ልጥፎች

ከኖቬምበር 21, 2023 ልጥፎች በማሳየት ላይ

19.11.2020 ረመጥ ነው ወልቃይትወጠገዴ።

ምስል
  ረመጥ ነው ወልቃይትወጠገዴ።   እፍታ። በድጋሚ ለጥ ብዬ እጅ እነሳለሁኝ። ህወሃት ከድል እስከ ውድቀቱ የጎንደር ሁነት ምን ነበር የሚለውን የነበርኩበትን በምልሰት ቅኝት አቅርቤያለሁ። ማንበብ ፀጋቸው ለሆኑ ወገኖቼ፣ ታሪክን እንደ አግባቡ ለሚያዳምጡ፣ ለሚይዙ ወገኖቼ፣ በጭልፋ ፕሮፖጋንዳ የወልቃይትጠገዴ ጉዳይ ላይ ለሚያላግጠው የኦዳ ሥርዕዎ መንግሥትም ነገረ ሥራው የሳሙና አረፋ ነውና ውስጤን ያይ ዘንድ የፃፍኩት ነው። ልቀት። የወልቃይት እና የጠገዴ ጥያቄ ከአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ዘመን መባቻ ብቻ የሚመስላቸው አሉ። ህወሃት ጫካ ሆኖ ሲወስን ከህወሃት ጋር የነበሩ የጠገዴ፣ የወልቃይት ልጆች አፈንግጠው ወጥተው በለመዱት ዱር ገደል ሲታገሉ ነበር። ውጭ የወጡትም ለአንዲት ሰከንድ ከተጋድሏቸው ዝንፍ አላሉም። በዘመነ ህወሃት ረጅሙ ተጋድሎ ጋር የዘለቅን በርካታ ጎንደሬዎች የህሊናችን ሞተር እርስታችን ነው። ይህ ሊታወቅ ይገባል። ውስጣችን የማይበርድ ረመጥ አለ። የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ሲነሳ አቶ አሥራት አብርኃ የገብያ ግርግር ሲሉት ወጥቼ ቅጥ አስይዠዋለሁ። ማንነት ሸቀጥ አይደለም በገብያ ህግ የሚተዳደር። ድፍረታቸው ልክ ስላልነበረው ነበር ወጥቼ የሞገትኳቸው በደጉ ሳተናው ድህረ ገፅ። ኢሳትም ሳቢያ እያለ ሲያላግጥ፣ ግንቦት ሰባትም የነፃነት ኃይል ተጋድሎ እያለ ሲለነቁጥ ልካቸውን እንዲይዙ የብዕር ቦንብ ተልኮላቸዋል። ጠቅላዩ ወደ ሥልጣን ሳይመጡ ጭምጭምታ ሳይኖር በዝርዝር ለዛን ጊዜው የኦህዴድ ሥራ አስፈፃሚ የፅህፈት ቤት ኃላፊ፣ ለዛሬው ጠቅላይ በስክነት አስረድቻቸዋለሁኝ። የወልቃይትወጠገዴ ጉዳይ አገር በማስቀጠል ጉዳይ ምክንያታዊ ነው። ገዢ መሬት ነው። ህወሃት ሞተ ተብሎ ማወጅ የሚቻለውም ይህ ርስት ወደ ባለቤቱ ሲመለስ ...

31.10.2020

ምስል
  በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ። አሜን።     "የሰው ልብ መንገድ ያዘጋጃል፣ እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።" ምሳሌ 16/9 የነግህ ፀሎት። 1) የተመድ ሰላም አስከባሪ ኃይል ኢትዮጵያ እንዲገባ መሻት። 2) የአማራ ክልል የከፍተኛ ተቋም ተማሪዎች ከክልላቸው ውጪ ወደ ሌላ ክልል እንዳይመደቡ መሻት። 3) በኦህዴድ ኦነግ የበቀል መሥመር እንደ ወጡ የቀሩት የአማራ እጩ ሊቃናት የደንቢደሎ ዩንቨርስቲ ተማሪዎችን መጨረሻ ለማወቅ መሻት። 4) ሰው አጥፊው የህወሃትወኦነግ ህገ መንግሥት ሙሉለሙሉ እንዲቀዬር መሻት። 5) መርዛማው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከኢትዮጵያ ይጠፋ ዘንድ መፀለይ። 6) የሥርዓት ለውጥን መሻት። ወሥብኃት ለእግዚአብሔር። ወስብኃት ለእግዚአብሔር።

