በቅርጥምጣሚ አጀንዳ ላይ ጉጉሱ ይቁም!

·       እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ።
ቅርጥምጣሚ አጀንዳ ላይ ጉጉሱ ይቁም!
ወኔው ከኖረህ ከኦሮሙማ ዴሞግራፊ ላይ ተነሳ!
„ጠላቴ እንደ በደለኛ፣ በእኔ ላይ የሚነሳም እንደ ኃጢያተኛ ይሁን።“

(መጽሐፍ ኢዮብ ምዕራፍ 27 ቁጥር 7)
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergut©Selassie
07.02.2020
ከ      ጭምቷ ሲዊዘርላንድ 


    እምታ!


እምታ ሆነ ውሎ አዳሩ የኦሮሙማ ዘመን። ይልቅ ሳቅ በጠፋ በስንት ዘመኑ ቤቱ እስኪደባለቅ ያሳቀኝ ነገር የጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ የአበባቸው መታገት ነበር። እኔን¡ አሳዘኑኝ¡ ግንንግን እሰይ¡ ለአበባም ቀን ወጣለት በዘመነ „ብልጽግና¡“ ለካንስ እውነታቸው ነው „አንዴ ከሚያምር ውስጥ ገብተናል“ ማለታቸው።

ግን እንዴት ናችሁ የኔዎቹ - ቅኖቹ የአገሬ ልጆች? ዛሬ እዚህ ፈታ ብሏል። ወጀብ ነበር የሰነበተው።
አያችሁ ግን ዶር አብይ አህመድ እሳቸው ያሉበት ዓለም እና እኛ ያለንበት ዓለም የተለያዬ ሰለመሆኑ። እሳቸው ከቅድስተ - ቅዱሳን ገነታዊ መንበራቸው ነው ያሉት። ሞት፤ ሃዘን፤ ለቅሶ ሰምተው አያውቁም። እልልታ ነው በሳቸው ዘመን በቤተ - መንግሥቱ አና ብሎ የሚናኘው። ፐፐፐ! የሁለት ዓለም ሰዎች። ለዚህ ነው ከጁቪተር ሲሄዱና ሲመለሱ እምለው እኔ።

ሌላው ግን ይህን መሰል መዝናኛ ለተደማሪ የፖለቲካ ሊሂቃን እና ለተደማሪ ሚዲያዎች ጥሩ ነው። ጭፍግግነታቸውን የሚከላ የመዝናኛ ክበብ። የተስፋ ጠቅላይ ሚኒስተራቸው ባዳጣቸው ቁጥር እኔን እያሉ! እነሱ በትርጓሜ ሲያቃኑ ልፋት ላይ ናቸው እና ያሉት። ስለዚህም ይህቺ የአበባ ፖለቲካ እንዲያው ዘና፤ እንዲህም ዘንከትክት ታደርጋለች። የውነት አጋጥሟቸዋል ለእነ ተደማሪውያን! ማርጠቢያ ወይንም ማዋዣ ትዕይነተ - ማይክ! የውነት እኔም ስቄያለሁኝ። ያው ረጅም የሥልጣን ዘመን ባልመኝም።

የሰለቸኝ መልቲነታቸው እና ሰውን እንዴት እንደ ናቁት ያላቸው የግንዛቤ ልኬታ ነው። ያባጭላሉ። በተመክሮ ሆነ በልቅና ልዕልና ብዙ የሚበልጧቸው ሰዎች እንዳሉ ትዝ ብሏቸው አያውቅም። አድማጩ ቅይጥ Hetrogeneous መሆኑን አላስተዋሉትም። አገርን መምራት ስክነቱም አቅሙም ልዕልናውም ያላቸው ወገኖች አሉ ከግንባራቸው ውጭ ውጪ አገር የሚኖሩ።

የሆነ ሆነ ባሳለፍናቸው ሳምንታት የድንገቴው ተውኔት ባለሟል ኦሮሙማ ግራጫማ የሲቃ ጉዞውን በጥድፊያ ቀጥሏል። ጫን ያለውን መርግ ይለቅ እና ውሽክ የሚያደርገውን የአበባ ትዕይንት ይዞ ብቅ ይላል። ወይንም „የአንታገሰምን፤ ወይንም የፌስታል ፖለቲካ፤ ወይንም የወረጃ የለም ፖለቲካ፤ ወይንም 100 ሺውን አይማረኝ አልመረውንም፤ ወይንም ወላዊውን ሰቆቃ ለቀቅ ያደርግ እና“ ለማዋዣ ማስረሻ ይህችን መሰል ስብሰባ ያካሄዳል ወይንም ግብረ ሰናይ ድርጅት ተገኝቶ ሞድ ያሳያል። አይዋ ማስረሻ እንበለው ይሆን የሰሞናቱ የምክር ቤት ዲስኩር።  

ማዘናጊያ፤ ቀልብ መሳቢያ፤ ነፍስ መስረቂያ በቃ በዓይነት ነው በኦሮሙማ ፖለቲካ። ማስመሰሉን ሲያውቁበት። ግራጫማው የመቃብር ሥፍራ ዘመነ አብይዝም እንዲህ ነው። የልቡን ያደርሳል ያን ለማዳፈን ደግሞ ሌላ መጋረጃ ይከፍትና አዲሱን ተውኔት ያስነካዋል። ነባሩ የስቃይ ድምጽ ደግሞ ድብ ይላል። ከታገቱት የአማራ ልጆች መከራ ሳንወጣ የቤተ - ክርስትያን ቃጠሎ እና የለጆቿን ሰማዕትነት አዬን። ሰሞኑን ደግሞ አስኮባ እና የአዲስ አበባ ጽዳት እንጠብቅ ይሆን? አያልቅብት ጠቅላይ ሚኒስተር ነው ያለን።

ወይንም የሴክራትርያት ገዳ ንጉሡ ጥላሁን ከሥልጣን መነሳት እና የረ/ፕ ምህረቱ ሻንቆን ምደባ ወይንም የአቶ ካሳሁን ጎፌን የኃላፊነት ሽግሽግ እንደዛ ነገር። ወይንስ የምክትል ፕሬዚዳንት ምርጫ እና ክንብንብን? ክኒን ቢጤ። ግን ግን የትምህርት ሚኒስተሩን መሰላል ላይ አወጧቸው አዲስ ፖሊሲ ምንትሶ ቅብጥርሶ ብለው ከዛ ሲያልፈሰፍሷቸው አባጅተው አፈረጧቸው።

ልክ እንደዛ ገዳ ንጉሡ ጥላሁንን መሰላል ሰጥተው ኮፈሷቸው። አሁን የአዬር መንገዱ የተርሚናል ጉዞ ከቤተ መንግሥት እስከ ቦሌ የጃዋራዊው የአቶ ንጉሡ ጥላሁን ንግሥናቸው የታወጀበት ዕለት ነበር። ሙሉው ጉዞ በሚዲያ ላይፍ ላይ ይተላለፍ ነበር። ሰሞኑን ደግሞ አፈረጧቸው። „በሬ ሆይ እሳሩን አይተህ ገደሉን ሳታይ“ ለመሆኑ ሰሞኑን ግዳ ንጉሡ ጥላሁን ከረባታቸውን ቂቅ አድርገው ይሆን? ግን ማን ይሆን ባለ ሳምንት ደግሞ? ለገመዱም ለስንብቱም ለመፈረጡም?! ለሳጥንም?

