ልጥፎች
ከኦገስት 23, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ
የክፋ ሃሳብ ወረራ #ግሎባል ነው። ቅሬታ፣ በቀል፣ ተጠቂ። (Beschwerde, Rache, Opfer.)
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
የክፋ ሃሳብ ወረራ #ግሎባል ነው።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
የክፋ ሃሳብ ወረራ #ግሎባል ነው። "እግዚአብሄርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደምሳሌያችን እንፍጠር …… እግዚአብሄርም ሰውን በመልኩ ፈጠረው፦ ወንድ እና ሴት አድርጓቸው ፈጠራቸው። እግዚአብሄርም ባረካቸው፥ …… " ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ፩ ከቁጥር ፳፯ - ፳፰ የክፋ ሃሳብ ወረራ በእኛ ብቻ ያለ አይደለም። ግሎባል ነው። የትም ቦታ፤ በዬትኛውም ሁኔታ ሊከሰት ይችላል። እርግጥ ነው ዬክፋ ሃሳብን ወረራ የተቋቋሙ፦ እራሳቸውን ያሸነፋ ሰብዕናወች ይኖራሉ። ለዛም ነው ያልጠፋነው ብዬ አስባለሁኝ። የእነሱ ደግነት ጠባቂያችን እንደሆነ እረዳለሁኝ። ክፋ ሃሳብ #ተፈቅዶም ፤ #ሳይፈቀድለትም በአካላችን ውስጥ ይሰርፃል። ተፈቅዶለት ስል አሉታዊ ሰብዕና ያላቸው #ወደው የሚያደርጉትን ሲያመለክት፤ ሳይፈቀድለት ያልኩት ግን በሁኔታወች አስገዳጅነት ከመከፋት፤ ከመገለል፤ ከመጨቆን፤ በደል ከመድረስ ጋር ተያይዞ በሚመጡ #ብስጭቶች ሳቢያ ክፋ ሃሳብ ውስጣችን ሊፀንስ ይችላል። ሲፀነስ የደረሰውን በደል በህሊና ለረጅም ጊዜ እንቅልፍ አልባ ሁነን ሁሉ #በማመላለስ ፤ በማላመጥ፤ ክፋ ሃሳብን በመገብ ከዛ አትሞስፌር እንዳይወጣ የሚደርጉ #የስሜት #ጫናወች ሊኖሩ ይችላሉ። ያን ክስተት በማውጣት በማውረድ ረጅም ጊዜ ማንሰላሰል - ማብሰልም። ከዛ ቀጣዩ #ቅሬታን ይጠነሳል። ቅሬታው ወደ #በቀል ሊያምራ ይችላል። ይህም ብቻ አይደለም ጉዳዩ ውሎ ሲያድር ያን የክፋ ሃሳብ ባህሪም ተጠቂ በመሆን #የራስ የማድረግ ዝንባሌ ሊኖር ይችላል። ሳይፈቅዱት የተዳበለን ክፋ ሃሳብ ጋር ጋር ቤተኛ መሆን ወይንም #መላመድ እንደማለት። ክፋ ሃሳብ ተጽዕኖ ፈጣሪ ነው። በውነቱ #የሰው ልጅ በክፋ ሃሳብ፦ ለ...