ልጥፎች

ከማርች 7, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ሰላሞች የተጎዳውን መንፈሳችን አከሙለን። ይባረኩ!

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ሰ ላሞ ች ! „ከቸር ሰው ጋር ሆነህ ቸር ሆነህ ትገኛለህ“ መዝሙር ፲፯ ቁጥር ፳፭ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 06.03.2019 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ። ·          መነሻዬ። መጣሁላችሁ ውዶቼ? እንዴት አላችሁልኝ። ስለ ሰላም ትርጉም ያለው ተግባር እንዲህ በኢትዮጵያ ህብራዊት ከተማ በነበረችው አዋሳ የሰላም ሐዋርያት ፈጠሙ። እሰቡ „በነበረችው“ ነው ያልኩት። አሁን ኦነጋውያኑ አዲስ የሰላ ቢላዋ ይዘው ደግሞ በአቶ ሌንጮ ለታ ፊታውራሪነት እዬሸነሸኗት ነው። መንፈሷን እያወኩት ነው አዋሳን፤ በሲዳማኛ ዜማ። የሆነ ሆኖ ዝርዝሩን ከጉዳዩ እንብርት ከፋና ቴሌቪዥን ዝግጅት እንድታዳምጡ በትህትና ጋብዤ እኔ ስለተሰማኝ ትንሽ ወግ ቢጤ ላዋጣ። https://www.youtube.com/watch?v=_15hZr_3BpE ሰላም የፋሺን ፌስቲቫል በሀዋሳ   „ሰላም“ ደስ ይላል። ይማርካል። ቢጠጣም፤ ቢበላም፤ በአፍ በአፍ በጉርሻ ቢያጣደፍም ተፈቅዶለት ነገረ ሰላም ሲፈጠር ታጥቦ ስለሆነ የተፈጠረው አይሰለችም - ለአደለው። እኮ ሰላም ድንቅ ነገር። የሰላም ሚኒስተር በማቋቋምም ከዓለም የመጀመሪያ ሆነናል። ይህን ስል መዋቅራዊ ይዘቱን ሳይሆን „ የሰላም ሚኒስተር “ የሚለውን ስንኙ መደፈሩን ማለቴ ነው። አዕመደ ማዋለ ምኸዋር ቃሉ ራሱ እንዲሆን መታሰቡ፤ መታጨቱ ድንቅ ነው። መዋቅራዊ ይዘቱማ የታጨቀ ነው።  በርካታ ጉዳዮች ተነባብረው ካልልክ ተወጥሮ በአንድ ሚ/ር ሥር ነው የወደቀው።  ነገር ግን „ሰላም“ የሚለውን ሃይለ ቃል እንዲህ አጉልቶ በማውጣት አረገድ ግን ዓለምን ሊያስተምር የሚችል ትልቅ ተምሳሌነት ተፈጥሟል። ቃል ሃይል አለውና።