ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም። ከዚያ የከበደ መከራ ላይ ናቸው አላዛሯ ኢትዮጵያም ሆነ እማማ አፍሪካም።
  „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤
እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“
 (ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱)
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።


·        እፍታ።

ጤናይስጥልኝ የአገሬ ቅኖች እና ቅኔዎች። እንደምን አላችሁ? ለረጅም ጊዜ ጠፋሁኝ - በምክንያት። እርግጥ ነው እሰከ ሚያዚያ ወር መጨረሻ በቀንበጥ ብሎጌ እጽፍ ነበር። ከዛ ደግሞ ቀንበጥ ብሎጌ ለተወሰነ ጊዜ መሰተጓጎል ቢገጥመውም ፌስ ቡክ ላይ ብዙ አድካሚ ያልሆኑ ግን በውስጤ እማምንበት አጫጭር ጹሁፎችን ስጽፍ ቆይቻለሁኝ። ዕይታዬ ያመለጣችሁ ይኽውና ሊንኩ።

በዚህ ሁሉ ሁኔታ ግን የድምጽ አልባዎችን የኢትዮጵያ ዕናቶች ዕንባ በፈቃድ ውክልና ለሚያደምጡኝ ደጋጎች መላኬን አላቆምኩኝ። አሁን ታስህሳስ ወር ነው በዚህ ወር ላይ ሰሚ የለም ክርስሚያስ ጥድፊያ ላይ ስለሆኑ ነጮቹ። ስለዚህ ታህሳስ እና ጥር አጋማሽ ረፍት ይሆናል ማለት ነው።

አዲሱ ጉዳይ የማይድኑ ሃሳቦች ላይ ጊዜ ማጥፋት ትቼያለሁ። አቁሜያለሁኝ። የማይድኑ ሚዲያዎችንም አላዳምጥም። ስለዚህ ሙግቱ ቀንሷል ማለት ነው። ሌላ በልቤ ሙዳይ የነበሩ ወገኖቼ ሲያዛልጣቸው ባይም ልወቅሳቸው ግን አልደፈርኩኝም። ስለምን? መብታቸው ስለሆነ። እርግጥ ነው በልቤ ያላቸውን ቦታ እንዳያጡ ባላዳምጣቸው ስለሚሻል አቅሜን ቆጥበውልኛል። እንዳከበርኳቸው ቢቀመጡ ይሻላል አድምጬ ከምቀንሳቸው።

በሌላ በኩል ደግሞ ስሞግታቸው የነበሩ ነፍሶች ደግሞ በሌላ ቭርዥን ጨለማ የዋጠውን ተስፋ ይነጋለት ዘንድ እዬታተሩ መሆኑን ሳይ መጽናናትን አግኝቻለሁኝ። ከእነዚህ ውስጥ አቶ ኤርምያስ ለገሰ አንዱ ነው። ይጨርስለት እንጂ አዲስ ታሪክ እዬሰራ ነው። እንደምታውቁት ብርኃን ሲደክም ጨለማ አጤ ይሆናል። ተስፋችን ብርኃኑ ስለደከመ ጨለማ ዋጠው።



·        የህምታ መፈወሻ።

በዚህ ዘመን ያዬሁት ብርቱ ነገር ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነው እያልኩ ለረጅም ጊዜ እጽፍ ነበር። ሞቶዬ ነበር ማለት ያስችለኛል። ቀደም ባሉት ሰሞናት በሲዊዲን፤ በጀርመን ፍራንክፈርት አማይን፤ በሲዊዲን፤ በሆላንድ ያዬሁትን አሁን በአሜሪካን አገር የተደመምኩበት ትዕይነት ህዝብ ይህንኑ ያረጋገጠ ሃቅ ነበር።

ኢትዮጵያዊነት እያሸተ የሚኖር ማንነት ስለመሆኑ ተመሰገን ብያለሁኝ። ኢትዮጵያዊነት ስታከብረው ያከብርኃል፤ ስትነቀው ደግሞ የድርሻህን ያስረክብኃል። በዚህ ሂደት አንድ ጹኑ ነፍስም ገጥሞኛል። ሥሙ ሰንደቅዓላማ ቢባል እመርጣለሁኝ። አቶ ሽመልስ ለገሰ። እንዴት ጽኑ ሰው ነው። ኢትዮጵያዊነትን በእሱ ውስጥ እንደዛ ዘውድ ደፍቶ ሳይ ሁሉን ነገር አስረሳኝ። ወጣትነቴን የገበርኩበት የነፃነት ተጋድሎ ለጃዋርውያን፤ ለሌንጮውያን፤ ለበቀላውያን ጭራቃዊ መንፈስ አልነበረም። በስል ገብተው ተስፋችን መነጠሩት። ድካማችን ቀሙን። ቀማኞች።

እዚህ እኔ በቀንበጡ የታገተ አንድ ማህበር ለመመስረት አስቤ ነበር። የማህብሩ ሥም „ቁራሽ እንጀራ“ ይል ነበር። በዛ ውስጥ ስምንት ክብቦች ነበሩ። አንዱ ስንቅ የሚያቀብል ለሌላቸው የነጻነት አርበኞች ለታሰረቱ ዋቢ የሚሆን፤ ሌላው ቋሚ የሆነ የሎቢ ሥራ የሚከውን ኃይል መፍጠር ነበር። „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል“ ያለው ይፈጸም ዘንድ በነፃነት ተጋድሎ ታሪካችን ከዲስኩር እና ከፈንድ ራይዚንግ የወጣ ተግባር የዲሲ ጉባኤ እንሆ ከወነ። ነፍስ ሆኖ ነፍስ ሰጠን።

የዲሲው ስብሰባ እጅግ የሰለጠን ነበር። ቋሚ የድምጽ አልባዎቹ የኢትዮጵያ እናቶችን ዕንባ ዋቢ የመሆን አካላቱን አቋቁሞ በቀጥታ ወደ ተግባር ነበር የገባው። ነፍስ ያለው መሪ ሲገኝ ነፍስን የሚታደግ ሙያ ያለው ተግባር እንዲህ ይከዋናል። አሁን እኛ በግል የምናደርገው ጥረት ይህ አካል በተደራጀ መልኩ ያግዛዋል ማለት ነው። በአንድ እጅ ማጨብጨብ ይቀራል። ስለሆነም የዲሲን የባላደራውን ግብር ኃይል እጅግ አድርጌ አመሰግናቸዋለሁኝ፤ አከብራቸዋለሁም። ብዙ ጫና ቀንሰውልኛል። ፈውስም ሸልመውኛል!

