ሃሳብ ጎዳና መሪ ነው፤ ስለምን ይፈራል?
ሃሳብ ጎዳና መሪ ነው፤ ስለምን ይፈራል? "በመጀመሪያ #ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሄር ዘንድ ነበር፥ #ቃልም እግዚአብሄር ነበር። ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሄር ዘንድ ነበር። " (ቅዱስ ዮሐንስ ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፩ - ፫።) #ምዕራፍ ፲፱። ሃሳብ ስለምን የቂም ፈል ማምረቻ - ለምን ይሆናል? ሃሳብ የፖለቲካ #መበቃቀያ ---- ስለምን ይሆናል? ሃሳብ ስለምን እንዲታመቅ ወይንም እንዲታቆር ይፈለጋል? የልዩነት ሃሳብ #ጠሐይን እንዳያይ ለምን ይበየንበታል? ሃሳብ ወልጋዳ እንኳን ቢሆን ገርቶ ህዝብ ጠቀም ለማድረግ እንዴት ያቅታል? ለመሆኑ ፖለቲካ ለሙጃው ወይንስ ለአቦካዶ? ፖለቲካ ለበቀል መፈልፈያ ወይንስ ለአብሮነት ማብቀያ? ፖለቲካ ለተፈጥሮ ህልውና ወይንስ ጥቃትን ለማበረታታት? ትትርናው ሃሳብን #በድቅድቅ ጨለማ እንዲከዘን ስለምን ይፈረድበታል? #ሰው ምንድን ነው? የቃል ስክነት አይደለንም? ቃል እኮ ሃሳብ ነው። ግን ግን ……… ሰው የሃሳብ ውጤት አይደለምን? " ሁሉ በእርሱ ሆነ፤ ከሆነውም አንዳችስ ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም። በእርሱ ህይወት ነበረች፥ ህይወትም የሰው ብርሃን ነበረች። ብርሃንም በጨለማ ይበራል። ጨለማም አላሸነፈውም። (ቅዱስ ዮሐንስ ከምዕራፍ ፩ ቁጥር ፫ - ፭) እኮ ጋብቻ ምንድን ነው? ጋብቻ ከሃሳብ አይደለምን የሚነሳው? እናስ --- ጋብቻ የትውልድ መሠረት አይደለምን? ሥልጣኔ - ታሪክ - ሃይማኖት - ባህል - ወግ - ልማድ ትውፊት - ዕምነት - ዕውቀት - መኖር - የሃሳብ ውጤቶች አይደሉምን? ይህ ከሆነ ለምን ሰው የተሰጠውን የማሰብ አቅሙ #ይታሠርበታል ? የማይገባኝም እንዲገባኝም የማልፈቅድለት በሃሳብ ዙሪያ ታቅዶ ...