ልጥፎች

ከጃንዋሪ 10, 2025 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ቡና እና ልብ የልብ ጓደኛሞች። "በጥዋቱ ቡና መጠጣት የልብ በሽታ ተጋላጭነትን እንደሚቀንስ ጥናት ጠቆመ" BBC

https://www.bbc.com/amharic/articles/cwyxygk1z18o "በጥዋቱ ቡና መጠጣት የልብ በሽታ ተጋላጭነትን እንደሚቀንስ ጥናት ጠቆመ" "በጥዋቱ ቡና የሚጠጡ ሰዎች ከልብ በሽታ ጋር በተያያዘ የመሞት ዕድላቸው ዝቅተኛ መሆኑን አንድ ጥናት ጠቁሟል። ቀኑን ሙሉ ቡና ከሚጠጡ ሰዎች ይልቅ በጥዋት የሚጠጡት ከልብ በሽታ አደጋ ከመራቃቸው በተጨማሪ ረዥም ዕድሜ ይኖራቸዋል ይላል ጥናቱ። ነገር ግን ከልብ በሽታ ለመራቅና ረዥም ዕድሜ ለመኖር ቡና ብቻ በቂ ነው ወይ የሚለውን ጥናቱ አይመልስም። በቱሌን ዩኒቨርሲቲ ኦቢሲቲ ሴንተር ተመራማሪ እና ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ሉ ኪ እንደሚሉት ምንም እንኳ ቡና ለምን የልብ በሽታ አደጋን እንደሚቀንስ ባይታወቅም ቀኑ ሲገባደድ ቡና የሚጠጡ ሰዎች የሰውነታቸው ዑደት ስለሚረብሹት ሳይሆን አይቀርም። ይህ ጥናት ረቡዕ ጥር 1/2017 ዩሮፒያን ኸርት ጆርናል በተባለው መፅሔት በኩል ነው ይፋ የተደረገው። ዶ/ር ኪ አክለው "ቡና የምንጠጣበት ሰዓት ምንም ያክል ለውጥ እንደሚያመጣ ለማወቅ ተግባራዊ ሙከራ ማድረግ አለብን" ብለዋል። "ይህ ጥናት በጥዋቱ ቡና መጠጣት ለምን ከልብ በሽታ አደጋ እንደሚታደግ የሚያስረዳው ነገር የለም" ሲሉ ይተነትናሉ። "ምናልባት የተሻለው ማብራሪያ ከሰዓት አሊያም አመሻሹን ቡና የሚጠጡ ሰዎች የሰውነታቸውን ዑደት [ሰውነታችን የ24 ሰዓታት አካላዊ፣ አእምሯዊ እና የባሕሪ መለዋወጥ ዑደት አለው] ስለሚያውኩት ይሆናል።"   "ይህ ደግሞ የልብ በሽታ ሊያመጡ የሚችሉ እንደ እብጠት [ኢንፍላሜሽን] እና የደም ግፊት ያሉ አደጋዎች ሊጥለን ይችላል" ሲሉ ያብራራሉ። ኒው ኦርሊየንስ የሚገኘው ቱሌን ዩኒቨርሲቲ አጥኚዎች ከአውሮፓውያኑ ...

ጉድ በል ጎንደርስ አሁን። እምም። ህምም። "በአማራ ክልል ዳኞች የሚፈጸምባቸው አካላዊ ጥቃት እንዳሳሰበው ኢሰመኮ አስታወቀ" ሪፖርተር።