·        የሶልዳሪት ትግል ስለማስፈለጉ።

አጋሰሱ የኦነግ ፖለቲካ አይጠረቃም። ቁንጥን ነው። ቅልብልብ ነው። ድንገቴ ይበዛበታል። ጭንቅ ይቀናበታል። በአፈጻጻሙ ደግሞ ዝክንትል እና ዝርክርክም ነው። ይህም ሆኖ ቅኝቱ ግን አፍሪካን እርሰተ ጉልት ለማድረግ ነው።

ይህን ጉዳይ ሉላዊ ዓለምም፤ አህጉራችንም፤ ኢትዮጵያዊ ዜጋውም ፍሬ ነገሩን ገና አላገኜውም። ጉዳዩ „ከፈረቃም፤ ከተረኝነትም“ የዘለለ ነው። ወረራ፤ መስፋፋት፤ መጠቅለል የሚቀረው ነገር የለም እና።
የቁም ሰማዕቱ ዶር አብርኃም አለሙ ምስጋና ይግባቸው እና ሁለት የአገርም የአህጉርም መርዝ ማንፌሰቶዎችን ተርጉመው ነገረውናል። የአቶ በቀለ ገርባ እና የአብይወለማ ዴሞግራፊ፤ ኢቦላ ይባል ኤድስ ወይንም ካንሰር ወይንም የጭንቅላት ክንታሮት ብቻ መርዝ ነው። ለራሱ ለኦሮሞ ህዝብም ማዕት ነው የታዘዘበት። እርግማን።

ሳዳምጠው በጣም ነበር የደነገጥኩት። በቀንበጥ ብሎጌ ብዙ ነገር ሰርቼበታለሁኝ። ብዙ ፖለቲከኛ፤ ጋዜጠኛ፤ አክቲቢስት፤ ተንታኝ፤ ሚዲያ ሁሉ ተስፋ የሚሰንቀው በኦዳው ሥርዕዎ መንግሥት ከነዚህ አገር አጥፊ አብይወለማ የዴሞግራፊ እና የዘፍጥረትን ህግጋት ከጣሰው፤ ከረገጠው፤ ከገነጠለው ጭራቃዊ አቶ በቀለ ገርባ ማንፌስቶ መነሳት ስለማይችል ነው።

የእኛ ያልናቸው ዘንበል ቀና የሚሉት ይህን ፍሬ ነገር የእኔ ሳላሉት ነው። የሚገርመው የ ፕ/ መራራ ጉዲና ኦፌኮ አቶ በቀለ ገርባን ከሥልጣናቸው አላገዳቸውም። አላወገዛቸውም። ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ፕ/መራራ ጉዲና ይህን አሉ ያን አሉ ሲባሉ አዳምጣለሁኝ። መጀመሪያ የእባቡን መርዝ ከቤታቸው ያጽዱ። በቅኔ የተለወሰ መርዛቸውን በዬዘመኑ ከሚቀልቡን።

የሚገርመው አለ ያላችሁት ሁሉ በአንዱ ገለጣው ወይንም ማብራሪያው ጠንከር ብሎ ለግለግ ብሎ የወጣው ሁሉ በሌላው ገለጣ ስታዳምጡት ሸብረክ ብሎ፤ አቅቶት ሲልፈሰፈስ ታደምጡታላችሁ። ሞት ላይ ሆኖ ቁርጠኝነት እና ጽናት ከሌላ ማግሥትን ማግኜት ፈጽሞ አይቻልም። መኖርን ለማኖር ወሳኝ አቋም ያስፈልጋል።

ትናንት የአማራ ልጅ ብቻ ነበር ህልውናው አደጋ ላይ የነበረው። ዛሬ አዲስ አበቤውም፤ ጋሞውም፤ ኢትዮጵያም፤ የኔታው ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶም የህልውና ችግር ላይ ናቸው። ጉልበታም ተጋድሎ ይጠይቃል ወቅቱ። ቀበቶም፤ መቀነትም ጠብቆም ከተቻለ መልካም ነው።

ኦሮሙማ የአፍሪካ ማንፌስቶ እንዲሆን ነው ትግሉ። ፊት ለፊት አጉሞ ያለውን ክፉነትን ለመረዳት የናዚን ንድፍ እና የሁለተኛ ዓለም ጦርነትን ቀውስ በምልሰት ከልብ ሆኖ መቃኜት ማጥናትም የተገባ ነው። ዓለም እራሷ ያሰጋታል። ኦሮሙማ ፈርኃ እግዚአብሄርም፤ ፈርኃ አላህም የሌለው አጋሰስ ምኞት ነው። ታውቃላችሁ ውዶቼ እኔ ዛሬ ዛሬ የጠሚር አብይ አህመድን ገጽ ሳዬው እዚህ ሆኜ እዬፈራሁት ነው። ያስፈራል። ይጨንቃልም። ይሰልባሉ።

አብሶ ከእነ ዶር አንባቸው መኮነን ሞት በኋላ ያለውን፤ የሆነውን ነገር ሳስበው ይሰቀጥጠኛል። ባሰቡት ልክ ለመተርተርም፤ ለመሰንጠቅም ያሰቡት አልተሳከም። ይልቁንም እንደ መርግ ምስላቸው እንዲከብድን ሆኗል። ልባችንም ላይመለስ ሸፍቷል።

ኦሮሙማ አቅም የተባለውን ያገኜውን ሁሉ መዋጥ፤ ማጥፋት፤ መደምስስ ነው ቅይሳው። ስለሆነም ፓን አፍሪካኒስት ንቅናቄ ያስፈልጋል። የእንግሊዘኛ ፌስ ቡክ፤ ቲተር አካውንት፤ ብሎጎች ሁሉ ያስፈልጋሉ በተለያዩ ቋንቋዎች። ይህን ፍሬ ነገር ለዓለም በስክነት ማሳወቅ ይገባል። መከራው ዓለምንም አካላይ ነው እና።

እርግጥ ነው ቂም፤ በቀል፤ ጥላቻን ከራስ ከውስጥ ማጽዳት ይጠይቃል። ትውልዱን ኢትዮጵያዊው ትውልድ የእኔ ነው፤ የራሴ ጉዳይ ነው ማለትን ይጠይቃል። የትውልዱ በዬዘመኑ በሃሳብ መባከን፤ በቤተ ሙከራ እንደ ጥንቸል መባዘን ውስጥ ማድረግን ይጠይቃል እና።

በዚህ አጋጣሚ ለቁም ሰማዕቱ ለዶር አብርኃም አለሙ በትህትና እማሳስባቸው የአብይወለማ እና የአቶ በቀለን ገርባን ሁለት መርዛዊ ማንፌስቶ በእንግሊዘኛ እንዲተረጉሙት ነው። እርግጥ ነው አማርኛውን ለተገባው አካል በተገባው ጊዜ ተልኳል። ግን በአማርኛ እንዳለ ነው የተላከው። የትርጉም ዝበት እንዳይፈጠር በማለት።

እጅግ የሚያሳፍረው፤ ኃላፊነት የሚሰማው መሪ ኢትዮጵያ ስሌላት ትውልዱ እንዲከስል የዚህ ማንፌስቶ ባለቤቶች የዩንቨርስቲ መምህራን ናቸው። እንዳሻቸው በኢትዮጵያ መሬት እዬተንቀሳቀሱ የሰው ዘር መንጣሪውን መርዛዊ ራዕያቸውን ያስፋፋሉ። ወንጀሎኞቹ እነሱው ሆነው የአዳማው ሥርዕዎ መንግሥት ሽፋን እዬሰጠ ግን ተጠያቂ አይደለሁም ይላል።

መቼም እንደ ቁቤ ትውልድ የፈረደበት መከረኛ ትውልድ የለም። የቀደመው ላይበቃ አሁንም ሌላ ክፉ ነገር ጠጣ እዬተባለ እንዲህ ያን የመሰለ የተጋድሎ ታሪክ ጠቀራ አለበሱት። ሃዘኔ የውስጥ፤ ጭንቀቴም የህሊና ነው። የትውልዱ ብክንት ይገደኛል እና።

ወደ ቀደመው ነገሬ ስመለስ የፖለቲካ ሊሂቃን በአንድ ነገር መስማማት ያለባቸው ይመሰለኛል። የኦሮሙማ ጉዞ „ተረኝነት ፈረቃ“ አለመሆኑን ማመን መቀበል ይኖርባቸዋል። ከችግሩ ፍሬ ነገር መነሳት ካልተቻለ መፍትሄውን ማግኜት አይቻልም።