19.11.2019 የኦዳ ኢንፓዬር ማፏሸኪያ ህወሃት ነው።

  የኦዳ ኢንፓዬር ማፏሸኪያ ህወሃት ነው። የኦዳ ኢንፓዬር ማፏሸኪያ ህወሃት ነው። ይህን ግርባው ብአዴን፣ ተደማሪው ግንቦት ሰባት እስከ ቲፎዞው፣ ሚዲያው ኢሳት፣ የኦዳው ኢንፓዬር መለከት ነፊ የአንድ አፍታ አወያይ ጦማሪ ስዩም ተሾመ ቀጥ ሰጥ ለጥ ብለው የማፏሸኪያ ብር አንባር በመሆን ያስፈፅማሉ። ሁሉም ሰው ህሊና ያለው ሁሉ ከማፏሸኪያ እንቅልፍነት ያወጣው ዘንድ አምላኩን ይማጠን። እኔ አፈንጋጯ ሥርጉተ ሥላሴ የኦዳ ኢንፓዬር ማፏሸኪያ፣ እንቅልፍ አማጭ ባለመሆኔ እግዚአብሄርን አመሰግናለሁ። ህወሃትን በሚመለከት የራሱን ድርጅት በቅጡ መምራት ያልቻለው የአብይ መንፈስ እኔን በዛ ቦይ ውስጥ ማስገር ፈፅሞ አይችልም። ፕሮፖጋንዲስትም አልፈልግም። ቀስቃሽም አያሰኜኝም። ምክንያት። ገና በልጅነት ዕድሜዬ በተደራጀ ፓርቲ በከፍተኛ ህዝባዊ የኃላፊነት ሆኜ ታግዬዋለሁ። ጫካውንም ካቴናውንም ስደቱንም አውቀዋለሁ። እነሱ ከህወኃት የሥልጣን ፍርፋሪ ለቃሚ ኦፋ በነበሩበት ጊዜ ሁሉ ሥርጉትሻ ህወሃትን ሞግታለች። የራሷም ወርቅ የሆነ አሻራ ከእነ ሙሉ ማስረጃው አላት። አሁን እነሱም ከፖለቲካ ድርጅት ተቆጥረው የጭካኔያቸው መለበጃ አዲስ ፀረ ህወሃት ዘመቻ ቢጀምሩ ሸማ በዬዘርፋ እንደሚለበስ ሥርጉተ ሥላሴ ጠንቅቃ ታውቃለች። ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ አንዲት ቀን ድርጅታቸውን መምራት ሳይችሉ ነው በአማራ አቅም የሚፎክሩት፣ የሚያቅራሩት። መቼ ነው እሳቸው ሙሉ ኢትዮጵያን የመሩት፣ ያስተዳደሩት? መቼ ይነገረና። እሩብ አገር እንኳን ይመራሉን? ይህ አቅም ሲያንሳቸው በሴራ ፖለቲካ፤ በህዝብ ሰቆቃ መንበራቸው የማይደፈር አድርገው ለማሳዬት ይጥራሉ። ውሽልሽል። ጉዳዩ የውሽማ ሞት ነው። ገናና አገር እንዲህ ላርባ መሆን እንኳን ባልቻለ አቅም ልትመራ አይገባትም። ህወሃት አረረም መረረም 27...

