መጥኒ ለእናታዊነት።
መጥኒ ለእናታዊነት። • ዘገባው የBBC ነው። "በትግራይ ከሥራ ቦታ፣ ከመንገድ እና ከመኖሪያ ቤት እየተካሄደው ያለው አፈሳ የፈጠረው ስጋት" https://www.bbc.com/amharic/articles/c3vywvgnv2qo «የትግራይ ክልል ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ በትግራይ "የተመለመሉ" ወጣቶችን ለሠራዊት እያሰለጠነ መሆኑን ለቢቢሲ ትግርኛ ገልጾ የምልመላው ሂደት ግን "በክልሉ መንግሥት እንደሚፈፀም" ተናግሯል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው በክልሉ የተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ወጣቶች ከሥራ ቦታቸው፣ ከመዝናኛ ስፍራ እንዲሁም ከሕዝብ ትራንስፖርት ላይ በግዳጅ ተወስደው ወደ ተለያዩ ካምፖች መላካቸውን ተናግረዋል። ቅድሚያ ለሰብዓዊ መብቶች ኢትዮጵያ በበኩሉ የትግራይ ፀጥታ ኃይሎች በክልሉ መጠነ ሠፊ አፈሳ እና የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ እያካሄደ መሆናቸውን በመጥቀስ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ድርጊቶቹ ይፈጸምባቸዋል በሚል ከዘረዘራቸው አካባቢዎች መካከል፣ ሰሜን ምሥራቅ ዞን፣ ማዕከላዊ ዞን እና ምሥራቃዊ ዞን ይገኙበታል። ለሁለት ዓመታት የተካሄደውን ጦርነት ባስቆመው የፕሪቶሪያ ስምምነት መሠረት የተቋቋመውን ጊዜያዊ አስተዳደር በማፍረስ ከጦርነቱ በፊት የነበረው የክልሉ ምክር ቤት ሥልጣን ከያዘ በኋላ በህወሓት መሪዎች እና በፌደራል መንግሥቱ መካከል ውጥረት ተፈጥሯል። ተመልሶ ሥራ የጀመረው ፈርሶ የነበረው የትግራይ ክልል ምክር ቤት ሕጋዊ የፓርቲ ዕውቅናው የተሰረዘበትን የህወሓት ሊቀመንበር ደብረፂዮን ገብረ ሚካኤልን የክልሉ ፕሬዝዳንት አድርጎ የሾመ ሲሆን፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ያሉበት ሁኔታ አስካሁን በይፋ አይታወቅም። በዚህም የተነሳ በክልሉ ሌላ ...