ልጥፎች

ከሜይ 26, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ዕንባ በጎርፍነት። መታመን ሲነጥፍበት።

  ዕንባ በጎርፍነት። መታመን ሲነጥፍበት።    «… ዓይኖቼ በሰወች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኽውንን ማዳንህን አይተዋልና፤ …» (ሉቋስ ምዕራፍ ፪ ከ፳፱ ጀምሮ …)   https://www.youtube.com/watch?v=LZGo2sNn_7s&t=156s «መጨረሻውን መገመት የማይቻል አሳዛኝ ታሪክ #story #lovestory #ethiopianpodacst #ethiopia ,»   #መግቢያ ።   አመንዝራነት #ዙነት ነው። ደዌም። ስሜቱን መቆጣጠር የማይችል ሰብዕና በሞቱ ውስጥ አዘውትሮ የሚኖር ይመስለኛል። በተለይ እሱን አምነው የተከዱ ነፍሶች ግን ሰማዕታት ናቸው። ምክንያቱም የተፈጠሩበት መክሊት፤ ጥሪ፤ መልዕክት ሁሉ በመከዳታቸው ውስጥ አለና ሊደረመስ ይችላል። ለዚህ ወንጀል ተጠያቂ የሚሆነው ሰብዕና በከረባቱ ይኖራል፤ በገበርዲኑም ይኖራ፤ ባለፈም የፖለቲካ ሰብዕናም ውስጥ ዘው ማለትም ይኖራል። ሁሉም ግን ወና ነው። #ቃ ያለም።   አንጎልማ ዲንቢጥም አላት። ሰውነት ህሊናዊነት ነው። ስሜትን መግዛት እንደምን ይሳናል? አመንዝራነት ህሊናን ወደ ዲንቢጥ ተፈጥሮ መልስልኝ የማለት ያህል ነው። ለዛውም በወግ በማዕረግ የተዳረ፤ የተኳለ ሰብዕና ውስጡ ጽዳት ከሌለው፤ አባትነቱም አባት አይሆንም። ባልነቱም እንዲሁ የግፋፎ ካንፓኒነት ይሆናል።   እሙኃይ ዓለምነሽ ለመጨረሻ ጊዜ ልጃቸውን የጠየቁት ---- "ትልቁ የዓለማችን #ዓውሬ ማን ነው ብለው ጠየቋት።" ዕጸገነትም የምታውቀውን ዘረዘረች። እናት መለሱላት። "የዓለማችን ትልቁ አውሬ #ሰው ነው አሏት።" እኔም እስማማለሁኝ። የምለየው የአውሬነቱ ሥራ አስኪያጅ ክፋ ሃሳብ ነው ብዬ አስባለሁኝ።   አውሬው ደግሞ አግብቶ ወግ አይቀርም ደግሞ ድጋሚ ትዳር ሲይዝ...