19.11.2019 የኦዳ ኢንፓዬር ማፏሸኪያ ህወሃት ነው።

 

የኦዳ ኢንፓዬር ማፏሸኪያ ህወሃት ነው።
የኦዳ ኢንፓዬር ማፏሸኪያ ህወሃት ነው። ይህን ግርባው ብአዴን፣ ተደማሪው ግንቦት ሰባት እስከ ቲፎዞው፣ ሚዲያው ኢሳት፣ የኦዳው ኢንፓዬር መለከት ነፊ የአንድ አፍታ አወያይ ጦማሪ ስዩም ተሾመ ቀጥ ሰጥ ለጥ ብለው የማፏሸኪያ ብር አንባር በመሆን ያስፈፅማሉ።
ሁሉም ሰው ህሊና ያለው ሁሉ ከማፏሸኪያ እንቅልፍነት ያወጣው ዘንድ አምላኩን ይማጠን።
እኔ አፈንጋጯ ሥርጉተ ሥላሴ የኦዳ ኢንፓዬር ማፏሸኪያ፣ እንቅልፍ አማጭ ባለመሆኔ እግዚአብሄርን አመሰግናለሁ።
ህወሃትን በሚመለከት የራሱን ድርጅት በቅጡ መምራት ያልቻለው የአብይ መንፈስ እኔን በዛ ቦይ ውስጥ ማስገር ፈፅሞ አይችልም። ፕሮፖጋንዲስትም አልፈልግም። ቀስቃሽም አያሰኜኝም።
ምክንያት። ገና በልጅነት ዕድሜዬ በተደራጀ ፓርቲ በከፍተኛ ህዝባዊ የኃላፊነት ሆኜ ታግዬዋለሁ። ጫካውንም ካቴናውንም ስደቱንም አውቀዋለሁ። እነሱ ከህወኃት የሥልጣን ፍርፋሪ ለቃሚ ኦፋ በነበሩበት ጊዜ ሁሉ ሥርጉትሻ ህወሃትን ሞግታለች። የራሷም ወርቅ የሆነ አሻራ ከእነ ሙሉ ማስረጃው አላት።
አሁን እነሱም ከፖለቲካ ድርጅት ተቆጥረው የጭካኔያቸው መለበጃ አዲስ ፀረ ህወሃት ዘመቻ ቢጀምሩ ሸማ በዬዘርፋ እንደሚለበስ ሥርጉተ ሥላሴ ጠንቅቃ ታውቃለች።
ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ አንዲት ቀን ድርጅታቸውን መምራት ሳይችሉ ነው በአማራ አቅም የሚፎክሩት፣ የሚያቅራሩት። መቼ ነው እሳቸው ሙሉ ኢትዮጵያን የመሩት፣ ያስተዳደሩት? መቼ ይነገረና። እሩብ አገር እንኳን ይመራሉን?
ይህ አቅም ሲያንሳቸው በሴራ ፖለቲካ፤ በህዝብ ሰቆቃ መንበራቸው የማይደፈር አድርገው ለማሳዬት ይጥራሉ። ውሽልሽል። ጉዳዩ የውሽማ ሞት ነው። ገናና አገር እንዲህ ላርባ መሆን እንኳን ባልቻለ አቅም ልትመራ አይገባትም።
ህወሃት አረረም መረረም 27 አመት ገዝቶ በእኛ በአማራዎች የውስጥና የውጭ ተጋድሎ መቀሌ ከትሟል። ለዚህም ልበ ሙሉ ማስረጃ አለን።
በዚህ የህውከት ዘመን የህወሃት እጅ በፀረ አማራነት ሊኖር እንደሚችል ቢታወቅም መዋቅሩም ፖሊሲውም ያው ስለሆነ፣ ዘመነ የድንጋይ ዘመን ምልሰቱ ግን የ16 ኛው ዘመን የኦሮሞ የመስፋፋት እና የወረራ ትልም ስለመሆኑ እኔን መሰል ህሊና ላላቸው ጠንቅቀው የሚረዱት አመክንዮ ነው።
