ደስታን በልክ መያዝ ይገባል። ሳያንጠራሩም //// ሳያንኳስሱም። የአምባሳደር ሬድዋን የእንኳን ደስ አለን መልዕክት

 

ደስታን በልክ መያዝ ይገባል። ሳያንጠራሩም //// ሳያንኳስሱም።
 

 
ለምን?
1) ዬአሳቸው ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ሶፍት ዌር ስለ ነገ ምን ፕሮግራም እንዳደረገ ስለማናውቅ።
አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በዚህ ቦታ ቢኖሩ ብላችሁ እሰቡ። ላይ ላይ ጋላቢው እና ፈረሰኛው የዶክተር አብይ ሶፍት ዌርን በማስተዋል እንደማለት። ይልቅ አቶ ሬድዋን ሲሸኙ ለአህጉር፤ ለዓለም አቀፍ ተቀጣሪነት እጮኛ ለመሆን መደላድሉ ተሠርቷል።
2) የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ልብ የሚጣልባቸው አይደሉም። ሁሉም።
3) ዬኢትዮጵያ ፖለቲካ ቅኝቱም ሆነ ተፈጥሮውም ጆሮ ደግፍ የያዘው ነው።
4) ሌላ ተጨማሪ ደሥታ ካገኛችሁ መደርደሪያው እንዳይሞላባችሁ ቀንሳችሁ ተደሰቱ።
5) በሌላ በኩል ደሥታው ህልም ዕልም ከሆነ ተስፋ ቆራጭነት፤ ሲከተል የሥና - ልቦና ህመም እንዳያመጣ።
6) በመጨረሻ ፈጣሪ አመጣጥኖ ባልተያዘ አመክንዮ ምርቃቱን ስለሚያነሳ በልክ ሁኑ፤ በልክ አግርጉት።
በፐርሰንት ቢወጣ አትራፊው፤ ድል ያደረገው ማን እንደሆን ሆዳችሁ ያውቀዋል። ደግሞ ፍርስርሳችሁ ወጥቶ ለሦስተኛ ጊዜ ኖ ሞርን እዘሉልን ካላላችሁ??? ለዚህ ሁሉ ዬህዝብ ሠላማዊ ሠልፍ ብክነት ነበር። ለዚህም ነበር ሽሬ ላይ እኒያን ዬእግዚአብሄርን ሰው ሚዲያ ላይ ስታወጡ፤ ወሎ ላይ አስተኳሹን ስታወጡ ተው ያልኩት።
ዬትናንትም የዛሬም ዬኢህዴግ ልሳን ይህን ብለዋል።
"ዬዛሬው ቀን ኢትዮጵያ እና ሰላም ድል ያደረጉበት ቀን ነው።
ልገልፀው ዬማልችለው ደስታ ተስምቶኛል።" አዲሱ የፋና አንባቢ እንዳቀረበው።
ለዚህን ጊዜ ማን እንደሚፈለግ ታውቃላችሁ።
ዬአንባሳደር ሬድዋን ሁሴን የጠቅላይ ሚሩ የደህንነት አማካሪ የተናገሩት ነው።
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ደግሞ ይህን አስፍሯል።
Daniel Kibret@danielkibret
«ኢትዮጵያ - ዛሬ የተቀኘሽውን ቅኔ፤ ትውልድ ለዘመናት ሲፈታው ይኖራል። ቀነየ ማለት ዛሬ ነው።»
የህወሃት የሥልጣን ሽኝት፤ የኖቬል ሽልማት፤ የጦርነት መንስዔ ምንድን ነው? እሱን በትክክል ስትመልሱ የቤተ መንግሥታት አማካሪወች ቅኔውም ይቃኛል፤ ሰላሙም ዘውድ ይደፋል፤ ድሉም ባለ ተክሊል ይሆናል። ጊዜሰጥታችሁ እዩት። በጉራጅ ኢህአዴግ ወደ አምስት ዓመት፤ በስንጥቅ ጥገና ደግሞ ስንት ጊዜ ቀናት ይመልሱታል። 
 
ያስቀረው፤ ያተረፈው፤ ዬከሰረውን ለመመዘንጊዜ ስጡት። ከደስታም፤ ከእልልታም ታቅቦ እግዚአብሔርን ማመስገኑ ማዕከላዊ ምርጫ ነው። ያልተደፈሩ ዕውነቶች አሉ። ረመጥ ታቅፈው የተቀመጡ። ተግ ማለት ይበጃል። ሳያቃሉም፤ ሳያገኑም። ሳይለጥጡም ሳይሸበሽቡም። ሳያሸበሽቡም ቅኔን ሳይዘርፋም። ያተረፈ አትርፏል። ዬከሰረም ከስሯል። ማግሥት እራሱን እንዲገልጽም ዕድል መስጠትይቸባል።
አዲሱን ዬፋና ሰውም ተዋወቁት።
የአምባሳደር ሬድዋን የእንኳን ደስ አለን መልዕክት
አሉታዊ ዴሞግራፊ ላይ ተቀምጦ ዘናነት ዕብንነት ነው።
የቤትህ ቅናት በላኝ።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
03/11/2022
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው። በዚህ እንስማማ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።