በቅርጥምጣሚ አጀንዳ ላይ ጉጉሱ ይቁም!
· እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ። በ ቅርጥምጣሚ አጀንዳ ላይ ጉጉሱ ይቁም! ወኔው ከኖረህ ከኦሮሙማ ዴሞግራፊ ላይ ተነሳ! „ጠላቴ እንደ በደለኛ፣ በእኔ ላይ የሚነሳም እንደ ኃጢያተኛ ይሁን።“ (መጽሐፍ ኢዮብ ምዕራፍ 27 ቁጥር 7) ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergut©Selassie 07.02.2020 ከ ጭምቷ ሲዊዘርላንድ እምታ ! እምታ ሆነ ውሎ አዳሩ የኦሮሙማ ዘመን። ይልቅ ሳቅ በጠፋ በስንት ዘመኑ ቤቱ እስኪደባለቅ ያሳቀኝ ነገር የጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ የአበባቸው መታገት ነበር። እኔን¡ አሳዘኑኝ¡ ግንንግን እሰይ¡ ለአበባም ቀን ወጣለት በዘመነ „ብልጽግና¡“ ለካንስ እውነታቸው ነው „አንዴ ከሚያምር ውስጥ ገብተናል“ ማለታቸው። ግን እንዴት ናችሁ የኔዎቹ - ቅኖቹ የአገሬ ልጆች? ዛሬ እዚህ ፈታ ብሏል። ወጀብ ነበር የሰነበተው። አያችሁ ግን ዶር አብይ አህመድ እሳቸው ያሉበት ዓለም እና እኛ ያለንበት ዓለም የተለያዬ ሰለመሆኑ። እሳቸው ከቅድስተ - ቅዱሳን ገነታዊ መንበራቸው ነው ያሉት። ሞት፤ ሃዘን፤ ለቅሶ ሰምተው አያውቁም። እልልታ ነው በሳቸው ዘመን በቤተ - መንግሥቱ አና ብሎ የሚናኘው። ፐፐፐ! የሁለት ዓለም ሰዎች። ለዚህ ነው ከጁቪተር ሲሄዱና ሲመለሱ እምለው እኔ። ሌላው ግን ይህን መሰል መዝናኛ ለተደማሪ የፖለቲካ ሊሂቃን እና ለተደማሪ ሚዲያዎች ጥሩ ነው። ጭፍግግነታቸውን የሚከላ የመዝናኛ ክበብ። የተስፋ ጠቅላይ ሚኒስተራቸው ባዳጣቸው ቁጥር እኔን እያሉ! እነሱ በትርጓሜ ሲያቃኑ ልፋት ላይ ናቸው እና ያሉት። ስለዚህም ይህቺ የአበባ ፖለቲካ እንዲያው ዘና፤ እንዲህ...