ህወኃት ኢትዮጵያ ትጋራይዝም ለማድረግ ነው የሰራው። አፍሪካን ትግራይዝም ለማድረግ አልሰራም። ኦሮሙማ ግን አፍሪካንም ኦሮማይዝድ የማድረግ ነገር ነው ንድፉ። ያልተወረረ መንፈስ፤ ያልተወረረ አመክንዮ የለም። በመሰከረሙ የ2011 ጉባኤያቸውም ይህንኑ በአጽህኖት ተናግረዋታል። ኢጋድ ጸሐፊ ዶር ወርቅነህ ገበዬሁ ሲሆኑ የኢጋድ አባል አገራት ጸጥ ነው ያሉት። አልገባቸውም ወረራ፤ መስፋፋት ስለመሆኑ። የዚህ ምደባ የታጨበት ጉዳዩ ዓላማ ስለምን ስለመሆኑ አልተረዱትም። በተመደም የታሰበው ይኸው ነበር።

በአህጉርም ሆነ በሉላዊ ዓለም ኢትዮጵያን የሚወክሉ ክፍት ቦታዎች ሲኖሩ የሚሞሉት የኦሮሙማ ማንፌስቶ አስፈጻሚዎች ናቸው። ዞግ ላይ የተቸከለ መንፈስ ነው በኢትዮጵያዊነት አቅም መንበር ላይ የዋለው።

ይህን ደግሞ ማንም አልጫነብንም። እኛው እራሳችን ፈቅደን በሰጠነው ቅጥ ባልነበረው ልቅ ፍቅር እና አክብሮት ነው እራሳችን እያስቀጠቀጥን ያለነው። ስለዚህ ተወቃሸም፤ ተነቃሽም እርስበራሱ ይሆናል ከእኔ ጀምሮ።

ሲጀመር በቅንነት ማዬት የተሰጠኝ ነው። ሲወጠን እዮባዊነትን መሰነቅ መንገዴ ነው። ግን አትኩሮቴ፤ ክትትሌ ግን የዋዛ አይደለም። ሲጓደል ወይንም ሲጓጉል ደግሞ ትዕግሥት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል። እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ከአብይ ሌጋሲ ተስፋ ከእንግዲህ አልጠብቅም።

·        በድንገቴ ተውኔት የተንቆጠቆጠው የኦሮሙማ ጥድፊያ።

ኦነጋውያን ያልሆነ የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅትም ሊሂቅም የለም። አንዳቸውም የተሻለ የሚባል ሃሳብ የላቸውም። ሁሎችም አንድ እናት ነው ያላቸው። የሚለያዩት የፍላጎት አፈጻጸም ብቻ ላይ ነው። ኦሮሞ አፍሪካን መግዛት አለበት ብለው ያምናሉ። ምኞት አይከለከል ኦሮሙማ  የዓለም ማንፌስቶም እንዲሆንም ይሻሉ። ጉዞውን ጀምረውታል። ይጨርሱት ይሆን?!ውጤቱ በእንቅልፋችን ልክ ይወሰናል። ልክ ዘነዘናውን እንደቀረው ግርባው ብአዴን።

የሚገርመው የወረራ ጥድፊያቸው ከብርኃን መፍጠኑ ነው። ለሰው ልጅ ህይወት ዋጋ የማይሰጡ መሆናቸው ሌላው መለያቸው ነው። ከዚህ በተጨማሪ ትዕቢታቸው ነው። አንድ ሁለት የኦሮሞ ሊሂቃን ሲቀሩ በስተቀር በመታበይ የተካኑ ናቸው። መታበይ ደግሞ የውድቀት መጀመሪያ ነው።  በእነሱ ቤት ሁሉ ነገር ጨርሰዋል። ሁሉ በእጄ ሁሉ በደጄ ባይም ናቸው። ፈጣሪ አላህ ያውቃል። የእዮር ደጅ ይንኳኳል። እኛ ሳይሆን የግፍ ደም ይጮኃል፤ የአራስ ደም ይጮኃል። ተስፋ የሚጠበቀው ከእዮር አደባባይ ብቻ ነው።  

የሆነ ሆኖ በዚህ በዘመነ በኦነጋውያኑ የኦፕሬሽን ሂደት የሚተርፍ አንድም ኃይማኖት፤ አንድም ትውፊት፤ አንድም ዞግ፤ አንድም ታሪክ፤ አንድም የጥበብ ዓውድ፤  አንድም ቅርስ፤ አንድም ማንነት የለም። አሁን የግንባር የፊት ተጠቂዎች የአማራ ህዝብ፤ አማርኛ ቋንቋ፤ ብሄራዊ ሰንደቅዓላማ፤ የኔታዋ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና የጋሞ ህዝብ ናቸው። ለዚህ የፊት ለፊት አጋፋሪው ደግሞ ግርባው ብአዴን የምድር እንቧዩ ነው።

የሆነ ሆኖ ቆይቶ ሁሉም በተራው ይደርሰዋል። 16ኛው መቶ ክፍለ ዘመንን በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ለመተካት ነው ጥረቱ። ይህን ለማስቆም ደግሞ የሶልዳሪት ትግል ግድ ይላል። ወሳኙ ግን „ተረኝነት ፈረቃ“ ከሚለው ዝቅተኛ ዝግመተኛ የፖለቲካ አስተሳሰብ ወጥቶ ወረራ፤ መስፋፋት ወደ ሚለው ፖለቲካ መሸጋገር ግድ ይላል።

አቅም ሁሉ መነሳት ያለበት ዴሞግራፊ እና ፍልስፍናው ጦሱና ግብዕቱ ከሚለው ላይ መሆን አለበት። በተቀባ ብልጭልጭ የቃላት ዲሪቶ መዘናጋት በፍጹም አይገባም። የሰው ልጅ ሰው ነው። የሰው ልጅ እንደ ከብት በአሞሌ ጨው መታለል አይኖርበትም። ሁሉንም ለሚያሳጣ የኦሮሙማ ሌጋሲ ሰማይና መሬት የማይበቃው ስለመሆኑ ልብ ሊባል ይገባል።

ማስቆም፤ ልጓም መስራት፤ መግታት ያስፈልጋል። በቃን! ማለት ይገባዋል የኢትዮጵያ ህዝብ። ጭካኔ አገር ሊመራ አይገባውም። እንሰሳዊ ዕሳቤ ህዝብ ሊቀጣበት አይገባም። አዘኔታ ያልፈጠረለት ኦሮሙማ በአገራችን እንዲነግሥ መፍቀድ አይገባንም። ተስፋ የሚደረገው በጨለማ ውስጥ ተሁኖ አይደለም። ተስፋ የሚደረገው በብርኃን ውስጥ ነው።

·        ክፉነት።

አላዛሯን እዬመራት ያለው መንፈስ ክፉነት ነው። እኔ ሁሉም እንደሚያውቀው በዶር አብይ አህመድ ሆነ ቲም ለማ ላይ፤ እንዲሁም በኦህዴድ አጀማመር የተደገኑት ፈተናዎችን ፊት ለፊት ወጥቼ ስሞግት እንደ ነበር ይታወቃል። ስለምን? አዬር ላይ የነበረውን፣ እንደ ባሎን የተነፋፋውን የነፃነት ትግሉ መሪ አምክንዮ ባዶነት ወናነት አውቅ ስለነበር። በእጅ ላይ ያን ጊዜ ምንም የለም ስል የሚያምን አልነበረም። ምንን ያልነበረው አቅም መሆን አለመቻሉን ግን ዛሬ ላይ ሁሉም እያዬው ነው። እሬሳ ሃሳብ በከንቱ ውዳሴ ነፍስ ሊዘራ አይችልም እና። የተስፋ ስንቅም መሆን አይችልም። የሌለው የለውም።