 https://www.ethiopianreporter.com/137175/   "በአማራ ክልል ዳኞች የሚፈጸምባቸው አካላዊ ጥቃት እንዳሳሰበው ኢሰመኮ አስታወቀ" January 8, 2025 "በሚኒስትሮች ምክር ቤት የወጣው አዋጅ ቁጥር 6/2015 ዓ.ም. መተግበር ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ፣ በአማራ ክልል በየደረጃው በሚገኙ ፍርድ ቤቶች፣ ዳኞች ከሥራቸው ጋር በተያያዘ የሚፈጸምባቸው አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጥቃት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ፡፡ ኮሚሽኑ በተጨማሪም አሰባሰብኩት ባለው መረጃ በዳኞች እስራት፣ ዛቻና ያልተገባ ተፅዕኖ እንደሚፈጸም በመግለጽ የግኝቱን ውጤት መሠረት በማድረግ ምክረ ሐሳብ አቅርቧል፡፡ ሪፖርተር የተመለከተውና በኢሰማኮ ተጠባባቂ ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ተጽፎ ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ፕሬዚዳንትና ለክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ የቀረበው ሪፖርት እንደሚያስረዳው፣ ኮሚሽኑ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ከሐምሌ 2015 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ጥቅምት 2017 ዓ.ም. ድረስ በዳኞች ላይ ድብደባ፣ እስርና ወከባ ደርሶባቸዋል የሚሉ መረጃዎችን መነሻ በማድረግ የሚመለከታቸውን አካላት በማወያየት ተፈላጊውን የሰነድ መረጃ በመሰብሰብ ክትትል ሲያደርግ መቆየቱን ይፋ አድርጓል፡፡ በዳኞች ላይ የሚፈጸም አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጥቃት በኢሰመኮ ግኝት ከቀረቡ ጉዳዮች አንደኛው ሲሆን፣ ኮሚሽኑ ባሰባሰበው የሰነድና የቃል ማስረጃ ለአብነትም ጥር 15 ቀን 2016 ዓ.ም. በአስቸኳይ አዋጁ ወቅት በአዊ ዞን በወረዳ ፍርድ ቤት አንድ ዳኛ በችሎት ላይ እንዳሉ የወረዳ ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የጦር መሣሪያ...

ክቡርነታቸው እንደማስበው የባከነ ጊዜ የላቸውም። ትልቅ የተግባር ሰው ሞተ አይባልም። እርግጥ ነው ትልቅ ሰው በስጋ ሲለይ ለአገር ረቂቅ የሆኑ ንጥረ ነገሮች ያጎላል። ብዙ የተጉ ሰላማዊ እረፍት ይሁንላቸው። አሜን። ለመላ ቤተሰብ፤ ለአክባሪወቻቸው መጽናናትን እመኛለሁ።

 https://www.ethiopianreporter.com/137186/  "አንጋፋው ፖለቲከኛና የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ቡልቻ ደመቅሳ (1923-2017)"   ሪፖርተር   "በኢትዮጵያ በንጉሠ ነገሥቱ ዘመን ቅድመ 1967 ዓ.ም. እና ከ1983 ዓ.ም. በኋላ በመጣው የፌደራል መንግሥት ዘመን በምጣኔ ሀብትና በፋይናንስ ሥርዓት እንዲሁም በፖለቲካው መስክ በአንጋፋነት የተሰማሩ ልሂቅ ባለሙያ ነበሩ፣ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ፡፡ ከምክትል የገንዘብ ሚኒስትርነት እስከ የዓለም ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት በላቀ አፈጻጸም አገልግለዋል፡፡  የዘመነ ደርግ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ማክተም ተከትሎ፣ የመጀመርያው የግል ባንክ የሆነውን አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክን (በኋላ አዋሽ ባንክ) ከመሠረቱት መካከል አንዱና የመጀመሪያው የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ እንዲሁም የመጀመርያው ፕሬዚዳንት ሆነው ሠርተዋል፡፡ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ዓለም ውስጥ የጎላ ስፍራ የነበራቸው አቶ ቡልቻ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልም ሆነው ሠርተዋል፡፡ በተለይ የፓርላማ አባል በመሆን ይሰጡዋቸው በነበሩ አስተያየታቸው ብዙዎች ያውቋቸዋል፡፡ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ( ኦፌኮ ) የተባለውን ፓርቲ በማቋቋምና እንዲቋቋም በማድረግ፣ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡   በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ገንዘብ ሚኒስቴር ከ1953 እስከ 1963 ዓ.ም. ለአሥር ዓመታት ያህል ሲሠሩ የበጀት ማስፈጸሚያ ክፍል ረዳት ዳሬክተር፣ የበጀት ማስፈጸሚያ ክፍል ዳሬክተር ጄኔራል፣ በመጨረሻም ምክትል ሚኒስትር ሆነው አገራቸውን በሙያቸው በታታሪነትና በታማኝነት ማገልገላቸው ዜና ዕረፍታቸውን ተከትሎ የገለጸው ሚ...

