት ይሆን የሚጠበቀው?

ከዚህ ላይ ልጅ እያለሁኝ አንድ መጸሐፍ ያነብኩት ትዝ ይለኛል። አባቴ የጻዲቁ ዮሖንስ ት/ቤት የቤተ መጻህፍት ሃላፊ ስለነበር ትልቁ ፕሮጀክቱ እኔን የመጻህፍት ጓደኛ ማድረግ ነበር። ደግሞ 7 ዓመት ላይ ነበር ያስጀመረኝ። መጸሐፉ እንዲህ ይል ነበር።  „የአንድ አገር ንጉሥ ህዝቡን ሊጎበኝ ወደ ከተማ ወጣ። ሲደርስ የከተማው ህዝብ ልብሱን አውልቆ፤ እርቃነ ነፍስ ሆኖ ጠበቀው ምነው ህዝቤ አበደ እንዴ አለ በመገረም፤ ወደ ሌላው ከተማ ሲሄደም መሰሉ ጠበቀው።"

"በዚህ መልክ ሁሉንም የሚያስተዳደራቸውን ከተሞች አዳረሰ። በሁሉም ቦታ ህዝቡ ልብሱን አውልቆ አገኘው። ከዛ ያበድኩት እኔ ነኝ እንጂ ህዝቤ አይደለም ብሎ እሱም ልብሱን አውልቆ ተቀላቀለ“ ይላል ታሪኩ።

ያላቸውን በቅንነት በመለገስ ቀን ከሌት ባተሉ፤ ቀን ከሌት ተጉ፤ ቀን ከሌት በዛኑ በዚህ ቅንነት ውስጥ፤ በዚህ ርህርህና ውስጥ መናድ - መጣስ - ለቅሶና ዋይታ ሲዩ ምኔ ይሆን ጥፋቱ ማዘን መራራት የማይበጅ ከሆነ ማለታቸው አይቀሬ ነው። እናደክማለን እኛ። እራሳችን ሃዘን ሆን እኮ።

ለቅሶ ፈብርክህ - አደራጅትህ በህዝብ ሰቆቃ ዋንጫ ታማታለህን? ሰው ሆነህ ተፈጥረህ አራስን በግሪደር ታርሳለህን? እንዴት? ከዬትኛው ዘመን ላይ ይሆን ያለነው እኛ? ለዚህም መንፈስ ነው አቶ ንጉሱ ጥላሁን ምንጣፍ ጋሻ እና ጦር የሆኑት። 

የnegusu tilahun ምስል ውጤት

ከፍና ዝቅ ያሉት እስከ ሚሊዬንም አዳራሽ ተጉዘው አቀባባል ያደረጉት። አሁን ጊዜያዊ ቦታቸውን አግኝተዋል ተልዕኳቸውን እዬፈጸሙ ነው። ነገ ደግሞ ያለሙትን። አጋርነታቸው ማይክ ላይ ብቻም አይደለም። ወገንተኝነታቸው ለማን ስለማንስ ነው?
  
በኦህዴድ ጉባኤ በቀጭን ትእዛዝ ነው አቶ ንጉሡ ጥላሁን የተወከሉት። ኢህአዴግ ጉባኤም ሲያልቅም እሳቸው ነበር መግለጫ አንባቢው። በዚህ ሁሉ ውስጥ ይህን ያደራጀው የመራው ማነው?

በዛ በኦህዴድ ጉባኤ ጠ/ሚር አብይ አህመድን እኔ እንዲያውም ደግሞው ሊቀመንበር አድርገው ይመርጧቸዋል ብዬ አላሰብኩም ነበር። ደግመው ሲመርጧቸው ራሱ ድንቅ ነው ያለኝ። እሳቸው ህዝብን ለማነጋገር በሚባክኑበት ወቅት „ሽርሽር“ እያሉ ሲያባጭሉ የነበሩት እኮ የራሳቸው ሰዎች ነበሩ።

ቀድሞ ነገር ለውጡንም ደጋፊዎች አልነበሩም። ለውጡን የደገፈው ሌላው ማህበረሰብ ነው። የአብይን መንፈስ ሆነ የለማን መንፈስ የደገፈ እኮ ሌላው ነው አብሶ አማራው የኔታ አማራ።

የሆነ ሆነ አንደም ቀን ዕድሜ ነውና እጅግ በሚገርም፤ በሚደንቅ ቅልጥፍና እና ችሎታ መከራውን ሁሉ እ! እያሉ ተሸክመው ለሰጡን የተስፋ ስንቅ እኔ ምስጋናዬም አክብሮቴም ከልብ ነው ለጠ/ሚር አብይ አህመድ። 

