የማያረጀው የህወሃት #አሳቻ አና #አዘናጊ ቧልት። ህወሃት በመግለጫ የወጣለት #አክሮባቲስት ነው።

 

የማያረጀው የህወሃት #አሳቻ አና #አዘናጊ ቧልት። ህወሃት በመግለጫ የወጣለት #አክሮባቲስት ነው። 
 
ዝም ብላችሁ ስታስቡት ሙሉ ፶ ዓመታት ኢትዮጵያ ምን ያህል ትሬኮላታ ሃሳብ ያዘለ መከራ ተሸክማ እንደ ኖረች ማመሳጠር ትችላላችሁ። ከዕዳም #የበለዘ እና #የማረተ ዕዳ። 
 
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 
ህወሃት ከፍጥረቱ እስከ ልደቱ፤ ከልደቱ እስከ ወጣትነቱ፤ ከወጣትነቱ እስከ ጉልምስናው፤ ከጉልምስናው እስከ እርጅናው፤ ከእርጅናው ምንአልባትም እስከ ህልፈቱ አሳቻው የህወሃት ቧልት ይቀጥላል። የሚገርመኝ ሴራ የዘለቀውን የነፍስ አድን ጥሪውን ተቀብለው መንፈሳቸውን የሚገብሩ ሰብዕናወች መኖራቸው ነው።
 
ህወሃት እንደ #እስስት ቀለሙን እዬቀያዬረ የፍዳ ማምረቻ ተቋምነቱ ቀጣይ ነው። መጥኒ አንቺ ኢትዮጵያ - የፈረደብሽ። በቅርቡ የመስተዳድር መሪ ለውጥ በውል ተደመጠ። አሁን እቴጌ ትግራይ በአዲስ አመራር ላይ ናት። ያው ዕድሏን ትሞካክረው እስኪ ፈጣሪ ይርዳት ብዬ ዝም ነው ያልኩት። 
 
ይህም ሆኖ በእቴጌ ትግራይ በዕድሏ፤ በዕጣ ፈንታዋ ላይ ግን መሪወቿ #አሳቻ ቧልታቸው ቀጥለዋል። ያለ መግለጫ አልባ ለህወሃት ህልፈቱ ነው። እንደምን መሽቶ ይነጋለታል? #ሱሱ መግለጫ ነው። የሚገርመው ጸንቶ የሚቆይ መንፈስ በመግለጫው አለመኖሩ ነው። የህወሃት መግለጫ የወጣለት አክሮባቲስት ነው። የህወሃት አካል ጥዋት አንድ ከሰዓት ከብት ግባት ማታ ለእንቅልፍ መዳህኒት ሌላ መግለጫ የተለመደ ነው በተለያዬ ሥያሜ።
 
የወረቀቱም የቀለሙም መከራው ጠንቷል። ህወሃት ዘለግ ያለ ምኞት ነው ያለው። አይደለም ዛሬ ሥልጣን ላይ እያለም ኢትዮጵያን እዬመራም፤ እስከ ጋንቤላ መጠነሰፊ ምኞት ነበረው። የወተት አንጀት የመሰለ ካርታ ሠርቶ ነበር። አባይን እስከምንጩ ለመቆጣጠር። ትልቁ የቀውስ ማዕከሉም ባለው ላይ ሳይሆን በሌለው ላይ ህልሙ ዕልቀተ ቢስ መሆኑ ነው። ውጤቱ ግን "የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች" ሆኖ መሻቱ ተኖ ቀረ እንጂ አቤቱ ህወሃት ምን የማይወጥነው ኮቴ አለና። 
 
የህወሃትን ፖለቲካ #አስታምሜ አድናለሁ፤ የጎበጠውን በፊትነስ ዱብዱብ አስተካክላለሁኝ፤ ወለምታም ቢገጥመው #ወጌሻን አክዬ፤ በአጥሚትም በመረቅም እጠግናላሁ ብሎ ማሰብ ከድንጋይ ላይ ውሃ ማፍሰስ ነው። ሊድን የሚችል አይደለም። በተለያዬ ሞድ እና ትወና -- መንፈስ፤ አካል፤ ህይወት ማስገበሩ ይቀጥላል። ህልፈቱ ቢመጣም ከቀብር መልስ አዲስ ስትራቴጂ እና ታክቲክ ሙት መንፈሱ ይፈጥራል። ዘመንም ሥልጣኔም የማይገራው #ችኮ ፈተና ነውና።
 
