#ፍቱን። • የአቶ በቀለ ገርባን #ጸረ ሰው የባቢሎን ግንብ ድምጥማጡን ያጠፋ ድንቅነት። የጸሐፊ ተስፋዬ ገብረአብ ፊክሽንም ነኮተ። • የህወሃትን ትብትብ ጸረ እኛነት ሴራ የበጣጠሰ ዕፁብነት። • ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።

 

የአቶ በቀለ ገርባን #ጸረ ሰው የባቢሎን ግንብ ድምጥማጡን ያጠፋ ድንቅነት። የጸሐፊ ተስፋዬ ገብረአብ ፊክሽንም ነኮተ።
• የህወሃትን ትብትብ ጸረ እኛነት ሴራ የበጣጠሰ ዕፁብነት።
• ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር። 
 
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
 
ምዕራፍ ፲፯
 
 እሷን ለማስደሰት ያለችኝን በግ አረድኩላት #story #lovestory
 
 
ዛሬ ሦስት ዕርዕስን በአንድ ኃይለ ጎዳና "ፍቱን።" አዋዶ የሚገልጽ የጭብጥ ውርርስ ናፈቀኝ። ዓጤ ኢትዮጵያዊነት ዲካህ ያሳሳኛል!
 
ይህን የአቶ ፍጹም ፍሰኃ ቃለ ምልልስ እና የመምህር ሲሳይ ቤተሰብ ታሪክ አዳመጥኩት እስኪ። ሊንኩ ከሥር አለ። ከላይም ይደረጋል። ልዕለ ነውና። 
 
«ኢትየጽያዊ ሁሉ ሊሰማው የሚገባ ታሪክ ፥የብሄር ልዮነት አይገድበንም ፍቅር ይበልጣል #story #lovestory»
የሲሳይ ዮቱብ ቻናል ይህ ነው https://youtu.be/uFWZD0avfVw?si=zMbBmggCobYfOW_u
Ethio School Tube
 
የአቶ ፍጹም ፍሰኃን ፔጁን ሳብስክራይብ ስላደረኩት ኖትፍኬሹኑ ስለመጣልኝ ብዘገይም አዳመጥኩት አርብ ዕለት። ይህን ያህል ግን ከደስታ በላይ ገኃዱን ዓለም እና ሰማያዊውን ዓለም የሚያገናኘውን ውስጣዊ #ሐሤት ይለግሰኛል ብየ አላሰብኩብም።
አቶ ፍጼ የሚሠራበት መስክ ላይ ወድቆ እንደማያውቅ ባውቅም። በዚህን ያህልም የረጅም ጊዜ ህልሜን ከተመድም፤ ከአውሮፓ ህብረት ጋር የተፃፃፍኩበትን የፍቅር ተፈጥሮን ካሪክለማዊ የማድረግ ህልሜን በቃለ- ምልልሱ ውስጥ አገኛለሁ ብዬ አላሰብኩም። ለማድመጥ የዘገየሁትም ምክንያቱ ይህ ነበር። 
 
ቅኖቹ የእኔወቹ፤ ደጎቹ የኛወቹ እንዴት አደራችሁ? ቀደም ብዬ እንደ ገለጽኩት ለዛሬ ለቅዱሱ ሰንበት ልኩ የሆነ ቅዱስ ሰብዕና ታደምጡት፤ ከፈቀዳችሁ ከእነኝህ ውብ ቀንበጦች ትማሩበት ዘንድ ፈቅጃለሁኝ። እኔ ተመድን ፤ የአውሮፓ ህብረትን #የዛሬ 15 ዓመት በትህትና የጠየቅሁበት፤ የጸጋዬ ራዲዮን፤ ቲክቶኬን ሁለቱንም ዩቱብ ቻናሌን በዚህ አቅጣጫ የገራሁበት ሚስጢር ድርጊት ላይ #በዩንቨርሷ ኢትዮጵያ አገኜሁኝ። ተመስገን። 
 