የሚሆነው ዝብርቅ መከራ ቅይጥ ኡኡታ አይደንቀኝም። የሚሆነው ሁሉ አያስበረግገኝም። ስለምን? አስቀድሜ መንፈሱ እንደተጠለፈ ስለወቅኩት። ግን አንደ እንጨት አይነድም አንድ ዳኛ አይፈርድም ሆኖ ሰሚም አላገኘም ጩኸቴ። ቢያንስ የሚጠረጥር አልተገኘም።

የሰኔ 16 ሰልፍ አስፈላጊ አይደለም ብዬ ሁሉ ጽፌያለሁኝ። የሀምሌው ዝመታም ያ የቅንነት የሚሊዮን የፍቅር መንፈስ መጠለፉን በተገዳጋጋሚ ሳይደክመኝ ጽፌያለሁኝ። ከዛ በመለስ ያሉ መልካም ነገሮችም ሁሉ በፈተና ውስጥ፤ በመሰናከል ውስጥ ያለፉ ስለመሆናቸው አሳምሬ አውቃለሁኝ። በህልሜም አምናለሁኝ። ወንበሩ ባዶ ነው። በሙሉ አቅሙ በሙሉ ክህሎቱ በሙሉ መክሊቱ እንዳይንቀሳቀስ እና አጀብ እንዳያሰኘን ትብትብ አለበት።
 
ገናም መከራው ይቀጥላል። በከተሞች የሳት ቃጠሎ እና ፈንጅ ፍንዳታ ሊኖር ይችላል። በተዋህዶ እራሱ ካራ ቅባት የሚል ሌላ ጦርነት ይከፈታል። በእስልምና እምነትም እንዲሁ …

ለዚህ ሁሉ ተፈናቃይ የሃይማኖት አባቶች አንድ የመረዳጃ ተቋም እንዲያሰናዱ አንድ ጹሑፍ ጽፌ ነበር። ሞት ይቀጥላል፤ ሰብዕዊ መብት ረገጣው ይቀጥላል፤ ተፈጥሮን በግሪደር መደርመሳችን ይቀጥላል ነው በልበ ሙሉነት በድፈርት የምናዳምጠው የዛሬዎቹ ባለጊዜዎች። ሰው ተገድሎ ተዝቅዝቆ የታሰቀለበት ዘመን አይተናል። ተወግሮም ተገድሎ አይተናል። ዘመኑ እጅግ አስፈሪ ነው። ይህን ተቃውሞ ሰው ቢወጣ ይረሸናል።

የሐይማኖት አባቶች የሱባኤ ጊዜ ብቻ ሳይሆን አንድ ጠንካራ የመልሶ ማቋቋሚያ መረዳጃ ማህበር ማቋቋም ይጠበቅባቸዋል። ሞቱም መፈናቀሉም የህዝብ ባለቤት አልባ መሆኑም ቀጣይነቱ በመታበይ ታውጇል። የምሾ ቀጣይነቱን ያወጀው ስውሩ መንግሥት ነው።

ስለዚህ አባቶች ምን ይጠብቃሉ? አባቶች እንደ ዕምነታቸው ህዝባቸውን ማረጋጋት ሞት ቢሆን መቀበል ያስፈልጋል። እንደ ቀደምቶቹ። ለነገሩ እነሱ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ላይ አንድ ኦሮምኛ ተናጋሪ ሊቀ ጳጳስ አግኝተው ጥምቀት ላይ ቡራኬ በኦሮምኛ ሲሰጡ ሰምቻለሁኝ። ቀጣዩ ፓትርያርክ መሆናቸው ነው። አሁን የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አንደበት ሆነው ተሹመዋል። ነገ ደግሞ ፓትርያርክ።

በትግራይ ኢንፓዬር ያዬነው አዬን፤ በኦሮሞ ኢንፓዬር ደግሞ ያንገሸገሸንን መገለል፤ መፈናቀል፤ መጨቆንን፤ ተስፋ ማጣት፤ ዕንባ እና ዋይታ እዬኮመኮም ነው። ሌላም አለበት- ክርስትና ወዮልሽ! ይህ አይቅሬ ነው። የሁለቱም እምነት አባቶች ይህን ዘመን በ አደብ እና በተደሞ በውል እንደ ተፈጥሯችን ሊያስተዳድሩት ይገባል። መቅደም ይገባል።

አቤቱ! እንደ ቸርነትህ እንጂ እንደ በዳላችን አትይብን።

የኔዎቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።