ስለሆነም ያን ጊዜ „ቢያንስ ልጅ የያዘውን ይዞ ማልቀስ“ አለበት የሚለውን ብሂል ልንከተል ይገባል ብዬ አስብ ስለነበር ጠንከር ያሉ ጹሁፎችን እጽፍ ነበር። ጥገናዊ ለውጥ መሆኑም በእጅ ምንም ከሌለ ባለው ነገር መጠቀም ግድ ይል ስለነበር ሞግቻለሁኝ። ያም ሆኖ ግን „አብይ ሆይ“ በሚለው በረጅሙ አቤቱታዬ ግንቦት 5 ቀን 2010 ዓ.ም ላይ በቀጥታ ሙግት ውስጥ ነበር የገባሁት።

·        ልክ።

በሌላ በኩል ሁለት ነገሮች ሊስተካከሉ እንደሚገባም አምናለሁኝ። የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ የወጣቶች ተጋድሎ ብቻ አልነበረም። ተጋድሎው ህዝባዊም ምክንያታዊም አብዮት ነው የነበረው። አርበኛ ሰማዕት ጎቤ ሆነ ኮ/ ደመቀ ዘውዱ ወጣቶች አልነበሩም። ይህን በቪዲዮ ስለሰራሁት ሊንኩን ይኸው እና።

ዕውነትን የወገነ ለሃቅ ንፉግ አይደለም። አማራነት እንዲህ ነው። አማራነት በጥበቡ ውስጥ ነው። ስለሆነም ምስክርነታችን ለጎዱንም ቢሆን ዕውነትን እንናገራለን በተገኙበት ቦታ ሃቁን ሳናዛባ እንዲህ እንመሰክራለን። ይህም ብቻ ሳይሆን በድቅድቁ ጨለማ ዘመን ፊት ለፊት ወጥተን ተጋፍጠናል ለዓለም አሳውቅናል። አማራ እጁ አመድ አፋሽ ቢሆንም።

Freedom! ነፃነት! 05.22.2018

በሌላ በኩል የኦሮሞ ንቅናቄ የግንጫው ሳቢያዊ አብዬትም ስለምን ቄሮ ሊባል እንደቻለ ለኤክስፐርቶች እተወዋለሁኝ።

በዚህ ውስጥ እስር ቤት የነበሩ የነፃነት አርበኞች እነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤን ጨምሮ ብዙ መስዋዕትነት የተከፈለበት ሲሆን፤ ብአዴን እና ኦህዴድም በበላያቸው ላይ ቤቱ እንዳይደረመስ ህዝባዊ ተጋድሎን ጠልፈው መጨረሻ ላይ ተጠቅመውበታል። ህወሃትን የሸኜው ግን የአማራ ምክንያታዊ የህልውና ታገድሎ ነበር። እነሱም እርግጡን ተናግረውታል።

ምክንያቱም የተነሳው ከወልጋዳው የህውሃት ማንፌስቶ እና ህገ መንግሥት ላይ ነበር እና። ብአዴን ሆነ ኦህዴድ ግን እራሳቸው የተፈጠሩበትን ማንፌስቶ የመሞገት አቅሙ ሊኖራቸው አይችልም። አመክንዮው ስለማይፈቅድላቸው።

የሚያሳዝነው ግን የአማራ የህልውና የማንነት ተጋድሎ ባዶ እጁን መለመላውን መቅረቱ ብቻ ሳይሆን ቀጣይ የጥቃት ኢላማ መሆኑ ታሪክ ይፍረደው ማለት ይሻለኛል። እዚህ ውጭ የምንገኝ ስደተኞችም እጅግ ረቂቅ የሆኑ ተጋድሎችን አድርገንበታል። ዛሬ እነ ሌንጮለታወባቲ ዝምንም የሚሉበትን የእኛ አርበኞች የተረሽኑት ተረሽነው፤ የታሰሩት ታስረው፤ በተገኙበት እንዲገደሉ የተወሰነባቸውን ጨምሮ ፍዳቸውን የሚዩበት ድል የአማራ መንፈስ ትሩፋት ነበር።

በዚህ የጥገናዊ ለውጥ ሂደት እማልክደው የ100 ቀኑ የጠሚር አብይ አህመድ ነገረ አማራን ሳይጨምር በሌላው መስፈርት ጉዞ አጥጋቢ ትጋት የተሞላበት የማይረሳም ነበር ማለት ይቻላል። እርግጥ ነው የሰኔ 16ቱ 2010 የምስጋና ህዝባዊ ሰልፍ የቸኮለ ነው፤ አደጋ አለበት፤ የኃይል አሰላለፉን ቀይሮ ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ ትግሉን ሊወስደው ይችላል በማለት በብሎጌ ላይ ሞግቼ ነበር። ሰሚ አልተገኜም እንጂ። እሱም ቢሆን ቀውሱ ታቅዶ እንደተከወነ ነው እኔ የሚሰማኝ።

በሌላ በኩል ከስሜን አሜሪካ ጉዞ ዋዜማ ጀምሮ ልብ የሚጣልበት አልነበረም። የኢንጂነር ስመኜው በቀለ ሞት የመጀመሪያው አዌርነስ ነበር። በስሜን አሜሪካ ጉዞ እና መልስ ያዬኋቸው አመክንዮችም ስላልተመቹኝ በጥዋቱ ነበር ሙግቴን አጠንክሬ የጀመርኩት። ነገር ግን እንዲህ ሆኖ ተስፋ ከፎቅ ይከሰከሳል ብዬ ፈጽሞ አላሰብኩም ነበር።

ዛሬ ላይ እኔ ስጽፍ ይህን ዘመን እንዲት ታይዋለሽ ብባል የመቃብር ሥፍራ ብዬ ነው። ሴራ ነው፤ ክፉ ነገር ነው፤ ስጋት ነው፤ በቀል ነው፤ ፍርኃት ነው፤ ጭንቅ ነው፤ ውሸትና ቅጥፈት ነው፤ ማታለልና ማስመሰል ነው፤ ቀወስ ተደራጅቶ ሲመራ ነው የሚታዬው፤ ቀድሞ ነገር ምን አለ የሚባል ጥሩ ነገር አለ እና። ብልጭታ የምላት ሚዲያ ላይ ያለው ነገር ብቻ ነው። ለዛውም ነገ ምን ሊሆን እንደሚችል የቆዬ ሰው ይዬው፤ ያ ምርጫ በእርግጫ ወይ በፍጥጫ ሲመጣ ይታያል ጉዱ የቤተዘመዱ ነው። „ፍትኃዊ ምርጫ“ ገለመሌ ሞኛቸውን ይፈልጉ ደህይቶም፤ ተጨቁኖም፤ ተርቦም የኢትዮጵያ ህዝብ በሰላም ውሎ ለመግባት በበቃ።  

·        የማዘነጋያ የፖለቲካ ግርዶሽ።

የማዘናጊያ ፖለቲካው ወዘተረፈ ሲሆን ጥቂቱን ላንሳ።

·        የዲስኩር ቋት። ያቅለሸልሻል።

·        ህወሃት እንደ ዋና ቁንጮ አጀንዳ እንዲሆን መሻት። አገር የሚመራው ያ የኦነግ ጨካኝ መንፈስ ሆኖ ማለት ነው። እያረደ፤ እያቃጠለ፤ ሰው ገድሎ ዘቅዝቆ እዬሰቀለ፤ ሃብት እዬዘረፈ፤ እዬወረረ፤ ወዘተ … እርግጥ ነው ህወሃትም በቀውስ ጠማኝ ፖለቲካ ድርሻ የለውም ማለት ባልችልም ግን አሁን ቁንጮ መከራ ያለው ከኦነግ አረንዛዊ ሴራ ነው።

