ተመድን #ሴት መርታው ደግሞ ተቋሙ ቢታይ ጥሩ ይመስለኛል። "ትራንፕ በተባበሩት መንግሥታት ጉባኤ ላይ `#ደባ #ተፈጽሞብኛል´ በማለት ምርመራ እንዲጀመር ጠየቁ፤" ( ዘገባው የBBC የአማርኛ ቋንቋው ፔጅ ላይ ነው ያገኜሁት።)
( ዘገባው የBBC የአማርኛ ቋንቋው ፔጅ ላይ ነው ያገኜሁት።)
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።

እንዴት አደራችሁ ውድ የአገሬ ልጆች። ይህን ዘገባ ሳነብ ብዙ ነገሮች መጡብኝ። የዓለም ፖለቲካ እና ዕድምታው #በታቀደውም ይሁን #በገጠመኝም እንዲሁም #በድንገቴ የሚከሰቱ ጉዳዮች እንደምን አትኩሮት እንደሚሰጣቸው አስተዋልኩበት። ፖለቲካ ስስ ተፈጥሮ እንዳለው ፊደል ቆጠርኩበት።
እርግጥ ነው ጉዳዩ #አንድ ብሎ፤ #ሁለትን አስከትሎ፤ #ሦስተኛ አመክንዮንም ደርቧል። እንዲህ ነው፤ እንዲያም ነው ብየ ልለው አልችልም። ፖለቲካ #የግምት ወይንም #የአቦ #ሰጥ ቀመር አይደለምና። ብቻ ግሎባሉ ዓለም እና የዘመኑ የፖለቲካ ባህሬን መነሻ አድርጌ #በዘለግታ ኢትዮጵያ ትናንት በዚህ መሰል ወይንም በተቀራራቢ ገጠመኞች ያለፈችበት የፖለቲካ ታሪክ፤ ዛሬ ስላለው የኢትዮጵያ የዘመኑ የፖለቲካ ባህሬን በውል ማጥናት እንደሚገባ አሰብኩኝ።
ይህ ሂደት አስተምህሮቱ ተወራራሽ የሆኑ ገጠመኞች፤ ወይንም ልዩ የሆኑ የአንድ አካባቢ ክስተቶች ፖለቲካዊ ይዘት ከኖራቸው በጥንቃቄ እና በአስተውሎት ሊመረመሩ እንደሚገባ፤ #ስሜትን ተቆጣጥሮ የተፈጠረውን ክስተት፤ አገላብጦ ማየት እና #ብይን በጥድፊያ ላለመስጠትም የሚያስተምር ሆኖ አግኝቸዋለሁኝ። ከውሳኔ በፊት የተጣራ ፋክትን የመጠበቅ አስፈላጊነት የሚያስተምር #ሐዋርያ ሆኖ አግኝቸዋለሁኝ። ለዚህም ነው ዜናውን ሼር ያደረግኩት።
በዚህ ሂደት ትናንት በጹሁፌ ያነሳሁት "#ለምን?" የሚለው ቃል በዚህ ሂደት ዘውድ ደፍቶ ከች ብሏል። ድርጊቱ ይሁን ክስተቱ ለምን ተብሎ ይሆን ይህ የተከሰተው? እንደምንስ እንዲህ ታሰበ? ወይንም ሆነ? ሂደቱ እና ውጤቱስ የትስ ይደርሳል? በውጤቱ ምን ያስገኛል ምንስ ያሳካል? ማን --- #ምን ያተርፍበታል? ትርፍ ካለውስ ግሎባሉ በትውልድ የውርርስ ፖለቲካ ምን ሊማርበት ይችላል? የሚሉ እንደ ሰንሰለት እርስበእርሳቸው የተያያዙ ወይንም የሚከታተሉ የጉዳዩ #አድራሻ #አፈላላጊ ኩነቶች አዕምሮን ይፈታትሻሉ።