እምታው! ዋይታው! ሰቆቃው ግን ቀጥሏል። የድምጽ አልባ እናቶች ዕንባ ይፈሳል እለት እለት። ሰቆቃው ፊት ለፊት ያለውን ብቻ ነው እያዬን ያለነው እንጂ ሀረር እና ድሬም መከራ ውስጥ ናቸው። እዬተቃጠሉ ነው ወገኖቻችን በቁማቸው። የገዘፈ ስቃይ ውስጥ ናቸው። የትራንስፖርት አገልግሎት ለአማራ እንዳይሰጥ ታግዷል። 

አማርኛ ቋንቋ የሚችል ተጓዥም ፍደኛ ሆኗል። አዬ ዴሞግራፊ እንዲህ እያለ ይመጣልኃል። አንተም ከኢህዴግ ግንባር በገለብጫ መኪና ወደ ብልጽግና የተገለበጥከው ደግሞ ተመስጠህበት ሥልጠና ላይ ነህ እንዳለህ አዳምጣለሁኝ? ? አረመኔነት በሰሜናር፤ በፓናል ዲስከሽን በአዳራሽ ይሽሞነሞናል።
በሰው መቀቀል መበልጸግ? እም። 

እኔ ማሽሞንሞንም፤ ማቅለጥም፤ ማቆላመጥም አልሻም ይህን የጭካኔ ጉዞ። ሰብዕናቸውን የጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ሰውኛ ነው ብዬ ባመንኩበት ሰዓት ሞግቻለሁኝ እሳቸውን ወግኜ። ለቁጥር የሚያታክት ጹሑፍም ጽፌያለሁኝ ለስለስ ያለ ወቃሳም ቢኖርበትም። እንዲህ መታመን በቁሙ ሲነድ ሲቃጠል ደግሞ በድፍረት እሞግታቸዋለሁኝ። ዘሃበሻ ከደፈረ ያውጣው። ካልደፈረም ይተዎው።

የድምጽ አልባዎቹ እናቶች ዕንባ እረፍት ይነሳኛል። ሰው በቁሙ እንዴት ይቃጠላል? በእኛ ዘመን? በዘመነ ናዚ አዲስ ታጋቾች ወደ ኦዎሾት ካንም ሲደርሱ አካባቢው የስጋ ጥብስ ይሸት ነበር ይላሉ በህይወት ያሉት ሲናገሩ። „የኦወሾቲዝ ሚስጢርም“ መጽሐፍም የገለጠው ሃቅ ይህን ነው። ፋሲለደስ 2ኛ መለስተኛ ደረጃ ት/ቤት እያለሁ ነበር እኔ ያነበበኩት መጽሐፉን። ዛሬ መሬታች ላይ እዬታዬ ነው።

በሃረሬ ክልል የሚኖሩ ኢትዮጵያዊ ዜጎች ስቃይ ውስጥ ናቸው። እዬተቃጠሉ ነው። ጠቅላይ ሚኒስተሩ ደግሞ አበባ ጠፍቷቸው አፋልጉኝ ላይ ናቸው። እሳት የታዘዘባቸው ነፍሶች፤ ተቋማትስ ማን ይፈልጋቸው።

 የሞጣ መስጊድ ቃጠሎ ላይ ወጥተው ተጎታች ካቢኔያቸውን አሰልፈው የተናገሩትን ስለምን ትናንት በቅድስት አርሴማ እና በቅዱስ ገብርኤል የተፈጸመውን ለምን ወጥተው አላወገዙም በአማርኛም በእንግሊዘኛም ስለምን አልጻፉትም? ማሳጣት የሚፈልጉት ሃይማኖትም፤ ህዝብ አለ። ጥበቃ የሚደረግለትም ቀውስ አለ። እንዲያውም በሞጣው መስኪድ ቃጠሉ ፈጣሪ ይመስገን የሰው ነፍስ አልጠፋም፤ በበቀደሙ ሌሊት ግን የሰው ነፍስ ጠፍቷል። እነኝህ ነፍሶች ለጠሚር አብይ አህመድ ዜጎች አይደሉም። 
   
ሌላ እቴ ተዚህ ላይ አንድ ነገር ትዝ አለኝ። አማራ ክልልም ሰላማዊ ሰልፉን የሚበቀል የገዳ ንጉሡ ቲም አንድ አዲስ ድራማ ከሰሞናቱ ይኖረዋል። ያልታደለ ነው የኦነግ ፖለቲካ ለክፉ ነገር ሌላ ተፎካካሪ ደግሞ ያዘጋጃል። የበታችነት ስሜቱ ነው ይህን የሚያስደርገው። ቀናተኛ ነው። ኦሮምያ ላይ አንድ ነገር ከተከሰተ አማራ ክልል መሰሉ ይከወናል። 

ስለሆነም ሰሞኑን ደግሞ አዲስ የጭካኔ ወይንም የውድመት ድራማ ይጠበቅ በአማራ ክልል። ሲመጣ፤ ሲከሰት ግን ተረጋግታችሁ እዩት። አታጯጩኹት። እዛው አጀንዳውን ለእነሱ አሸክማችሁ እናንተ በትጋታችሁ ልክ ቀጥሉ። የታገቱ ልጆቻችን ጉዳይን አትልቀቁት አጥብቃችሁ ሞግቱ። እርም ማውጣት ካለብንም ይነገረን።

ወደ ቀደመው ምልሰት ሲሆን አሁን የሞጣ የመስጊዱ ቃጠሎ ለዛ ፖለቲካ የታለመ ግብ ነበር። ለክፋት ፉክክር አቻ ፍለጋ። እንዴት አይነት ውሎ ጉዞው የጠፋ የፖለቲካ ቅርሽርሽ እንደሆነ ውልብልቢቱን ለመያዝ አትችሉም። ጥቃቱ መንግሥታዊ ነው። 

ለእስልምና ሃይማኖት ታዝኖ አልነበረም ያ ሁሉ መንግሥታዊ ቃለ ምልልስ። ትናንት የድምጻችን ይሰማ ኮሜቴዎችን ያሰሩ የጭካኔ ባላባቶች ናቸው ዛሬም ሥልጣን ላይ ያሉት። አይደለም ወይ? ለዛውም ቅዱስ ነን ፉከራም አለበት።

"News Analysis: Hidden Truth About Lemma Megersa"


ወደ ቀደመው አጀንዳዬ ምልሰት ሳደርግ አማራ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች እገታም እኔ እንደማስበው የዲሲው ህዝባዊ ስብሰባ ወስኖ የጀመረውን የጆኖሳይድ ክትትል የቁንጫን፤ የበቀል መወጣጫ ነው። ይህም እገታ ከኦሮሙማ መንግሥት ዕውቅና መንፈስ ውጭ ነው ብዬ አላስብም። የእኔ አስተሳሰብ ፈንገጥ ያለ ነው።  

·        አዲስ አበባ እርህርና ገጽታ በፅኑ ስለመታገቱ።

አዲስ አበቤ ልዩ ነው። የሰጠው። መንፈሱ ቅዱስ ነው። ስለ አዲስ አበቤ ርህርህና በተለያዬ ኮርስ ምክንያትም፤ ኖሬ ስላዬሁት የወጣለት ለጋስ እና አዛኝ ህዝብ ነው። በዘመነ ኦሮመሙማ እርህርህናው አደባባይ እንዳይውል ታግቷል። አያሳዝንም! ኮሚቴው ምልጃውን አሻም ካለ ይሄኔ በዓይነ ቁራኛ እዬተጠበቀ ይሆናል። 

እኔ እንደማስበው ብቻ ሳይሆን እማምንበትም አዲስ አበባን ለኦሮምያ ክልል በጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ትዕዛዝ ተላልፋ ተሰጥታለች ብዬ በጽኑ ነው እኔ እማምነው። ያው እንደ አባይ ወንዝ ፖለቲካ ማለት ነው።

