ልጥፎች

ከሴፕቴምበር 26, 2025 ልጥፎች በማሳየት ላይ

እንጎሮጎባሽ። እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሰን፦ አደረሳችሁ። አሜን።

ምስል
  እንጎሮጎባሽ። እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሰን፦ አደረሳችሁ። አሜን። ለእኛ ለቅኒት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማንያን መስቀል ሁለመናችን ነው።   "መስቀል ኃይላችን፤ መስቀል መዳኛችን፤ መስቀል መጽናኛችን።"     #መስቀል ህይወታችን። #መስቀል ትንፋሻችን። #መስቀል ሩኃችን። #መስቀል ፈውሳችን። #መስቀል ትህትናችን። #መስቀል ክብራችን። #መስቀል ፍቅራችን። #መስቀል ማንነታችን። #መስቀል ውስጣችን። #መስቀል ደግነታችን። #መስቀል ጸሎታችን። #መስቀል ቅዳሴያችን። #መስቀል ዕውቀታችን። #መስቀል ጥበባችን። #መስቀል ዊዝደማችን። #መስቀል ማዕረጋችን። #መስቀል ሞገሳችን። #መስቀል መርኃችን። #መስቀል ተስፋችን። #መስቀል ጎዳናችን። #መስቀል መኖራችን። #መስቀል ብርኃናችን።   ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን። ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን። መልካም ዓውድ ዓመት። አሜን።   ኑሩልኝ። አሜን። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 26/09/2025 ወስብኃት ለእግዚአብሄር።

ፈላስፊት ኢትዮጵያ ሆይ! አማኑኤል አባቴ #ከመፈንቅለ #መንግሥት ሙከራም፤ ስኬትም ያውጣሽ። አሜን።

ምስል
  ፈላስፊት ኢትዮጵያ ሆይ! አማኑኤል አባቴ #ከመፈንቅለ #መንግሥት ሙከራም፤ ስኬትም ያውጣሽ። አሜን።   "እግዚአብሄር ገርና ትሁት ልቡናን አይንቅም።"   #ምዕራፍ ፲፯።    በፖለቲካ ህይወቴ ከሚያሰጉኝ ጉዳዮች ትልቁ መፈንቅለ መንግሥት ነው።          #ምክንያቴ በስሱ። 1) መንፈቅለ መንግሥቱን የሚያደርገው አካል ምን ገጽ? ምን ባህሪ? ምን የፖለቲካ፤ የኢኮኖሚ አቅም፤ ምን የፖለቲካ አቋም እንደሚያርምድ ድፍን ነው። ሥም የለሽ።   2) መፈንቅለ መንግሥቱ በግል ወይንስ በወል እንደምን ሊፈጸም ይችላል ለሚለውም መገመት አይቻልም። ፎርም የለሽ ነውና።   3) #ፈንቃዩ ቢሳካለት ለለት የሚገባው ቃል እና እዬቆየ እያከረረ ሊሄድ የሚችለው ፖለቲካዊ አቋምን መተንበይ አይቻልም።    4) የመፈንቅለ መንግሥቱ ባለቤት ማንን #ጠላት አድርጎ እንደሚነሳ አይታወቀም። ስለዚህ ያልተሰናዳው ተጠቂ እጅግ የሚሰቀጥጥ ኢሰባዊ እርምጃ ሊደርስበት ይችላል።    5) የመፈንቅለ መንግሥቱ ተጠሪ #ከወገቡ በላይ #ሰውኛ ፤ ከወገቡ በታች #ምንኛ ሊሆን እንደሚችልም ዝግ ነው።    6) ይህም ብቻ አይደለም #እስር ቤት የሚገኙ ወገኖቻችን ላይ ሥልጣን ላይ ያለው የብልጽግና መንግሥት ይሁን፤ የመፈንቅሉ አስተናባሪ ሊወስድባቸው የሚችለው እርምጃ እና የደህንነታቸው ዋስትና አሁን ካለው የከፋም ሊሆን ይችላል። የፖለቲካ እስረኞች ለፈንቃዩም፤ ለተፈንቃዩም ለግራ ቀኙ እንደ ስጋት ስለሚታዩ። ጥቃቱም ባለቤት አልቦሽ ሊሆን ይችላል። በሰው እጅ ያሉ ከአዲስ አበባ ጀምሮ በሌላው ክልል በትናንሽ ከተሞች የታሰሩ ፖለቲከኞች ዕጣ ፈንታ ጨለማ ነው።...