·        አቶ ለማ መገርሳ አጀንዳ እንዲሆኑ መፈለግ። ይህን ጉግሥ እራሳቸው አቻቸው ይወጡት። እኛ ምን ይዶለናል? አቅምን ሊባክን አይገባም።

ስለሆነም ሦስቱም መስምር ብላሽ ናቸው። አቶ ለማ መገርሳ ይሁን ጠሚር አብይ አህመድ ከአንድ ወንዝ የተቀዱ ናቸው። የስንጥር ያህል በኦሮሙማ የድል ስኬት ላይ ልዩነት የላቸውም። ችግራቸው የሥልጣን፤ የዝና፤ የመወድስ መበላለጥ ነው። በልባቸው እኛ ሁላችንም ባዕድ ነን። ውስጣቸው አስቀርቦን አያውቅም። ይህ እከሌ ተከሌ የለበትም። ሃቁ ቢመርም ይኸው ነው። ስለዚህ ለማይዝምን ወቅቶ አብይዝምን የማንገሥ አባዜ ሊስተካካል ይገባዋል።

ኢትዮጵያ አምና ለሰጠችው ቁልፍ ኃላፊነት ሳይፈሩ ሳይቸሩ ለኦነግ መረጃ አቀብላለሁ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒሰተር አብይ አህመድ እኔ ወ/ሮ ማዕዛ አሸናፊን ብሆን ፍርድ ቤት ነበር እምገትራቸው ዶር አብይ አህመድን። አገር የከዳ ነፍስ እንዴትስ የአገር መሪ ይሆናል? ያ ቢቀር ቅጣት እንዴት አይበይንበትም? ዕውነት ላይ ነው መሆን ነው ያለብን። ይሰቀጥጣል፤ ያንዘፍዝፋልም።
  
ሌላው ህወሃትን በሚመለክት ታግለን አስወግድነዋል። አሁን አቅም እንዲኖረው ያደረገው እራሱ  የአብይ ሌጋሲ ነው የአማራን አቅም እንዲያዳክምለት፤ እንዲያሽለት፤ እንዲወቃለት ስለሚፈልግ። ህውሃት ሚኒስተሮች ፌድራል ላይ አሉት፤ የፌድሬሽን ሰብሳቢ ህውሃት ነው። ባጀት የበለጠውን ድርሻ ለህወሃት ነው የሚሰጠው፤  አማራን በእርግጫ እና በፍጥጫ ህወሃትን በቁልምጫ ነው የ አብይ ሌጋሲ መርሁ።

 ህወሃት 27 ዓመት ሙሉ በዘረጋው የሌብነት መዋቅር ያን ያህል ብር ተዘርፎ አምስት ሳንቲም እንዲመለስ አልተደረገም፤ ይህም ብቻ ሳይሆን ይባስ ብሎ የአብይ ሌጋሲ ኦነግን በሎጅስቲክስ በመደገፍ ተጨማሪ የስርቆት ይፋዊ መረብ ተዘርግቶለታል። በሌላ በኩል ለቀጣዩ ትውልዱ ደግሞ ሌላ የዕዳ ናዳ ይታጭለታል። ይህ ደግሞ አንደ ክብር ይዘከራል። ለመሆኑ መንፈሳችን ኡራኖስ ላይ ጁቢተር ላይ የት ላይ ይሆን ያለነው?
  
የህወሃት ህገ - መንግሥት እንዲነካ አይፈቀድም፤ የህወሃት ፖሊስ የሚመነጨው ከህገ መንንግሥቱ ነው እሱም እንዳለ ነው። ህውሃት የዘረጋው መዋቅር እንዳለ ነው።

የሚገርመው የኦነግ ቀንዶች ህውኃትን ያስታሙ ዘንድ ውሎ አዳራቸው እዛው መቀሌ ላይ ነው፤ ይህን ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ያውቅሉ፤ አማራ ሊሂቃን በመዳዳ ተመትረዋል፤ ጠሚር አብይ አህመድ ለህውኃት ጥቃቱን በማውጣት ደም መላሽ ሆነዋል።

አብን አይሆኑ ሆኖ አመራሩ አባላቱ ታስረዋል፤ ተሳደዋል፤ ተሰቃይተዋል፤ በሌላ በኩል እንደ ጦማሪ አቶ ስዩም ተሾመን ዓይነት ሰው አሰልፈው ደግሞ ህወሃትን ሲያብጠለጥሉ ውለው ያድራሉ። የሚፈለገው የኢትዮጵያ ህዝብ በኦሮሙማ ጭካኔ፤ ግፍ፤ ወረራ እና መስፋፋት ላይ አትኩሮት እንዳይኖረው ያን የህወሃት ጭካኔ እዬአመነዠከ ህዝብ እንዲቀመጥ ብቻ ነው የሚፈለገው። አቅም እዛ ላይ እንዲፈስ። ሞኛቸውን ይፈልጉ።

ለዚህ ነው „ከቀን ጅብ፤ ከጸጉረ ልውጥ ፓለቲካ ወደ ውስኪ ፖለቲካ“ ዶር አብይ አህመድ የተሸጋገሩት። ተኑ ቀረ። ደግነቱ ባይረሱን የተሸከመላቸው የለም። እራሱ „የቀን ጅብ፤ የጸጉረ ልውጥ ፖለቲካን“ ቃሉን እንኳን ተጠቅሜበት አላውቅም። እድገፍቸው በነበረበት ጊዜ ነው የተናገሩት። „ጸጉረ ልውጥ“ ታጋሩ ከዬት ነው የመጣው? ኢትዮጵያዊ አይደሉምን እነ ተጋሩ?

የሆነ ሆኖ በዚህ 19ኛ ወራት አንደ አማራ ህዝብ የደቀቀ የለም። ዓመቱን ሙሉ ኦነጋውያን  የራሳቸውን አቅም ሲያደራጁ፤ ሲመሩ ግርባው ብአዴን ደግሞ የኦዳን ሥርዕዎ መንግሥት ጥምቀት ተቀብሎ እንግዳ ሲቀበል፤ ሲሸኝ ጃኖ ሲያልበስ ባጀ። 

በሁሉም የሃላፊነት ቦታ ደግሞ ከማዕከል ተባረረ። „ውጭ ጉዳይ“ ሚኒስተር እንዳትሉ እና እንዳታስቁኝ። ምስል መሆንን አይተካም እና። ሌላውን አመክንዮ ትቼ።

ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ በአዲስ አባባ ዙሪያ ሲሰፍር ትግሉ አማራዊ ትውፊትን፤ አማራዊ ታሪክን፤ አማራዊ ቅርስን መወረር ስለመሆኑ ቃሬዛ ላይ የባጀው ብአዴን ኳሽታ አላሰማም። የሚገርመው አሁን ደግሞ ሁለት ልዑክ ነው ያለው ስሜን አሜሪካ ላይ። ለማደንዘዝ። ድግምት ወይንም አዚምን ለማስጨለጥ። ዕውነት ግን ብትቀበርም ማቆጥቆጧ አይቀርም።

·        እግዚአብሄር ይመስገን።

እግዚአብሄር ይመስገን ከጨረሰላቸው ኢትዮ 360፣ ሞጋቹ ርዕዮት ሚዲያ፤ ማህል ላይ ያለው መረጃ ቲቢ ደህና እዬሞገቱ ነው። ካለ ሚዲያ ምንም ማድረግ አይቻልም። ሚዲያ ለዚህ የጨለማ ዘመን መድህን ነው። ስለሆነም የቻለ በሚችለው ሊደግፋቸው፤ በሃሳብ ሊያጠናካራቸው ይገባል። ቢያንስ ሸር እና ሳብስክራይብ ማድረግ የቤት ሥራችን ሊሆን ይገባል።  

