#የቁልል #ዕፍረት ማጣት በበርሊን።

#የቁልል #ዕፍረት ማጣት በበርሊን።
 
 May be an image of 4 peopleMay be an image of 4 people and animal
ማንበቡም፤ ማድመጡም የተፈራ ትግሉማ እንዴት ይደፈር????No photo description available.May be an image of 8 peopleMay be an image of mushroom and morel mushroom
ትናንትና በቅኔው ጎጃም በወበራ አዝመራ በመከወን ላይ የሚገኙ ትንታጎቹ የኢትዮጵያ ጉሮሮወች የጎጃም አርሶ አደሮች በፋሽስት አነጋዊ ኦህዴድ መንግሥት ሠራዊት በግፍ በባዕታቸው መረሸናቸውን ኢኤምኤስ ዘግቧል።
 
ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አለማፈራቸው ይገርመኛል። ሰሞኑን በርሊን ጀርመን ነበሩ አሉ። የገረመኝ ከውጭ ጉዳይ ሚር አንሰው ኢትዮጵያ ምድር ላይ አቀባበል የተደረገለት የጀርመን መንግሥት ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድን የጀርመን ካንስለር በክብር አቀባበል እንዳደረጉላቸው፤ እንደተቀበሉ አዳምጫለሁኝ። ቅጣቱ የህሊና ይመስለኛል ለጎግ ማንጉጉ የኢትዮጵያ የፕሮቶኮል አልቦሽነት።
 
የሆነ ሆኖ ህዝቡን በድሮን የሚጨፈጭፍ ፍፁም ጨካኝ፤ ገበሬው እርሻ እንዳይሠራ ማዳበሪያ የከለከለ፤ በእርሻ ወቅት በባዕቱ ሄዶ ጦርነት የገጠመ፤ ልጆቹ ከ12993 በላይ ለ12ኛ ክፍል ፈተና አትቀርብም ብሎ የቀጣ፤ ስንት አሳር አይተው ተምረው ዩንቨርስቲ የገቡ የአማራ ልጆችን ድብዛ ያጠፋ፤ ያሠረ፤ ያገተ፤ ያንገላታ፤ በመድፍ የፈጄ፤ በራህብ የሚቀጣ፤ በማደህዬት የሚበቀል፤ መጽናኛ የዕምነት ቦታወቹን ያረከሰ፤ ህዝብ ወቶ ለመግባት ዋስትና መስጠት የተሳነው #ቁልል በበርሊን መገኜት ዓይን በጥረጨው ማሸት ብሂሉ በውን የተገለጠበት ሂደት ነበር። 
 
በጣም የሚገርመኝ አቶ ቀን፤ ባላንባራስ ሳምንት፤ ደጃዝማች ወራት እንዲህ አረመኔን ከረባት እና ገበርዲን አጎናጽፈው አደባባይ ማዋላቸው ብቻ ነው። ለዚህ የሰገዱ ኑዛዜወች ደግሞ አደግድገው አገልጋይ ሆነው ማይክ ጨብጠው መገኜታቸው ነው።
1) የተመረተ የእግዚአብሄር አዝመራ የሚያነድ፤
2) ያለን የሚያራቁት በቅናትም የሚዘርፍ፤
3) ቅርስን በበቀል የሚያወድም፤
4) ሃይማኖትን በማን አንሼ የሚዳፈር፤
5) መፈናፈኛ የነሳን እሩጉም በንግግር መክላት ይቻል ይሆን?
6)ማዳበሪያን የሚያግት፤ በተፈጥሮ መብቀሉም የሚቆጨው፦
7) እራህብን ድርቅን ደብቆ ህዝብ የሚፈጅ፤
8) ከተሞችን አንድዶ አመድ የሚያስተቃቅፍ፦
9) ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና አማራን ለመጨረስ የማይደክመው፤ ጥዲፊያ ላይ ያለ ደራጎን፤
10) ሊለምኑ ዬፈሩ ሚሊዮኖችን አስቀምጦ ሰርክ በግብረ ሰላምቅብጥ ቅልጥ የሚል፤
11) በቁጭት እና በንዴትስ ይገፋ ይሆን? ጥያቄ ነው። ያለንበት ሁኔታ እና ዙሪያ ገባው ፍዳ በቁንጽል ተከታትፎ፦ ተቀረጣጥፎ
ሲብከነከን ስለማስተውል።
12) ለቅዱሳን እንሰሳት አዘኔታ ላልፈጠረለት፦
13) አይዟችሁን ለማያውቅ ፍፁም አረመኔ፦
14) ማቅ መልበሳችን ፌስታው የሆነ ጽልማሞት፦ እዬገዛ፤ እያረደ፤ እዬረሸነ፤ እያገተ፤ እያፈናቀለ፤ ዘር እዬመነጠረ፤ ሁለመናችን እርቃኑን እያስቀረ ………
 
መከራው ካለበት ለመድረስ ቀርቶ ሙቀቱ #ለብም አላደረገንም። ለምን? መሃል መንገድ ደክሞን ሁሉንም እርግፍ አድርገን የተውነው ወዘተረፈ ነን። ለመሆኑ ማህል ላይ ያሉትም ዬተያያዘ የልብ የሚያደርስ ስክነት ላይ ናቸው እንል ይሆን? እኔን ስለማይገባኝ ነው እምጠይቀው?
 
#ኢትዮጵያ #በጠላት #አገር #ብትወረር #ከሚደርሰው #የከፋ #ሁኔታ ላይ መገኜታችን በቅጡ ገና ገና አልገባንም። ዊዝደም።
የሚቀናው ውግዘቱ፤ ግለቱ እና ዱላው ላይ ነው። ልክ እንደዛ ትጋቷ ተግባርን ተከታታይ ማድረጉ ላይ ስለምን #ዳም #ቃ ተባለ???
"ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ።"
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
21/11/2023
ጉዟችን ለሥር ነቀል ለውጥ ብቻ!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።