የጢስ ፖለቲካ ጦሱ ... የአሉታዊ ዴሞግራፊ ቤተኝነት ነው።


ተስፋ ዝልቅ
ተስፋ ልቅ
ተስፋ ፍልቅ ነው።
እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ።
የአሉታዊ ዴሞግራፊ ዕሳቤ 
ለአላዛሯ ኢትዮጵያ የታዘዘ
የጢስ አይዲዎሎጂ ነው።

„የሰዎች መፈጠር በበጎም ብክፉም ነውና።“
መጸሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፴፱ ቁጥር ፭

ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
15.06.2019
ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።


·       መቅድም።

የኢትዮጵያ ጌጦች እንዴት ናችሁ። ደህና ናችሁ ወይ? ዛሬ የጢስ ፖለቲካን እናያለን።

·       መነሻ። 

መረጃ ሳይኖረን የማንንም ስም አላጠፋንም፦ ትርጉም በአብርሃም ዓለሙ (/)“

April 1, 2019 | Filed under: ነፃ አስተያየቶች | Posted by: -ሐበሻ
ነጋዴ በኦሮምኛ ካልሸጠ አትግዙ – አቶ በቀለ ገርባ
March 23, 2019

·       እፍታ

እንዴት ናችሁ የአገሬ ፈርጦች? ደህና ናችሁ ወይ? ጢስ የዕለቱ ዕርዕሰ ጉዳዬ ነው። የአሉታዊ ዴሞግራፊ ዕሳቤ በብሄራዊ ደረጃ ሲታሰብ ለአላዛሯ ኢትዮጵያ የጨፈገገው ጢ እንደታዘዘባት ነው እኔ አማስበው። ስለሆነም የጢስ ፖለቲካ ዛሬ በመጠኑ ይፈታተሻል። 

የአብይወለማ ድፍን አይዲወሎጂ እያራመደ የሚገኘው ለእኔ ለሥርጉተ ሥላሴ ቀለሙ የጢስ ፖለቲካ ነው። ጢሱ ሲበረታብህ ዓይንህ እንኳን የሚሆነውን ነገር ለማዬት ይሳነው እና ጥለህ ለመውጣት ትገደዳለህ። 

የንጉሦች ንጉሥ የአጤ ሚኒልክ ቤተ መንግሥት ቅይጥ የቋሳ ፍላጎትን አዝሎ የተወጠነው ዕድሳትም የዚህ የጢስ ፖለቲከ ሰለባ ነው፤ በቀሉም በአቶ ዮናስ ደስታ ተወራርዷል። ልክ ነገረ አባይ እንደ ቆሞስ ኢንጂነር ስመኛው በቀለ ደመ ከልብነት ማለት ነው። በሰሞናቱም አንድ ጠንካራ መንፈስም ለመስዋዕትነት ቀርቧል ቆሞስ ተስፋዬ ጌታቸው የዛሬ ዓመት። ሰማዕታት ከከአውነት ጋር ተገብረዋል። 

በዚህ አንጀት አረስ በሆነ አለስልሴ ዲስኩር ደግሞ በመንፈስ ምልዕቱን አሰከሩት በዕብለት ዲስኩር። ከኦነግ መንፈስ የራቀ ቅንጣት እውነት ብናኝ ብሄራዊነት የለበትም በጢሳማው አብይ ወለማ አሉታዊ የዴሞግራፊ አብዮት። 

በነገራችን ላይ የባቢሎን ግንብ ቀራጩም የኦፌኮን እና የመድረክ ድርጀት ማህበርተኛው አቶ በቀለ ገርባም ይህንኑ ነው የሚያርምዱት። ስለሆነም ትንሽ ዘለግ ባለ ሁኔታ ዕለቱ እና እኛ እንቀኛኝበታለን። 

እውነት እንጂ ውሸት ትውልድ አይገነባም። በእውነት ውስጥ ያለው ንጥረ ነገር እውነት ነው። በውሸት ውስጥ ያለው ንጥረ ነገር ደግሞ እብለት እና ሸፍጥ ነው። የጢስ ፖለቲካ አካዳሚው ሸፍጥ ነው። በ አውነት ውስጥ ያለች ቅንጣት ሃቅ የምህረት መንገድ ስትሆን በሸፍጥ ውስጥ ያላች ቅንጣቢ ዕብለት ደግሞ ትውልድ ገዳይ ነው። አብሶ ቤተመንግሥት ላይ ሲሆን ጥፋቱ ሱናሜ ነው።