·        ባለ አደራው እና ተስፋነቱ።

በባለ አደራው ላይ ያለው አፈና እራሱን በቻለ ሁኔታ መረጃውን አጠናክሮ መጻፍ ያለበት የታሪካችን ክፍለ አካል ነው። እንኳንም ተፈጠረልን። እኔ ቀደም ሲል በፌስ ቡኬ ስሞግት ነበር እንጀራውን ጋግራችሁ ለማን ልትሰጡ ነው እያልኩኝ። አሁን ወደ ፖለቲካ ድርጅት ሊያድግ ስለሆነ እውነተኛ ሞጋች ዘር ዋጭው ኦሮሙማ ይገጠምዋል ብዬ አሰባለሁኝ።

መታመን የበለጸገበት የዕውነት ጉዞ ጊዜው ቢረዝምም አሸናፊ ይሆናል ብዬም አስባለሁኝ። ደህና ሞጋች እንጂ እጁ እስኪላጥ የሚያጨበጭብ የፖለቲካ ሊሂቅ ለኢትዮጵያ አያስፈልጋትም። ሊሞገቱ ይገባል ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ። ለነገሩ ፈሪ ናቸው።

 ገና አቶ ክርስትያን ታደለ በምርጫ ተወዳድሮ ቢያሸንፍ የተወካዮች ምክር ቤት ላይ ይሞግተኛል ብለው ነው አስቀድመው ያሰሩት። አቶ በለጣ ካሳ ለመናጆ ነው የታሰረው። ኢላማው አቶ ክርስትያን ታደለ ነው። አቅሙን ፈሩት። ለነገሩ ስብሰባ ጠርተው የጠየቃቸውን እዬለቀሙ የሚያስሩ ጉድ እኮ ናቸው። እኔ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እያሉ የነበራቸው አጓጊ ሰብዕናን ለማን እንደሸጡት አላውቅም። እንዲህ አልነበሩም እኮ።

ወደ ቀደመው ጉዳዬ ምልሰት ሳደርግ በዚህ አጋጣሚ ለባለ አደራው ታምራዊ ጉዞ የፈጣሪ እጅ እንዳለበት እኔ አምናለሁኝ። ልደታ ዕለት መጋቢት 1 ቀን 2011 ሲጀመር የታዬው እዮራዊ አስተምኽሮ በራሱ በቂ ነው። ፉክክር ነበር ገና በውጥኑ እዮር መልስ የሰጠበት። 

ያን ጊዜ ለማወአብይ ትቢያ ነስንሰው አቤት ይበሉ፤ ሱባኤ ይግቡ ብዬ ብሎጌ ላይ ሁሉ ጽፌያለሁኝ። ከዛም በኋላ የሆኑት ሁሉ በእዮራዊ ታምራት የታገዙ ናቸው። ፈቃደ እግዚእብሄር አለበት ብዬ አምናለሁኝ የባልደረሱ ምስረታ። ለነገሩ ከውጥኑ ጀምሮ በኢተዮጵያ ታይተው የማይታዩ የሰማይ ቁጣዎች በሳቸው ዘመን ታይተዋል።

·        ዕውነት መሆን ያቃተው ዙፋን።

ውሸት በጠሚር ደረጃ ሲሆን አያምርም። እንኳንስ ውሽት የማይመጥን ቃል „ላፍ“ አድርጎ ወዘተ … እንደዚህ ዓይነት ቃሎች እራሱ አይመጥኑም። ያው „ግልጽ ጦርነቱን እንገባለን፤  ለአንድ ክልል ተብሎ ህገ መንግሥት አይቀዬርም፤ እኔ ስሾም ችግር ከሆነ ስወርድ ችግሩ ይቀራል መስቃም“ የሚሉ ስንኞችንም አዳምጠናል።

የሆነ ሆኖ ብዙ ውሸቶችን፤ ስላቆችን ስናዳምጥ ያው አገራዊ ስለነበር ብዙም አያሸማቅቅም። በዓለም አደባባይ ግን „አንድም እስረኛ የለም“ ብሎ ሙልጭ ያለ ውሸት መዋሸት ግን ያስገምታል።
„የሰላም ስብከቱ“ ሌላው የእንቧይ ካብ ውሎ ነበር። የትኛው ሰላም? በኮማንድ ፖስት የተካሄደው የሲዳማ የክልልነት ድምጽ አሰጣጥ? ወይንስ በኮማንድ ፖስት የሚመሩ አካባቢዎች? ወይንስ ከጠቅሚሩ ቀጥሎ ያለው የሰራዊቱ አዛዡ ህልፈት እንደዛ መሆን? ሩብ አገር እንኳን የለም የሚመራ።

 ያው መከረኛው አማራ ክልል እና አዲስ አባባ ነው ርግጫውም ፍጥጫውም ጫናውም ያለው። ለመሆኑ ሰላም ግን ትርጉሙ „የሰ“ „የላ“ እና „የም“ ፊደላት መጣመር ነውን? እግዚኦ ነው።

እኔ  እንደ አንድ ዜጋ እንዴት እንደተሸማቀቅኩኝ ፈጣሪዬ ነው የሚያውቀው። ምክንያቱም እስረኞች መኖራቸውን ብቻ ሳይሆን ዕለታዊ የኢትዮጵያ ጭካኔያዊ ሰቆቃ የኖቤል ሸላሚው ኮሜቴ በሚገባ ያውቀዋል። ከዚህም በዘለለ ብዙ አካላት ስለሰው ጭንቅ ጥበብ የሚሉ ያውቁታል።

ሽልማት ለእኔ የህዝቤ የኑሮ ዋስትና ማግኜት ነው። አዲስ አበባ ላይ ለባላደራሱ ስብሰባ ጋዜጣዊ መግለጫ ቤተ መንግሥት ላይ መጥታችሁ አድርጉ ስለሚፈጠረው ነገር ዋስትና መስጠት አልችልም ያለ መንግሥት ጠሚር እኮ ነው አሁን ስለ ሰላም ያን ያህል የአመክንዮ ትንተና በ ዓለም አደባባይ የሚያስደምጠን? ጋዜጠኛ፤ አክቲቢስት በጠባቂ ዘብ ባለበት አገር?

የሚገርመው እስረኛ መኖሩ ብቻ አይደለም የሚታወቀው። ሞት በቀጣይ የሚያሰጋቸው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፤ ጋዜጠኛ ተመስገን ደስ አለኝ እና አቶ ክርስትያን ታደለ ስለመሆናቸው ይታወቃል። የማንን ጎፈሬ እምናበጥር ይመሰላቸዋል ጠሚር አብይ አህመድ?