#ክፋ ሃሳብ እና መርዙን መርታት ይቻላል፤ የህይወት ጀግና እንዲህ ሲገኝ።
 
ክፋ ሃሳብ ለእኛ አልተፈጠረም። የሰው ልጅ ጸድቆ እና ተቀድሶ በፈጣሪ አምሳል ነው የተፈጠረው። ግን ነገር ግን ያን ቅድስና፤ ያን ጸድቆ የተፈጠረ ሰብዕና የሚያስቀጥል ተቋም ዓለማችን የላትም። እና ክፋ ሃሳብ በምድሪቱ ነገሰ። እናም ክፋ ሃሳብ ክፋ ተግባሩ በረታ። ይህን ለመቋቋም ዓለም ለጦርነት የምታወጣውን ትርሊዮን ዶላር ቀንስ #ለፍቅር ተፈጥሮ የትምህርት ካሪክለም ነድፋ ልክ እንደ ሶሻል ሳይንስ እና ማህበራዊ ሳይንስ በመደበኛ ትምህርት ታስተምር። አንዱ ሙግቴ ይህ ነው።
 
ይህ ብቻ አይደለም #ወንጀል በረከተ። ምክንያት ኢትዮጵያን ጨምሮ የዓለም ህዝብ ህግን አያውቅም። ህግ የጥቂት ባለሙያወች ነው። ወንጀልን ለመቀነስ ይሁን ለማስቆም ህግ የማህበረሰቡ የዕውቀት ዘርፍ ሊሆን ይገባል ሁለተኛው ሙግቴ ነው። ለኢትዮጵያ አዲስ ትውልድ ብቻ ሳይሆን ለዓለምም መጪ ትውልድ ክፋ ሃሳብ፤ ወንጀል፤ ጦርነት ውርስ ሊሆን አይገባም። አንድ ሰው ግዴታውን ካላወቀ ግዴታውን ይጥሳል። መብቱንም በአግባቡ አያውቅም። ካላወቀው ጥቅሙንም ይስታል።
 
በዚህ አግባብ ስንሄድ አንድ ሰው በማያውቀው የህግ ድንጋጌ ጥፋት ቢፈጸም "አጥፊ" መባል እንዴት ሊሆን ይችላል? ብቻየን እምሟገትበት አመክንዮ ነው። የአንድን አገር ህገ መንግሥት ማንበቡ ብቻ በቂ አይደለም። ትርጓሜውን እና አፈፃጸሙን #በዕውቀት ማስደገፍ የግድ ያስፈልጋል። ዓለማችን ወንጀልን ለመቀነስ ካሰበች። ከወሰነች። አጀንዳዋም ከሆነ። ብዙ ጥፋቶችን፤ ብዙ ውድመቶችን ማስቀረት ይቻላል። 
 
ጆሮ ማድመጥ ከቻለ በርካታ ችግሮች ከመድረሳቸው በፊት መቅደም ይቻላል። ግን ወንጀልም ጥፋትም በረከተ።
መፍትሄው ከላይ በስሱ እንደጠቀስኩት ህግ የጥቂት ባለሙያወች ብቻ ሳይሆን፤ ከልጅነት ጀምሮ እያንዳንዱ የዓለም ህፃናት የአገሩን ህገ - መንግሥት እና የዓለም ዓቀፋን የሰብዓዊ መብት ድንጋጌ የታህሳስ 10/1948 እንደ ዕድሜው ደረጃቸው የትምህርት ሥርዓት ተነድፎለት ልጆች ከመዋለ ህፃናት ጀምሮ ሊማሩት ይገባል። 
 
መብት ምንድን ነው? ግዴታስ ከምን ይጀምራል? ይህ ሳይታወቅ እንደምን ከጥፋት መዳን ይቻላል። ስለሆነም ያለፈን እንደኛ ያለውም በቀበሌ ውይይት ሊያደረግበት ይገባል የእኔ ዕይታ ነው። ይህ ምኞቴ ተቋም ሆኖ በእነኝህ ሁለት ጥንዶች ተተርጉሞ አገኜሁት።
 
#በጥምር ህግ ለመዳኜት ፈቃደኝነት።
 
እኔ ኢትዮጵያ በተፃፈ ህግ እንደሚመሩት አገሮች በተፃፈ ህግ፤ ባልተፃፈ ህግ እንደሚመሩት አገሮችም ባልተፃፈ ህግ ትመራለች። የሃይማኖታዊ ህግም አለ። ጥምር ህግን የመቀበል አቅም ኢትዮጵያ አላት ብየ አምናለሁኝ። ለዚህም ነው ኢትዮጵያ ህግም ናት ብየ እምጽፈው። የፊዚክስ ምሩቋ ልዕልት የባለቤቷን እግር ጎንብስ ብላ ማጠብ በአማራ ማህበረሰብ ዘንድ ያለ ያልተፃፈ ህግ ውስጥ ነው መደቡ። ጥንዶቹ ህጋዊ ህጎችንም፤ ትውፊታዊ የአደራ ህግጋትንም ሥራ ላይ አውለው አግኝቻቸዋለሁኝ። ይህ ለእኔ ከድንቅ በላይ #ዕጹብ ነው። አሳዳጊወቻቸውን ይባርክ መዳህኒተዓለም። 
 
#ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነው። 
 
ስንቱን ዳጥ፤ ስንቱን ረግረግ፤ ስንቱን ወጀብ፤ ስንቱን የኢትዮጵያ ጉድጓዳማ ጎድጓዳም ምልከታ ተቋቁመው የፊዚክስ ሙሁራን እሚበሉት #እስኪያጡ ድረስ የእየሱስ ክርስቶስን የቀራኒወ ሚስጢር በገሃዱ ዓለም ተርጉመውታል። ወሸኔ። ማለፊያ ትንግርት። የጸረ ሰው የአቶ በቀለ ገርባ የመርዝ ባቢሎን ግንብም እንሆ ተናደ። ተመስገን። የሟቹን የጸሐፊ ተስፋዬ ገብረአብ በኢትዮጵያ ላይ የለቀቀው #አረማሞም ናዳ ተንኮታኮተ። ተመስገን። 
 
*** #አረማሞም እህል ዘርን ወደ ጠቀራ የሚለውጥ የአዝዕርት በሽታ ነው።
 
#የትውልድ። ስለትውልድ። ለትውልድ።
 
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ትውልድን የሚያምስበት የመኖር መሰናክልም እነኝህ ድንቆች ጥሰው ወጡ። ህወሃት የኦሮሞ ወጣቶች በአማርኛ ፊደል እንዳይመሩ፤ አማርኛ ቋንቋን ሃራማቸው እንዲሆን ያደረገበት የሴራ ኔትም እንሆ ተበጣጠሰ። ተመስገን ልዑል እግዚአብሄር ሁሉ ይቻልኃል። የአክብሮትን ልዕልና የታምር ያህል ማዕረግ አገኜ። የሰብአዊነትን ልክ በአብነት ጎመራ። 
 
የኢትዮጵያዊነትን ልቅና የፍቅር ተፈጥሮ እንዲህ ገቢር ሲያገኝ የውስጥ ሰላም በፍጹም ሁኔታ ይሰፍናል። እንኳንም ሰነበትኩ። እንደተከፋፋሁ አፈር አለመቅመሴን ወደድኩት። አምላኬንም አመሰገንኩት። 
 
በዚህ ዘመን የሰመራ ዩንቨርስቲ የፊዚክስ ምሩቅ ርህርህት እናቷን ለማስታመም ሥራዋን መተው እኔኑ መረመረኝ። ለኢትዮጵያ ድምጽ አልባ እናቶች ብየ በብዙ ያስከፋኋትን ወላጅ እናቴ እሙኃይ የእሽታ ልዕልቴ እብየ ሆዴ ይቀር በይኝ። የት አግኝቼ ድፍት ክንብል ብዬ ይቅርታሽን ልቀበል??? 
 
ይህቺ ድንቅ፤ ይህቺ ተደሟዊት ትዳሯን ለማስቀጠል ከፊዚክስ መምህርነት #ጉልት ገብያን መምረጥ፤ ትምክህትን፤ መታበይን አሸንፋ እንደ አባት አደሩ ጉንብስ ብላ የባለቤቷን #እግር አጥባ የምትስም ሚስት በከተማ ማግኜት #ድርሳን ነው ለእኔ። እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ የተነሳችው እኮ ከዚህ መሰል የደግነት መንበር ነው። ስለሆነም አዲስ የትምህርት ካሪክለም ነው ለትውልዱ። 
 
ኢትዮጵያዊው ትውልድ ይህ ዩንቨርስቲው ሊሆን ይገባል። ይህ ኮሌጁ ሊሆን ይገባል። ወገቧን በመቀነት ሸብ አድርጋ እናት አገሯን ኢትዮጵያን ከውስጧ ሰንቃ መሆንን አስቻለችው እቴጌዋ የጎጃሟ ቅኔያዊት። የ2018 ምርጥ የማርች ፰ የመጋቢት 29/2018 ዓም የህሊና ተሸላሚ ልትሆን ይገባታል። 
 
