#ፍቱን። • የአቶ በቀለ ገርባን #ጸረ ሰው የባቢሎን ግንብ ድምጥማጡን ያጠፋ ድንቅነት። የጸሐፊ ተስፋዬ ገብረአብ ፊክሽንም ነኮተ። • የህወሃትን ትብትብ ጸረ እኛነት ሴራ የበጣጠሰ ዕፁብነት። • ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።
#ፍቱን ። • የአቶ በቀለ ገርባን #ጸረ ሰው የባቢሎን ግንብ ድምጥማጡን ያጠፋ ድንቅነት። የጸሐፊ ተስፋዬ ገብረአብ ፊክሽንም ነኮተ። • የህወሃትን ትብትብ ጸረ እኛነት ሴራ የበጣጠሰ ዕፁብነት። • ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር። "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። ምዕራፍ ፲፯ #ዕፍታ ። ዛሬ ሦስት ዕርዕስን በአንድ ኃይለ ጎዳና "ፍቱን።" አዋዶ የሚገልጽ የጭብጥ ውርርስ ናፈቀኝ። ዓጤ ኢትዮጵያዊነት ዲካህ ያሳሳኛል! #ጠብታ ። ይህን የአቶ ፍጹም ፍሰኃ ቃለ ምልልስ እና የመምህር ሲሳይ ቤተሰብ ታሪክ አዳመጥኩት እስኪ። ሊንኩ ከሥር አለ። ከላይም ይደረጋል። ልዕለ ነውና። «ኢትየጽያዊ ሁሉ ሊሰማው የሚገባ ታሪክ ፥የብሄር ልዮነት አይገድበንም ፍቅር ይበልጣል #story #lovestory » https://www.youtube.com/watch?v=TRFKBTVzcRs የሲሳይ ዮቱብ ቻናል ይህ ነው https://youtu.be/uFWZD0avfVw?si=zMbBmggCobYfOW_u Ethio School Tube የአቶ ፍጹም ፍሰኃን ፔጁን ሳብስክራይብ ስላደረኩት ኖትፍኬሹኑ ስለመጣልኝ ብዘገይም አዳመጥኩት አርብ ዕለት። ይህን ያህል ግን ከደስታ በላይ ገኃዱን ዓለም እና ሰማያዊውን ዓለም የሚያገናኘውን ውስጣዊ #ሐሤት ይለግሰኛል ብየ አላሰብኩብም። አቶ ፍጼ የሚሠራበት መስክ ላይ ወድቆ እንደማያውቅ ባውቅም። በዚህን ያህልም የረጅም ጊዜ ህልሜን ከተመድም፤ ከአውሮፓ ህብረት ጋር የተፃፃፍኩበትን የፍቅር ተፈጥሮን ካሪክለማዊ የማድረግ ህልሜን በቃለ- ምልልሱ ውስጥ አገኛለሁ ብዬ አላሰብኩም። ለማድመጥ የዘገየሁት...