የክፋ ሃሳብ ወረራ #ግሎባል ነው።

 

የክፋ ሃሳብ ወረራ #ግሎባል ነው።
"እግዚአብሄርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደምሳሌያችን እንፍጠር ……
እግዚአብሄርም ሰውን በመልኩ ፈጠረው፦ ወንድ እና ሴት
አድርጓቸው ፈጠራቸው። እግዚአብሄርም ባረካቸው፥ …… "
ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ፩ ከቁጥር ፳፯ - ፳፰
 May be an image of heart and text
የክፋ ሃሳብ ወረራ በእኛ ብቻ ያለ አይደለም። ግሎባል ነው። የትም ቦታ፤ በዬትኛውም ሁኔታ ሊከሰት ይችላል። እርግጥ ነው ዬክፋ ሃሳብን ወረራ የተቋቋሙ፦ እራሳቸውን ያሸነፋ ሰብዕናወች ይኖራሉ። ለዛም ነው ያልጠፋነው ብዬ አስባለሁኝ። የእነሱ ደግነት ጠባቂያችን እንደሆነ እረዳለሁኝ። 
 
ክፋ ሃሳብ #ተፈቅዶም#ሳይፈቀድለትም በአካላችን ውስጥ ይሰርፃል። ተፈቅዶለት ስል አሉታዊ ሰብዕና ያላቸው #ወደው የሚያደርጉትን ሲያመለክት፤ ሳይፈቀድለት ያልኩት ግን በሁኔታወች አስገዳጅነት ከመከፋት፤ ከመገለል፤ ከመጨቆን፤ በደል ከመድረስ ጋር ተያይዞ በሚመጡ #ብስጭቶች ሳቢያ ክፋ ሃሳብ ውስጣችን ሊፀንስ ይችላል። 
 
ሲፀነስ የደረሰውን በደል በህሊና ለረጅም ጊዜ እንቅልፍ አልባ ሁነን ሁሉ #በማመላለስ፤ በማላመጥ፤ ክፋ ሃሳብን በመገብ ከዛ አትሞስፌር እንዳይወጣ የሚደርጉ #የስሜት #ጫናወች ሊኖሩ ይችላሉ። ያን ክስተት በማውጣት በማውረድ ረጅም ጊዜ ማንሰላሰል - ማብሰልም። ከዛ ቀጣዩ #ቅሬታን ይጠነሳል። 
 
ቅሬታው ወደ #በቀል ሊያምራ ይችላል። ይህም ብቻ አይደለም ጉዳዩ ውሎ ሲያድር ያን የክፋ ሃሳብ ባህሪም ተጠቂ በመሆን #የራስ የማድረግ ዝንባሌ ሊኖር ይችላል። ሳይፈቅዱት የተዳበለን ክፋ ሃሳብ ጋር ጋር ቤተኛ መሆን ወይንም #መላመድ እንደማለት።
 
 ክፋ ሃሳብ ተጽዕኖ ፈጣሪ ነው። በውነቱ #የሰው ልጅ በክፋ ሃሳብ፦ ለክፋ ሃሳብ ፦መሳሪያነ - ት፣ አገልጋይነትም አልተፈጠረም። የሰው ልጅ ሲፈጠር #ለምስጋና#በከበረ - የአፈጣጠር #ሚስጢር #ሚስጢር ሆኖ ነው። የሰው ልጅ እኮ አፈጣጠሩ ሚስጢር ነው። እራሱም ሚስጢር ነው። 
 
ከሰው በላይ ውብ፤ ማራኪ፤ #ድንቅ እና ልዩ ተፈጥሮ ፈጣሪ አምላካችን አልፈጠረም። ባርኮም ነው የፈጠረው። ነገር ግን ይህ ልዩ፦ #ምስጉን በምርቃት የተፈጠረ ፍጡር የአፈጣጠሩን ንጽህና የሚያስጠብቅለት ተቋም እንደ ተወለደ በአራስ ቤቱ #ስለማይቀበለው በቀጥታ ከጩኽታሟ ዓለም ጋር #በግላጭ ይቀላቀላል። 
 
ዕድል ከረዳው ቤተሰቦቹ በመልካምነት ላይ የሚተጉ ከሆነ የመዳን ዕድሉ ሰፊ ነው። ይህም ቢሆን አንድ ልጅ ሲያድግ ከማህበረሰቡ ጋር ስለሆነ፤ በትምህርት ቤት፤ በሥራ - አካባቢ፤ በመኖሪያ ሰፈር ክፋ ሃሳብን የሙጥኝ ካሉ ሰብዕናወች ጋር መገናኘቱ አይቀሬ ነው። ለዚህም ነው ትናንት በደግነቱ የሚታወቀው አዲስ የሆነ ሰብዕና ተላብሶ ሲመጣ ምን ነካው ብለን የምንደነግጠው። 
 
#ጉልህ ምክንያት።
 
ምክንያቱም ወጥ የሆነ የመልካምነት ዓውደ ተቋም ዓለማችን የላትም። ቤት በጎ ነገር ቢኖር ውጪ ደግሞ #ክፋት ይጠብቃል። ስለሆነም የሰው ልጅ #በቅይጥ ፍላጎት እና #ስሜት ወጀብ ውስጥ እንዲንገላታ ሆኗል።
 
 #ክፋ የሚባሉትም #በጎ ነገር ላይጠፋቸው ይቻላል። መልካም የሚባሉትም በጥቂት - ጥቂቱ በስሱ የክፋ ሃሳብ #ሽውታ ወይንም ንክኪ ሊታይባቸው ይችላል። ባይፈልጉት እንኳን የክፋ ሰወችን ድርጊት #ያደምጣሉ። እንደ ሰውም በክፋ ሃሳቡ ክንውን ቁጭት አነሳሽነት የሚሞግቱበት ስልት ሊቀይሱ ይችላሉ። ፈፃሚውንም ሊያቄሙት ይችላሉ። ሳይወዱ እና ሳይፈቅዱ ባልፈለጉት ቦታ ሊገኙ ይችላሉ። 
 
ክፋ ሃሳብ በውስጥ በተያዘ ቁጥር የመዋለ ዕድሜ፦ የማይወለድ ጽንስ ሆኖ በሆድ መሸከም ነው። ጤናን ያውካል። እራስን ያሳጣል። ማንነትን ይቀይራል። ከተፈጥሯዊነት መሃባም ያወጣል። ከሁሉም ለምስጋና የፈጠረ አምላክ ይከፋል። 
 
እሱ ሲከፋ ደግሞ ምርቃት ይነሳል። ምርቃት ሲነሳ ጥበብ ይጎድልበታል። የጥበብ ወላቃነት ከዊዝደም ጋር ያፋታል። ይህ ሲሆን ጥረት ሁሉ ከንቱ ድካም የማያፈራ መሃን ሊሆን ይችላል። 
 
ይህ እንዳይሆን ክፋ ሃሳብን በውስጥ ላለማስቀመጥ ከራስ ጋር መታገል በእጅጉ ያስፈልጋል። እራስንም ማሸነፍ ይገባል። የክፋ ሃሳብ ጥሪት ለትውልድም ለዓለም ህልውና ስልጣኔም መርዝ ነው። 
 
©ድካማችን ለትውልድ ከሆነ ………
©ልፋታችን ለአደራ ከሆነ ………
©ትትርናችን ለማግሥት ከሆነ ክፋ ሃሳብን በውስጥ ላለማስቀመጥ እንትጋ። ፈጣሪም ይርዳን። አሜን። 
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
 
ኑሩልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
23/08/2024
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።