19.11.2019 የሞት ጠረን ለሴራ ፖለቲካ ቀመር በኦዳ ኢንፓዬር።

ምስል
  የሞት ጠረን ለሴራ ፖለቲካ ቀመር በኦዳ ኢንፓዬር።     እንዴት ናችሁ ጤና አዳሞቼ? ደህና ናችሁ ወይ? ኦዳና ጃራ ግብግባቸው በጉልህ እስኪወጣ ቀዳሚው የአህድዮሽ ጉዞ በፀረ ኢትዮጵያዊ መንፈስ ይቀጥላል።    ከዚህ መከራ የሚድነው አሁን ባለው ሁኔታ የአድዋ ሥርዕዎ መንግሥት ብቻ ይሆናል። 18 ወራት የኢትዮጵያን መከራ ያልወቀጠው እሱ ብቻ ነው ማለት ይቻላል። የቀረበት የማህል አገር ዘመናይነት ብቻ ነው። እርግጥ ነው በራሱ መስመር አገርን አምሷል። ሰፊ ስለሆነ እሱን አቁሜ ወደ ዋናው እርእሴ ልሂድ።   በዚህ 18 ወራት የበቀል ማወራረጃ፣ የጭካኔ የመሞከሪያ ጣቢያ የነፍስ ይማር ባዕት ያልሆነ አዬር ባዕት አልነበረም። ቁንጥንጡ፣ ዝርክርኩ፣ መሰሪው፣ ሸፍጠኛው የአብይወለማ ሌጋሲ ተጭኖ በያዘው የአማራ ህዝብ እና መንግሥት ከቀደሙው ዘመን ባላነሰ ፍላጎቱን ለማስፈፀም የመሞከሪያ ጥንቸል አድርጎት ባጅቷል።   አሁን ግዙፋን ኦፕሬሽን በእንደልቡ አቶ ዮኋንስ ቧያለው እና በአቶ መላኩ ፈንታ የስሜን አሜሪካ እና የለንደን ጉዞ ሀ ብሎ ይጀምራል። ሲመለሱ የእራሱ እግር የእግሩ ራስ ሆኖ ይጠበቃቸዋል።   በዚህ ማህል ሁለት አውራ ጉዳዮችን እንይ። ሃሳብን የማስተናገድ አቅም። ጥያቄ መጠዬቅ በህግ ያስቀጣል በዴሞክራሲ አሻጋሪው ጠቅላይ ሚኒስተር የህሊና አቅም። ሽብሽብ። የተገደሉት ሊሂቃን በሙሉ የሞገቱ ስለመሆናቸው እኔ በግሌ አልጠራጠርም። የታሠሩትም ቂሙ የሚመነጨው ሞገታችሁኝ ነው። ጠቅሚሩ ቶለራንሳቸው ዜሮ ነው። ፈሪም ናቸው።   መናገር መናገር መናገር ጥሪያቸው ይህ ነው። ማድመጥ አቻችሎ መጓዝ አልተፈጠረባቸውም። ስለዚህ ዴሞክራሲ ሞቶ የተቀበረው እሳቸው በህይወት የተፈጠሩበት ዕለት ነበር። እኔ ዴሞክራሲን ...

19.11.2019 የድንጋይ ጫጉላዊ ሽርሽር።

ምስል
  የድንጋይ ጫጉላዊ ሽርሽር።       ብር ትር የድንጋይ ሽርሽር። ስንድድ ተሰራለት ጨሌ ዘነበለት በጭካኔ ዜማ ጫጉላው ከበረለት። ሸማ ቀረበለት ገዳ ሰገደለት በዕንባ ቅልቅል ሜጫ ፈነጨበት። ድንጋይ እና ሜጫ ውሉ የእርግጫ ህሊናው ግራጫ ዘመኑን ገደሉት እንዲህ በፍጥጫ። ቀርቶ እንደ ዋዛ፣ የጥንት የጥዋቱ ሰውነት ማጣቱ እርስቱ ሆነለት መታበይ ስባቱ። ያ የድንጋይ ዘመን ተመልሶ መቶ፣ እንዲህ ዘመነበት በድንጋይ ሽርሽር፣ መኖርን ፈጨበት። ህይወት ቀጠፈበት ቤት ንብረት ጠፋበት ስጋት ሰፈነበት ዋይታ ነገሠበት።

