ልጥፎች

ከኦክቶበር 26, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

አላዛሯ እምዬ ኢትዮጵያ እናቷንም አገኘች።

ምስል
አላዛሯ ኢትዮጵያ ራሷን አገኘች። አላዛሯ ኢትዮጵያ እናቷንም አገኘች። አላዛሯ ኢትዮጵያ ውስጧንም አገኘች! „አድርገህልኛል እና ለዘላለም አመሰግንሃለሁ።“ መዝሙር ፶፩ ቁጥር ፱ ከሥርጉተ© ሥላሴ 26.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ·       መ ቅድመ አንስት። ኢትዮጵያ ዓለም ናት። ኢትዮጵያ መለያ ናት። ኢትዮጵያ ነባቢት ናት። ኢትዮጵያ ሥነ- ህይወት ናት። ኢትዮጵያ አናባቢም ናት። ኢትዮጵያ ተነባቢም ናት።፡ኢትዮጵያ ሥህነ - ነፃነት ናት። ኢትዮጵያ ብጡለ -ክብር ናት። ኢትዮጵያ የመሆን እጬጌ ናት። ኢትዮጵያ ጥልቅ ናት። ኢትዮጵያ የዕድማታ ቅኔ ማዕዶት ናት። ኢትዮጵያ ንጥር ትርጉም ናት። ኢትዮጵያ መነሻ መሠረት ናት። ኢትዮጵያ ሉላዊ ህሊና ናት። ኢትዮጵያ ድርብ ግርማ ናት። ኢትዮጵያ ህላዊ ሞገስ ናት። ኢትዮጵያ ስመኝሽ ናት። ኢትዮጵያ ስናፍቅሽ ናት። ኢትዮጵያ ተስፋ ናት። ኢትዮጵያ ተናፋቂ ፋና ናት። ኢትዮጵያ ትርጉም ናት። ኢትዮጵያ አዲስ አመት ናት። አገር ሃይማኖት ነው። አገር አካል ነው። ኢትዮጵያም ሃይማኖትም አካልም ናት። ኢትዮጵያ ውስጥም ናት። አዎን! ኢትዮጵያ ውስጧን እንሆ አገኘች። ውስጧን ብቻ ሳይሆን አላዛሯ ኢትዮጵያ እናቷን ጥበብ ሰጣት።  ለለበጣ ሳይሆን፤ ለፖለቲካ ፍጆታ ሳይሆን፤ ቀልብ ለማሳቢያ ሳይሆን፤ ለጊዜያዊ የሥልጣን ሹመት ሳይሆን ኢትዮጵያ ውስጧን ውስጥ ያደረገች እናቷን  በእርግጥም አገኘች። ኢትዮጵያ የኖረ የተከመረ መከራ ቢኖርባትም፤ ችግሯ እፍ ተብሎ በአንድ ጊዜ ባይተንም፤ ግን መተንፈሻ ቧንቧዋን አግኝታላች ብዬ አምናለሁኝ። የራሄልን ዕንባ የሰማ አምላክ እንሆ አደማጣት እላለሁኝ። ኢትዮጵያ የሚለውን ሥሟን መቀበል ጋዳ በሆነበት ዘመን፤ እንሆ አላዛሯ