እሳቸው ለካዱት መታመን፤ እሳቸው በግርዲር አፍር ለጫኑት የህዝብ ፍቅር እኛ የሚጨንቀን ይመስላቸዋልን?! በውነቱ ቀልደኛ ናቸው። ለሳቸው ስንመሰከር እዚህ ብራና ላይ ብቻ አልነበረም። አልፈን ሄደንም ነበር ቢሾሙልን ብሄራዊ ቀናችን ይሆናል ብለን የመሰከርነው። ያ ድካም የሎጥ ሃውልት ሲሆን ህሊና በጅ ይል ይመስላቸዋልን? ብልጠት ብልህነት መሰላቸውን? ለመሆኑ ሽልማቱ ይገባኛል ብለው ያምኑበታል ዶር አብይ አህመድ ሙሳናን እጠላላሁ ስለሚሉ? ሙስና መሆኑ አይገባቸውንም? ምን አለ ቀስ አድርገው ዝቅ ብለው ቢይዙት። ደስታውንም በልክ ቢያስተዳደሩት። ለነገሩ መካሪ የላቸውም።  
  
የሆነ ሆኖ መታመኑ ሲጣስ ደግሞ የለመደበት ብዕር ዕውነቱን አብዴት ማድረግ ግድ ይለዋል። ይልቅ ማባጨሉን ትተው ዕውነት ይሁኑ - ከቻሉ። ውሸት የሳሙና አረፋ ነው። ውሸት ጤዛ ነው። ለራሳቸው እራሳቸውን ያታልሉት እኛ ግን ልብ አለን። ልብ እንዲገጠምልን አንሻም።  

ሌላው ያላወቁት ነገር እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ መክሊት ይዞ መወለዱን ነው። እያንዳንዳችን የተፈጠርንበት ጥሪ አለን። ከእጄ አስገባሁት ያሉት ዲያስፖራ እውነቱን ካጣ መንፈሱ ይሸፍታል።
እምነቴን የኔታዋ ቅድስት ኦርቶዶክ ተዋህዶ እንደ ችቦ እዬነደደች፤ ብጹዑን አባቶቼ ዕንባ አውጥተው እያለቀሱ፤ በጭንቀት ሰጥመው እዬተሰቃዩ፤ እዬታገቱ፤ ምዕምኑ እዬተሰዉ፤ ቅዱስ ወንጌል እዬነደደ፤ መስቀል እዬተረገጠ፤ ድምጽ አልባዋ እናት ልጇ እዬተመተረ፤ አካሉ እዬተቃጠለ፤ አማራነቴ በሁሉም መስክ የጥቃት ኢላማ እዬሆነ ሥርጉተ ሥላሴ እምትተኛ ይመስላቸዋልን? አይሰቡት።

ለሳቸው ስታገል በነበረው ልክ አሁንም ሴራቸውን እና ዕብለታቸውን እታገላለሁኝ። እኔ አቶ ለማም መገርሳም፤ ግራጫማ በሲቃ ሰብዕና እምገልጸው አቶ ጃዋር መሃመድም፤ ጊዜ የሸሸውን ህወሃትም አይደሉም ቀዳሚ አጀንዳዎቼ። አቅምም ስለ እነሱ አላፈስም። አጀንዳዬ እሳቸው ናቸው። መሪ መሆን፤ ዕውነት መሆን፤ ቃል መሆን የተሰናቸው የራስ አምላኪ ሥልጣኑ እያላቸው የክት እና የዘወትር ዜጋ አበጅተው አገርን መከራ ላይ ያስቀመጡ፤ ህግ ማስከበር ያልቻሉ።

ኃላፊነት መመውሰደም ተጠያቂነትንም የሚሸሹት እሳቸው ናቸው። ሺ ሚሊዮን ጊዜ ይህ አገር አንድ ጠሚር ነው ያለው ያም እኔ ነኝ አይደለም የሚሉት። ስለዚህ አጀንዳ ሊሆኑ የሚገባቸው እሳቸው እና እሳቸው ባዳለጣቸው ቁትር ዕንባ ማዋጣት የማይሰለቸው ካቢኔያቸው ነው። 

እኔን መሸንገልም፤ በለበጣ የሥንኝ ውበት መማረክም አይቻልም። እኔ እኔ ነኝ። ልብ እንዲገጠምልኝ አልሻም። ዕንባ ሲያቆም፤ ዋይታ ሲቀር፤ ሰቀቀን ሲቀበር ያን ጊዜ ስብከታቸው ይደመጣል። ይልቅ የራስ ካድሬነታቸው ገልምቶኛል። እመወደው ደጉ ሳተናው፤ አብዝቼ እመከታተለው ዘሃበሻ መግባት እንኳን ሰልችቶኛል። ሁሉ ቦታ ፎቷቸውን ማዬት ስለገለማኝ። ቋቅ ብሎኛል። ትንሽ ቢደበቁ ደስ ይለኛል።
እሳቸው ብቻ እኮ ሆኑ አራጊ ፈጣሪ የሆኑት፤ ተጽዕኖ ፈጣሪ፤ ሞድ አሳይ፤ ሰባኪ፤ ካድሬ፤ ፕሮፖጋንዲሰት፤ መሪም።

እኔ የናፈቀኝ እንዲህ የራሳቸው ዞጋዊ መንፈሶች የ ኢትዮጵያን ህዝብ የውስጥ ሰላሙን ነፍገው በጭንቅ የሰነጉትን ህዝብ አዟችሁ የሚል መሪ ነበር የናፈቀኝ። ሶርያውያን ብዙዎቹ ሴት ልጆቻቸውን አንጌላ ብለዋል። የደግነት ተምሳሌት ስለሆኑ መራኂተ መንግስት የጀርመኗ ጠሚር አንጌላ ሜርክል ዕንባ ላይ ቀዳሚ እናታዊ ተግባር ፈጻሚ ስለሆኑ እበዝተው ሶሮያውያን ይወዷቸዋል። እጠብቀው የነበረው መሪ ይህን ነበር። ግን ህልም እልም ህልም እልም ሆኖ ነው ባክኖ ነው የቀረው። ከንቱ ሁሉም ነገር ከንቱ አለ መጽሐፉ።

እርግጥ ነው ዓለም ስላበደችም ስለታመመችም በቀን 100 ሺህ ሰው እረሽናለሁ ላለ የሰላም ሽልማት ሸልማለች። ነገ ታገኛታለች። ያ ክብር ሳይሆን ቅጣትም ነበር። ቢሆን ጥሩ የነበረው ጊዜ ተሰጥቷቸው ካለተቃርኖ ከድክመታቸው ተምረውበት ካለሰቀቀን እንዲወስዱ ነበር። የፕሬስ ጉባኤ እንኳን መቀበል አልተቻላቸውም። አምና ይህን ጊዜ የ ኢኮኖሚ ፎረም ላይ ደረታቸውን ነፍተው ተገኝተው ነበር። አሁን የዱቤ ክብር ነው የወሰዱት። ሽልማቱ ቀብድ የመሆን አቅም እንኳን የለውም እንኳንስ ዓይነታ። እርግጡ ይሄ ነው። ድልዝም ልብጥም አያስፈልገውም ያለ ቀኑ ያለ ጊዜው ያለ ብቃቱ በግርግር የተገኜ ፑፓ አጋጣሚ ነው።  