·       ጢስ።

የአብይወለማ አይዲኦሎጂ ለእኔ የጢስ ፖለቲካ ነው የሚያራምደው ብዬ ነው እማምነው። የጢስ ፖለቲካ አደናግሬና ሸፍጠኛ ነው። የጢስ ፖለቲካ ግራጫማ ሰብዕና ካላቸው የሚለዬው እያጣጤያሱ ፍንቀላውን በለበጣ ለማካሄድ መሞከሩ ነው ልዩነቱ። የግራጫማው ፖለቲካ እንደ ተፈጥሮው ሆኖ ሲቀርብ የጢስ ፖለቲካ አረማጆች ግን በተፈነ፤ በተዳፈነም አስመሳይነት እረመጦ እዬቀቀሉ በጢስ የሚያውክቡበት ይሆናሉ።

የጢስ ፖቲካ ፈላስማዎች ድንገቴዎችም ናቸው። ድንገቴ ተውኔት ያበዛሉ። የከፋው ደግሞ ለእኛ ከደህነት ሙያ ጋር የተጋባ መሆኑ የፊት ለፊታችን ፈተና እጅግ የከፋም፤ የሚፈትንም ይሆናል። 

በዬትኛውም ሁኔታ የሚነሳው ግፍ፤ በደል፤ ጭቆና ግለት እነሱ እንደሌለቡት ይሰብኩናል፤ ወደ ሌላ አላከን አቅማችን ወደዛ እንድናፈስ፤ አላስፈላጊ መስዋዕትነት እና ቅራኔ እንደንገባም ይጎሰጉሱናል። ቀውሱን ሁሉ እነሱ እንዳልመከሩበት ይነግሩናል፤ እንሱ እንዳልወሰኑበት ይደሰኩራሉ። ፋላጎታቸውን ግን በሌሎቹ ትክሻ ማስፈጸም ተያይዘወታል።

ሲያሰኛውም የጢስ ፖለቲካ የቄሮ ሰራዊትን፤ ሲያሻው የቄሮን ጠቅላይ አዛዥ ጄኒራል፤ ሲላቸውም ደግሞ በያንዳንዱ ነጥብ ጣቢያ የመደቧቸውን ዞጎች' ሲላቸው ደግሞ የጉለሌለው የጦር አዛዥ በማሰለፍ፤ በይፋም ዴሞግራፊን አውጆ በድርጊት በማዋል። ፋታ በመንሳት በጢስ ህወከት ይንጡታል ምደረ ቅንነትን። አሁን ለእነሱ ዴሞግራፊ አገረ ግንቢ ነው፤ ወንጀል አይደለም። ኦሮማዊነትም አይደለም። ከእነሱ ላነሰ አሰተሳሰብ ላለው ድውይ ይህን የእንቅልፍ ክኒን ይዘዙለት። 

የግራጫማ ሰብዕና አገልግሎት ላይ እንዲውል የሚረዳውም ሥልጣነ መንበሩን የያዘው በጢስ ፖለቲካ የሚገራው ቤተ መንግሥት በመሆኑ ነው። እያያችሁ አታዩም፤ እዬሰማችሁ አትሰሙም፤ እያሰባችሁ አታስቡም እዬኖራችሁ አትኖሩም … ወልደ ግራዎች።

ግፊት የሚደረገው በሌላ ወገን ልክ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤን የኦህዴድኦዴፓ ምንጣፉ ብአዴን መሪ ዶር አንባቸው መኮነን አገር እንዲለቅ እንደመከሩት ማለት ነው። ያ እንኳን አቅላቸውን አደብ ሊያስገዛው አልቻለም። በነገራችን ላይ የጢስ ፖለቲካ ቁርጠኛ ውሳኔ የመወሰን አቅሙም አናሳ ነው።፡ ደካማ እና ፈሪም ነው። 

አቋሙም ዝል እና ዝንፍ ነው ከባለግራጫማዎቹ ጋር ሲነጣጠር፤ ግራጫማዎች ደፋሮች እና ለሚያምኑበት ነገር ፊት ለፊት ሲወጡ የጢስ ፖለቲካ አራማጆች ግን ሾላኮች ናቸው። ለተጠያቂነትም፤ ለወሳኝነትም፤ ለሚዛናዊነትም ቅርብ አይደሉም የጢስ ፖለቲካ አራማጆች። 