ተመድን #ሴት መርታው ደግሞ ተቋሙ ቢታይ ጥሩ ይመስለኛል። "ትራንፕ በተባበሩት መንግሥታት ጉባኤ ላይ `#ደባ #ተፈጽሞብኛል´ በማለት ምርመራ እንዲጀመር ጠየቁ፤" ( ዘገባው የBBC የአማርኛ ቋንቋው ፔጅ ላይ ነው ያገኜሁት።)

ምስል
  #ኦኦ ፤ #ይህም #አለ #ለካ ።   "ትራንፕ በተባበሩት መንግሥታት ጉባኤ ላይ ` #ደባ #ተፈጽሞብኛል ´ በማለት ምርመራ እንዲጀመር ጠየቁ፤"   ( ዘገባው የBBC የአማርኛ ቋንቋው ፔጅ ላይ ነው ያገኜሁት።)   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።       እንዴት አደራችሁ ውድ የአገሬ ልጆች። ይህን ዘገባ ሳነብ ብዙ ነገሮች መጡብኝ። የዓለም ፖለቲካ እና ዕድምታው #በታቀደውም ይሁን #በገጠመኝም እንዲሁም #በድንገቴ የሚከሰቱ ጉዳዮች እንደምን አትኩሮት እንደሚሰጣቸው አስተዋልኩበት። ፖለቲካ ስስ ተፈጥሮ እንዳለው ፊደል ቆጠርኩበት።   እርግጥ ነው ጉዳዩ #አንድ ብሎ፤ #ሁለትን አስከትሎ፤ #ሦስተኛ አመክንዮንም ደርቧል። እንዲህ ነው፤ እንዲያም ነው ብየ ልለው አልችልም። ፖለቲካ #የግምት ወይንም #የአቦ #ሰጥ ቀመር አይደለምና። ብቻ ግሎባሉ ዓለም እና የዘመኑ የፖለቲካ ባህሬን መነሻ አድርጌ #በዘለግታ ኢትዮጵያ ትናንት በዚህ መሰል ወይንም በተቀራራቢ ገጠመኞች ያለፈችበት የፖለቲካ ታሪክ፤ ዛሬ ስላለው የኢትዮጵያ የዘመኑ የፖለቲካ ባህሬን በውል ማጥናት እንደሚገባ አሰብኩኝ።    ይህ ሂደት አስተምህሮቱ ተወራራሽ የሆኑ ገጠመኞች፤ ወይንም ልዩ የሆኑ የአንድ አካባቢ ክስተቶች ፖለቲካዊ ይዘት ከኖራቸው በጥንቃቄ እና በአስተውሎት ሊመረመሩ እንደሚገባ፤ #ስሜትን ተቆጣጥሮ የተፈጠረውን ክስተት፤ አገላብጦ ማየት እና #ብይን በጥድፊያ ላለመስጠትም የሚያስተምር ሆኖ አግኝቸዋለሁኝ። ከውሳኔ በፊት የተጣራ ፋክትን የመጠበቅ አስፈላጊነት የሚያስተምር #ሐዋርያ ሆኖ አግኝቸዋለሁኝ። ለዚህም ነው ዜናውን ሼር ያደረግኩት።    በዚህ ሂደት ትናንት በጹሁፌ ያነሳሁት ...