ቅጣት እንዳያመጣ፤ ፈጣሪ የእውነት መስራች ነውና።




በመገፋት ላይ የሰከነ 30ኛ የ4ኛው ፓትርያርከ ዘኢትዮጵያ የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መሪቆርዮስ በዓለ ሲመት አከባበር በአዲስ አባባ።


„ደቀ መዛሙርቱም፤ --- የቤትህ ቅናት ይበላኛል 

ተብሎ እንደተጻፈ አስቡ“

 

ዮሖንስ ወንጌል ምዕራፍ ፪ ቁጥር ፲፯ 

ከሥርጉተ©ሥላሴ

06.09.2018

ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።

v     

በስም አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ አሜን!

እንዴት ናችሁልኝ ደህና ናችሁ ወይ ውዶቼ? ዛሬ አንድ ዜና አዬሁኝ። ብጹዑ ወቅዱስ አባታችን 4ኛው ፓትርያርከ  ዘኢትዮጵያ ባዕለ ስመትን በሚመለከት። ውስጤን ቀዘቀዘቀዘው። ብርድ ብርድ አለኝ።

 

ለብጹዕን አባቶቻችን ውጪ አገር እኮ ቁልምጫው ከ - እስከ አይባልም ነበር። እንዲያውም አንድ ጊዜ ይህ የበዕለ ሲመት ሲዘጋጅ የሊቢያ ሰምዕታት ጉዳይ ስለነበር አልሻም ማለታቸውን አውቃለሁኝ። ንዑዱ - ብጹዑው አቡነ መሪቀርዮስን ለመተርጎም ሆነ ለማመሳጠር መዘገበ ቃላት የለውም። ለኢትዮጵያ ልዩ ምርቃት ናቸው። ለ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክስተት ናቸው። እርጋታቸው የሰማይ እና የምድር ያህል ነው። 

 

ዜናው ላይ ብጹዕ ወቅዱስ 6ኛው ፓትርያርከ ዘኢትዮጵያን አቡነ ማትያስን አላዬሁኝም። ያዬኋቸው የቀድሞው ፕ/ ግርማ ወልደጊዮርጊስን አሳቸውን ነው።

 

እሳቸው መገኘታቸው ለይምሰል ወይንም ለላንቲካ አለመሆኑን አሳምሬ አውቃለሁኝ። ቀድሞም ሲጥሩ ነበር ሁለቱን ሲኖዶስ አንድ ለማድረግ፤ በጫና ብዛትም ቃላቸውን ሲያጥፉም አዳምጬ ነበር።

 

የሆነ ሆኖ መሰረታዊ ጉዳዩ ከልባቸው ስለመሆኑ ስለማምን የተባረከ ተግባር ከውነዋል። እንዲያውም ውጪ አገር የሚገኙ የብጹዕ ወቅዱስ አባአተችን የልጆቻቸውን ኃላፊነት ተረከብው ተውጥተዋል ብዬ አሰብለሁኝ። መረር ያለ መልዕክትም አሳተላልፈዋል። ይባረኩ። 

 

እኔ እንደ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጅነቴ ግን ፈጽሞ አትኩሮት የተነፈገው፤ የተገለለው፤ ጉምማ፤ በርዶማ፤ ቀዝቃዛ፤ የቅጣት ዝግጅት ነበር ማለት ይቻለኛል።

 

በዚህ ደረጃ እንዲህ ወርዶ ማክበሩ ምን ማለት እንደሆነ ህሊና ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ጉዳዩን የእኔ ብሎ ሊፈትሸው ይገባል ባይ ነኝ። 


መገፋት ብቻ ሳይሆን ንቀትም አለበት። ይህ ባዕል እኮ የሚሊዮኖች የማተብ የጽናት፤ የሃይል፤ የ ዕምነታችን ልዩ ምልክታችን ዓርማችን መሰረታችን ነው። 


እንዴት እንዲህ እንደዋዛ እንደ አልባሌ ሊታይ ወይንም እንዲታይ ተፈለገ? ድል እኮ የፈጣሪ ፈቃድ ነው። የሰው አይደለም። ስለነገ ማሳብ፤ ስለነገ የማድረግ አቅምም የልዑል እግዚአብሄር ፈቃድ ነው። እኔ ስለተናገርኩት ይቀልኛል። 


ብፁዕኑ እነሱ ግን በዝምታቸው ወስጥ ያለውን ረቂቅ ምርቃት ይሁን ርግማን የሚያወቀው ፈጣሪ ብቻ ነው። እነሱ ይሁን ቢሉት እንኳን ልዑል እግዚአብሄር አያልፈውም፤ ቅዱሳን መላዕከት ቸል አይሉትም። ቤተ ክርስትያናችን የተደፈረች ያህል ነው የተሰማኝ።

 

ገና በውጥኑ ይህን ያህል መገፋት እጅግ ይመራል?