የኛ ነገር። "አብዛኛዎቹ እርቃናቸውን የታገቱ 26 'ኢትዮጵያውያን' ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በፖሊስ ተገኙ" BBC

 https://www.bbc.com/amharic/articles/cwyw3e2d2x5o   "አብዛኛዎቹ እርቃናቸውን የታገቱ 26 'ኢትዮጵያውያን' ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በፖሊስ ተገኙ" BBC "የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ በአንድ ቤት ውስጥ ታግተው የቆዩ እና ኢትዮጵያዊ ናቸው ተብሎ የሚታመኑ 26 ሰዎችን ጆሃንስበርግ ውስጥ ማግኘቱን አስታወቀ። በቤቱ ውስጥ ከተገኙት ስደተኞች መካከል 15ቱ እርቃናቸውን የነበሩ ሲሆን፣ በቤቱ አቅራቢያ የተገኙት ቀሪዎቹ አስራ አንዱ ደግሞ ጉዳት የደረሰባቸው መሆናቸው ተነግሯል። ሃያ ስድስቱ ሰዎች የተገኙት ሐሙስ አመሻሽ ላይ በጆሃንስበርግ ከተማ ሰሜን ምሥራቅ ዳርቻ ላይ ባለ ሰፈር ውስጥ ከጎረቤቶች በተገኘ ጥቆማ አማካይንት መሆኑን ፖሊስ ገልጿል። ከጉዳዩ ጋር በተያያዘም ሦስት ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ኢትዮጵያውያን ናቸው የተባሉት ስደተኞች ወደ ደቡብ አፍሪካ እንዴት እንደገቡ ግልጽ ባይሆንም ባለሥልጣናት የሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባ መሆናቸውን ለማወቅ ምርመራ እያደረጉ ነው። ፖሊስ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ "የሕገወጥ የሰዎች ማዘዋወር ቡድን" መዋቅርን ማፍረሱን አመልክቷል።   የተወሰኑት ስደተኞች ከተያዙበት ቤት ለማምለጥ ሲሞክሩ የሰበሩት መስኮት ባለሥልጣናት የተገኙት ስደተኞቹ ታግተው ስለቆዩበት ሁኔታ እና አንዳንዶቹም ለምን እርቃናቸውን እንደነበሩ ምንም ዓይነት ዝርዝር መረጃ አልሰጡም። ከቤቱ አቅራቢያ የተገኙት ስደተኞች "መስኮት ሰብረው ያመለጡ ናቸው" በማለት የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ የከባድ ወንጀሎች ክትትል ቡድን ቃል አቀባይ ኮሎኔል ፊላኒ ንኳላሴ ተናግረዋል። ከቤቱ ለማምለጥ የመስኮት መስታወት ሲሰብሩ እና ብረቱን ለመገነጥል ሲሞክሩ ጉዳት የደረሰባቸው ስደተኞ...

ኧረ ድንግል ሆይ ድረሺ።" በሰሜን ወሎ በከፍተኛ የምግብ እጥረት ህፃናትን ጨምሮ ሰዎች መሞታቸውን የዳሰሳ ጥናት አመለከተ" BBC