ጓሮ ለጓሮ ሲትበሰብሱ ጊዜው እዬሸሎካቸው፤ አቅማቸው ውሃ የባለው ቅል እዬሆነ እዬሟሸሸ ይሄዳል። እየታዬ ያለውም ይኸው ነው። በኢትዮጵያዊነት ዲታ የመንፈስ አቅም ላይ ተንጠላጥለው የኦነግን ተልዕኮ ሊያሳኩ አቅል አጥተው ሲንደፋደፉ አንዳለጣቸው እና ተያይዘው እንቦጭ ሆነው ቀሩ። ማያያዣ ክር እንኳን የላቸውም አሁን። 

እውነት ለመናገር አብይወለማ መንገድ ኤክስፓዬርድ አድርጓል። ተመልሶ ማገገም አይችልም። እንኳን እነሱ ከእነሱ መንፈስ ጋር ተዳማሪው ኢዜማ እራሱ ጊዜው ሾልኮታል። የአንድ ድርጅት አመሰራረቱ ነው ዝልቀትን የሚያውጀው፤ አመሰራረቱ በሸፍጥ የተከዘነ ነው፤ በሌላ በኩልም በወደቀ መሰረት ላይ ላይ የታነጸው።

 ይህም አልባቃው ብሎ ከወደቀው የጢስ ፖለቲካ ጋር ተንጠላጣይነቱ ወይንም ተጠማኝነቱ የተጽዕኖ ፈጣሪ አምላኪነቱ እንደ ለመደበት አቅም ጥገኝነቱ ዘመኑ እያሾለከው እያላፈበትም ነው። ለነገሩ እኔ አጨብጫቢውም አልነበረኩም። "አያያዙን አይቶ ሸክሙን ይቀሙታል" እንዲሉ። በፍርሰት ለተከደነ ብቃት አለ ብዬ የሙት ተስፋ አምላኪ ስላልሆንኩኝ። ሁልጊዜ ጥማና ሃሳብ አቅም የለምና።  

ነገሩ እነሱ ሲቢል ሆነው መደራጀቱ ነበር የሚበጃቸው መንግሥትም ፓርቲም ነን ከሚሉን እነ ኢዜማኦደፓዎች። እነሱም የጢስ ፖለቲካ አራማጅ ተባባሪ ሆነው የተገኙ ለነገሩ ውረስና ቅርሱም ያው ነው፤ የአሳ ግማቱ ከጭንቅላቱ እንዲሉ በማባጫል እና በብልጭልጭ በኩሸትና በውሸት የተገነባ ተቀባይነት። ዙሪያ ገባው የድቡሽት ቤት ነው ለቀጠሮኞቹ። 

የራሳቸው አልበቃ ብሎ ደግሞ እኛን ሊያጃጅሉ የምታዩት ሁሉ ነገር ከአብይ ልቅና በታች ነው እያሉን ነው። ድንቄም ልቅና? ከእነሱ በፊት እነሱን እራሳቸውን በሃሳብ ሙግት ያራገፈ ብዕር እኮ ተዚህ ተሲውዝ ላይ አለ። የሥርጉትሻ ብዕር።

ብቻ አሁን ተፎካካሪ መሆን ቀርቶ ድርጎው ወደ ካድሬነትም፤ እንደ ፕሮፖጋንዲስትም ለኦነጋውያን እያሰኛቸው ነው። ገመና!

ቀድሞውንም የኦነግን ጠረኑ ክፍላቸው ነበር። እሁን ለይቶላቸዋል። በዚህ ውስጥ የተማገዱ ንጹሃን ሳይቀሩ ሌልኛ እዬሆኑብን ነው … ይገለማል፤ መከራን ተቀበልኽ እንደ ገና መንጨቧረቅ ... እብለትን እጬጌ ለማድረግ። ግን መብትም ስለሆነ ... እሰተ ውድቀቱ መጠበቅ ነው። 

ጢስ የታዘዛባት አላዛሯ ኢትዮጵያም ዓይኗን ገልጣ አቅጣጫዋን ማስተካካል እንዳትችል በስጋት ጭስ አፍነው አሳሯን እያሳዮዋት ነው በግራ በቀኝ። በነገራችን ላይ ፈሪዎቹ የጢስ ፖለቲካ አራማጆች አስመሳይነት እና ካህዲነትም ዋነኛ መለያቸው ነው። ተለዋዋጭነቱ ከግራጫማው በተለዬ ሁኔታ ፌካዊም የታከለበት ነው

