ለፖለቲካ እስረኞች ማን ይሆን ጠበቃው? ስለምንስ ከአጀንዳ ውጪ ሆኑ???? #አልገባኝም።
ለፖለቲካ እስረኞች ማን ይሆን ጠበቃው? ስለምንስ ከአጀንዳ ውጪ ሆኑ???? #አልገባኝም ። "የቤትህቅናት በላኝ።" በሁሉም ዘርፍ ያለውን ሁነት ስከታተለው የፖለቲካ እስረኞች ጉዳይ #ባለቤት #አጥቶ ነው እምመለከተው። ሁሉንም አቅጣጫ ዳስሱት። በዬእስር ቤቱ ያሉ የፖለቲካ እስረኞች አጀንዳ የሚሆኑት በስሱ #የፍርድ #ቤት ቀጠሮ ሲኖራቸው ብቻ ነው። ይህ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ትግል #ያልተለመደ ተመክሮ ነው። ምክንያቱም የፖለቲካ እስረኞች ጉዳይ በዬትኛውም የትግል መስመር ያሉ ተቋማት፤ ንቅናቄወች፤ የፖለቲካ ድርጅቶች ሁሉ #በኽረ #አጀንዳ ሆኖ ነበር እማውቀው። ከእስር ይለቀቁ ዘንድ ህብረ ድምጹ #አህቲ ነበር። አሁን ግን ያ ህብረ ድምጽ የለም። ለምን ይሆን? ጥናት ስላላደረኩበት ያ ነው፤ ይሄ ነው ልል አልችልም። የሆነ ሆኖ ቢያንስ #የእስረኛ ቤተሰቦች እንግልት ላይ ስለመሆናቸው እንኳን ጉዳይ ሊሆን አለመቻሉ ይጨንቃል። ልጆች ያላቸው የፖለቲካ እስረኞችም አሉ። እነኝህ የእስረኛ ልጆች በትምህርት ገበታቸው ላይ ሊያሳድር የሚችለው የሥነ ልቦና ጫናም ከፍተኛ ነው። በሌላ በኩል ሁሉም እናት አለው እና ይህቺ #እናት በልጇ ሃዘን እንደ ተጎሳቆለች የሰይጣን ጆሮ ይደፈን እና አንድ ነገር ብትሆን #እርግማን ይሆናል። ጭራሽ በአብይ ዘመን የእስረኛ ፍቺ ድፍንፍን ያለ ጉድ ነው የሆነው። ምንም ፍንጪ የለም። ቢያንስ ለቤተሰቦቻቸው ተስፋ ይሆን ዘንድ የፖለቲካ እስረኞች ጉዳይ በግልም ሆነ በጋራ በሰባዊነቱ አጀንዳ ሊሆን ይገባል ባይ ነኝ። እርግጥ ነው #የቅን እና #ቀና ዜጎች #ስጋት በስሱም ቢሆን ትንሽ ይገባኛል። ልፋታቸው ሆነ ድካማቸው አድማጭ ማጣቱ፤ ከእስር የሚፈቱ ወገኖች ለህዝብ ድካም ዕውቅና ለ...