የአቶ ሽመልስ አብዲሳ ጣሪያ የሚመተረው ከዚኸው ምንጭ ነው። ልባቸውን እንደ ፈርኦን ያደነደነው ሃቅ ይኸው ነው። አዲስ አበባ ሰልፍ እንድታደርግ የአቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የአማካሪያቸው የደቡብ ንጉሰ ነገሥት የምርኮኛው የአጤ አባ ዱላ ገመዳ ማህተም ያስፈልጋታል። 

ደግሞስ እርህርህና ለገዳ ምኑ ነው? ጀግንነት አሰጣጡስ በርህርህና ወይንስ በጭካኔው ልክ? አዲስ አበባም ዴሞግራፊውን ትተገብር ዘንድ ጭካኔውን እያባበለች እንዲህ ማስታመም ይገባታል ልምምድ ላይ ናት። አሁን አዲስ ተቋም ተከፍቶላታል ጥምቀተ - ሞጋሳ።
  
በጋዜጠኛ ማዕዛ መሃመድ የሚመራው የወጣቶች የርህርህና ሰልፍ አስተባባሪ ኮሜቴ የትልሙ ክልከላው የጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ እና የኢንጂነር ታከለ ኡማ የእዝ ሰንሰለት ጉዳይ አይደለም። መርኽ መጣስ የለበትም ባዮች ናቸው ኦነጋውያኑ። ምን ማለት ነው ይሄ? የአዲስ አበባ ህዝብ በኦሮምያ አስተዳደር ሥር ነው ያለው። 

ስለዚህ ትንፋሹን መወሰን ያለበት ለአዲስ አበቤ ኦሮምያ እንጂ ፌድራሉ ምን አገባው ነው ቁም ነገሩ? የስብሰባ አዳራሽም ፈቃጁም ነሹም የትዕቢተኛው ጃንቦ የአቶ ሽመልስ አብዲስ ካቢኔ መብት ብቻ ይሆናል።

ኦሮምያ እኮ አገር እዬመራ ስለሆነ አልታወቅ ብሎ እንጂ እንደ እቴጌ ትግራይ የራሱን መንግሥታዊ ሉዕላዊነት ያወጀ ክልል ነው። የትኛውንም ዓይነት ትዕዛዝ ካለመነበት አይቀበልም የፌድራሉን። የሚያሳዝነው ከዛ የሚኖረው ህዝብ አሁንም እዬተቃጠለ መሆኑን ነው። ረመጥ ሁኗል ኦሮምያ። ተቋማት ካለርህራሄ ይነዳሉ። የሰው ልጅ ይነዳል። መኖርም ይናዳል። ተስፋም በቃጠሎ ይጨሳል። አሳዛኙ ነገር ሀረሬ በሌላ ጦርነት ውስጥ ናት። ነዲዱ እዬተቀጣጠለ አገር አዳርሷል። እኛ ደግሞ እከሌ ተሸሞ፤ እከሌ ተሻረ በዛ ላይ ቸክለን እንቧከሳለን።  

እናቶች በግራ በቀኝ ጡንቸኞች አሁንም ያለቅሳሉ እዛው ኦሮምያ ላይም ወለጋ። እናቶች አሁንም በግራ በቀኝ ጉልበተኞች አሳራቸውን ይበላሉ ሀረሬ ላይ። የአሮሞ ሊሂቃኖቻቸው ደግሞ ከራባት፤ ገበርዲን፤ እና ማይክ ሸማታ ልባቸው ውልቅ ብሏል። ነፃነት ይሉሃል ይህ ነው፤ ብልጽግና ይሉሃል ይህ ነው፤ ለውጥ ይሉሃል ይህ ነው፤ አዲስ ዓለም ይሉሃል ይህ ነው። መንገድን ለማሳመር እነሱ አበባ ምርት ላይ ናቸው። ደስ አይልም¡?

አዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፉ የተጋደው ለአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ነው ተብሏል። አይደለም። በፍጹም አይደለም። በአፍሪካው ህብረት ስብሰባ ማግሥት ስለ ርህርህና ይፈቀድለታል አዲስ አበቤ ወይ ሲባል አይፈቀድለትም። በፍጹም አዲስ አበቤ አትሰበው። አዲስ አበባዊ ሆነ ብሄራዊ ሰልፍ እዛ ማዘጋጀት ፈጽሞ አይቻልም። ከኦሮምያ ፈቃድ ውጪ። ይህ ለአዲስ አበቤ ብቻ ሳይሆን በብሄራዊ ደረጃ ያሉ ማናቸውም የሃይማኖት፤ የሲቢል፤ የፖለቲካ ድርጅቶች ሁሉ የሚሠራ ህግ ነው።

ለጊዜው ስውር ነው ነገ ግን ይፋ ይሆንልሃል። „የቂጣም እንደ ሆን ይጠፋል፤ የልጅም እንደ ሆን ይጋፋል“ እንደሚባለው። ለዚህ ነው እኔ „ከፈረቃ፤ ከተረኝነት“ ፖለቲካ ይወጣ የምለው። ጉዳዩ የአዲስ አገር ምስረታ ነው። 

ህልሙ ልክ እንደ አውስትራልያ አህጉርነትም አገርነትም ነው። አሁን ለሽ ብሎ የተኛው አዲስ አበቤ ኑሮው በራሱ ላይ እዬፈረሰ ስለመሆኑ ገና አልታዬውም። አሁን ትናንትና በነበረው የሰማዕታቱ ቀብር ፆታም፤ ሃይማኖትም፤ ዕድሜም፤ ሙያም ሳይለዬው አዲስ አበቤ ግልብጥ ብሎ ወጥቶ ሰማዕታቱን መሸኜት ነበረበት። ያን ወርቅ አጋጣሚ መጠቀም ነበረበት። እርህርህናውንም ማሳዬት ነበረበት።

በግፍ የተገደሉ ልጆችን በክብር መሸኜት ክብር ነበር። በረከተም ነው። ይህ የሃይማኖት ጉዳይ ብቻ አልነበረም። የህልውና ተጋድሎም ነው። ሌላው ሰልፍ ሲታገድበት አዲስ አበቤው ቢያንስ በዝምታው ውስጥ ሆኖ ሰላማዊ የሆነ የትግል አጋርነቱን ማሳዬት ነበረበት - ትናንት። ግን አመለጠው። እራሱ የተያዘው ሰንደቅ ዓላማ የኦነጋውያኑን ፍላጎት የጠጣ ነበር። ዴሞግራፊ? ነገ ኦዳ ጉብ ብሎ ይመጣልኃል። ጠበቀው።

·        ይልቅ።

በዚህ ትዕይንት ያዬሁት አዲስ ነገር ይልቅ የቀብር ሥርዓቱ በቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት መዝሙር ነበር „ማርያም አዘነ ልቦና ታቀልል፤ ማርያም የልብን ሃዘን ታቀላለች ነው በአማርኛ ትርጓሜው። አንመካም በጉልበታችን እግዚአብሄር ነው የእኛ ኃይላችን“ በሚል ነበር። 

የባህርዳር ታዳጊ እና የወጣት ሰልፈኞች ስለ ታገቱ የአማራ ልጆች ጉዳይ በጥር 19 ቀን በ2012 ዓ.ም ጥቁር የለበሱ ነበሩ መድረኩን የመሩት ስለ ሴት ልጅ ጥልቅ ተፈጥሯዊ ጸጋ በዕድምታ ያመሳጠሩ የወል ድምፆችን በማሰማት ነበር። የደበረታቦሩ ደግሞ በ24 ቀን 2012 ዓ.ም ነበር የወጣቶች ሴቶች የለቅሶ ውሎ ነበር። ዕጹብ ድንቅ የሆነ ትውልድ ነው ያለው።

