ካቴና ያሉት ሳይደክሙ፤ ጫካ ያሉት ሳይዝሉ እኛ ግን ተዳከምን። ምን ነካን?
እንዴት ናችሁ? ካቴና ያሉት ሳይደክሙ፤ ጫካ ያሉት ሳይዝሉ እኛ ግን ተዳከምን። ምን ነካን?
የእኛ ቤትማ በረድ መሆን ከጀመረ ቆያዬ። በቃ ሁሉም ነገር ተረሳሳ። አባት ታዲወስም ተዘነጉ፤ መስኪም ተረሳች፤ ጎበዙ ጎበዜም ተረሳ፤ ሁሉንም እርግፍ አድርገን ትውት።
አሁን አሁንማ ሳስበው እኔ ስለጥፋቸው ሁሉ አሰልቺ እንደምትሉኝ እያሰብኩኝ ነው። የሆነ ሆኖ ነፃነት በአፍላ፤ በወረት በወፍ አወጣኝ አይገኝም። የቆረጡ፤ የፀኑ የትውልድ ፈርጦች በትጋታቸው በትትርናቸው የሚያስገኙት ሰማያዊ ፀጋ ነው። መኖራቸውን፤ ቤተሰባቸውን፤ ተስፋቸውን እራሳቸውንም ገብረው።
ማገልገልን የመሰል የጽድቅ ጎዳና የለም። በተለይ በነጣ ሲሆን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
21/11/2023
#ክብር በብላሽ አይገኝም።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