ልጥፎች

ቅጣት እንዳያመጣ፤ ፈጣሪ የእውነት መስራች ነውና።

ምስል
በመገፋት ላይ የሰከነ 30 ኛ የ4ኛው ፓትርያርከ ዘኢትዮጵያ የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መሪቆርዮስ በዓለ ሲመት አከባበር በአዲስ አባባ። „ደቀ መዛሙርቱም፤ --- የቤትህ ቅናት ይበላኛል   ተብሎ እንደተጻፈ አስቡ“   ዮሖንስ ወንጌል ምዕራፍ ፪ ቁጥር ፲፯   ከሥርጉተ©ሥላሴ 06.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። v       በስም አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ አሜን! እንዴት ናችሁልኝ ደህና ናችሁ ወይ ውዶቼ? ዛሬ አንድ ዜና አዬሁኝ። ብጹዑ ወቅዱስ አባታችን 4ኛው ፓትርያርከ  ዘኢትዮጵያ ባዕለ ስመትን በሚመለከት። ውስጤን ቀዘቀዘቀዘው። ብርድ ብርድ አለኝ።   ለብጹዕን አባቶቻችን ውጪ አገር እኮ ቁልምጫው ከ - እስከ አይባልም ነበር። እንዲያውም አንድ ጊዜ ይህ የበዕለ ሲመት ሲዘጋጅ የሊቢያ ሰምዕታት ጉዳይ ስለነበር አልሻም ማለታቸውን አውቃለሁኝ። ንዑዱ - ብጹዑው አቡነ መሪቀርዮስን ለመተርጎም ሆነ ለማመሳጠር መዘገበ ቃላት የለውም። ለኢትዮጵያ ልዩ ምርቃት ናቸው። ለ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክስተት ናቸው። እርጋታቸው የሰማይ እና የምድር ያህል ነው።    ዜናው ላይ ብጹዕ ወቅዱስ 6ኛው ፓትርያርከ ዘኢትዮጵያን አቡነ ማትያስን አላዬሁኝም። ያዬኋቸው የቀድሞው ፕ/ ግርማ ወልደጊዮርጊስን አሳቸውን ነው።   እሳቸው መገኘታቸው ለይምሰል ወይንም ለላንቲካ አለመሆኑን አሳምሬ አውቃለሁኝ። ቀድሞም ሲጥሩ ነበር ሁለቱን ሲኖዶስ አንድ ለማድረግ፤ በጫና ብዛትም ቃላቸውን ሲያጥፉም አዳምጬ ነበር።   የሆነ ሆኖ መሰረታዊ ጉዳዩ ከልባቸው ስለመሆኑ ስለማምን የተባረከ ተግባር ከውነዋል። እንዲያውም ውጪ አገር የሚገኙ የብጹዕ ወቅዱስ አባአተችን የልጆቻቸውን ኃላፊነት ተረከብው ተውጥተዋል ብዬ አሰብለ

ጥያቄው የብትን አፈር የነፍስ ጉዳይ ነው!

ምስል
ኢትዮጵያ የቁጥር ተማሪ አይደለችም። ከሥርጉተ©ሥላሴ 05.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። እንደምን አላችሁልኝ የኔዎቹ? ደህና ናችሁ ወይ። በነገረ ጣይቱ ላይ ዛሬ ጥዋት እጅግ ከማከብረው ከአንድ የፖለቲካ ድርጅት በላይ በግሉ ስለ ኢትዮጵያኒዝም የተጋ እና ያታገለ የአክቲቢስት አቶ መስፍን ፈይሳን ምልከታ አዳመጥኩኝ። ባለፈው ሳምንትም የርዕዮት ሚዲያን ምልከታ ተከታትያለሁኝ።  የወዳጄን የመስፍኔን ከቅንነት ስለሆነም በትርጉም ባቃናው፤ ትንሽ ዘለግ አድርጌ እንደ አንዲት ኢትዮጵያዊት ሴት ምልከታየን በሚል ነው እንዲህ ማለት ፈልግሁኝ።  እሱ ቅን ኢትዮጵያዊ ስለሆነ በሃሳብ ልዩነቱ ልናዝንበት የሚገባ አይሆንም። ምንግዜም በአንደኛው ሃሳብ ባንግባባ በሌላው ደግሞ እንስማማለን ወይንም በድምጽ ተዕቅቦ እንለያለን። ይህ የእውነተኛ ዴሞክራሲ ፈላጊው እውነት ነው። ግራው ዘመም መንፈስ ያደረበት ብቻ ነው ሞጋች ሃሳቦችን ወይንም ፈንጋጣ ሃሳቦችን የሚፈራው። ያው ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት አምላኩ ስለሆነ።  ·        የሆድ የሆድን።   ኢትዮጵያ የክት እና የዘወትር ልጅ የላትም። ኢትዮጵያ ስለ ልጆቿ ክፍልፋይ አሰናድታ አታውቅም። ኢትዮጵያ የቁጥር ተማሪ አይደለችም ። ኢትዮጵያ ላይ ያለው ንጹህ አዬር ኦክስጅን አንተ / አንቺ የእኔ አይደለህም /ሽም ብሎ ገድቦ አይዋቅም፤ ለይቶም አያውቅም። አንድ ተራራ ላይ ያለው ነፋሻ አየር እኩል ነው ለሁሉ ፍቅሩን የሚያዳርሰው፤ ዝናቡም ሲመጣ እንዲሁም መቻቻልን በእግሩ አንዲሄድ ያደርገዋል፤ የኢትዮጵያ ጸሐይም ስትመጣ ለሁሉም ብርሃነኗን በሐሤት ትለግሳለች። ስታኮርፍም ስትስቅም እኩል ነው።  ኢትዮጵያዊ ወቅታት ሲመጡ ጸደይ በጋ በልግ ክረምት ሲመጡም እንዲሁ ሁሉ ለሁሉ ተደራሽ ይሆናሉ