ጢስ የተዘዘባት እናት አገር ኢትዮጵያ አሁን በጢስ ውስጥ ለሚመጣው መከራ ተጋልጣለች። ከጢስ አምንጭነት ዋነኛው ዕንባ ነው። ዕንባ ከጢስ አያመልጥም። አንድ ዓመት ሙሉ የጢስ ፖለቲካ አራማጆች በለቀቀቱ የስጋት፤ የጭንቀት፤ የሽብር ጢስ አላዛሯን ኢትዮጵያን ከጫፍ እስከ ጫፍ እያመሳት ነው፤ ጎንደር ላይ ቅማንትን ለአማራ፤ አዋሳ ላይ በኩሽኛ ዘይቤ፤ አዲስዬን በሰፋሪ በመመደብ እያኘኩት ነው
ብአዴን ሙት መሬት ላይ ተነጥፎ በአዳራሽ ዝግጅት እና ቅንብር፤ ቀን እና ሌት ጃኖ በቦንዳ ሲቸረችር መሽቶ ይነጋለታል። በሁሉም አቅጣጫ ይለፍልሽ ያልተባለች ባዕትን እንዲህ በሽታ ሽቶ እያመሷት ዕንባማ አድርገው እዬገዟትእዬገዘገዟትም ይገኛሉ ኦነጋውያኑ

ምኞት አያልቅም በቀጣይም እነሱው በጢስ ፖለቲካቸው ይቀጥሉ ዘንድ አሁንም ትጋት በማድረግ ላይ ናቸው። ጢስ የናፈቀው ካለ አብሮ አሸሼ ገዳሜውን ማስነካት ይችላል እንደ ኢዜማና እንደ ሚዲያው ከገናናት ወደ ኮሳሰንት ካወረደው ሚዲያው ኢሳት ጋር።

ኢዜማ ዓይኑ ጢሱ ደህና አድርጎ ወግቶ ስላጠቃው የቤተ መንግሥቱ ጊዜያዊ ባለሟል ነው ሥጋጃ አንጣፊ አሁን ላይ … ለነገሩ እንደ ገለጣቸው ከሆነ ሲቢል ሆነው ቢደራጁ ይሻላቸው ነበር። መጣሐፍ ገላጫቸው፤ ኮከብ ቆጣሪያቸው፤ ዕድል ሰፋሪያቸው የቀስተደማናው ፕ/ብርሃኑ ነጋ ቢፈቅዱ።

ለነገሩ ማጫውን ወደ ድንኳን ሦስት ጉልቻ ለመቀዬር የቸገራቸው እንደሚመስለኝ አውራው ድርጅት የኦህዴዱ ኦደፓ የዞግ ድርጅት ስለሆነባቸው ነው እንጂ ለአመል ታህል ትንሽ ወደ ዜግነት ቢጠጋጋ ዓይናቸውን አያሹም ጠቅልልው ሲጠቃለሉ። አሁን በደባልነት ነው ያሉት። ከእነማህበረ ሌንጮንም ከሥራቸው ወደቀው ልምምጥ ላይ ናቸው። አዬ ዘመን? ዘመን ሆይ? ሆይ? አንድምን አድረግህስ ትናዳ ... 

ይህን እኔ እነ አይዋ ሾላኪ አጋጣሚወን ካገኙ ሹልክ ነው ብዬ በ2016 እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ጥፌ ነበር በነገረ አማራ የህልውና ታገድሎ ሙግቴ ዘመን። የሆነውም ይኸው ነው። 

ያሳማማቸው ግን ያው አደናገሬው የፖለቲካ መስመር ወጥነት እና የስሜን ፖለቲካ ጥላቻ ነው። ይህ መቼም አሊ አይባልም። የስሜን ፖለቲካ አብዝተው ይጠየፉታል። አገር የሰራ፤ አገር የገነባ፤ አገር ያሰረከበ ነበር የስሜን ፖለቲካ። ብቻ የጥምረቱ አካዳሚ ድፍን ቅልነት።