19.11.2019 ድንጋይ ቀን ወጥቶለት።

ምስል
  ድንጋይ ቀን ወጥቶለት።      ድንጋይ ቀን ወጥቶለት ቄሮ ተፈጥሮለት የጭካኔ ሃውልት በሥምረት ቆመለት የአረማዊ ድርሳን ዘሞ ቀረበለት። ድንጋይ ቀን ወጥቶለት ድንኳን ተጥሎለት የሰው እርድ ቀርቦለት ዕንባ ጎረፈለት። ድንጋይ ቀን ወጥቶለት መንገድም አልፎለት እርፍት አግኝቶበት ሃኒ ሙን ሁኖለት ተጓዥ አልቅሶበት ቄሮን አንግሦለት ማህፀን መክኖበት። ድንጋይ ቀን ወጥቶለት መውገሪያ ሰምሮለት ኦዳ ተቀብሎት በጥቁራማ ዘመን ይሁንታ ቅብነት። የትውልዱ ሞራል ዝቅዝቅ ተጉዞበት የማረጉ ኩራት በኵረት በቅሎበት በስጋት ዳመና አገር ታመሰበት በሰቆቃ ስቃይ ፍጥረት አረረበት ድንጋይ ቀን ወጥቶለት።

ካቴና ያሉት ሳይደክሙ፤ ጫካ ያሉት ሳይዝሉ እኛ ግን ተዳከምን። ምን ነካን?

ምስል
እንዴት ናችሁ? ካቴና ያሉት ሳይደክሙ፤ ጫካ ያሉት ሳይዝሉ እኛ ግን ተዳከምን። ምን ነካን? የእኛ ቤትማ በረድ መሆን ከጀመረ ቆያዬ። በቃ ሁሉም ነገር ተረሳሳ። አባት ታዲወስም ተዘነጉ፤ መስኪም ተረሳች፤ ጎበዙ ጎበዜም ተረሳ፤ ሁሉንም እርግፍ አድርገን ትውት።    አሁን አሁንማ ሳስበው እኔ ስለጥፋቸው ሁሉ አሰልቺ እንደምትሉኝ እያሰብኩኝ ነው። የሆነ ሆኖ ነፃነት በአፍላ፤ በወረት በወፍ አወጣኝ አይገኝም። የቆረጡ፤ የፀኑ የትውልድ ፈርጦች በትጋታቸው በትትርናቸው የሚያስገኙት ሰማያዊ ፀጋ ነው። መኖራቸውን፤ ቤተሰባቸውን፤ ተስፋቸውን እራሳቸውንም ገብረው።   ማገልገልን የመሰል የጽድቅ ጎዳና የለም። በተለይ በነጣ ሲሆን። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 21/11/2023 #ክብር በብላሽ አይገኝም።  

#የቁልል #ዕፍረት ማጣት በበርሊን።

ምስል
#የቁልል #ዕፍረት ማጣት በበርሊን።     ማንበቡም፤ ማድመጡም የተፈራ ትግሉማ እንዴት ይደፈር???? ትናንትና በቅኔው ጎጃም በወበራ አዝመራ በመከወን ላይ የሚገኙ ትንታጎቹ የኢትዮጵያ ጉሮሮወች የጎጃም አርሶ አደሮች በፋሽስት አነጋዊ ኦህዴድ መንግሥት ሠራዊት በግፍ በባዕታቸው መረሸናቸውን ኢኤምኤስ ዘግቧል።   ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አለማፈራቸው ይገርመኛል። ሰሞኑን በርሊን ጀርመን ነበሩ አሉ። የገረመኝ ከውጭ ጉዳይ ሚር አንሰው ኢትዮጵያ ምድር ላይ አቀባበል የተደረገለት የጀርመን መንግሥት ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድን የጀርመን ካንስለር በክብር አቀባበል እንዳደረጉላቸው፤ እንደተቀበሉ አዳምጫለሁኝ። ቅጣቱ የህሊና ይመስለኛል ለጎግ ማንጉጉ የኢትዮጵያ የፕሮቶኮል አልቦሽነት።   የሆነ ሆኖ ህዝቡን በድሮን የሚጨፈጭፍ ፍፁም ጨካኝ፤ ገበሬው እርሻ እንዳይሠራ ማዳበሪያ የከለከለ፤ በእርሻ ወቅት በባዕቱ ሄዶ ጦርነት የገጠመ፤ ልጆቹ ከ12993 በላይ ለ12ኛ ክፍል ፈተና አትቀርብም ብሎ የቀጣ፤ ስንት አሳር አይተው ተምረው ዩንቨርስቲ የገቡ የአማራ ልጆችን ድብዛ ያጠፋ፤ ያሠረ፤ ያገተ፤ ያንገላታ፤ በመድፍ የፈጄ፤ በራህብ የሚቀጣ፤ በማደህዬት የሚበቀል፤ መጽናኛ የዕምነት ቦታወቹን ያረከሰ፤ ህዝብ ወቶ ለመግባት ዋስትና መስጠት የተሳነው #ቁልል በበርሊን መገኜት ዓይን በጥረጨው ማሸት ብሂሉ በውን የተገለጠበት ሂደት ነበር።    በጣም የሚገርመኝ አቶ ቀን፤ ባላንባራስ ሳምንት፤ ደጃዝማች ወራት እንዲህ አረመኔን ከረባት እና ገበርዲን አጎናጽፈው አደባባይ ማዋላቸው ብቻ ነው። ለዚህ የሰገዱ ኑዛዜወች ደግሞ አደግድገው አገልጋይ ሆነው ማይክ ጨብጠው መገኜታቸው ነው። 1) የተመረተ የእግዚአብሄር አዝመራ የሚያነድ፤ 2) ያለን የሚያራቁት በ...