ኦሮሙማ ሁሉንም የሃዘን ዓይነት በረድፍ ረድፉ፤ በፈርጅ ፈርጁ እያለመማደን ነው። ማስተዋልን ብናውቀው ምን ዓይነት ዘመን ውስጥ እንዳለን ይነገረናል። እነሱ ባጣደፉን ቁጥር እኛ ሳንጣደፍ ተግ ብለን አንዷን ዘለላ አመክንዮ ብቻ አውጥተን በአስተውሎት ብምንመረምራት ብዙ አፍራሽ የበቀል ምርት እንደታጨቀባት መረዳት ይቻላል። ኢትዮጵያዊነት እግር ብረት ታዞለታል። ኢትዮጵያዊነት ታግቷል። 

ለእኔ በውጭ ጠላት እጅ እንደገባን ይሰማኛል። እነሱም አላፈሩበትም „ነፍጠኛን በሰበረን ቦታ ሰብረን  የአገሪቱን ዋና ከተማ ተቆጣጥረናል“ ብለውናል። ሁሉም ኢትዮጵያዊነትን ያቀሰሰ መንፈስ ሁሉ እግር ብረት ታዞለታል። ወከባ ታዞለታል። ፈተና ታዞለታል በበቀለኛው ኦሮሙማ።

የሚገርመው የግንዛቤያችን ወጣ ገብነት ነው። „ፈረቃ፤ ተረኝነት፤ የወያኔን የመሰለ“ ይልኃል አባወራው ፖለቲካ ተንታኝ። በፍጹም አይደለም። አፍሪካን ኦሮማይዝድ የማድረግ ተልዕኮ ነው። ለዚህ ነው እኔ የሶልዳሪቲ ትግል ያስፈልገናል የምለው። በእንግሊዘኛ ቋንቋ የሚሰሩ ማህበራዊ ሚዲያ ይኑሩም የምለው።

ይህ የወራራ አባዜ ህጋዊ ዕውቅና ለማስገኘት ሁለገብ ተግባር በጥድፊያ እና በችኮላ እዬተከወነ ነው። አገር ውስጥም ውጭም። ሽፋኑ ግን ኢትዮጵያዊነት ነው። በጠቅላይ ሚኒስተሩ ምላስ ላይ ያለው ወና ምራቅ። ግን ንደት ላይ ነህ። ውስጥህ እራሱ ንደት ላይ ነው። ወይ ተዳፈረው ወይንም ተደፈረው። ምርጫው የአንተ ነው።

ትናንት ቅድስት ኦርቶዶክስ በኦነጋውያኑ ካድሬዎች የተሰጣትን ሰንደቅ ይዛ ስትወጣ መሸነፏን አውጃለች ለእኔ። የዘመናት ሐዋርያዊት ቅድስት ኦርቶዶከስ ተዋህዶ ሃይማኖት ነፃነቷን 60 ዓመት ለማይሞላው የኦነግ መንፈስ ስትሸልም ያቃጥላል። ከሌንጮወዲማ ሥር ወድቃ የትንፋሽ ፍርፋሪ ምጽዋት ስትጠይቅ እንደ አንድ የተዋህዶ ልጅ ውስጥን ይበላል። „የቤትህ ቅናት በላኝ“ እንዳለው ንጉሥ ዳዊት።

ነገ ደግሞ ከብክበው ሸጉጠው የያዟቸውን በ2011 ዓ.ም ጥምቀት ላይ ቡራኬ እንዲሰጡ የተደሩጉትን ሊቀ - ጳጳስ ዓይኗ እያዬ ትሾማለች ለፕትርክና። ይህን አባይ ሚዲያ አርኬቡ ላይ ሄዶ መፈተሽ ነው ጥምቀት ላይ ማን ቡራኬ በ2011 ዓ.ም እንደ ሰጠ፤ የተሰጠው ቡራኬም በኦሮምኛ ነበር።

አሁን ማን ፈቀደላቸው ቀሲስ በላይ ታቦት ይዘው የሄዱት ይባላል። በውስጥ ታዋቂ እኮ ጳጳስ ኦሮምኛ ተናጋሪ አላቸው። ስሜን አሜሪካ የነበሩ። ከጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ጋር ሰፊ ቃለ ምልልስ አድርገው ነበር። ያ የሰብዕና ግንባታ ሂደት ነበር። አሁን የፓትርያርክያኑን ቦታውን ባዶ ስለማድረግም ያልማሉ። በሚከሉት ይከሉ እና አምጥተው ጉብ ያድርጓቸዋል። ሞትም አለ። ለዚህ ነው ጊዜ ስጡን ተማህጽኖው።

እንደ ልጅ በከረሚላ የሚታለል ሁነት ነው እኔ እማዬው በቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት አቨው። ጥበብ ተሰወረች። የኔታዋ ሞት ደጃፏ ቁሞ ተልፈሰፈሰች። በአቅሟ ልክ ብትንቀሳቀስ ይህን የኦነጋውያኑን መታበይ ታስተነፍሰው ነበር። ግን መሸብለል ሆነ። እግዚኦ ነው።   

·        ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና ተላላነቷ እራሷን ያሳጣታል።

ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና ተላላነቷ ህንፃውን ብቻ ተሸክማ እንዳትቀር እስገለሁኝ። አዲስ አበባ ላይ አይደለም አዲስ ቤተክርስትያን ነባሮቹም ስለመቀጠላቸው የጊዜ ጉዳይ ነው። ከእንግዲህ አዲስ አበባ ላይ አዲስ የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን እነጻ አይፈቀድም። ቢፈቀድም ተሰርቶ ሲያበቃ ይቃጠላል። መራራ ሊሆን ይችላል ቋንቋ አጠቃቀሜ ግን እውነቱ እሱ ነው።

አዲስ አበባ ላይ የተከለከለው የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሰላማዊ ሰልፍ ስለምን አማራ ክልል ብቻ ተፈቀደ? ይህም ብቻ አይደለም የራሺያ ኦርቶዶክስ አጋርነት እና የጠቅላይ ሚኒስተሩ የራሺያ ጉዞ ተልዕኮ ለዚህ ለተደሞ፣ ለእድምታ ሊቀ - ሊቃውንታት እኔ በምን አቅሜ መተርጎም ማመሳጠር እችላለሁኝ? ማፍታታት ከተዳፈነባቸው ሊቀ - ሊቃውንታት አምላካቸውን በሱባኤ ቢጠይቁ መንፈስ ቅዱስ ይነግራቸዋል በራዕይ ሆነ በሆነ መንገድ።

 „እግዚአብሄር በአንድም በሌላም መንገድ ይናገራል ሰው ግን አያስተውልም“ ይላል አካል የሌለው የእግዚአብሄር አገልጋይ። ቢያንስ የደወል ምህላ መጀመር እስቲ ትሞክረው ብዬ ጽፌ ነበር። ይፈቀድላት ይሆን ቢባል? አይመስለኝም። „ካለ አበደ በቀር ዱባ ቅል አይጥልም“ ይላሉ ብልሆቹ የጎንደር የሥነ - ቋንቋ ሊቀ - ሊቃውንታት። መሞከሪያም ይሆናት ነበር ስለመታገቷ የድወሉን ምህላ ብትጀምረው።
የኔታዋ የደወል ምህላን፤ ብትደፍረው፤ የአርሲ ነገሌ መስቀል ጉዞ ወደ ቀራንዮ።

