ልጥፎች

ከኖቬምበር 3, 2022 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ደስታን በልክ መያዝ ይገባል። ሳያንጠራሩም //// ሳያንኳስሱም። የአምባሳደር ሬድዋን የእንኳን ደስ አለን መልዕክት

ምስል
  ደስታን በልክ መያዝ ይገባል። ሳያንጠራሩም //// ሳያንኳስሱም።     ለምን? 1) ዬአሳቸው ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ሶፍት ዌር ስለ ነገ ምን ፕሮግራም እንዳደረገ ስለማናውቅ። አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በዚህ ቦታ ቢኖሩ ብላችሁ እሰቡ። ላይ ላይ ጋላቢው እና ፈረሰኛው የዶክተር አብይ ሶፍት ዌርን በማስተዋል እንደማለት። ይልቅ አቶ ሬድዋን ሲሸኙ ለአህጉር፤ ለዓለም አቀፍ ተቀጣሪነት እጮኛ ለመሆን መደላድሉ ተሠርቷል። 2) የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ልብ የሚጣልባቸው አይደሉም። ሁሉም። 3) ዬኢትዮጵያ ፖለቲካ ቅኝቱም ሆነ ተፈጥሮውም ጆሮ ደግፍ የያዘው ነው። 4) ሌላ ተጨማሪ ደሥታ ካገኛችሁ መደርደሪያው እንዳይሞላባችሁ ቀንሳችሁ ተደሰቱ። 5) በሌላ በኩል ደሥታው ህልም ዕልም ከሆነ ተስፋ ቆራጭነት፤ ሲከተል የሥና - ልቦና ህመም እንዳያመጣ። 6) በመጨረሻ ፈጣሪ አመጣጥኖ ባልተያዘ አመክንዮ ምርቃቱን ስለሚያነሳ በልክ ሁኑ፤ በልክ አግርጉት። በፐርሰንት ቢወጣ አትራፊው፤ ድል ያደረገው ማን እንደሆን ሆዳችሁ ያውቀዋል። ደግሞ ፍርስርሳችሁ ወጥቶ ለሦስተኛ ጊዜ ኖ ሞርን እዘሉልን ካላላችሁ??? ለዚህ ሁሉ ዬህዝብ ሠላማዊ ሠልፍ ብክነት ነበር። ለዚህም ነበር ሽሬ ላይ እኒያን ዬእግዚአብሄርን ሰው ሚዲያ ላይ ስታወጡ፤ ወሎ ላይ አስተኳሹን ስታወጡ ተው ያልኩት። ዬትናንትም የዛሬም ዬኢህዴግ ልሳን ይህን ብለዋል። "ዬዛሬው ቀን ኢትዮጵያ እና ሰላም ድል ያደረጉበት ቀን ነው። ልገልፀው ዬማልችለው ደስታ ተስምቶኛል።" አዲሱ የፋና አንባቢ እንዳቀረበው። ለዚህን ጊዜ ማን እንደሚፈለግ ታውቃላችሁ። ዬአንባሳደር ሬድዋን ሁሴን የጠቅላይ ሚሩ የደህንነት አማካሪ የተናገሩት ነው። ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ደግሞ ይህን አስፍሯል። Daniel Kibret@danielkibret «ኢትዮጵ...