ልጥፎች

ከሴፕቴምበር 7, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ሌላስ? ህም ተዚህ፤ ህም ተዚያ፤ ህም ተዚያ ማዶ!

ምስል
  ጭላጭ ሳይስቀሩ …  እም እንዳይሆን ስለ ጸዮን ዝም አልልም፤ ስለ እየሩሳሌም ጸጥ አልልም፤  ጽድቅዋ እንደ ጸዳል፤ መዳናዋም እንደሚያበራ  እስኪወጣ ድረስ።  ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፷፪ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ 07.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። የሚገርሙኝ ነገሮች የበረከተበት ወር ነበር ነሃሴ። ብዙ ብርካታ የሚባሉ ጉዳዮችን አስተውያለሁኝ። ዛሬም እንደ ትናቱ የሞገድ ጉጉሱ እንደ ተጠበቀ ሆኖ። ትልቁ ጥያቄ ግን ወያኔ ሃርነት ትግራይ ተዳክሟል ወይ የሚለው ጉዳይ ነው ለእኔ ለህሊናዬ ቅርብ የሆነው፤ ዕውን ወያኔ ሃርነት ትግራይ ተዳክሟል ወይ ትልቁ አምክንዮ ነው - ልንዘናጋበት የማይገባው። እርግጥ ነው ወያኔ ሃርነት ትግራይ አንድ ክንፉን ተመቷል ከሰሞናቱ። ችግሩን ከእርሱ ብዙ ማይልስ ርቆ መሬት ሲያስነጥስ፤ የራሱንም ህዝቤ የሚለውን ዕንቁውን ሳያስጨንቅ  በዕንባም ሳያሳጥብ "በሞኝ ክንድ" እንዲሉ መፈተኛው ሌላ ቦታ ነው፤ የምስራቅ ኢትዮጵያን ህዝብን ሲያስለቅስ የቆዬበት ሁኔታ የመፍትሄ አሰጣጥ ዘይቤን ብዙ ሰው አላስተዋለውም፤ ልብም አላለውም፤ አላደነቀውም፤ ዕውቅና ለመስጠት አልደፈረውም እንጂ የኢትዮ ሱማሌ ጉዳይን መስመር ለመሳያዝ የተሄደበት መንገድ እጅግ ዘመናዊ፤ ስልጡን ብቻ ሳይሆን እምነት የሚያስጥል ነው። ዶር አብይ አህመድ የመጨረሻውን የእውቀት ደረጃ ያዋዋሉበት ሙያ የሰላም እና የደህንነት ነው፤ ጥበብ መሬት ላይ በውን በዳግሚያ ትንሳኤነት እንዲታይ የተደረገበት፤ ከተከናወኑት ግዙፍ አገራዊ ጉዳዮች እንደ አንዱ ሊታይ የሚገባው ነው በሥርጉተ ዕድምታ። ልክ እንደ ኢትዮ ኤርትራ። እውነት ለመናገር በዚህ በአጭር ጊዜ ውስጥ ይህን መሰል የመንፈስ ተረገጥ ልዕልና ይገኛል ብዬ አስቤ አል