ልጥፎች

ከጁን 3, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

„ቀጥል አብይ!“ ከኢትዮጵያ ቅኖች።

ምስል
          „ ቀጥል አብይ!“ ከኢትዮጵያ ቅኖች።           ከአቶ አበራ የማነ አብ እና ከዶር ነገደ ጎበዜ              የተላለፈ የመልካም ተስፋ ምኞት።                                              ከሥርጉተ ሥላሴ 03.06.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።)                           „አስተዋይ መልካም ምክርን ገንዘቡ ያደርጋል።“ (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ምሳሌ ፩ ቁጥር ፭)         ·          መነሻዬ። http://www.zehabesha.com/amharic/archives/91647 „ሊታይ የሚገባው : አበራ የማነ አብ እና ዶ / ር ነገደ ጎበዜ ስለዶ / ር ዓብይ አህመድ ያልተጠበቀ ነገር ተናገሩ“ ·          የእኔ ብሩኮች እንዴት ናችሁ? እንዴት ነው አገሩ፤ ሰፈሩ፤ ከብቱ እንዲያው ሁለመናው ጫታን ነውን? የኔዎቹ ዘሃበሻ የልተጠበቀ አይደለም። የመኢሶን አቋም እኮ ከዶር ነገዴ ጎበዜ SBS ቃለ ምልልስ ቀደም ባሉት ቀናት ከመሼ እንዴት ትዝ እንዳሏቸውም አላውቅም፤ መቼም በኢትዮጵያ ፖለቲካ አንዱ ልጅ ሌላው እንጀራ ልጅ ነው፤ ስለ ኢትዮጵያ ጉዳይ ተብሎ ዕወቅና በተሰጠው በሌላ ሚዲያ አላችሁን ተብለው ከመኢሶኖች አመራር አካሉ በአንድ ወገኔ አማካኝነት አቋሙን ግልጽ አድርጓል። አሁን ለሦስተኛ ጊዜ መሆኑ ነው።   ስለዚህ ለእኔ የጠበቅኩት ነው የሆነው ስላችሁ ነው የእኔዎቹ ዘሃበሻዎች። ለኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ለሚፈቅድ ሁሉ እኮ ሌላ ቦታ ሳይሄድ የኦህዴድን ሙሉ ቁመና እንደ ድርጅት ማጥናት ብቻ ይበቃው ነበር። ስለምን ግዮን ላይ መንፈሱን