ዓይን ያለው፤ ዕዝነ ህሊና ያለው እራሱን ለማስበዎዝ በጢስ ፖለቲካ አብሮ የሚሰለፍ ነፍስ በውነቱ ለባርነት ያደረ መሆን አለበት።

ለዚህም ነው ዓይን እንዳይስተውል፤ ቅርጥምጣሚ ከሰባዕዊነት ጋር ንክኪ ያላቸው ጉዳዮች አልፎ አልፎ ለማጣፊያ የምናዬው። የጢስ ፖለቲካ ዋንኛው ኢላማው ህሊና እናዳያስተውል፤ ዓይን እንዳያይ፤ በጢስ እፍን አድርጎ በታፈገ መከራ ቀጥቅጦ መግዛት ነው መርሁ ነው፤ መግዛት መርህ አለው ከተባለ።

መግዛት ግን የመርህ ጉዳይ አይደለም አምክንዮው። በመፈቃቀድ መተዳደር ነው መርህ። "አልጠግብ ባዩ ሲተፋ የሚያድረው" የኦሮሙማ የሊሂቃኑ ጢስ አፍኖ እራስን ከማሳጣቱ በፊት አሻም ማንነቴ አይበወዝም! እኔነቴን ቁሜ አይሰለሰለም! አይከስልም! እኔ እራሴ አልቀለበሰም ቁሜ እዬሄድኩኝ! አልቀያዬጥም! ብሎ መነሳት ሰው ሆኖ መፈጠርን ብቻ ይጠይቃል።

ፈቅዶ ባሪያ ለመሆን ለተሰናዳ ግን ከልካይ የለበትም በግ፤ በመሪነት ቦታ ተቀምጦ ከሆነ ግር ብሎ አብሮ መንጎድ ግን አይፈቀደም። ይቻላል እሰከ ጣጣ ምንጣጣው ራስን ችሎ፤ ነገር ግን ከህዝብ ራስ መውረድ ይኖርበታል። 

ለባርነት መሪነት የለም እና። ለባርነትም አዝማች አያስፈልገውም ይህን አቤቶ ኤዜማ ሊያውቀው ይገባል። ለነገሩ የፕ/ ብርሃኑ ነጋ ነገር ያደክማል። ኢትዮጵያ ለሳቸው 2/3ኛ ናት። ስሜን ኢትዮጵያን የማታክትት። ከዛ ደግሞ አይወጡም እዛው ነው የሚትበሰበሱት። ጥያቄ ሲነሳባቸውም ለአቅመ አዳም እና ህይዋን ባልደረስ አገላለጥ አባጭለው ቀልደው ተረበው ለማለፍ ይሻሉ አገር ከወገብ በላይ እና በታች እትፈረጅም። አገር ሙሉዕዘኩሉ ናት።

ሌላው አሁን የዶር አንባቸው መንገድ ይሕውን የባርነት፤ የሎሌነት፤ የተጠማኝነት፤ የጥገኝነት ሞፈር ዘመት የተጠማተማጠነም ነው። ሁሉ ያለህ ግን ተረገጠህ ለመገዛት ያደርክ ለዛም መዳከር። እግዚኦ ነው!መሃከነ ነው! ተሰህለነም ነው!

አንተ ብቻኽን መረገጥ መብትህ ቢሆንም ሰፊውን የአማራ ህዝብ ግን አይቻልም። አማራ ከፈጣሪው ከአላህ በታች የራሱ ጌታ እራሱ ነው። አብይወለማም ጌቶቹ አይደሉም፤ ሌንጮወዲማነግዖም ንጉሦቹ አይደሉም፤ ጃዋርወንግሱም አጤዎቹ አይደሉም። አማራ የራሱ ንጉሥ፤ የራሱ አጤ፤ የራሱ ገዢ የራሱ ልቅና እና አቅም ብቻ ነው ገዢውም አስተዳዳሪውም።

የግማሽ ሚሊዮን የአዲስ አባባ እና አካባቢው የዲሞግራፊ ክንውን ያን ያህል ባለድል ሲሆን ም/ጠ/ሚሩ አማራን የወከሉት አቶ ደመቀ መኮነን እዛው ቤተ መንግሥት ተቀምጠው ነው። አዲስ አባባ ላይ ያን ያህል በጠራራ ጠሃይ ያ ግፍ ሲፈጠም እሳቸው ነበሩ፤ ቡራዩም ለጋጣፎም የሆነውን አሳምረው ያውቃሉ፤ ዘመቻው ግቡ መዳረሻው ማንን ሰልቦ ሎሌ ለማድረግ ስለመሆኑ ግልጽ ነው።

