ልጥፎች

ከጃንዋሪ 6, 2020 ልጥፎች በማሳየት ላይ

50በ60 ያረጠ ፖለቲካ።

ምስል
እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ።  „ ለሰዎች ትታዩ ዘንድ ምጽዋታችሁን     በፊታቸው እንዳታደረጉ ተጠንቀቁ። “ ( የማቴዎስ ወንጌል ምእራፍ ፮ ቁጥር ፩ ) 50 በ 60 ያረጠ ፖለቲካ። ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ 06.01.2020 ·         እፍታ። ወይ ጉድ ሦስት ዜሮ እኛን ቁጭ አደርገው ወደ 20 ተሸጋገሩ። ግርም ይላል። ከመቼው 2020 እንደ ተደረሰ። ግን ቅኔዎቹ የአገሬ ልጆች እንዴት ናችሁ? የትውልድ የሃሳብ ብከነት አጀንዳችን ቢሆን ምን ትላላችሁ? ትህትናዊ አክብሮት፤ ትህትናዊ አድማጭነት፤ ትህትናዊ ህዝባዊ ፍቅር፤ ትህትናዊ አስተዳደር ቤተ - መንግሥት ላይ ይተጋጋጠ እዬሆነ ነው። ይትብኃል ሱባኤ ላይ ነው። ቀኑ ይመለ ስ ለት ዘንድ አቤት እያለ ነው ወደ እዮር።  ትህትና ግዞት ላይ ሆኖ በዚህ ፈንታ ፉከራ፤ መታበይ፤ ማን አለብኝነት፤ ደንታ ቢስነት፤ ግዴለሽነትን፤ ጉድለተ - ኃላፊነት የሚያውጁ ሥንኛት፤ ቃላት ቁሙ ተሰቀሉ እያሉን ነው። „ቃል ይተክላል ይነቅላል“ የተባለው ከተከላው ነቀላው ማዘንበሉን እያስተዋልኩ ነው። ሁሉን ነገር ሳልጠራጠር እንደሚቀበል ቅን አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ በማደምጣቸው ነቃይ ቃላት፤ ነቃይ ሥንኛት የትውልዱን ማግሥታዊ ተስፋ ሳስበው ያምጥብኛል። ይቀጭጭብኛል። ዛሬ ለዕርእሴ ተያያዥ እና ተወራራሽ የሆኑ ጉዳዮችን አነሳለሁኝ። ከ ቅኖች የጹሑፌ ታዳሚዎችም ትዕግስታችሁ እንደማይለዬኝም አስባለሁኝ። ወቀሳዬን እምልክላቸውም ቢሆኑም ያተርፉበታል እንጂ አይከስሩ በ ትም። ለእነሱ የማይታያቸው ለእሷ ታይቷት ይሆ...