ለነገሩ እኔ በወቅቱ የተባበሩት መንግሥታት አመራር እንደ አባት ክቡር ኪም ዘመን አልሆነልኝም። በብልጽግና እና በህወሃት መካከል በነበረው ጦርነት የተቋሙ ሚዛኑ ትክክል አልነበረም። ለነገሩ ህወሃት ማለት ምን ማለት መሆኑን አሁን በዝርግ ዓለማችን እያዬች፤ እየታዘበች ይመስለኛል።
አቤቱ ህወሃት ከማህል አልታረስ፤ ከዳር አልመለስ ብሎ የዘወትር የፖለቲካ ተንታኞችን፤ የኢትዮጵያ ህዝብ መንፈሳዊ የጸጥታ አቅምን ያለ አግባብ በብክነት #እየሰለቀጠ አለ አጀንዳ ሆኖ። ያው ዓለም አቀፍ መነጋገሪያነቱ ሊቀጥል ባይችልም፤ በብሄራዊ ደረጃ አሁንም አጀንዳ ነው። የበቃን ብቻ በትዝብት እያዬነው ነው አቤቱ ህወሃትን።
ለአቤቱ ህወሃት ሞጋችም፤ ጠበቃም ሆነው የነበሩ የግሎባል ተቋማት እራሳቸውን ቢመዝኑት፦ #አጤ #ፊድባክ በታሪኩ ስህተት ፈጽሞ አያውቅም እና ፋክቱን ቁልጭ አድርጎ ያቀርብላቸዋል ባይ ነኝ። ከተጸጸቱበት ወይንም ከተማሩበት። ይቅርታ መጠየቁ የማይታሰብ ቢሆንም።
የሆነ ሆኖ በሰባዕዊ መብት ዓለም ዓቀፍ አያያዝ ወጣ ገብነትም የማስተውለው ተደማጭ አቅም ከተቋሙ ከተመድ በእኩልነት ለየትኛውም የዓለም ዜጋ አላስተዋልኩም። ምን አልባት በቀጣዩ ምርጫ ክብርት ዶር. #አንጌላ ሜርክል የቀድሞ የአገረ ጀርመን ካንስለረ፤ የአውሮፓ ህብረት ጹኑ አከርካሪ የነበሩት፤ ወደ ፖለቲካው የመመለስ ዕድል ከኖረ ተቋሙ አዲስ የአቅም፤ የተሻለ የተደማጭነት ሁነት ሊያመነጭ ይችል ይሆናል።
ተመድን #ሴት መርታው ደግሞ ተቋሙ ቢታይ ጥሩ ይመስለኛል። ተመድን አለ ወይ ሊያስብሉ የሚችሉ እጅግ በርካታ ግሎባል አመክንዮች አሉና። የራሺያ እና የዩክሬን ጦርነት፤ የፍልስጤም እና የእስራኤል ጦርነት ብዙ አገሮችን ያካተተ ነው፤ የሱዳኑ የእርስበርስ ጦርነት እና የኢትዮጵያ ያላባራው፤ መቋጫ ያላገኜው ጦርነት ሌሎችንም ጉዳዮች ሲታሰቡ #ተመድ የሚጠበቅበት ኃላፊነት፤ የተደማጭነቱ ደረጃ እና አቅሙ ለእኔ የሚመጣጠን ሆኖ አላገኘሁትም።
ስለሆነም አሁን በአሜሪካ መንግሥት በፕሬዚዳንት በክቡር ዶናል ትራንፕ እና በክብርት ቀዳማዊ እመቤት ሜላንያ ትራንፕ ላይ ተፈጠረ የተባለው ክስተት ከተመድ የቅድመ ዝግጅት #ስስነት ወይንም የኮኦርድናሽን ችግር ወይንስ ከዚህ ከፍ ባለ የፖለቲካ ውስብስብ ጉዳይ?