ከፈረስ ግልቢያ ሱስ፤ ከመልካምነት ባለ - ራዕይነት፤ ከንጽህና ጋር የተወዳጀው መምህር ሲሳይን የመሰለ የትዳር አጋር ማግኜትም እንደገና መፈጠር ነው። በትክክል እኔ እምፈልገው ትውልድ ይህ ነው። ለቀደሙት የተመድ ዋና ጸሐፊ ክቡር አቶ ኪም ሃሳቤን ስጽፍላቸው እስኪ ለአገርሽ መንግሥት አማክሪ ብለውኝ ነበር። 
 
ጉዳዩ ፖሊስ ይጠይቃል የሚል መልስ በአድራሻየ በፖስታ ቤት ላኩልኝ። ህወሃት ይገዛ ስለነበር አልሞከርኩትም። በለውጡም ተስፋ ነበረኝ። ግን አልሆነም። 4ኛው// 5ኛው// 6ኛው// 7ኛው መጽሐፌ ስለ ትውልድ፤ ለትውልድ ስለመሆን ያዘክራሉ። መነሻቸውም መዳረሻቸውም ትውልድ ነው። ለመነሻ የሚሆኑ ደግ ሃሳቦችን መፃህፍቱ አላቸው። እንዲህ ዓይነት በተፈጥሯዊነት የለመለመ ትውልድ የአቅጣጫየ ማህለቅ ነው። ተፈጥሮ ውብ፤ ድንቅ እና ዕፁብ ነው። ድህነትም እንዲህ ያምርበታል የውስጥ ድንግልና እሺ ሲባል። 
 
ከህሊና ውስጥ ያለ የጥላቻ ሃውልት ተማረ - አልተማረ፤ ኖረው - አልኖረው ሚና የለውም። በዘርፋ ተከታታይ፤ ያልተቋረጠ መምህራዊ ተግባር በትጋት ሊከወን ይገባል። ሰሞኑን ቲክቶኬ ላይ " ክፋ ሃሳብ ላይ " ማተኮሬ ያልገባቸው ሰብዕናወች ጠይቀውኝ ነበር። አሁንም ቅድምም፤ ነፍሴ እስካለች ድረስ ለትውልድ ሁለገብ መከፋት እርካታ መራቅ፤ አለመረጋጋት መካሻው በክፋ ሃሳብ ላይ የሚወሰድ የፈቃድ የውስጥ ለውጥ ብቻ ነው። እግዚአብሄር ይመስገን እንደዚህ ያሉ እራሳቸውን ያሸነፋ፦ የፍቅር ተፈጥሮ ኤቲክስን የተረጎሙ፤ ያመሳጠሩ ህይወታቸው የሚያስተምር ድንቆች ሲገኙ ከሽልማት በላይ ናቸው - ለእኔ። ልዩ ስጦታ።
 
ክብራችን ይደመጥ። ክብራችን ዕውቅና እንስጠው። ለክብራችን እንሳሳ። ክብራችን ከጥላቻ፤ ከቂም እና ከበቀል ፈቅደን መፋታት ነው ጎዳናችን ሊሆን የሚገባው። የእኔ ውዶች ክብረቶቼ እረፍት ታገኛላችሁ እና ቃለ ምልልሱን አዳምጡት። የውስጥ መረጋጋት ፈጣሪው፤ የሰላም ራህባችሁን የመቋቋም ድርሻ ያለው ፃዕዳው #የእኛነት ህይወት ነውና።
 
በተረፈ ሰው መሆን በሰውነት ልክ በተቋምነት ከዚህ ህይወት ይገበያል እና ቲኒወቻችሁ ጋር ብታደምጡት ምኞቴ ነው። እኔ የድርጅት መሰረት ጋብቻ ነው ብየ አምናለሁኝ። የጋብቻ መሠረትም አዳም እና ህይዋን ናቸው ብየ አምናለሁኝ። ጄኔባ ዩንቨርስቲ በሲዊዝ የቅንጅት መሥራች ጉባኤም ፕረዘንቴሽኔ የተነሳው ከዚህ ላይ ነበር። ትዳር ላይ ብዙ ቅናዊ ተግባር መፈጸም ላዕላዩን ያነፃል፤ ያጸናልም።
#መምህር ሲሳይ ፖድካስት አለው። 
 
