ለፖለቲካ እስረኞች ማን ይሆን ጠበቃው? ስለምንስ ከአጀንዳ ውጪ ሆኑ???? #አልገባኝም።
ለፖለቲካ እስረኞች ማን ይሆን ጠበቃው? ስለምንስ ከአጀንዳ ውጪ ሆኑ???? #አልገባኝም።
በሁሉም ዘርፍ ያለውን ሁነት ስከታተለው የፖለቲካ እስረኞች ጉዳይ #ባለቤት #አጥቶ ነው እምመለከተው። ሁሉንም አቅጣጫ ዳስሱት። በዬእስር ቤቱ ያሉ የፖለቲካ እስረኞች አጀንዳ የሚሆኑት በስሱ #የፍርድ #ቤት ቀጠሮ ሲኖራቸው ብቻ ነው። ይህ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ትግል #ያልተለመደ ተመክሮ ነው።
ጥናት ስላላደረኩበት ያ ነው፤ ይሄ ነው ልል አልችልም። የሆነ ሆኖ ቢያንስ #የእስረኛ ቤተሰቦች እንግልት ላይ ስለመሆናቸው እንኳን ጉዳይ ሊሆን አለመቻሉ ይጨንቃል። ልጆች ያላቸው የፖለቲካ እስረኞችም አሉ። እነኝህ የእስረኛ ልጆች በትምህርት ገበታቸው ላይ ሊያሳድር የሚችለው የሥነ ልቦና ጫናም ከፍተኛ ነው።
በሌላ በኩል ሁሉም እናት አለው እና ይህቺ #እናት በልጇ ሃዘን እንደ ተጎሳቆለች የሰይጣን ጆሮ ይደፈን እና አንድ ነገር ብትሆን #እርግማን ይሆናል። ጭራሽ በአብይ ዘመን የእስረኛ ፍቺ ድፍንፍን ያለ ጉድ ነው የሆነው። ምንም ፍንጪ የለም። ቢያንስ ለቤተሰቦቻቸው ተስፋ ይሆን ዘንድ የፖለቲካ እስረኞች ጉዳይ በግልም ሆነ በጋራ በሰባዊነቱ አጀንዳ ሊሆን ይገባል ባይ ነኝ። እርግጥ ነው #የቅን እና #ቀና ዜጎች #ስጋት በስሱም ቢሆን ትንሽ ይገባኛል። ልፋታቸው ሆነ ድካማቸው አድማጭ ማጣቱ፤ ከእስር የሚፈቱ ወገኖች ለህዝብ ድካም ዕውቅና ለመስጠት ያላቸው ቅንነት ድብ ያለ መሆኑ። የደከሙ ሰብዕናወች የሚሰጡት ቅናዊ ዕይታ ከቁጥር አለመግባቱ ሊሆን ይችላል።
ባጠቃላይ የጥረቱን ቀጣይነት ሁሉ ያመከኑ ያልሰከኑ ሁነቶች እንዳሉ አውቃለሁኝ። ግን ምንጊዜም ካቴና ላይ ላሉ የፖለቲካ እስረኞችን #ከህሊና #ማራቅ የተገባ አይመስለኝም። አሁን ባለው ሁኔታ ምን ያህል? እነማን በፖለቲካ ጉዳይ በዬክልሉ እንደ ታሠሩ እንኳን የተደራጄ መረጃ የለንም። በጣም የተዳከመ ሁኔታ ነው ያለው። #ለማን እና #ለምን ይሆን ደፍረው ሞግተው ለካቴና የተዳረጉት ሰብዕናወች የካቴና ማገዶ የሆኑት???
ግን ማህበረ ቅንነት እንዴት አደራችሁ? ደህና ናችሁ ወይ?
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
10/05/2025
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