ከዚህ አንፃር ጉዳዩን ወደ አገራዊ ስናመጣው ብዙ ልንማርበት የሚገባ ይመስለኛል። ቸኩሎ እና ተጣድፎ ብይን መስጠት እንደማይገባ፤ በሌላ በኩል የፕሮቶኮል ደረጃ፤ በተጨማሪም የአፈፃጸሙ ዲስፕሊን አካሄድ በተደራረበ ሁኔታ መከሰቱ። ለማንኛውም BBC የአማርኛው የዘገበውን ከሥር ሙሉውን ሃሳብ ለጥፌዋለሁኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
25/09/2025
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ሰክና ማሰብ፤ ረግቶ ማስተዋል ይጠቅማል።
-----------------------------------===============--------------------------------
• «ትራምፕ በተባበሩት መንግሥታት ጉባዔ ላይ 'ደባ ተፈፅሞብኛል' በማለት ምርመራ እንዲጀመር ጠየቁ»
«ዶናልድ ትራምፕ ረቡዕ ዕለት በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ንግግር ሊያደርጉ በሄዱበት ወቅት "ሶስት ጊዜ ደባ እንደተፈጸመባቸው" በመግለጽ ድርጅቱ ጉዳዩን እንዲመረምር ጠየቁ።"
"በማኅበራዊ ሚድያቸው መልዕክታቸውን ያሰሙት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ከቀዳማዊ እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ ጋር አሳንሰር (ኤስካሌተር) ሊጠቀሙ ሲሉ ማሽኑ መበላሸቱን አውስተዋል።"
"አክለው ንግግር ሊያደርጉ ሲዘጋጁ ፅሑፍ የሚያሳየው ማሽን (ቴሌፕሮምፕተር) እና የድምፅ መቆራረጥ እንደነበር ጠቅሰው "ሶስት ጊዜ ደባ ተፈፅሞብኛል" ብለዋል።"
"የተባበሩት መንግሥታት ባለሥልጣን ድምፅ ማጉያው የቀነሰው አንዳንድ ግለሰቦች በትርጉም እንዲሰሙት ለማስቻል ነው ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።"
"የተባበሩት መንግሥታት ቀደም ብሎ በሰጠው ምላሽ አሳንሰሩ የተባለሸው የትራምፕ ቪድዮን የሚያነሳ ግለሰብ ወደኋላ በመውጣቱ ማሽኑ ሳይቆም እንዳልቆረ ጠቁሞ ቴሌፕሮምፕተሩ ደግሞ የአሜሪካ ልዑካን ይዘው የመጡት ነው ብሏል።"
"ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል ገፃቸው ሁኔታውን የተቹት ሲሆን ለተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ምርመራ እንዲካሄድ የሚጠይቅ ደብዳቤ እንደሚልኩ አስታውቀዋል።"
"ትናንት በተባበሩት መንግሥታት የሆነው በጣም አሳፋሪ ነው። አንድ ብቻ አሊያም ሁለት ብቻ ሳይሆን ሶስት ጊዜ ደባ ተፈፅሟል። ይህ በግጥጥሞሽ የሆነ አይደለም። ሶስት ጊዜ ነው ደባ የተፈፀመው። በራሳቸው ሊያፍሩ ይገባል።"
"ፕሬዝደንቱ ኤስካሌተሩን ሲቆጣጠሩ የነበሩ ሰዎች በቁጥጥር ሥር እንዲውሉም ጠይቀዋል። "ይህ ደባ ነው። በኤስካሌተሩ አካባቢ ያሉ የደኅንነት ካሜራዎች ሊታዩ ይገባል። ሲክሬት ሰርቪስ ሁኔታውን እየተከታተለው ነው" ብለዋል።"
"በተባበሩት መንግሥታት የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ማይክ ዋልትዝ ሁኔታው "ተቀባይነት የለውም" በማለት ምርመራ ይካሄድ የሚለውን የትራምፕ ሐሳብ አንፀባርቀዋል።"
"ዩናይትድ ስቴትስ መሰል የደኅንነት ስጋቶችን እና ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ክብር የሚነኩ ጉዳዮችን አትታገስም። ፈጣን የሆነ ምላሽ እንጠብቃለን" ሲሉ በኤክስ ገፃቸው ፅፈዋል።"
"ረቡዕ የዋይት ሐውስ ፕሬስ ሴክሬታሪ ካሮላይን ሌቪት አሳንሰሩ እንዲቆም የተደረገው ሆነ ተብሎ ነው ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል።
"ፕሬዝደንቱ እና ቀዳማዊ እመቤቷ ወደ አሳንሰሩ ሲወጡ ሆነ ተብሎ ከሆነ እንዲቆም የተደረገው በፍጥነት ምርመራ ሊደረግ ይገባል።"
ትራምፕ ወደ ተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባዔ ዘልቀው ንግግር ሊያሰሙ ሲዘጋጁ ፅሑፍ የሚያሳየው ማሽን እንደማይሰራ ለተሰብሳቢዎች አሳውቀዋል።"
"ይህን ቴሌፕሮምፕተር የሚያንቀሳቅስ ግለሰብ ትልቅ አደጋ ላይ ነው" በማለት ቀልድ ቢጤ ማስጠንቀቂያም አሰምተው ነበር።
አንድ የተባበሩት መንግሥታት ባለሥልጣን ለቢቢሲ እንደተናገሩት ቴሌምፕሮምፐተሩን ይዘው የመጡት የዋይት ሐውስ ልዑካን ናቸው።»
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