የዴሞክራሲ ሎተሪ ቢደርስ እንደምን በኢትዮጵያ ምድር ይስተናገድ ይሆን? ጓዘ ቀላል ጥያቄ።
የዴሞክራሲ ሎተሪ ቢደርስ እንደምን በኢትዮጵያ ምድር ይስተናገድ ይሆን? ጓዘ ቀላል ጥያቄ።
ከአንቀጸ ብርኃን የኢትዮጵያ ሊቀ ቅዱስ ያሬድ የተወሰደ እንዲህም ይላል ………
"የአምላክ እናት ምስጋና፤ በዕውነተኛ ፈራጅ በአምላክ እናት ምስጋናና ይገባታል።"
የእኛን ነገር እሷ እምዬዋ ድንግልዬ ታሰናዳው እንጂ እኛስ አላወቅንበትም።
ብፁዑ አባታችን እንደ ሰው፤ እንደ ብሄራዊ ዜጋስ አስተያዬት የመስጠት መብታቸው የማን ይሆን? እንደ ተሰጣቸው ሰማያዊ ቅብዓስ በክህነታቸው፤ በሥልጣነ ጵጵስናቸው ልጆቻቸውን የመገሰጽ መብት ማን ይሆን የሚመድብላቸው? ይህም ብቻ አይደለም የሚያጽናኑ ብፁዓን ናቸው መንግሥተ ሰማያትን ይወርሳሉ ያለው ቅዱስ ቃሉ ህይወት ዘርቶ ትንፋሽ የሆነበት ዘመንንስ አዳራሻውን የማሳጣት ሥልጣነ ክህሎቱ የማን ይሆን?
እኔማ ሁሉንም አዳመጥኩት። ምንም ሳልጨምር ቃልም ሳልተነፍስ ከእኔ የቀደሙትን፤ የእኔን ዘመን፤ እኔን ተከትሎ የመጣው ትውልድን ገፀ ባህሬ በውን ስላዬሁበት ቀድቸዋለሁኝ። ለታሪክም አስቀምጠዋለሁኝ። ከእኛ ቤት እንኳንስ ጵጵስና የእኔ ቢጤ ባተሌም ዘቅዝቆ፤ ኤክስ አድርጎ ማቅረብ ስለማይፈቀድ መራራ ስንብት ሆኗል።
እርግጥ ነው አክብረው ያዘኑበትን የገለፁ እህት እና ወንድሞቼ ግን መብታቸው ስለሆነ አክብሬ ትቻቸዋለሁም። እረኛም ከበጉ፤ በጉም ከእረኛው ልክን ደረጃን ጠብቆ መነጋገር በጎ ስለሆነ። ከሁሉ በላይ እመ ቅኒት፤ እመ እዮቢት ቅድስት ተዋህዶ የደረሰባትን፤ ያለችበትን ጥልማሞት ዘመን በማስተዋል መዋጀትም ይገባል። ብዙ በጣም ብዙ የከፋ ቀናት ይጠብቁናልና። ሌላው በርሃ ለበርኃ የሚንከራተተው ደግ ህዝባችን እና ተስፋውንም በማስተዋል ማሰብ ይገባል። ግን መጀመሪያ የራሳችን ጉድፍ ብናጥበው ባይ ነኝ።
#ሌላው እና ግን ግን። ………
……… አንድ ሰው አንድ ድምጽ እያለ እድሜውን በፖለቲካ የፈጄ አንድ ሞጋች ሲገጥመው ልክ እንደ ጠላቱ ያዬዋል። ያሳድምበታል። ያስገልለዋል። እራሱም ጭስ ንድድ ይላል። ይህ የታዘብኩት ዕውነት ነው።
ሌላም ላንሳ 120 ሚሊዮን ህዝብ በአንድ ቱቦ ይንዶልዶል ባዩ እከሌ ተከሌ የለበትም። ከሊቅ እስከ ደቂቅ የእሱን ጭንቅላት ለሌላው ካልገጠመ ፖለቲካዊ ብስለት አይመስለውም። ይህም ከሊቅ እስከ ደቂቅ የሚታመስበት ነው።
የሚገርመው የጊዜ ዑደት እንዳለም አይረዳም። አይደለም ታች አምና እና ዘንድሮ በደቂቃወች ልዩነት እንደ ጊዜው ሁሉ አቋም ሊለዋወጥ ስለመቻሉም ፋክቱን መቀበል የሚሳነውም ከሊቅ እስከ ደቂቅ ነው።
ሌላም ይነሳ በአንድ ጉዳይ ያልተስማማ ዘመኑን ሁሉ በዛው ሲቆዝም ቂሙን ቆጣጥሮም በተገኜው አጋጣሚ ያን መከረኛ መገዘግዝም፤ በዘወትሩ የሚስተዋለው ገጠመኝ ነው በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ህይወት።
ዴሞክራሲ የሁሉም የልሳን ማጣፈጫ ነው። ያን ያለውን ስቶ ስትሞግተው ያው አንጡራ ጠላቱ ሆነህ ትፈረጃለህ፤ ትረገማለህ ትተለተላለህ።
የሚገርመው ከሊቅ እስከ ደቂቅ ስስታምነቱ ነው። ሁሉም ሰው ወልዶ አሳድጎ አስተምሮ ስንቅ የቋጠረ ይመስል አንጋቹ፤ ሰጋጁ፤ አወዳሹ እንድትሆኑለት መሻቱ የራሱን ህሊና ይዞ በወረራ ደግሞ የሌላውን ህሊና ባለርስት ልሁን ብሎ ያዙኝ ልቀቁኝ ማለቱ ነው። በዚህ ውስጥ ወልደው ያሳደጉት እንኳን በጅ እንደማይል እዬታወቀ በሞፈር ዘምት ልጠቅልል መባሉ አሳፋሪው ገጠመኝ ነው።