አዲስ አበባ ላይ አንዲትም ስንዝር ከኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ፈቃድ ውጪ መንቀሳቀስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አይፈቀድላትም። ታግታለች። የቁም እስር ላይ ናት። ቀበሮ ቁድጓድ እንዳለች ትሰበው። ይህንንም ዕውቅና ትስጠው። 

ኦሮምያ ክልል ላይ የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መንፈስ እዬተፈተነ ነው ያለው። ሀረሬ ክልል እራሱ ስቃይ ላይ ነው ያለው የቅድሰት ኦርቶዶክስ መንፈስ።

አማራ ላይ ደግሞ የሥልጣን አካላት የዬትኛው ሃይማኖት እዬተፈለገ ምደባ እዬተካሄደ እንደሆነ እዬተከታተልነው ነው። ለባርዳር ከተማ ማንን አምጥተው እንደ ሾሙ እኛም እናውቃለን እነሱም ያውቁታል። የአብይ ኢንፓዬር በወግ ቅብጥ ቅልጥ እያደረገ የልቡን ይሠራል። ያው ግርባው ብአዴን ለሁሉም ባርነት ምቹ ነው። መጅ።  

ግን ግን ነፍሱን አጥቶ ሲባትል የባጀው የአብይ መንፈስ አማራ ክልል ውሎ አዳሩ ነበር በዛን ሰሞናት። አሁን ልቡን የገጠመለት መንፈሱን ከመደበ ወዲህ ዎህ ብሎ ሃኒ ሙን ላይ ነው ያለው። ያሰረውን አሰረ፤ ያረደውን አረደ፤ ያከሰለውን አከሰለ፤ የበተነውን በተነ፤ በከሁለት የሚተረትረውን መንፈስ ተረተረ፤ ጉልበታሙን አቅም በጥያቄ ውስጥ እንዲገባ አስደረገ፤ የልቡን ሠራ …. አሁን „ „አንዴ እሚያምር ውስጥ ገብተናል“ ይልኃል የአማራ ሊሂቃንን በረድፍ ረሽኖ፤ የአማራን ህዝብ ተስፋ ቀምቶ እረኛ አልባ አድርጎ። የተበተነው ወጥ መንፈስ ቀላል አልነበረም።  

የሚገርመው አንዲት ቅርጥምጣሚ አጀንዳ ብን ያደርጋል ኦሮሙማ በዛ ትርምስምስ ሲል ውሎ ያድራል ማህበራዊ ሚዲያው፤ ያን ጊዜ እነ አጅሬ ሌላ ተልዕኳቸውን በአቀዱት መልክ ይከውናሉ። እዬተናድክ „እራሱ ይፈርሳታል ኢትዮጵያ አትፈርሰም“ ድንፋታ ጣልቃ ገብቶ ከች ይልልሃል፤ አንተም ተስፋ ሰንቀህ ታዘግማለህ። 

ባልተለመዱ ሚዲያዎችም የመዝናኛ ክበብ ደግሞ ከች ይልልህ እና እያዋዛ „በሬ ሆይ“ ይሳለቅበሃል። አንተ በዛች ቄንጠኛ ንግግር ስትፍለቀለቅ እሱ መቋሚያህን ይነጥቅሃል፤ መሰላሉን ይነሳህ እና ያፈርጥሃል። የእትብትህን ሙጫውን ይቦጫጭቅዋል። „ወንዝ ሲወስድ እያሳሳቀ“ እንዲለ …

ሊዚህ ጥሩ ካታሊስት ተደማሪ አለልህ የእሱን ሠራዊት ደግሞ ረቦ እውነተኛውን መንገድ፤ መርኃዊውን ጉዞ እኔ በቅንነት ነው እምለው ያዛባልሃል። ይሞግትሃል፤ ያፍልስኃል። አንተ እና እሱ ጉጉስ ላይ ስትሆን ኦነጋውያን የሌንጮወዲማ ግብረሃይል የልቡን በሚያደርስለት የግርዶሹ ባላባት ተዋናይ ልጁ በአብይዝም አቅም ቂም በቀሉን እያስማማ አፍንጫህን ሰንጎ ይግትሃል።

ኢትዮጵያዊነትንም ተዥጉርጉሮልሃል። ተነስ! ለጦርነት አይደለም። የእኔ የፌስ ቡክ ወዳጆቼ አንድም ባለ ሳንጃ አልቀበልም። ጦርነት በቃት ኢትዮጵያ። ተነሳ! የምለው የዴሞግራፊ ፍልስፍና ትርፍ እና ኪሳራውን መዝን ለማለት ነው። በእሱ ላይ አትኩሮት ይኑርህ ለማለት ነው። አያታወቅህም ክብርህ በበላይህ ላይ እዬተነነ ስለመሆኑ። መሰረቱ እና ጉዳዩ ዴሞግራፊው ነው። የሁሉም ነገር መነሻ እና መድረሻ ፌርማታ እሱ እራሱ ዴሞግራፊ ነው። ትበወዛለህ። እዬተበወዝክም ነው።

ከዴሞግራፊ ላይ ስትነሳ ናዚን በምልሰት እንዴት አውሮፓን እጠቅልላለሁ ብሎ ተነስቶ በእስራኤላውያን ተወላጆች እና ሃይማኖት እንዲሁም በንጹህ የአውሮፓውያን ህይወት ላይ እንዴት ሪሰርች እንደሰራ ታዬዋለህ። ለዚህ ምሳሌ የጋሞን፤ የጌዴኦ ህዝብ ማሰብ ነው። የአንድ የአማራ ህዝብ ጥፋት ብቻ እንዳይመስለህ። ኢትዮጵያ በሁለመናዋ ደቃ በፍራሿ ላይ ኦሮምያ ታብባለች፤ ትበለጽጋለች ነው ዕውነቱን ለመድፈር አቅሙ ከኖረህ፤ ፈሪም ካልሆንክ ወኔው ከተሰጠህ ብቻ።

ሂትለር ካወጀው አንድም የቃል፤ የሥንኛት እወጃ የተለዬ የለውም የኦሮሞ ፖለቲካ ሊሂቃን በአደባባይ እዬሰበኩ ያሉት፤ ራዲዮ ፕሮግራማቸውም እዬታተረ ያለው። ግርባው ብአዴን ለዚህ ደጀ ጠኝ ሆኖ ከፍና ዝቅ ሲል ታገኘዋለኽ።  ቀፎ።አቶ ገዱ ወደ አዲሱ የአፍሪካ ህብረት መዋቅር የሚደረግ ሽግግር ግልጽነትን ያረጋግጥ“ ይልሃል። እሱ እኮ በዬለም ተባዝቶ ነው ይህን የብአዴን ልሂቅ የሚነግርህ። ሥልጣን አያስፈልግም ያለ ድርጅት እኮ መፍረስ ነው የነበረበት። ለነገሩ ፈርሷል። ወና!