የዴሞክራሲ ሎተሪ ቢደርስ እንደምን በኢትዮጵያ ምድር ይስተናገድ ይሆን? ጓዘ ቀላል ጥያቄ።

ምስል
  የዴሞክራሲ ሎተሪ ቢደርስ እንደምን በኢትዮጵያ ምድር ይስተናገድ ይሆን? ጓዘ ቀላል ጥያቄ። ከአንቀጸ ብርኃን የኢትዮጵያ ሊቀ ቅዱስ ያሬድ የተወሰደ እንዲህም ይላል ……… "የአምላክ እናት ምስጋና፤ በዕውነተኛ ፈራጅ በአምላክ እናት ምስጋናና ይገባታል።" የእኛን ነገር እሷ እምዬ ዋ ድንግልዬ ታሰናዳው እንጂ እኛስ አላወቅንበትም።      ይጨንቃል። የመብት እና የግዴታ ጣሪያ እና ግድግዳ ያለማወቅ። ይቸግራል። "" "" "" "" " ይጠባል። " "" "" "" " ብፁዑ አባታችን እንደ ሰው፤ እንደ ብሄራዊ ዜጋስ አስተያዬት የመስጠት መብታቸው የማን ይሆን? እንደ ተሰጣቸው ሰማያዊ ቅብዓስ በክህነታቸው፤ በሥልጣነ ጵጵስናቸው ልጆቻቸውን የመገሰጽ መብት ማን ይሆን የሚመድብላቸው? ይህም ብቻ አይደለም የሚያጽናኑ ብፁዓን ናቸው መንግሥተ ሰማያትን ይወርሳሉ ያለው ቅዱስ ቃሉ ህይወት ዘርቶ ትንፋሽ የሆነበት ዘመንንስ አዳራሻውን የማሳጣት ሥልጣነ ክህሎቱ የማን ይሆን? እኔማ ሁሉንም አዳመጥኩት። ምንም ሳልጨምር ቃልም ሳልተነፍስ ከእኔ የቀደሙትን፤ የእኔን ዘመን፤ እኔን ተከትሎ የመጣው ትውልድን ገፀ ባህሬ በውን ስላዬሁበት ቀድቸዋለሁኝ። ለታሪክም አስቀምጠዋለሁኝ። ከእኛ ቤት እንኳንስ ጵጵስና የእኔ ቢጤ ባተሌም ዘቅዝቆ፤ ኤክስ አድርጎ ማቅረብ ስለማይፈቀድ መራራ ስንብት ሆኗል። እርግጥ ነው አክብረው ያዘኑበትን የገለፁ እህት እና ወንድሞቼ ግን መብታቸው ስለሆነ አክብ...