ይህን ተሸከመህ፤ ይህን ሳትሞገት በዬስብሰባው ጃኖ እና ገበርዲን አሞልተህ ተኮፍሰህ መገኘት ከሞት ያልተሻለ ዕብንነት ነው። ዕውነት ብናገረው ለአቶ ገዱ አንዳርጋቸው፤ ለዶር አንባቸው መኮነን እና ለአቶ ደመቀ መኮነን ጥቁር ዘመን ነው።  ቀለም የሌለው እስክርቢቶ እንደማለት ነው። 

የጢስ ፖለቲካ አፍዝዝ አደንዝዝ ነው። ለመጣው ሁሉ ሲያነጥፉና ሲጎዘጎዙ አሉ ይኸው እንዳሉ ….ዓመት አለፋቸው በድግስ ድንኳን - ግርባው ብአዴን። ቀኑም አያልቅ፤ ወሩም አያልቅ፤ ዓመቱም አያልቅ … እነሱም ለመነጠፍ አይደክሙም … ለዛውም ለአዲስ ለሎሌነት፤ ለአዲስ ግርዳና፤ ለአዲስ ባርነት።

ጠ/ሚር አብይ ከመጡ ወዲህ የተሰጠው ሹመት ስንመለከት ከደህዲን በስተቀር ሁሉም ውክልናቸውን ያገኙት በብአዴን ኮታ ነው። የጤና ጥበቃ ሚ/ሩ የህወሃት ናቸው፤ የጎሙሩክ ኮሚሸንሩ የኦህዴዴ ናቸው፤ የፕሬስ ሰክሬታርያቱ የኦህዴድ ናቸው /አሪሰኛ ጢቾኛ/። ሁሎችም በጅሉ አማራ ኮታ ቁልፍ የፌድራሉ ባለስልጣኖች ናቸው። ህወሃትስ ከዚህ ሌላ ምን አደረገ? ማገፈፍ መውረር በስግብግብነት ... 

የአማራ ልጆች አገር መቀመጣቸው አንገብግቦ እንዲሰደዱ ጉትጎታ ይደረግባቸዋልእየተሳደዱም ነው። ይህን የአውሮፓ ህብረት የሰማ ዕለት ከጠ/ሚር አብይ አህመድ ጋር ፍቺው ይፈጸማል። አውሮፓ እንደ ጦር የሚፈራው የስደተኛ ቁጥር መጨምርን ናውና

አሁን የጢሱ ፖለቲካ ብቻ ሳይሆን ዘመነ ናዚ በኢትዮጵያ እያቆጠቆጠ ስለመሆኑ ግልጡ አልተነገራቸውም። ዘመነ ናዚ ደግሞ አውሮፓን ምን ዋጋ እንዳስከፈለው ለቀባሪው አረዱት ይሆናል። የሚሻሻል ነገር ከኖረ ተብሎ ነው ዝም ብለን በተደሞ እዬተከታተልን ያለነው።

አሁን ሳያሰበው ባላለመው ሁኔታ ሚስጢሩ እብድ የዘራው አዝመራ ሲሆንበት የጢሱ ፖለቲካው ሲደናበር ይታያል አውራው ድርጅት ኦዴፓ። ያው እሱንም ጢሱ ዓይኑን ስለሚደባብሰው።

 መጋቢት 1 ቀን ለነበረው የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ህዝባዊ ስብሰባ ቤተ መንግሥት ጉባኤ አሰናዳ፤ ከዛም እሱ ጋዜጣዊ መግለጫ ሊሰጥ ሲያስብ ጠ/ሚሩ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ፤ የአማራ ሰላማዊ ሰልፍ የመጀመሪያውን ሲያደርግ የርብ ምርቃ ተሰናዳ፤ ሁለተኛው ሰላማዊ ሰልፍ ሲሰናዳም ሌላ ድራማ ተደገመ። አሁን ዕለተ ሰንበትን የባልደራስ ንቅናቄ ባህርዳር ይካሄዳል ሲባል መራዘሙም ሆን ተብሎ ሊሆንም ይችላል ብቻ አሁን ደግሞ ወሎ ተገኙ ጠ/ሚሩ።

 ለነገሩ የወሎ ማህበር ታቅዶ ስለመከወኑ አንድ ጹሑፍ ጽፌ ነበር። አሁን የዚያ ግርፍ ነው ሰንበትን ተንትርሶ የተከወነው። የጢስ ፖለቲካ እንዲህ ነው ህሊናን ለመሰወር እዬተጋ የሚገኘው። ለማዳዳጥ፤ ለማደናቀፍ። ለማሰናከል።