 https://www.bbc.com/amharic/articles/c2exeywdz1do  " በሰሜን ወሎ በከፍተኛ የምግብ እጥረት ህፃናትን ጨምሮ ሰዎች መሞታቸውን የዳሰሳ ጥናት አመለከተ"   10 ጥር 2025, 06:42 EAT "በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ በተከሰተ ከፍተኛ ምግብ እጥረት የእናቶች እና የህጻናት ሕይወት ማለፉ በዳሰሳ ጥናት ተረጋገጠ። ካለፈው ወር ጀምሮ በወረዳው ከፍተኛ የምግብ እጥረት መከሰቱን ቢቢሲን ጨምሮ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን የዘገቡ ሲሆን፤ ለዕይታ የሚረብሹ ምሥሎችም ይፋ ሆነዋል። የአካባቢውን የምግብ እጥረት ለማረጋገጥ አጭር ዳሰሳ ያደረገው ወልዲያ ዩኒቨርስቲ ቀውሱ ከተነገረው በላይ "ከባድ ሆኖ አግኝቼዋለሁ" ብሏል። ስድስት ባለሞያዎችን ያካተተ ቡድን በቡግና ወረዳ አራት "ቁልፍ" ቀበሌዎች ላይ ባደረገው ምልከታ ከፍተኛ የምግብ እጥረት፣ የህክምና አገልግሎት እጦት እና የውሃ ችግር ማኅበረሰቡ መጎዳቱን አመልክቷል። ቡግና ወረዳ በድርቅ የሚታወቅ አካባቢ ከመሆኑ ባለፈ የሰሜኑ ጦርነት ጠባሳ ያረፈበት እና ባለፈው ዓመት የጎርፍ እና የበረዶ አደጋዎችን በማስተናገዱ ማኅበረሰቡ "ፍሬ" እንዳላገኘ አርሶ አደሮች ለቢቢሲ ተናግረዋል። ወረዳው ከአንድ ዓመት በላይ በፋኖ ኃይሎች መያዙን ተከትሎ፤ ወደ አካባቢው ማደባሪያን ጨምሮ የመድኃኒት እና የህክምና ግብዓቶች፣ የአንቡላንስ አገልግሎት፣ የባንክ አገልግሎት እንዲሁም የሴፍቲ ኔት እገዛዎች መቋረጣቸው ታውቋል። "ተፈጥሯዊ እና ሰው ሠራሽ አደጋዎች ተዳምረው ነው [ማኅበረሰቡን] ለእንዲዚህ ዓይነት ችግር የተዳረገው" ሲሉ የወረዳውን የቀውስ ምክንያት የተናገሩት አንድ የጥናት ቡድኑ አባል፤ የሰው ሕይወ...

እግዚአብሄር ሆይ ምህረት አምጣ። አሜን። ለሰው ልጅ የተፈጥሮ አደጋው በቂ ነው። በሰው የሚሰራ ችግር ሊቆም ይገባል። "የሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት ከ135 ቢሊዮን ዶላር እንዳወደመ ተገመተ" BBC

 https://www.bbc.com/amharic/articles/cj3e5nyj35lo  "የሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት ከ135 ቢሊዮን ዶላር እንዳወደመ ተገመተ" BBC 10 ጥር 2025, 11:10 EAT "በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመተ ያለው የሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት በአሜሪካ ታሪክ ከፍተኛ ውድመት ያስከተለ እንደሆነ ተነገረ። ያደረሰው ጉዳት ከ135 ቢሊዮን በላይ እንደሆነም ተገምቷል። አኩዌዘር የተሰኘው ባልደረባ የሆኑ የግል ትንበያ ባለሙያ በሰጡት ቅድመ- ትንበያ መሰረት እሳቱ ያደረሰው ውድመት ከ135-150 ቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ ሙያዊ ግምታቸውን ሰጥተዋል። በአሜሪካ በጣም ውድ የሆኑ መኖሪያ ቤቶችን የያዙ ስፍራዎች በእሳት መያያዛቸው ተከትሎ ዋጋውን ከፍ አድርጎታል ተብሏል። እንደ ሞርኒንግ ስታር እና ጄፒ ሞርኒንግ ያሉ የፋይናንስ ተቋማት ተንታኞች በሰጡት አስተያየት የመድን ኩባንያዎች የሚሰጡት ሽፋን እስከ 8 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስወጣቸው ትንበያቸውን አስቀምጠዋል። ፓሊሳዴስ በተሰኘው ሰደድ እሳት ከ5 ሺህ 300 በላይ ህንጻዎች ሲወድሙ በኤቶን እሳት ደግሞ ከ5 ሺህ በላይ መውደማቸውን የእሳት አደጋ ባለስልጣናት አስታውቀዋል። ባለስልጣናቱ አሁንም ሰደድ እሳቱን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ባለበት በአሁኑ ወቅት የጉዳቱ መጠን እየጨመረ መምጣቱ እንደማይቀር ይገመታል። "በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመቱ ያሉ እና በነፋስ እየተጓዙ ያሉ ነበልባሎች በዘመናዊ የአሜሪካ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ውድመትን ካስከተሉ የእሳት ሰደድ አደጋዎች አንዱ ሆኗል" ሲሉ የአኩዌዘር ኩባንያ የሜትሮሎጂ ኃላፊ ጆናታን ፖርተር ተናግረዋል። በአውሮፓውያኑ 2018 በሰሜናዊ ካሊፎርኒያ በፓራዳይዝ ከተማ አቅራቢያ የተቀሰቀሰው እሳት 12.5 ቢሊዮን ዶላር ...