መቼ ይሆን አሉታዊ ቁርቁሱ የሚያበቃው? ይንፍቀኛል ...

ምስል
„አማራነት መንፈስ ነው።“ „ብዙ ነገርን እንናገራለን፤ የነገሩ መጨረሻ እሱ ብቻ ነው፤ እንጂ ነገር ግን መጨረስ አንችልም።“ „መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፵፫ ቁጥር ፳፯“ ከሥርጉተ©ሥላሴ 04.09.2018 ከጭምቷ ሲወዘርላንድ ·        ግ ራሞተ ተሰሞናተ። የሰሞናቱ ትርምስ ግርም ይለኛል። አሁን ጠ/ሚር አብይ አህመድ እና ዶር ለማ መገርሳ መድረኩን እስቲ እንዳሻችሁ ሁኑበት ያሉ ይመስለኛል። ምክንያቱም የስሜን አሜሪካ የነበረው የመሰናዶ ውጣ ውረድ ብዙ እንዳሰተማራቸው አስባለሁኝ። በዝርዝር ሥም አቀማማጥ ሁሉ ቦክስ እንደነበር የዲያቆን ዳንኤል ክብረት ሪፖርት አስረድቶኛል። የሆነ ሆኖ በቤተመንግሥትም ደረጃ የአደባባይ ሥራ እንብዛም ኑሯቸው የማያውቀው ዶር ሙሉቱ ተሾም ሳይቀር ብዙ ጊዜ ብቅ እያሉ በቴሌቪዥን መስኮቶች እያዬናቸው ነው - አሁን አሁን። እንኳን ለዚህ አበቃቸው ያሰኛል። መቼስ መነቃነቅን የመሰለ ነገር ስሌለ …. ተነቃነቅ ስንፍናን ነቅንቅ ሞራልን አድምቅ ኢትዮጵያን አልቅ>>  አማራ ተጋድሎ እና ቄሮ ነፃ አውጥቷቸዋል ፕ/ ዶር ሙላቱ ተሾመን። የቀድሞውን ጠ/ ሚር ኃይለማርያም ደሳለኝንም ታጋድሎው ገላግሏቸዋል። ግንቦት ሰባቶችንም „የት ናችሁ? የት ደረሳችሁ? ምን ያዛችሁ“ ከሚለው ፈተና ገላግሏቸዋል። ተመሰገንም ሊሉት ይጋባል። ማጣፊያው ያጠረ መከራ ነበረ እና በዬጊዜው የመልስ ቀዳዳ ማጮለቅ…  በሌላ በኩል የአንዱ ሥም ላይ ለልዕለና የሌላው ደግሞ ታች ወድቆ ሲፈጠፈጥ፤ የሌላው ደግሞ „የእኔ የእኔ“ እዬተባለ ሽሚያ ላይ - ለወረት ከፍ እና ዝቅም ሲባልለት ይታያል። ሌላው ደግሞ ግራው እና ቀኙ ማህል ላይ ሰቅዘውት እንደ ገመድ ጉተታ  ሲጓተቱት መንፈሱን ሲቦጫጨቁት እምለከታ