ልጥፎች

ከጁላይ 22, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#ስለጣምራው #ተጋድሎ የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ የዬትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ማኒፌስቶ #ጥገኛ፤ #ተቀጥላ ሊሆን አይገባም።

  #ስለጣምራው #ተጋድሎ የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ የዬትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ማኒፌስቶ #ጥገኛ ፤ #ተቀጥላ ሊሆን አይገባም።  በተለይ ሙሉ 50 የነቀለውን #የሶሻሊዝም ጠንቀኛ ርዕዮት እስከ እንጥፍጣፊው #አክ ሊለው ይገባል። ይህ ራሱን የቻለ የህሊና ብስለትን #የውስጥ #መረጋጋትን የሚጠይቅ ስለመሆኑ ይረዳኛል። ሕዝባችን ቋያ ላይ ስላለ። አንዱን ባነሳስ ስለአሰጋኝም እርስ በርስ #ዬመጠፋፋት ጉዳይ ሊታሰብበት ይገባል። አማራን ሙሉ በሙሉ የበቀሉ መሪወችን የቀጠፈውም ይህ ዕሳቤ ነው።  ባለቤት አልባ አድርጎ ማህበራዊ መሠረቱን ያጣው ሁሉ የተመመበትም። የአማራ ፖለቲካ ከተኖረበት የሴራ እና የአድማ፤ የሳይለንት ኒግሌሽን ወዘተ እራሱን ሊያጠራ ይገባል። ይሄ አድመኝነት፤ #በቀለኝነት ።  አንድም የአማራ ሚዲያ ሁሉንም አማራ #ሲያቅፍ አላዬሁም፤ አንድም የአማራ ድርጅት ሁሉንም የአማራ አቅም #ማዕከል አድርጎ ሲነሳ አላዬሁም።  የአማራ ፖለቲካ ሳያውቀው የሶሻሊዝም ጠረን ተጠቂ መሆኑን አስተውያለሁኝ። #ጣምራ #ተጋድሎው ፦ የነጠረ ውስጡን ያዬ የርዕዮተዓለም አቅጣጫን መንደፍ ይገባል።   #ሶሻሊዝምን እስከ #ዝክንትሉ #ሃራም ሊለው ይገባዋል የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ።  ሥርጉ2024/07/022

#መተንፈስ #ለተገደበበት ቅን የአማራ ህዝብ፦ #መፀነስ አይገባህ ለተባለ ደግ የአማራ ሕዝብ፤

  #መተንፈስ #ለተገደበበት ቅን የአማራ ህዝብ፦ #መፀነስ አይገባህ ለተባለ ደግ የአማራ ሕዝብ፤ #መማር አይገባህም ለተባለ ትዕግስተኛ የአማራ ህዝብ?  ዌልካሚንግ ለሆነ የአማራ ሕዝብ ማረስ - መነገድ - መታከም - #መጓጓዝ - ሃብት ማፍራት በፍፁም ሁኔታ ማዕቀብ ለተጣለበት ህዝብ?  ልጆቹ #እንደወጡ ለሚቀሩበት ሩህሩህ የአማራ ሕዝብ? በመላ ኢትዮጵያ በፖለቲካ፤ በዕድል፤ በዕውቅና ስልታዊ ጥቃት ለሚደርስበት የህግ አምላክ ተገዢ ለሆነው የአማራ ህዝብ፤ #ካቴና ቤቱ ትዳሩ፤ #ድሮን ኑሮው ለሆነ ትሁት የአማራ ሕዝብ?  ሙሉ 8 ዓመታት #በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለሚሰቃይ የአማራ ሕዝብ? #በግሪደር ለሚቀበር ምንዱብ ሕዝብ? ከአንተ #ደን ይበልጣል ለሚባል የተገፋ ሕዝብ? መሪወቹን ሰርክ #በሸፍጥ በሚያጣ ግን የመቻቻል ፀጋ ለተሰጠው የአማራ ሕዝብ 6 ዓመት በመላ ኢትዮጵያ ያደራጃቸው ተቋማት፤ ከተሞች የዶግ አመድ ለሆኑበት የአማራ ሕዝብ የህልውና እና የማንነት ግዙፍ ተጋድሎ #አቃቂር ፤ #ቅልጣን ? #መሞላቀቅ ? #ዝነጣ ?  #ሌግዠሪ ያስፈልገው ይሆን???? ሥርጉትሻ 024/07/22

From America to Ethiopia || ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ | Ari Floyd || Manyazewal Esh...

ምስል