እግዚአብሄር ሆይ ምህረት አምጣ። አሜን። ለሰው ልጅ የተፈጥሮ አደጋው በቂ ነው። በሰው የሚሰራ ችግር ሊቆም ይገባል። "የሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት ከ135 ቢሊዮን ዶላር እንዳወደመ ተገመተ" BBC

 https://www.bbc.com/amharic/articles/cj3e5nyj35lo

 "የሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት ከ135 ቢሊዮን ዶላር እንዳወደመ ተገመተ" BBC

"በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመተ ያለው የሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት በአሜሪካ ታሪክ ከፍተኛ ውድመት ያስከተለ እንደሆነ ተነገረ።

ያደረሰው ጉዳት ከ135 ቢሊዮን በላይ እንደሆነም ተገምቷል።

አኩዌዘር የተሰኘው ባልደረባ የሆኑ የግል ትንበያ ባለሙያ በሰጡት ቅድመ- ትንበያ መሰረት እሳቱ ያደረሰው ውድመት ከ135-150 ቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ ሙያዊ ግምታቸውን ሰጥተዋል።

በአሜሪካ በጣም ውድ የሆኑ መኖሪያ ቤቶችን የያዙ ስፍራዎች በእሳት መያያዛቸው ተከትሎ ዋጋውን ከፍ አድርጎታል ተብሏል።

እንደ ሞርኒንግ ስታር እና ጄፒ ሞርኒንግ ያሉ የፋይናንስ ተቋማት ተንታኞች በሰጡት አስተያየት የመድን ኩባንያዎች የሚሰጡት ሽፋን እስከ 8 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስወጣቸው ትንበያቸውን አስቀምጠዋል።

ፓሊሳዴስ በተሰኘው ሰደድ እሳት ከ5 ሺህ 300 በላይ ህንጻዎች ሲወድሙ በኤቶን እሳት ደግሞ ከ5 ሺህ በላይ መውደማቸውን የእሳት አደጋ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

ባለስልጣናቱ አሁንም ሰደድ እሳቱን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ባለበት በአሁኑ ወቅት የጉዳቱ መጠን እየጨመረ መምጣቱ እንደማይቀር ይገመታል።

"በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመቱ ያሉ እና በነፋስ እየተጓዙ ያሉ ነበልባሎች በዘመናዊ የአሜሪካ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ውድመትን ካስከተሉ የእሳት ሰደድ አደጋዎች አንዱ ሆኗል" ሲሉ የአኩዌዘር ኩባንያ የሜትሮሎጂ ኃላፊ ጆናታን ፖርተር ተናግረዋል።

በአውሮፓውያኑ 2018 በሰሜናዊ ካሊፎርኒያ በፓራዳይዝ ከተማ አቅራቢያ የተቀሰቀሰው እሳት 12.5 ቢሊዮን ዶላር በማስወጣት ከፍተኛ የመድን ወጪ በማስወጣት ቁንጮ ስፍራ ላይ መቀመጡን ግዙፉ የመድን ኩባንያ ኦዎን (ኤኦን) አስታውቋል።

የካምፕ ፋየር የሚል ስያሜ በተሰጠው በዚህ ቃጠሎ 85 ሰዎች ህይወታቸው ሲቀጠፍ 50 ሺህ ሰዎች ተፈናቅለዋል።

ኩባንያው በአሁኑ የሰደድ እሳት ከፍተኛ የንብረት ዋጋ ያላቸው ውድመት ማጋጠሙን ተከትሎ ከፍተኛ ዋጋ ከሚያስወጡ ሰደድ እሳቶች መካከል አንዱ ሊሆን ይችላል ብሏል።

የመድን ሽፋን የሌላቸውን ንብረቶችን ጨምሮ አጠቃላይ ኪሳራው የከፋ ሊሆን እንደሚችል እየተነገረ ነው።

ሁኔታዎች በቁጥጥር ውስጥ ቢገቡም ትተውት የሚያልፉት ጠባሳ በጤና እና ቱሪዝም ላይ የረጅም ጊዜ ተጽእኖ ሊኖራቸው እንደሚችል ፖርተር አስረድተዋል።

በተለይም ቀድሞውንም በከፍተኛ ቀውስ ውስጥ ላለው የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ ተጨማሪ ተግዳሮት ነው ተብሏል።

በአሜሪካ በብድር የተገዙ ቤቶች የንብረት የመድን ሽፋን እንዲኖራቸው በባንኮች ይገደዳሉ።

ነገር ግን የመድን ኩባንያዎች እንደ እሳት፣ ጎርፍ እና አውሎ ንፋስ ያሉ የተፈጥሮ አደጋዎች እየጨመሩ ባሉበት ሁኔታ የዋጋ ጭማሬ እያደረጉ ወይም ሽፋኑን ሙሉ በሙሉ እየሰረዙ ይገኛሉ።

እነዚህ የመድን ኩባንያዎች ሽፋን መስጠት ማቆማቸውን ተከትሎ በርካቶች የተለያዩ ግዛቶች መንግሥታት ወደሚያቀርቧቸው የቤት መድኖች ፊታቸውን አዙረዋል። እነዚህ ሽፋኖች በዋጋቸው በጣም ውድና አነስተኛ የጥበቃ ሽፋን አላቸው ተብሏል።

በሎስ አንጀለስ ታሪክ አውዳሚ በሆነው በዚህ የሰደድ እሳት አምስት ሰዎች መሞታቸው የተረጋገጠ ሲሆን ከ137 ሺህ ሰዎች በላይ ተፈናቅለዋል።

ፓሊሳድስ የሚል ስያሜ የተሰጠው ሰደድ እሳት በሎስ አንጀለስ የተቀሰቀሰው ማክሰኞ እለት ሲሆን በግዛቲቷ ትልቁ ነው። የፓስፊክ ፓሊሳድስ አካባቢን ጨምሮ ከ17 ሺህ 200 ሄክታር በላይ የሚሸፍን ሰፊ ግዛት አውድሟል። ኢቶን የተሰኘው ደግሞ በሰሜናዊ የሎስ አንጀለስ እን አልታዴና ባሉ ከተሞች እየተዛመተ የሚገኝ ሲሆን 10 ሺህ 600 ሄክታርን መሬት በመሸፈን በግዛቲቷ ሁለተኛው ትልቁ እሳት ሆኗል።

ሶስተኛው ሰደድ እሳት ኸረስት የሚሰኝ ሲሆን ማክሰኞ እለት ተከስቶ ከሳን ፈርናንዶ በስተሰሜን በኩል እየተዛመተ ይገኛል። ይህም እሳት 855 ሄክታርን ይሸፍናል። ሌላኛው ሊዲያ ረቡዕ ከሰዓት በኋላ በሎስ አንጀለስ በስተሰሜን ተራራማዋ አክቶን አካባቢ ተቀስቅሶ ወደ 350 ሄክታርን መሬት በመሸፈን ተዛምቷል።"

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።