የ60ዎቹ ፖለቲካ ቅኝታዎች የሚፈሩት የሚርዱት የሚያንቀጠቅጣቸው መንፈስ አለ። ተፈሪው መንፈስ አማራነት ነው። ከንባታ፤ ጉራጌ፤ ጋሞ፤ ወላይታ ድርጅት ፈጠረዋል የዞግ ነገ ወደ ኢዜማ የሚጠቃለሉ ናቸው ጠብቁት። እነሱን የሚናገር የለም። 

የሚፈራው ግን የአማራው በፖለቲካ ዘርፍ ጎልቶ መምጣት ነው። ይህንን ደፍረን እንናገራዋለን። ምን እንዳለን፤ ምን እንደምንችል፤ ምን እንደሚፈቀደልን እና እዮራዊ ቅብዕ ምን እንደፈቀደል አሳምረን ስለምናውቅ። 
  
"አሻናፊዎች ነን፤ ከሞት አዳናችሁ" በተባልን ማግሥት ህወሃት "እናንተ በምን አቅማችሁ ዕድሜ ለአማራ በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር ለሚኖሩ ህዝብ በሉ፤ ድምጹን ደግሞ በግንባራችን ለስልቡ ብአዴን፡ ብሎ እንቅጩን ሲነግራቸው አረፍን።

እንሆ ያ ኩፍታ ኩፈሳ ረብ አለ። ከዛች በኋዋላ አንድም የኦሮሞ ፖለቲካ አራማጅ ቃሏን ሲያወጣት አልተሰማም። አሁንም ይጠብቁ …. እነ አደናግሬ …. የጢስ ፖለቲካ አራማጆች። እዮባዊነት ተንጠፍጥፎ ያለቀለት ተጋድሎው ይጎመራል። አሁን በጥቂቱ በጥቂቱ ነው የታያዘው። 

መታገስ ጥሩ ነው በማለት ነው እንጂ የስሜን ኢትዮጵያ ፖለቲካ ቅብዐም ስለአለበት፤ ከመንግሥት አመሰራረት ጋር የቀረበ ክህሎት ስላለው ውርሱ ቅርሱ ትውፊቱ እና ትሩፋቱ መነሻውም መድረሻውም አጥጋቢ አሸናፊም ይሆናል።

የጢስ ፖለቲካማ ታዬ እኮ እንዲህ መያዣ ማጣበቂያ ማስትሽ አጥቶ በዝብርቅ፤ በድብልቅልቅ፤ ዳጥ ሲያረገርጉ ለዛውም ሰማይ እና መሬት፣ ሳር ቅጠሉ የዱር አራዊቱ ሁሉ ዘምሮላቸው በባንድ … ያን ህዝባዊ አደራና ሃላፊነት ተረክበው ግን ጠቅጥቀው የራሳቸውን የኦነግ የበታችነት ስሜት ተልዕኮ በዴሞግራፊ ፍልስፍና ሲያስኬደቱ ቅጭጭ አላላቸውም ነበር። ፈጣጦች። መታመን? ? 

የሚገርመው የፌድራሉ ምደባ እኮ ለሌሎች ማህበረቦች የኮታ ድልደላ የሚሸነሸነው  የአማራ ድርሻ ስለመሆኑ ራሱ ልብ ያለው የለም። መቼመው ውሸት ነጥፎባቸው የማያውቁት ጠ/ሚር አብይ አህመድ ማጣፊያው ሲያጥራቸው ደግሞ የመተንፈሻ ፍርፋሪ ለማገኝት ወሎ ላይ ባደረጉት ንግግር ....

ethiopian news / አብይ የሚባለው እውነት ከሆነ 24 ሰዓት ስልጣኔን እለቃለሁ። 

የግራጫማው ጃዋር ፖለቲካ እንዲህ በዬፌርማታው ውልቅልቃቸውን ያወጣዋል። ተቀባይነታቸው እርር ድብን እድርጎ አሳብዶት ነበርና። ተማቻቸሉት። የውሸት አነባባሮ እየጋጋሩ .... 