ይህም ብቻ አይደለም እያንዳንዱ ዜጋ የራሱ ጌታ፤ የራሱ እንደራሴ ስለመሆኑ ጭርሱ አይታይም ወይንም አይመዘንም። አቶ እከሌ ወይንም እትዬ እከሊት እሷ /// እሱ የሚያስበውን /// የምታስበውን ካልታሰበ ውግዝ ከአርዮስ ነው። እርግማኑ ብቻ ሳይሆን ከቤተ እግዚአብሄር የገባ ውሻ ዓይነትም አለበት። በሂደት ሲያሙረቀርቁት እነሱ ትክክል ናቸው። ማን ነክቷቸው።
ከነጭቃቸው ዘው ብለው ሲያምስሉትም እነሱ አባ እና እማ ወራ ናቸው። ማን ሃግ ብሏቸው፤ አብዛኛው በዛ ውስጥ ሲዛግጥ ቆይቶ ወፍ አውጥቶት ቀድም ካለም ቀንድ ነኝም አለበት። በዚህ ውስጥ ደግሞ ያ መከራኛ ዴሞክራሲ አብረህ ውደቅ ተነስም አለበት።መሃከነ። መጥኒ ለእናት አገር ለሳይንሷ ፈላስፋዋ ኢትዮጵያ።
ኢትዮጵያ ዴሞክራሲው ቀርቶባት የአባት አደሩ መከባበር መከበር ቢችል በስንት ጣዕሙ። ከእኛ ቤት እግር ጥሎት ዴሞክራሲ የገባ ዕለት እሱን አያድርገኝ። ጭብጥብጡን አውጥተው እሳት ውስጥ እንደ ፕላስቲክስ????
ስለ ዴሞክራሲ የሚተጋው ከእሱ ሲደርስ አይሰራም፤ የሰበሰበውን ሲበትን ሆነ ያፀደቀውን ተዳፍሮ ቅጥልጥሉን ሲቀጣጥል ማን ጠያቂ አለበት። አጤ ነዋ።።
በዚህች ሁለት ቀን በብፁዑ አባታችን በአቡነ ኤርምያስ ማቱ ይወርዳል። ብፁዑነታቸው ሰው ናቸው። የተመረጡ ባለ ቅብዓ ሰው። እንጂ አክናፋት ያላቸው መላዕክ አይደሉም። በዕድሜም ለጋ ናቸው።በሳቸው ዕድሜ የሚታሰቡ ነገሮች ተፈጥሮዊ ናቸው በሳቸው ህይወት መከሰት አይቀሬ ነው። ከሁሉም ቋያ ላይ በግራ ቀኝ የተጣዱትም ብፁዑነታቸው ናቸው። እኛ የጨረቃ እንጀራ ጋጋሪ ነን። ወላፈኑም አይነካን እንኳንስ የጋመው።
የዛሬ ሁለት አመት እምዬ ብፁዑ አባታችን አቡነ ኤርምያስ/// ዛሬ??????? ቢያንስ እንደኛ መብት አላቸው፦ ያሻቸውን የመደገፍ፤ የፈለጉትን የመቃወም ብሎ ማሰብ እንደምን ይሳን? ጥድፊያው ለርግማን? ኦ! አምላኬ ዴሞክራሲን ኢትዮጵያ ምድር አፍልቀህ ጉዱን ሳታሳዬኝ እንዳትጠራኝ አደራህን። አሜን።
የሚገርማችሁን ልንገራችሁ። እኔ ሥርጉተ©ሥላሴ \\\ ሰብለ©ህይወት እማምንበትን አቋም ከመያዝ የሚያግደኝ አንዳችም ምድራዊ ኃይል የለም። ፈጽሞ። የሚሰማኝን እጽፋለሁኝ። በማምንበት ጉዳይ እተጋለሁኝ። ከሚመቸኝ አቋም ጋር እዘልቃለሁኝ። Punkt.
እኔ የሥላሴ ባርያ አምላኬን እና ህግጋቱን፤ የቅድስት አገር የሲዊዝ ህገ መንግሥት ሥር እንጂ ሲሞላ እና ሲጎድል ውሎ በሚያድር የግል ዕይታ እና የፖለቲካ አቋም ሥር ልሆን ፈጽሞ አልችልም። ለዚህም ነው በተከረከመ በይበቃኛል ህይወት ገድሜ የምኖረው። ነፃነቴ ይኽው ነው። ሌላው ይደግፍ ይቃወም። እኔ ግን የእኔ ብቻ ነኝ። የእኔን ራዕይ እና ዕይታ የማራምድ።
በተረፈ የሥልጣን እጮኛሞች ዴሞክራሲ ከእናንተ ዘንድ ጥሎት ለማዬት በእጅጉ እጓጓለሁኝ። ሽው እንዲያው ሽው እምርም ብሎኛል።
ስኩን ወዳጆቼ ቸር እደሩልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
21/11/2023
አቤቱ አማኑኤል አባቴ ሆይ! ቸርነትህን፤ ቅንነትህን፤ አድማጭነትህን አትንፈገኝ።አሜን።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