ስለ አፍሪካ ከመንጠላጠሉ በፊት እስኪ ኢትዮጵያ መኖሯ ይረጋገጥ። ቀድሞ ነገር ከዴሞግራፊ በላይ ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ሊሂቃን የላቀ አጀንዳ ምን እንዲሆን ይሆን የሚጠበቀው? በአጀንዳም አንዱም ክልል ውይይት አላካሄደበትም። ብልጽግና እኮ የኦነጋውያኑ ኢትዮጵያን የማፍረስ የሃሳብ ልዕልና ነው። ልብ አላቸው የሚባሉት ነፍሶች ሳይቀር ዴሞግራፊን አንስተው ተወያይተውበት አያውቁም።

ይህም ብቻ አይደለም አዲስ አበባ ላይ የሚታዬው ወጣ ገብ፣ ደራሽ እና እያሰረገ የሚከሰተው ቀውሱ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫነቱ ከአዲስ አባባ እንዲነሳ ይሆን የሚልም ዕድምታ ሁሉ አለኝ።  ኦሮሙማ በኢትዮጵያ ድብን ብሎ ነው የሚቀናው። የሥነ - ልቦና ደዌ ችግሩም ምንጩ ይህ ነው።
·        ልብ በዚህ ላይ ቢያተኩር ለቅርጥምጣሚ አጀንዳ የሚባክን ጊዜ አይኖርም ነበር።

ዴሞግራፊ የዴሞክራሲ ውደቀት እንጂ የተሰፋ ልቅና አይደለም። {ክፍል አንድ}

አሉታዊው የዴሞግራፊ ፍልስፍና የበቀል ፍልስፍና ነው። {የወግ ገበታ}

አሉታዊ ዴሞግራፊ የቂም ደም ነው።

አሉታዊ የዴሞግራፊ ንድፍ የበታችነት ስሜት የሚያበቅለው ሙጃ ነው። {የወግ ገበታ}

የጢስ ፖለቲካ ጦሱ ... የአሉታዊ ዴሞግራፊ ቤተኝነት ነው።

የአሉታዊው የዴሞግራፊ ዕሳቤ ለአላዛሯ ኢትዮጵያ የታዘዘ የጢስ አይዎሎጂ ነው። {የወግ ገበታ 17.06.2019}


·        የአማራ ህዝብ እና ተጋድሎው።

ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ በአሁኑ ልዝ ዲስኩራቸው ሞቷቸው አንድ ጉዳይ ነበር። በዛ የተወካዮች ምክር ቤት የመገኘታቸው ሚስጢር አሰኳል አንድ ጉዳይ ብቻ ነበር። አማራ የለም የሚለውን ውስጣቸውን እናይ ዘንድ ቀንጨብ አድርገው የማለመማጃ የቤት ሥራ ለመስጠት። ነገ በድፍረት ይናገሩታል። ልክ ለኦነግ መረጃ አቀብል ነበር እንዳሉት።

 „ተማሪ ብሄር የለውም“ ይህ ዝንባሌ ከፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም የተቀዳ ዝንባሌ ነው። ከአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጋር በነበረው የቤተ - መንግሥት ቆይታቸው ውስጥም የሰረጣቸው ህመም ነው። ጥሩ አጋጣሚ ነበር የሰሞናቱ ዲስኩር። ቁሊቱ ወይንም መቅሎውን ሥሩን ለማግኘት አልተቻለም ነበር። 

ይህን ያህል እርድ በአማራ ሊሂቃን እና ህዝብ ላይ የታዘዘበት ግልጽ የማግለል እና የመጨፈለቅ ዲስክረምኔሽን ሆነ ጭፍጨፋ ዕወጃው መሰረቱ ይህ ነው። የሚገርመው ከፍተኛ ነጥብ ያሙጡት ተማሪዎች የተለዬ የስኮላርም፤ የልዩ አያያዝ ዕድል ሲሰጥ አማራ ክልል ተገሎ እንደ ነበረ እናውቃለን። „ተማሪ ብሄር“ ከሌለው ይህ መሰሪ ፖሊሲ ስለምን ምራን ተባለ። ንገሩኝ ባይ።

የዩንቨርስቲ የአማራ ተማሪዎች ባለፈው ዓመት ሺዎች ተሰተጓጉለው ነበር። ዘንድሮ በ10 ዕጥፍ ጨምሯል። ይህን ስታዩት በዕውቀት ማሳማ ዴሞግራፊ ሥራውን እዬሠራ እንደሆነ ታስተውላላችሁ። ኦሮሞያዜሽንን ከለ አማራ ሊሂቃን የመፍጠር ሰፊ ተልዕኮ አለው። አሁን ውሉ ተገኝቷል። አዲሱ ፈርኦን አርድተውናል። የሚደንቀኝ ስለ ሰባአዊነት ግድ ይለናል የሚሉት ነፍሶች ይህን የማደመጥ አቅማቸው ወና መሆኑ ነው። ክልሎች እራሳቸው አጀንዳቸው አይደለም።
  
ሄሮድስ መለስ ዜናዊ „አማራ አለ“ ብለው ያምናሉ። ነገር ግን አማራን እራሱን መመንጠር ወይንም መጫን እና የአማራ ሥነ  - ልቦና ያለውን በአማራ ኮታ ቦታ ሌላውን ዞግ ማስያዝ የሚል አቋም ነበራቸው። እኒህ ደግሞ አማራ የለም ግን አለሁ የሚል ካለ ከምድረ ገጽ ይወገድ ነው። እዬሰሩበት ነው። ዘር ሲቆጥሩ ነው የሚውሉት ለምደባ። ፍርፋሪ መቆናጠጫ የሌላ ዘር ደም ይሻሉ ለነፍሳቸው ማሳረፊያ። ከንቱነት።  

አቀረቧቸው፣ ሾሟቸው የሚባሉት አማራ መሰል ወገኖች ዘራቸውን በርቀት ቆጣጥረው በደረሱበት ተደሞ ነው ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ የሚያቀርቧቸው። የአማራ ህዝብ ከሄሮድስ መለስ ዜናዊም በላይ በላይ ችግር ውስጥ ነው ያለው። ተጽዕኖ ፈጣሪ ሆነው ሊገፏቸው ያልቻሉትን የአማራ ልጆች ደግሞ ለጊዜው ተጠቅመው „በሬ ሆይን“ ይጉራሳሉ። አረንዛነት!

ሌላ የሚገርመው ነገር የህወሃትን ሰው ከሥልጣን ሲያነሱ የብአዴን ሰው በዛ ቦታ ይመድባሉ። ይህም ሌላው ቲያትራዊ ደባ ነው። የሁለቱን ጉጉስ አጥብቀው የሚሹት መሰረታዊ ጉዳይ ነው። ለምን? ለኦነጋዊ ድል እረፍት ማግኘት። የስሜን ፖለቲካ ማሰበርም በኽረ አጀንዳቸው ነው። አለቅትነት! ትምህርት ሚኒሰተርን ሻታ ሲዞሩ ሲዞሩ አሁን የልባቸውን አድርሰዋል።

እሳቸው ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሲሾሙ ሁለት ወዳጆቻቸውን ወደ እራሳቸው የሚኒስተር መስሪያ ቤት አሹመው ነበር። ይህን የነገሩን እራሳቸው ናቸው “በጃኬትህን አውልቅ“ ሞቷቸው። አሁን አንዱን ነፍስ ወደ ትምህርት ሚኒስተር አዛውረዋል። 

ያው የሳቸውን መሥፈርት ያሟላ ነፍስ። የአብይዝም ኢንፓዬር የዞግ፤ የሃይማኖት፤ የጓደኛነት፤ የሰፈር ምንትሶ፤ የኩሻዊ ስሜትና ዝንባሌ ዝባዝንኬ ድሪቶማ ነው፤ የደቡብ ፖለቲካ መስፈርትም አለበት። ይህ የተበጠረው ዕውነት ነው። ይህ መድፈር ካልቻልክ የሞጋሳ ሪሞርኬነቱን ተቀብለሃል ማለት ነው።