እኔ እንዲህ ወዘተረፈ ሰብዕና አይቼም ሰምቼም አላውቅም። ስንት ገጸ ባህሬ ነው ያላቸው።  ምኑ ነው እንዲህ ግጥብጥብ አድርጎ የቀደመውን አቅማቸውን የተላመጣ አገዳ አድርጎ ማዛቢስ ያደረገው። 

Ethiopia: ታከለ ኡማ በአዲስ አበባ የኦሮሚያን ልዩ ጥቅም ለማሳካት ቀን ከሌት እየሰሩ መሆኑን አቶ አዲሱ አረጋ ቂጤሳ በአንደበታቸው አረጋግጠዋል፡፡

Published on Mar 9, 2019

ግራጫማዋ ጃዋር ውልቅልቃቸውን አወጣው። መሬት ላይ ነው የዘረራቸው። በዚህ ወሎ ላይ በተናገሩት እድፍ ቃል ውስጥ ስንት ግድፈት ስንት ውጥንቅጥ እንዳለ ፈጽሞ አልተረዱትም። እኛን ይተውን ዓለም እራሱ ይሞግታቸዋል። 

ብዙም ሳይራቅ የአዲስ አባባን የግማሽ ሚሊዮን ህዝብ ዴሞግራፊ ለመለወጥ እንዴት ሱማሌ ላይ ቀድሞ ቀውስ እንደተደራጀ ግብዕቱ ይመሰክራል። ሌላው የጉርጂ የጌዲኦ ህዝብ መከራ ብቻ በቂ ነው። ለዚህ የጢስ ፓለቲካ ሲባል ነው ሁለት ነጥብ አራት ሚሊዮን ህዝብ ያን የመሰለ መከራ ያስተናገደው የጅጅጋውና የጌዴኦ ብቻ።

በሌላ በኩል ይህን እሳቸው ሊያሰተባብሉ ሲሹ ሲያስኬዱት ዋልታን ደግሞ ወደ ጂጂጋ ልከው ከማከብረው ደፋር ሞጋች ጋዜጠኛ አቶ ሥመነህ ባይፈርስ ጋር የሰባዕዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ሙስጡፌ ጋር በነበረው ቆይታ ብዙ ቦታ ኦሮሞዎቹ ቢይዙት ከቁጥር አንጻር ትክክል ነው የሚል ዕድምታ እንዲገልጹ አድርገዋል። እንዴት እንደሚያምታቱት ተመልከቱ። ጂጂጋ ላይ ኦሮሞ በህዝብ ቁጥር ብዙ ስለሆነ ብዙ ቦታ ይገባዋል ብቻ መባል ሳይሆን ሌላው አማራም ብዙ ስለሆነ ተመጣጣኝ ቦታ ሊሰጠው ይገባል አልተባለም። ከዚህ ላይ ጋዜጠኛ አቶ ሥመኔህ ባይፈርስም ደከም ብሎ አግኝቸዋለሁኝ። መሞገት ነበረበት አቶ ሙስጡፌን።

ከዚህ ጋርም ወ/ሮ አዳናች አቤቤ በዛ ሰሞን "እኛ ኦሮሞና አማራን ስልጣን ለማውጣት" አይደለም ሲሉ አንድ ዲስኩር አሰምተዋል። እነሱ ተልዕኳቸው አማራን ከስልጣን ከማንነት ማስወገድ ነው እንጂ በእኩልነት አለማዬት ስላለመሆኑማ ታዬ እኮ እናትነት ተገፍትሮ ምን ላይ እንደተከላወሰ፤ 

በተመሳሳይም የፌድራል ፍርድ ቤት ፕዚዳንቷም ተመሳሳይ ግድፈት ነው የፈጸሙት። ተዝርዝሮ በማያልቅ ኦሮማዊነት ዝክንትል የተዘፈቀው የአብይ መንፈስ አንደበቱ ተከፍቶ ቃል ለማውጣት መድፈሩ እራሱ እዮርን መዳፈር ይሆናል። ጢሱ ወደ አውሮፓ ከመምጣቱ በፊት ጠብቅ አድርገን በራችን እንጠብቃለን። ለዕንባ፤ ለክህደት ፖለቲካ አንገደድምና።

በጢስ ከመጨናበስ በጠራ እውነት መጓዝ ካሰቡት የሚያደርስ መንገድ ነው።
ትውልድ በእውነት እንጂ በውሸት አይገነባም!
ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል፤ ፍቅርም ሲያልቅ ትእግስት ይሰደዳል። 

የኔዎቹ ኑሩልኝ መሸቢያ ጊዜ።


የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።