ስለዚህ ህወሃት ስለተጠላ ህወሃት እንዳይመለስ ከአብይ ጋር አብረን እናልቅስ ከሚሉት ፍዝ ማፏሸኪያወች ጎራ መዳበል ለአገራቸው ሉዑላዊነት ሲሉ በአርበኝነት የተሰውትን ሰማዕታት አጥንት አውጥቶ የማቃጠል ያህል ይሰማኛል። ውርዴትም ውርዴም ነው።
እስስቱ መንፈስ ጎንደሬዎችን ሲያገኝ በትዳር አጋርነት፣ አማራ ሲገኝ በተሸጠው የፖለቲካ ገብያ በእናት አማራነት ትርክት፣ እስልምና ሲገኝ ለአንድ ቀን ቤተ መንግሥትን ሳያዩ ያሸለቡት የአባት ሙስሊምነት የአረብ ዓለሙን ጨምሮ በኵሸት በማማለል፣ ክርስትና ሲመጣ ፕሮቴስታንትን ይዞ ሎተራውያን እስከ አውሮፓ ቀፍድዶ በማሳሳት፣ ፀረ አማራነት ሲመጣ ፀረ አማራ ኃይሎችን በተለዬ ጉርሻ ጠርንፎ በማስተባበር፣
ኩሽኛ ሲመጣ ፀረ ሴማውያንን አስተባብሮ በጠላትነት በማሰለፍ፣ ኦዶኛ ሲያስፈልግ ቤተኛ እና ባዕደኛ ተለይቶበት በተገኜው ብሄራዊ፣ አህጉራዊ ሉላዊ መዋቅር በራስኛ ዘይቤ በመውረር፣ አቅጣጪ።ጫዊ ሲመጣ ፀረ ስሜናውያንን በማቀናጀት እና በረቂቅ ስውር መንገድ በመምራት፣ ንጉሳዊ መንፈሶችን በቤተ መንግሥት ዕደሳት በማማለል፣
ሙሁሩ ሲመጣ የሁሉም ዕውቀት ባለፀጋነት እና በማይንድ ሴት ህልም በማስቀዘፍ ቀመር ቤተኝነትን አጉልቶ ኧረ ምኑ ቅጡ።
አንድ ሰው በወዘተረፈ ካራክረት እዬተልሞጨሞጨ፣ እንደ ገበታ ውሃ እዬዋለለ፣ እንደ ተልባ ሥፍር እዬተንሸራተተ፣ እንደ ላንቁሶ እዬተንዘላለጠ በአገር ውስጥ መፈናቀል ሪከርድ ሰባሪ በኢ ሰባዊነት አገዳደል ሻንፕዮን ተሁኖ በመቃብር ሥፍራ በሌላ ገፁ የሞት የብልፅግና ፓርቲ መሥራች እና የደም አሻጋሪነት?
የሚገርመው ነገር ተዘርዝሮ በማያልቀው የገመና የፕለይ ድራማ በዚህ ማህል ህወሃት አጀንዳ እንዲሆን ይፈለጋል። አቅም ለዛ እንዲባክን ይፈለጋል። የጅል ማህበርተኛው ኦርኬስተር መስርቶ ይጨፍር የኦዳ ኢንፓዬር። የአማራ ልጅ ግን ከልግጫ የፖለቲካ ማህበር በፍጥነት ወጥቶ አቅሙን ይቆጥብ። አቅሙን አያባክን።
አማራ ጥሞና፣ ልቅና፣ ልዕልና፣ ጥበብ ትውፊቴ ነው ካለ በዚህ ውስጥ ለመስከን እራሱን ያሸንፍ። የእራሱ እንደራሴ እራሱ ያድርግ። የራሱ ጌታም እራሱ ያድርግ። በመሆን ውስጥ ይፅና ይርጋ። እንጥፍጣፊ አቅም ከእሱ መንፈስ በተፃራሪ ለቆመ ማዋል አይገባውም። የማንም አጀንዳ ባይረስ ተሸካሚ እና የፎቶ ሞዴሎች ሸቀጥ ማራገፊያ ሊሆን አይገባም። ነፍስ ያለው ነፍስ የዘመን ሥጦታ የት ላይ እንዳለ ያውቀዋል። ለዛ አቅሙን ያበርክት። ይኽው ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።