የሚያበረታተው ቁምነገር ብዙ ሰው እዬተረዳው ነው ሴረኛ መንፈስ ኢትዮጵያን እዬገዛ እየገዘገዘም እንዳለ። በሌላ በኩል የጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ጉዞ „ገድሎ እግዚአብሄር ይማርህ“ ስለመሆኑ ከልጅ እስከ አዋቂ ተገንዝቦታል። ከአማራ ጠል የፕሮፌሰር መስፍን ተጠማቂዎች በስተቀር። አማራ ጨቁኖናል ከተበላ አማራ የሚባል ማህበረሰብ ከሌለ ጨቋኙ ንፋሱ? ጋራ ሸንተረሩ? ወጀቡ? ማን ይሆን የጨቆናቸው? ደመነፍስ ፍልስፍና።

·        ሥነ - ልቦና በሽተኝነት።

የሥነ  - ልቦና በሽተኝነት በአማዛኙ በሊሂቃኑ የሚታይ መከራ ነው። በጸረ አማራ የተሰለፈው ኃይል ሁሉ የሥነ - ልቦና ችግር አለበት። ሲቃይ ኑሯል። አማራ የሚባል ማህበረሰብ ሲነሳ ጸጉሩ ይቆማል። አማራ የሚባል ማህበረሰብ አቅም ሲወጣ ልዩ ህግ ይደነገጋል። የሚያሳዝነው ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ እራሱ የዚህ ችግር ሰለባ መሆናቸው ነው። ይህን እኔ በጣም ዘግይቼ ነው የተረዳሁት።

ይህን በቀል ለመወጣትም የአማራ ህዝብን በሥነ - ልቦና ሰቆቃ ውስጥ ይወድቅ ዘንድ የጭካኔ ዓይነት በቡፌ አሰናድተዋል። በበላይነት የሚመሩት እሳቸው ናቸው። ለአማራ ያሰናዱት ጭካኔ ግን እርህርህና መለያው የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ እራሱ እርህርህርናን እንዳይንከባከብ ታግቷል። ጭካኔ ድል ላይ እርህርህና ሽንፈት ላይ ነው። ሃይማኖቶች እራሱ በራሳቸው ዶግማ ላይ ሸፍተዋል - አምጸዋል። የሆነ ሆኖ ቤተ - መንግሥት እንደ የፍሪንባ ውሎው የሥነ - ልቦና ማገገሚያ ሆስፒታል ቢከፍት መልካም ነው። ያዋጣዋል። ያተርፍበታልም።

·        ለቅርጥምጣሚ አጀንዳዎች ቀልብ መስጠት ብክነት ነው።

በዓዋጅ „ደብረ - ሊባኖስን ገዳምን አፍርሳችሁ ያዙ፤ ደናግልን ቅዱሳን ንቀሉ፤ ቤተ - መንግሥቱን አፍርሱና ሃውልት አቁሙ፤ ነፍጠኛን ስለሰበርን እልል በሉ፤ ከነፍጠኛ ጋር „ገውገው“ ጋር አትገበያዩ - አትጋቡ - አትዛመዱ - ቋንቋውን አትናገሩ - ብሄራዊ ሰንድቅ ዓላማውን አቃጥሉ - ዴሞግራፊን አስክኑ -„ ያሉ ወገኖች ቤተ - መንግሥት ናቸው። ነኪ - ቆንጣጭ - በህግ ጠያቂ  የለባቸውም። ውሸትም የቤተ መንግሥቱ ታዳሚ ነው። ታድሎ አይዋ ቅጥፈት¡ ቀን ሰጠው ውሸትንንንንንን።

ለዚህ ድርጊታቸው ወሸኔ የሚል ተደማሪ ደግሞ ከበሮውን ይደልቃል አብሮ። ነገ ተረኛ መሆኑ አልገባውም። የባሌ ሮቤ ህዝብ ተሰብስቦ አዋጁ ጥሞናል እንቀጥልበታለን በጸረ ጋሞ እና በጸረ አማራ ህዝብ ሲል ያወገዘ የሰማነው የለም።

 የከሰሰ የሰማነው የለም። በዬመድረኩ ሞድ የሚያሳዩን ሰዎች ሁሉ የት እንደሚኖሩ ይገርመኛል። ግርባው ብአዴን በሞገሳ መጥምቅነት አብሮ አሸወይና ይላል። ማፈሪያ!

ይህን የመሰለ ሰፊ ናዚያዊ ዓዋጅ በዬዕለቱ እዬተደመጠ ህዝበ - አዳም፤ ህዝበ - ህይዋን የግራጫማው አቶ ጃዋር መሃመድ ጠባቂ ተነሳ አልተናሳ አጀንዳ ሆኖ አቅም ያባክንለታል፤ ሰሞኑን ደግሞ ህውሃታዊቷ ወ/ሮ ኬርያ በዋልታ ብቅ አድርገዋል። 

ኢትዮጵያ ውስጥ ናዚ ያወጀው አዋጅ ነው ታውጆ ሥራ ላይ እዬዋለ የሚገኘው። ይህ ደግሞ በመንግሥት ሙሉ አቅም ነው እዬተፈጸመ ያለው። አጀንዳህ ሊሆን የሚገባው ይህ ነው። ቢያንስ የናዚን ታሪክ በምልሰት አጥናው።

ሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ለእኔ የኦነግ ናዚያዊ መንግሥት ነው። ከኦነግ ናዚያዊ መንግሥት እርህርህና፤ ሰባዕዊነት፤ ተፈጥሯዊነት፤ መቻቻል፤ መደማመጥ፤ ጥበብ፤ የልቅና ክህሎት ኢትዮጵያዊ ትውልድ መጠበቅ ዕብንነት ነው። ሁሉም ተራውን ይጠበቅ። ያገኛታል። 

የናዚ የኦወሾቲዝም ክፉ መንፈሳዊ ውርርሶች ኢትዮጵያ መሬት ላይ እዬታዩ ነው። በወልም በተናጠልም መከራው እያሰገረ እዬታዬ ነው። ምልክት አይደለም፤ በገቢር እዬተተረጎመ ነው። ለዚህ ቀስቃሽ ፕሮፖጋንዲስትም አያስፈልግም። መከራውን የሚኖረው ህዝብ ህይወቱን እዬገበረበት ነው። ይህ አሳር አጀንዳ በቀለጤ ፖለቲከኞች አይሞከርም። ደፋር ፖለቲከኞችን ይሻል። ህሊናው ለመርህ የተገዛ።

·        ኢትዮጵያዊ እስልም እና ኢትዮጵያዊ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በክስ ለመጥመድ ወጥመዱ ይገባናል።
በዚህ ውስጥ የሚገርሙኝ ነገሮች አሉ። በምንም ቀመር ኢትዮጵያዊው እስልምና ለኢትዮጵያዊው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ፤ ኢትዮጵያዊው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለኢትዮጵያዊው እስልምና ስጋት ሆነው አያውቅም። ግለሰቦች ሊኖሩ ይችላሉ በሁሉቱም ወገን። ሁለቱ ሃይማኖች በተቋም ደረጃ ግን የደም ውህደት አላቸው። ያ ደግሞ ቀለሙ ኢትዮጵያዊነት ነው። ይህን መነጣጠል አይቻልም።

ያው የፈረደበት አሳዛኙ የቁቤ ትውልድ 27 ዓመታት ታግቶ ኖረ። አሁን ደግሞ ሁለት ዓመቱን ታግቶ ነው የሚገኘው። ልክ እንደ ትግራይ ህዝብ። እና መስኪድ ሲቃጠል ኦርቶዶክሳውያን፤ ቤተክርስትያን ሲቃጠል እስላማውያን የሚለው አመክንዮ ስክነትም፤ ብልህነትም፤ ጥበብም የጎደለው ወልጋዳ ጮርቃ ግንዛቤ ነው። ከዚህ ልፍስፍስ እሳቤ መውጣት በእጅጉ ያስፈልጋል።

