ልጥፎች

ከሴፕቴምበር 4, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

መቼ ይሆን አሉታዊ ቁርቁሱ የሚያበቃው? ይንፍቀኛል ...

ምስል
„አማራነት መንፈስ ነው።“ „ብዙ ነገርን እንናገራለን፤ የነገሩ መጨረሻ እሱ ብቻ ነው፤ እንጂ ነገር ግን መጨረስ አንችልም።“ „መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፵፫ ቁጥር ፳፯“ ከሥርጉተ©ሥላሴ 04.09.2018 ከጭምቷ ሲወዘርላንድ ·        ግ ራሞተ ተሰሞናተ። የሰሞናቱ ትርምስ ግርም ይለኛል። አሁን ጠ/ሚር አብይ አህመድ እና ዶር ለማ መገርሳ መድረኩን እስቲ እንዳሻችሁ ሁኑበት ያሉ ይመስለኛል። ምክንያቱም የስሜን አሜሪካ የነበረው የመሰናዶ ውጣ ውረድ ብዙ እንዳሰተማራቸው አስባለሁኝ። በዝርዝር ሥም አቀማማጥ ሁሉ ቦክስ እንደነበር የዲያቆን ዳንኤል ክብረት ሪፖርት አስረድቶኛል። የሆነ ሆኖ በቤተመንግሥትም ደረጃ የአደባባይ ሥራ እንብዛም ኑሯቸው የማያውቀው ዶር ሙሉቱ ተሾም ሳይቀር ብዙ ጊዜ ብቅ እያሉ በቴሌቪዥን መስኮቶች እያዬናቸው ነው - አሁን አሁን። እንኳን ለዚህ አበቃቸው ያሰኛል። መቼስ መነቃነቅን የመሰለ ነገር ስሌለ …. ተነቃነቅ ስንፍናን ነቅንቅ ሞራልን አድምቅ ኢትዮጵያን አልቅ>>  አማራ ተጋድሎ እና ቄሮ ነፃ አውጥቷቸዋል ፕ/ ዶር ሙላቱ ተሾመን። የቀድሞውን ጠ/ ሚር ኃይለማርያም ደሳለኝንም ታጋድሎው ገላግሏቸዋል። ግንቦት ሰባቶችንም „የት ናችሁ? የት ደረሳችሁ? ምን ያዛችሁ“ ከሚለው ፈተና ገላግሏቸዋል። ተመሰገንም ሊሉት ይጋባል። ማጣፊያው ያጠረ መከራ ነበረ እና በዬጊዜው የመልስ ቀዳዳ ማጮለቅ…  በሌላ በኩል የአንዱ ሥም ላይ ለልዕለና የሌላው ደግሞ ታች ወድቆ ሲፈጠፈጥ፤ የሌላው ደግሞ „የእኔ የእኔ“ እዬተባለ ሽሚያ ላይ - ለወረት ከፍ እና ዝቅም ሲባልለት ይታያል። ሌላው ደግሞ ግራው እና ቀኙ ማህል ላይ ሰቅዘውት እንደ ገመድ ጉተታ  ሲጓተቱት መንፈሱን ሲቦጫጨቁት እምለከታ