እዛም ገብቼ ሙሉውን አንድ መሰናዶ አዳመጥኩት። ትንሽ የገብያ ያህል ኦሮምኛ እችል ነበር። አሁን ጠፍቶኛል። የኦሮምኛ #ቃናው ግን ስለሚስበኝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን የኦሮምኛም የትግረኛንም መዝሙሩንም አዳምጣለሁ። የዚህ የልብ የሆነ ወጣት ኮንፊደንሱ፤ የሚዲያ ሰብዕና አቅሙ ከጠበቅኩት በላይ ሆኗል። የቤተሰብን ኃላፊነት እና ተቀባይነት የመወጣት አቅሙ ዓይነታ ነው። #ቢስ አይይብን። አሜን። አለባበሳቸው እራሱ ንጽህናቸውን ያዘምረዋል።
 
የመምህር ሲሳይ ድምጹ ወርቅ ነው። የአቀራረብ ሞዱ ልምድ ያለው ይመስላል። ማግኔት አለው። ሚዲያ ላይ በጣም እረጅም ጊዜ እንደመስራቴ ታለንትድ ነው ወጣቱ። ጸጋም አለው በአየሁት ልክ። እና አቤቱ #ፋና ምን ይጠብቃል እንደዚህ ዓይነት የውስጥ ንጽህና ያለውን ሕይወቱ መምህር የሆነ ደማም ሰብዕናን ወደፊት ማምጣ #ፍትኃት ነውና ይሰብበት።
 
የመምህር ሲሳይ የአማርኛ ቋንቋው ለዛ የቅኔው ጎጃም ነው። ከባለቤቱ እንደወረሰው ገልፆል። በጣም ጣፋጭ ነው። ለወደፊት ታሪኩን በመጽሐፍ መልክ በአማርኛ ቋንቋ ሊያሳትም እንደሚችል ተስፋ አድርጊያለሁኝ። ሰንበትን ለቅድስናው የሚመጥን ቅዱስ መረጃ ነው ያቀረብኩት። 
 
ባርች እህቴ ትናንት ፈቃዴን ጠይቃኝ ነበር። ሊንኩን ልላክልሽ ወይ ብላ። እኔ ግን ቀድሜ አዳምጨዋለሁኝ ስላት። እያለቀሰች እንዳዳመጠችው ነው የነገረችኝ። እሷ ከመዝሙር ውጪ አታዳምጥም። እጅግ ከጨመተው ማህበረሰብ ወገንም ናት። ግን #እኛነት እንደምን ናፍቋት እንደነበር ነው የተረዳሁት። ይህን ያክል ሰብዕናው ሙሉዑ የሆነ ድምጽ ለውስጥ ፈውስ የመስጠት አቅም አለው። 
 
#ሊንኩ። 
 
«ኢትየጽያዊ ሁሉ ሊሰማው የሚገባ ታሪክ ፥የብሄር ልዮነት አይገድበንም ፍቅር ይበልጣል #story #lovestory»
የሲሳይ ዮቱብ ቻናል ይህ ነው https://youtu.be/uFWZD0avfVw?si=zMbBmggCobYfOW_u
Ethio School Tube
////////////////////////////////////////////////
 
ይህ እኔ በጽኑው፤ በአጽናኙ፤ በአይዟችሁ ባዩ ኢትዮጵያዊነት ላይ ከሰራኋቸው ውስጥ ጥቂት መጣጥፎች እና ሥነ - ግጥሞች በድምጽ የተሠሩትን ለጥፌያለሁኝ። ምኞቴን በእነኝህ የትውልድ ሮልሞዴሎች አግኝቻለሁ። አምላኬን በበዛ አመሰግናለሁኝ።
• ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር። 
 
ኢትዮጵያዊነት የመንፈስ ንባብ ነው … ለእኔ!
ኢትዮጵያዊነት የደሜ ዕምነት ሥነ ሕይወት!
ዘቢበቤ ሥነ ግጥም ልዕልት ኢትዮጵያ ዘቢቤ ናት። ትክበርልኝ።
ኢትዮጵያ ማህለቀ ዕውነት!
ልበልሽ ይሆን ውዳሴ? ይመቸዋል እና ለነፍሴ፨ Sehnsucht, Heimwehe. (Dichtkunst.)
 
ቸር አስበን፥ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
16/11/2025
 
ተመስገን አማኑኤል አባቴ።
የፍቅር ተፈጥሮ ፍቱን ነው።
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
እሷን ለማስደሰት ያለችኝን በግ አረድኩላት #story #lovestory

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።