ጠቅላይ ሚኒስተሩ እራሳቸው እኮ „ቃጠሎው እንደሚቀጥል“ ነግረውናል። ምኑ ይሆን የሚደንቀን? መንግሥታዊ ተቋም ተደራጅቶ፤ ሌላም አደራጅቶ ነው ጥቃቱን እዬከወነ የሚገኘው። በመዲናዋ ላይ እኮ ነው የአብያተ ቤተክርስትያን ቃጠሎ፤ የሰንደቅ ዓላማ ገፋፋ የሚካሄደው።  

ከሱማሌ ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ ወደ አዲስ አባባ እና ዙሪያው ሲነቀል እርህርህና የለም - ለኦነጋውያኑ። ለአቤቶ ለማ መገርሳ ልዕልና፤ ለአቤቶ አብይ አህመድ ቅቡልነት እና የሥልጣን ቀጣይነት ሚሊዮን ከቀዩ፤ ከባዕቱ፤ ከኖረበት ዘይቤ ካለፈቃዱ፤ ከአለ ይሁንታው ተገዶቶ በግፍ እንዲነቀል ተደርጓል። ሌላ ላይ ሌላ የስደት ሰቆቃ እንዲሸከም ሆኗል። በጭቆና። እነዚህስ ኦሮሞዎች አይደሉምን።

 በዚህ ፍልሰት ልጅ እና ወላጅ ተለያይተዋል። ነፍሰጡሮች ሰቆቃ ተቀብለዋል። አዛውንቶች ፍዳውን ተጋርተዋል። ህጻናት ከአለ አሳዳጊ ቀርተዋል። ለማን ሲባል? በኩራት ለተነገረን የከተማ ፖለቲካ ስብጥር እና ምህንድስና ሲባል።

እንደ ገና ደግሞ የተሰፈረበት ህዝብ ይህን የኦሮሙማ መንፈስ ይቀበል ዘንድ ሌላ ዲስክርምኔሽ ተፈጸመበት። በሁለቱ መሃል አሁን አይታዬነም ቆይቶ ግን ግጭት ይቀሰቀሳል። ከሱማሌ የመጣው የኦሮሞ ወገናችን ከቆዬው አዲስ አበቤ እና አካባቢው ኗሪ ጋር። በዚህ ማህል ተጠቃሚው ኦነጋውያን ብቻ ናቸው። ይህን ካላደረጉ የፖለቲካ ሱቅ በደረቴያቸው ይከረቸማል። ግጭት ጠማኝ ናቸው። ስለምን? አቅም የለም። በዬመድረኩ ስታዳምጡ ምን መሬት አበቃላቸው ያሰኛል። ይህ እራሱ እንደ ዜጋ ያሸማቅቃል።

·        ስሞተኛው መፈንቅለ መንግሥት።

ሁለት ዓመት ሙሉ ያልረጋው በኦነግ መንፈስ የሚመራው ቤተ - መንግሥት ሁልጊዜ መፈንቅል፤ ዘወትር ግድያ ሙክራ ተደረገብኝ ስሞታ ነው። አምል ነው። ግርሻ። አሁን ሰሞኑም እንዲሁ ልንገደል ነበር ይልሃል ቤተ - መንግሥት። አቅም ከሌለው ስለምን አቅም ላለው በክብር አያስረክብም። ጡጦ ፍለጋ ኤርትራ ሰርክ ከሚባዝን። በታሪክ በዬወሩ መፈንቅለ መንግሥት ያሰጋው መንግሥት ቢኖር በዓለም ደረጃ ኦሮሙማው የኦዳ ሥርዐዎ መንግሥት ብቻ ነው። አለሁ አይበል። ማፈሪያ!

እቴጌ ኤርትራ ግን የልቧ ደርሷል። አሁን እኩል ተኩል ነው። ደካማ ኢትዮጵያ በመዳፏ ገብታለች። ህልሟን አሳክታለች። ሁለት ደቦሏቿን አሰልጥና ላከች። ዲል ብሎ አቀባበሉ እንዲከወን ቅድመ ሁኔታ አሟላች። አንዱን በማተረማስ ሌላው በማዛል ተልዕኳቸውን ይፈጽሙ ዘንድ ሚሽን ሰጠች። ኢላማዋን ደልደል ብላ መንበሯ ላይ ሆና አሳካች። የአገሩ ውስጥ ግንኙነትም የውጩም እንኩሮ ሆነ። 

·        ይከወን።

እዬፈረስክ ሳቅ¡ አንተ ምንቸገረህ ቅድመ አያቶችህ ያስረከቡህን አገር አስረከብህ ለቀጣዩ ትውልድ ብትን አፈር አስነስተህ። ተንከትከት¡ አንተ ምን አለበህ በስብከት ደንዝዘህ እዬፈረስክ ሰርክ ላፈር ስትቀለብ። ተፍለቀልለቅ¡ ቀን ከሌት የተቃጠለ የወገን እሬሳን ተገድሎ ተዝቅዝቆ ተሰቅሎ፤ እጅና እግሩ ተቆራርጦ ብትን አፈር ተነስቶ እያዬህ። ይመርብህ¡ ደስ ካላቸው አትክልተኛ ባለሙያ ጠቅላይ ሚኒስተር አለህና።

ሐሤትም አድርግ¡ ዕለታዊ የነፍስ ይማር ውሎ አዳርህ ሆኖልሃል እና። እንኳን ደስ አላህ¡ ሃይማኖትህን፤ ባህልህን፤ ትውፊትህን፤ ሰንደቅ ዓላማህን፤ ቋንቋህን፤ ታሪክህን፤ አዲሱን ትውልድህን እዬገበርክ የብልጽግና ዘመንህን በሰላም ሚኒስተር አጋፋሪነት አለልህ ተብሎ ታውጆልሃልንና። ለሽ ብለህ ተኛም ታጣፊ አልጋ በነፍስ ወከፍ በአዲስ የወግ ገበታ የምራቅ ሐዋርያ ተሰጥቶልኃል እና። ስጦ ዘመን። የመቃብር ሥፍራ ዘመን።

ስክነት በልባምነት፤ ጥማና በማስተዋል እንታደል ዘንድ በርትተን እንጸልይ። መንገዱ ጠፍቶብናል። ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ብቻ አይደሉም አሳቻ መንገድ ላይ ያሉት። እኛም አሳቻ መንገድ ላይ ነው ያለነው።

እዬተጎረጎርክ ስለመሆኑ ዘመኑን በማስተዋል መርምረው ለመኖርህ ካሰብክ። እዬተፈረፈርክ ስለመሆኑ ዘመኑን በጥበብ ላቅበት ተስፋ ፈላጊ ከሆንክ። እዬተቦረቦርክ ስለመሆኑ ዘመኑን በጥሞና አጣጥመው የትውልድ ብክነት አጀንዳህ ከሆነ።

 ዴሞግራፊ ፍልስፍናውን ውስጥህ አድርግ እና ከዛ ስትነሳ ሚስጢሩን ይነግርሃል። እያለቅህ መሆንህን። ህሊናህ ተነቅሎ አዲስ ህሊና እንደ ተተከለልህ እና ምርኮኝነትህን እምታውቅው ዘግይተህ ሊሆን ይችላል። ከጸጸት ለመዳን ዴሞግራፊን እና ጦሱን አጀንዳህ አድርግ።

ለትውልድ የሚበቃ ብቃት ያለው ንቃተ ህሊና ናፈቀኝ!
የኔዎቹ ኑሩልኝ መሸቢያ ቀን።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።