·        ቢስተካከል። ይህን አሁን ከሆነ ፌስ ቡክ ላይ ስለምሳተፍ የታዘብኩት ነው።

1) „መንጋ“ የሰው መንጋ የለውም። የእንሰሳት እንጂ። ስለዚህ ቢታረም እሻለሁኝ። ቡድን እዬተባለ ቢጠራ።
2) „ጋላ“ አንድ ማህበረሰብ አልጠራበትም፤ አልፈልገውም ካለ ማስከፋትን ማቀንቀን ሰውኛ ስላልሆነ ኦሮሞ በሚለው ቢስተካከል። በዚህ ውስጥ ጤነኛ መንፈሶች ሁሉ አብረው ሊወቁ አይገባም። እንደ ቅኔው ልዑል ብላቴ ጌታ ሎሬት ጸጋዬን የመሰለ፤ በህይወት ያሉም እንደ ድንቁ ዶር ሼክስፒር ፈይሳ ዓይነት ወገኖች አሉን። ብዙ እጅግ በርካታ የድንግልና መንፈስ ያላቸው ወገኖች አሉን።
3) ይሄ ፎቶ የሚዘቀዘቀው፤ ፎቶን ከእንሳሳ ጋር አመሳስሎ የሚሰራው ነገር የፈጣሪን የአላህን ሥራ መጋፋት ስለሆነ እያንዳንዱ ዜጋ እራሱን በራሱ በማረም ቢያስተካክለው።
4) የፖለቲካ ሊሂቃን ባጠፉት ጥፋት ልጆቻቸውንም ወቃሽ አድርጎ ማቅረቡ። ይህም እንዲሁ የማይመቸኝ ጉዳይ ነው።
5) የከፋቸው ወጣቶች ብድር ላይ ያለች፤ በዕዳ የተዘፈቀች፤ ዕዳውን ሳትከፍል የተገዛው ወይንም የተሰራው ነገር ሃብቷ ይነዳል፤ እዚህ አገር አሮጌ እቃዎች ክብር አላቸው የቱሪዝም ክፍለ አካል ናቸው፤ የእኛ ደግሞ ክብራችን ማቃጠል ነው። ኑሮን ማቃጠል እራስን በራስ መግደል ምን የሚሉት ፈሊጥ እንደሆን አይገባኝም።  መንገድ ተዘግቶ ህዝብ ይጉላል፤ ኢኮኖሚም ይደቃል። ይህም ያልተገባ ጅልነት ነው። በስጋት እድገትም፤ ብልጽግናም አይገኝም።
6) „ሰፋሪ፣ መጤ፣ ስደተኛ“ ሰው በአገሩ ስደተኛ አይደለም። ለዛውም ኢትዮጵያን በእጁ ላበጀ የአማራ ህዝብ ነው ይህ ቅጥያ የሚሰጠው። ይህም የተገባ አይደለም መስተካከል ይገባዋል። ለዚህ ሥልጣን የተበቃው ግርባው ብአዴን በሰጠው ሙሉ ድምጽ የአማራ ልጅ ህይወቱን በገበረበት አብዮት ነው።  
7) „ጋለሞታ“ አንዳንድ ሰዎች ሲጽፉ ኢትዮጵያን „ጋለሞታ“ ይሉታል። ሎቱ ስብኃት ስለቃሉ። አንደኛ የሴቶችን ክብር ይነካል። ቃሉ ጸያፍ ቃል ነው። ሴቶች በፈቀዱትም ይሁን ባልፈቀዱትም አሰገዳጅ ሁኔታ ትዳራቸው ሊፈረስ ይችላል። ያ መሰደቢያቸው ሊሆን አይገባም። ወደ አገር ስንዘልቅ ደግሞ ኢትዮጵያ ፈትም አይደለችም። ኢትዮጵያ ድንግል ናት። ድንግልናውም እሸት ነው። „አዲሲቱ ኢትዮጵያ“ የሚለው እራሱ አይመቸኝም። ኢትዮጵያ ሁልጊዜ አዲስና እሸት ናት።

·        መከወኛ።

መፍትሄ አምንጪ ችግርን ማወቅ ነው። ኢትዮጵያ ላይ ያለው መከራ „ተረኝነትም፤ ፈረቃም“ ፈጽሞ አይደለም። መንግሥታዊ መዋቅርን ቦታውን ማስያዝ ጥድፊያ ላይ ያሉት ረጅሙን ጉዞ ለማሳካት ጥርጊያ መንገድ እዬደለደሉ ነው። አስፓልቱ ኢትዮጵያዊነትን አስመጦ ኦሮማዊነትን በኢትዮጵያም በአፍሪካም ማጨግዬት ነው። ስለዚህ ተጋድሎው ጠንከር ያለ የፖለቲካ የሃሳብ ልቅና አቅምን ይጠይቃል። ራሱን ያሸነፈ አቅም ብቻ ነው ይህን መራራ፤ እጅግም ጎምዛዛ የመከራ ዘመን መሻገርም፤ ማሻገረም የሚችለው።

ተስፋ ተስፋ በሚሆን ላይ ነው መጠበቅ ያለበት። ተስፋ በማይሆን ነገር ላይ የራስን አቅም አጠራቅሞ፤ የራስን አቅም ቆጥቦ በማስተዳደር የራስን ጉዞ አህዱ ማለት ነው። አይ ይህ  የኦሮሙማ ጥምቀትም የኦዳ ሥርዕዎ መንግሥትም ተመችቶኛል ካለ ግለሰብ፤ ቡድን፤ ሆነ ተቋም፤ ወይንም የፖለቲካ ድርጅት ጋርም በእሰጣ ገባ ጊዜ ማባከን አያስፈልግም። አቅም አላግባብ ማጎሳቆልም አይገባም።

ለዚህ መሰል የቤተ - መንግሥት ቅልጥመኛ „መንገዱን ጨርቅ ያድርግልህ ብሎ መተው ነው። ጸጸቱ ሲቀቅለው ያውቀዋል። በሌላ በኩል አብይዝምን መደገፍም መብት መሆኑን አምኖ መቀበል ይገባል። ዴሞክራሲ ማለት መሬት ላይ ፈተናው ይኼው ነው። የማትፈልገውን ነገርም  በአቅምህ ልክ ሞግተህ ማሸነፍ የመቻል ጥበብ። ብትሸነፍ እንኳን መቀበል።

በዚህ ውስጥ ጋዜጠኛው፤ አክቲቢስቱ፤ የፖለቲካ ሊሂቁ፤ ተንታኙ እንደ ፈረሰኛ ውኃ ከመጋለብ ለራስ ጊዜ ሰጥቶ ጥሞናዊ ጊዜ ሊኖረው ይገባል። እራሱ ጠሚር አብይ አህመድ 365 ቀናት ካሜራ ጋር ቃልኪዳን ከሚያስሩ የጥሞና ጊዜ ቢኖራቸው ይመረጣል። የቀደሙት የጥበብ መጀመሪያቸው የጥሞና ጊዜ በተግባር ሰሌዳቸው የታቀደ በኽረ ጉዳይ ስለነበር ዛሬ የማይገኙት አሻራዎች የተገኙትም በዛ የልቅና ልዕልና ነበር።

ንግሥናውን ጥለው ገዳም የገቡት መዋለ ታሪክ የሚናገረው ይሕንኑ ነው። የኢትዮጵያ ድንቅነት የሚለካውም እንደ ካህን ታቦት በተሸከሙት አጤ እያሱ፤ ንግሥናውን ትቶ ገዳም እንደገባው እንደ ጻድቁ ላሊበላ ወዘተ ያሉት ልጆች ስለነበሯት ነው - ኢትዮጵያ። ዛሬም ቢኪነ ጥበቡ መኖር ያቻለችው በቀደሙት የጸሎት እርሾ ነው።   

·        የልቅና ልዕልና የተደሞ አርምሞ። አማራነት ይሄ ነው።

የኔታዋ የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት የምህላ ተደሞ ጎንደር በአርምሞከጥቅምት 01 ቀን እስከ ህዳር 10 ቀን 2012 ዓም።

ከጥቅምት 23 ቀን እስከ ህዳር 23 ቀን 2012   30 ተከታታይ ቀናት የተካሄደው የዱአ ሥርዓት 

በጎንደር።


ሌላው የቃጥላል፤ ያውካል፤ ቀውስ አደራጅቶ ይመራል፤ ያሸብራል። ደጉ አማራ ደግሞ ስለ አገሩ ሰላም ሌት ተቀን ይጸልያል።

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነው።
ትዕግሥት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።
ፍቅርም ሲያልቅ ትዕግሥት ይሰደዳል።

የኔዎቹ ኑሩልኝ። መሸቢያ ጊዜ።




አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።