በሌላ በኩል መኖሪያ ቤታቸውም እጅግ ጠባብ መፈናፈኛ የሌለው መሆኑ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ሊጎበኟቸው ሲሄዱ ተመልክቻለሁኝ። ምንማለት ነው ይሄ? የህሊና መሰናዶው እና ቅንነቱ ገና ነው ወይንም አልተጀመረም ወይንም ልገመት አለበት ማለት እችላለሁኝ።

 

አገር ለገቡት ብጹዕና የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አገልጋዮች አባቶች የተሰጣቸው ቤት በሚመለከት የረባ አይደለም የሚል መረጃ ነበር፤ ነገር ግን ራሳቸው ደውለው ትክክለኛው መረጃ ስለሰጡ፤ በጥሩ ሁኔታ እንደሚገኙ አዳምጫለሁኝ። በዚህ ውስጤ የተረበሸበት ሁኔታ ተግ ብሎልኛል።  

 

ንዑዱን ወቅዱሳን አባት አቡነ መርቅርዮስን በሚመለከት ግን ያለው ሁኔታ ትንሽ ተስፋ እያሳጣኝ ነው። ትንፋሼንም እያሳጠረኝ ነው። ተከበረ ከሚባል ተቀጣ ቢባል ይሻለዋል።

 

እያዬን እኮ ነው መንግሥት ለአንድ ቀንጣ ነፍስ ምን ያህል ሲያንጥፍ እና ሲጎዘጎዝ ውሎ እንደሚያድር። ገዝቶም ይሁን ከፍሎ ደጋፊን ሲያሰማራ እዬታዬ ነው።

 

ይህን ለመመዛዘን ብዙ ሩቅ መሄድ አያስፈልግም፤ ምክንያቱም ሰኔ ላይ ዶር አብይ አህመድ ድጋፍ ሲደረግ ይህን ያህል የህዝብ ፍላጎት ኑሮ ቢሆን ማንም ከልካይ አልነበረውም ፎቶን ለጥፎ ለመውጣት፤ ዛሬ ግን ታቅዶ ሲከውን ደግሞ እያስተዋልኩኝ ነው። ስለምን? ለሚለው ለሥርጉተ ሥላሴ አስተርጓሚ አያስፍልጋትም።

 

የሆነ ሆኑ እኔ ብጹዕ ወቅዱሱ - ንጹሁ - ቅኑ - ርጉ ደግ አባት በቁማቸው ሰማዕት የሆኑ ናቸው። እኔ ወደ አገር ሲገቡ የነበረው ሂደት ሁሉ እጅግ አርክቶኛል። 


እርግጥ ነው አስተዋዋቂዎች የአጠራር ቅደም ተከትል ግድፈት እንደፈጸሙ አስተውያለሁኝ። በሚሊዬነም አዳራሽም መሰሉን ግድፈት አዳምጫለሁኝ። ጠፍቷቸውም አልነበረም።


ቤተ ክርስትያናችን ለሁለመናው ቀኖናዊ ሥርዓት አላት። አሁን ከመላዕክታን ቅዱስ ሚኬኤልና ቅዱስ ገብርኤልን ተመልከቱ ቅደመተከተላቸውን። ከአንስት ቅዱሳንም  የእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ክብር እሰቡት።

 

ስለሆነም ቅደም ተከተል በተፋለሰ ቁጥር የሚያዝነው ልዑል እግዚአብሄር ነው። ለእያንዳንዱ የሰጠው የአቅም፤ የክብር፤ የልቅና ደረጃ አለው። ያን መጣስ ንጉሥ ዳዊት „ህግ ተላላፊዎችን ጠላሁ“ የለውን በእኛ ይፈጸም እንደ ማለት ነው። እንኳንስ ሌት እና ቀን ስለ ነፍሳት ለሚተጉ አበው ቀርቶ፤ ለ እኔ ቢጤ ተማላለም እንዲህ ሆኖ በደቀቀ መንፈስ ያን ክብር ወደ ታች ማውረድ ወዮልሽ ኢትዮጵያ ነው።

 

እኔ በአባቶቼ መንፈስ ቅርቦት በሚመለከት በጣም ቁጥብ ነኝ። በሊቀ - ሊቃውንታት ቤት እንደማደጌ አይደለሁም። አልቀርብም። ነገር ግን እኒህን ንዑድ ፍጽምናቸው ረቂቅ የሆኑ አባትን ግን እጅግ አድርጌ እንደ ታቦቴ ነው የማያቸው። ሻማ አብርቼ ሁሉ የጸጋ ስግደት እሰግድላቸዋለሁኝ። መንፈሴ ናቸው። 

 

ምክንያቱም አንደበታቸው የተከረከመ፤ በሱባኤ እድሜ ልካቸውን የኖሩ በቁማቸው ሰማዕት የሆኑ፤ በህሊናቸው ለሁሉም የሰው ልጅ እኩል ቦታ ያላቸው ናቸው። ውስጣችሁ ብታኖሯቸው የማይከብዱ፤ የዘመኑ ገድለኛነት ምስክር ናቸው። ዕሴትም - ትሩፋትም  - ታሪክም ናቸው። ለሳቸው ማዕካላቸው ሰው እና ተፈጥሮ ብቻ ነው።

 

እና ክብርን በተጋፋን ቁጥር ቅጣቱ ብዙ ነው። ስለሆነም የጠቅላይ ቤተክህነት አሰተዳደር ቢያስብበት መልካም ይሆናል። የጎረበጡኝ ነገሮች አሉና።


ዶር አብይ አህመድ ባይሆኑ እኒህን አባት ከስደት ወደ አገርቤት ንቅንቅ እንዲሉ አይፈቅድም ነበር። ይህን ያደረገው ደግሞ እራሱ ፈጣሪ ነው። እና ከፈጣሪ ጋርም መጣላት እንዳይሆን ቅጣትም አብዝቶ እንዳይታዘዝ ጠንቃቃ እንሁን።

 

ወስብሃት ለእግዚአብሄር።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።