ልጥፎች

ከሜይ, 2021 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ጸጋዬ ራዲዮ የ27.05.2021 መሰናዶ ኢትዮጵያ እና አስቸጋሪ ጊዜዋ። (Äthiopien und seine schwie...

ምስል

Ethiopian Renaissance Part I Fekadu Bekele

ምስል

የኔታዋ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኢትዮጵያዊ፤ አፍሪካዊ ግሎባላዊት ናት! የኔታዋ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዩንቨርስም ናት!

ምስል
    እንኳን ወደ ከበቡሽ ሚዲያ በሰላም መጡልኝ።     በስመ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ። አሜን። ·        የኔታዋ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኢትዮጵያዊ፤ አፍሪካዊ ግሎባላዊት ናት! ·        የኔታዋ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዩንቨርስም ናት!   ዕለተ አርብ ማዕዶተ ኢትዮጵያ! በከቡብሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ሕይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ።   „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“ (ምሳሌ 16 ቁጥር 9)   ·        ዕለተ አርብ ማዕዶተ - ኢትዮጵያ!   የኔታዋ አርቶዶክስ ተዋህዶ አገረ ኢትዮጵያን በተፈጥሯዋ ልክ ያበጀች አንቱ ዓይነታ ሃይማኖት ናት። ዕውነት ከተደፈረ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የተፈጥሯዊነት በቅዱስ መንፈስም ናት። የሰውኛነት ውስጡ ናት። ይህቺ ቤተ-   ክርስትያን በጸበሏ ሁሉን በህመም የተንገላቱ ወገኖችን ሁሉ የፈወሰች። በፍቅር ያስተናገደች።  የፍቅራዊነት ያጠጣች፤ የሰበከች ሐዋርያም ናት። በጸሎቷ ለሁሉ አጥር ቅጥር ሆነ የኖረች ያኖረች ህልውናም ናት። ዕውቀት አፍልቃ አጽድቃ ያሰበለች ፈርጥ ኃይማኖት ናት። የሥልጣኔም ብሩህ ጎዳናም ናት … ዝማሬዋ፤ ማህሌቷ፤ መልዕክተ ዮኋንሷ፤ ሀሁ ገበታዋ፤ አቡጊዳዋ ለሁሉ እኩል የህሊና መስኖ ሆኖ ሰብዕናን ገንብቷል። አንፆዋልም። ቅድስቷ ቅድስናዋ በማለት ሳይሆን በተግባር ከብራ ያስከበረች የጽረ አርያም ቤተኛም ናት። ቅድስታችን ትምክህትን የናቀች በመከራ በቅላ፤ በመከራ ኖራ፤ መከራን ድል ያደረገች የድል ሁነኛ ተቋም፤ የችሎት ኮከብ አደባባይም ናት። በቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ውስጥ ህፃፅ የለም። ግድፈት የለም። በዶግማ እና በቅኖናዋ ውስጥ ሳንክ የለም። ተዋህዶ

ኢትዮ እስራኤላዊቷ ኤደን አለነ የምሥራች ለኢትዮጵውያን ናት! ለ2021 Eurovision Song Contest ለፋይናል አለፈች።

ምስል
  እንኳን ወደ ከበቡሽ ሚዲያ በሰላም መጡልኝ።   ·        ኢትዮ እስራኤላዊቷ ኤደን አለነ የምሥራች ለኢትዮጵውያን ናት! ·        ለ2021 Eurovision Song Contest ለፋይናል አለፈች። ·       አገረ እስራኤልን ወክላ የ21 ዓመቷ ወጣት ኢትዮ እስራኤላዊቷ አርቲስት ኤድን አለን ለ2021 Eurovision Song Contest ለፋይናል አለፈች። ጠንከር ያለ ውድድር ቅዳሜ ይጠብቃታል።   ዕለተ ሃሙስ   ማዕዶተ ሰጋሪው በከቡብሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ሕይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ።   „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“ (ምሳሌ 16 ቁጥር 9) ·        እፍታ። ዕለተ አርብ ማዕዶተ ኢትዮጵያ የሚናፍቀኝ፤ የምጓጓለት ለት ነው። በኢትዮጵያዊነት ጥበብ ዙሪያ ነው የሚያተኩረው። ዛሬ አውሮፓዊው የጥበብ ማዕዶትን አስመልክቶ በጨረፍታ መረጃ አቀርባለሁኝ። የኢትዮጵያ ጠረንም በላይኛው ጥበብ ፈቃድ ተሳታፊ ሆኗል። ይገርማል። ይደንቃል።  የፈጣሪ ሥራ ግሩም ነው። „ ሃሌ ሉያ። እግዚአብሔርን አመስግኑ ስሙንም ጥሩ፥   ለአሕዛብም ሥራውን አውሩ። ተቀኙለት፥ ዘምሩለት፥ ተአምራቱንም ሁሉ ተናገሩ።“ መዝሙር ምዕራፍ 105 ቁጥር ከ 1-2 ·         ወግ ቢጤ …   በአውሮፓ በየዓመቱ በወርሃ ግንቦት የሚካሄድ የሙዚቃ ውድድር አለ። Eurovision Song Contes ይባላል። የአንድ ጎልማሳ ዕድሜ አሳልፏል። ባለፈው ዓመት በኮረና ምክንያት ተቋርጦ ነበር። እርግጥ ጀ ርመኖች እዛው የሚኖሩትን የተለያዩ አገር ዜጎችን በማሳተፍ አስበውት ውለዋል። ቁምነገር ናቸው እና።