የሚገርመኝ #ሽንገላው ነው። ጄኒራል ታደሰ ወረደ የመስተዳድሩ ፕሬዚዳንት ናቸው። እሳቸው ሁለት፤ ሦስት ከዚህም ያለፈ ገጸባህሬ ይኖራቸዋል። ህወሃት ባህሉ እስስታዊ ገፀባህሬው የተፈጥሮው ገላጭ ምስክር ስለሆነ። እራሱ በነፍሱ ህወሃታዊ የሆነ መንፈስ የሚፈጥረውን ትርምስ፤ #ለብዶ አሻግሮ ለባዕድ ገላ መስጠት #ማጭበርበር ነው። የህወሃት መንፈስ ያደረበት ማንኛውም ክስተት ከገዘፈው እስከ ቀጨጨው ድረስ የሚመራው፤ የሚተነፍሰው የሚያምንበትም የህወሃት ፖለቲካ መሻትን መፈጸመ ነው። ጄኒራል ታደሰ ወረደ ማለት ዶር ደብረጽዮን ማለት ናቸው። 
 
እራሱን ተቃርኖ "ከውጭ መንግሥት ጋር የሚደረግ ማናቸውም ግንኙነት ኃራሜ ነው፤ እኔን አይመለከተኝም" ብሎ #የታደሰይዝም መግለጫ #ሽንገላ ነው። ማጭበርበርም ነው። ጲላጦስነት። ሽንገላው ከኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግሥት የሚያገኜው ማናቸውም ጥቅማ ጥቅም እንዳይቋረጥ። እስኪደራጅ እና አንድ እርከን እስኪሻገር ድረስ ለበጣ የተለመደ ነው።
 
በሂደቱ ማዕከላዊ መንግሥትንም ማዘናጊያ ነው። ሲፈጠር ህወሃት ዕውነት ሆኖ አያውቅም። አጤ ዕውነትም ህወሃትን አያውቀውም። አጤ ዕውነት የህወሃት ግጥሙ ስላልሆነ። ህወህት ፍጥረተ ነገሩ ይሁን መኖሩ ዕውነትን #ሸሽቶ ነው።
 
የሚገርመኝ ይህን ሽንገላ ከልብ እንደሆነ አድርገው የሚቀበሉ ገራገሮች መኖራቸው ነው። ሌሎች አማራጮችን ሁሉ ለማዬት የሚጨነቁ፤ የሚጠበቡ ተንታኞች አድምጫለሁኝ። በቅንነት ማዬት የተገባ ቢሆንም፥ ህወሃት ከቀበረ በኋላ ሃዘን ላይ እንደሚቀመጥ ልማዱ ነው። የህወሃት መንፈሱ ለዕውነት፤ ለሃቅ፤ ለግልጽነት ለትውልድ ተስፋ ሰጪ አይደለም። አቤቱ ህወሃት ያሸነፈ ሲመስለው ቀና ብሎ #መታበዩን ይቸረችራል። የሚጠቃ ሲመስለው አንገቱን ቀብሮ እንደ እባብ አፈር ውስጥ መሬት ለመሬት ይሄዳል። 
 
#ማሳጣቱ፤ ማሳደሙም ይታከልበታል። ሲጠቃ #የብሶት ፖለቲካ አራማጅ ይሆናል። ለዓለም ህዝብ የማሳጣት ሴራውን ይነሰንሰዋል። ፖለቲከኛ ነኝም፤ ተንታኝ ነኝም የሚል ሰብዕና በግልቡ ሳይሆን ሙሉ የህወሃትን ቁመና እና መንፈስ አደብ ገዝቶ ከቂም፤ ከበቀል፤ ከጥላቻ እራሱን ለይቶ ሊገመግመው ይገባል ትርፍና ኪሳራውን ከትውልድ አንፃር። 
 
በሌላ በኩል ምንጊዜም ህወኃት በአገኜው ቀዳዳ ሁሉ ህልሙን ለማሳካት ትጉህ ነው። አድብቶ እና አስልቶ የሚጠብቀውም ተፎካካሪ ሆኖ የሚወጣበትን አጋጣሚ ነው። የፋኖ ይሁን ሌላ የትግል መሥመር ከተሳካ ልምድም፤ ተመክሮም ያለኝ እኔ ነኝ ብሎ #ጠቃጥቆ ጥሶ በቀሉን ያሳካል። ታዬ እኮ ዕድል ሲያገኝ ብድሩ ያልተመለሰ ተቋማትን በጭካኔ ሲያነድ፤ ሲዘርፍ።
 
አቤቶ ህወሃት ቢማር፤ ተሽሎ ቢገኝ በእሱ ምክንያት የጠፋው የሰው ልጅ መኖር መከራ ቢጎረብጠው፤ የበደለው በደል ቢጸጽተው ኢትዮጵያዊ የዞግ የፖለቲካ ድርጅት ነው። የሁሉም የዞግ ድርጅቶችም ምንጭም ነው። ግን ህወሃት #የሚድንም#የሚያድንም ድርጅት አይደለም። የተመክሮው አቅም ዘመኑን ለሚመጥን የፖለቲካ #ሥልጣኔ አላበቃውም። እንዲያውም ኪሳራ ነው ድሌ ነው ጉዞው።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
 
መልካም ሰንበት። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
14/05/2025
ትዕግሥት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?