ኢትዮ እስራኤላዊቷ ኤደን አለነ የምሥራች ለኢትዮጵውያን ናት! ለ2021 Eurovision Song Contest ለፋይናል አለፈች።

 

እንኳን ወደ ከበቡሽ ሚዲያ በሰላም መጡልኝ።

 

·       ኢትዮ እስራኤላዊቷ ኤደን አለነ የምሥራች ለኢትዮጵውያን ናት!

·       ለ2021 Eurovision Song Contest ለፋይናል አለፈች።


·     አገረ እስራኤልን ወክላ የ21 ዓመቷ ወጣት ኢትዮ እስራኤላዊቷ አርቲስት ኤድን አለን ለ2021 Eurovision Song Contest ለፋይናል አለፈች። ጠንከር ያለ ውድድር ቅዳሜ ይጠብቃታል።

 

ዕለተ ሃሙስ  ማዕዶተ ሰጋሪው

በከቡብሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና

በቢሆነኝ የተብራራ ብራ

በሰብለ ሕይወት አዝመራ

ለራህብ የሚራራ።

 

„የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል

እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“

(ምሳሌ 16 ቁጥር 9)



·       እፍታ።


ዕለተ አርብ ማዕዶተ ኢትዮጵያ የሚናፍቀኝ፤ የምጓጓለት ለት ነው። በኢትዮጵያዊነት ጥበብ ዙሪያ ነው የሚያተኩረው።

ዛሬ አውሮፓዊው የጥበብ ማዕዶትን አስመልክቶ በጨረፍታ መረጃ አቀርባለሁኝ።

የኢትዮጵያ ጠረንም በላይኛው ጥበብ ፈቃድ ተሳታፊ ሆኗል። ይገርማል። ይደንቃል። የፈጣሪ ሥራ ግሩም ነው።


ሃሌ ሉያ። እግዚአብሔርን አመስግኑ ስሙንም ጥሩ፥

 ለአሕዛብም ሥራውን አውሩ። ተቀኙለት፥ ዘምሩለት፥

ተአምራቱንም ሁሉ ተናገሩ።“

መዝሙር ምዕራፍ 105 ቁጥር ከ1-2


·       


ወግ ቢጤ …

 

በአውሮፓ በየዓመቱ በወርሃ ግንቦት የሚካሄድ የሙዚቃ ውድድር አለ። Eurovision Song Contes ይባላል። የአንድ ጎልማሳ ዕድሜ አሳልፏል። ባለፈው ዓመት በኮረና ምክንያት ተቋርጦ ነበር። እርግጥ ጀርመኖች እዛው የሚኖሩትን የተለያዩ አገር ዜጎችን በማሳተፍ አስበውት ውለዋል። ቁምነገር ናቸው እና።

ዘንድሮ በ2019 እስራኤል አገር በነበረው ውድድር አሸናፊ የነበረው ሆላንድ ነበር እና በሆላንድ በሮተርዳም በመካሄድ ላይ ይገኛል። ሁልጊዜ አሸናፊው አገር ላይ ነው የሚካሄደው። በዚህ ውድድር ለሴሚ ፋይናል ማክሰኞ ዕለት ማለትም በ18.05.2021 ከቀረቡት 16 አገሮች መካከል እስራኤል አንዷ ነበረች። ተወዳዳሪዋም ኢትዮ እስራኤላዊቷ አርቲስት ኤደን አለነ ነበረች። እናም በሁለተኛ ደረጃ ማጣሪያውን አልፋለች። ዕድሉ ዕንቁ ነው። የሰማይ በረከት ነው። ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር አምለውም ለዚህ ነው።



እኔ ሥሙን ሳዬው እንዴት አንደተደሰትኩኝ።ኤድን አለንኤደን የሌላም አገር ሰው ሊጠራበት ይችላል። ግንአለነእማውቀው የተባዕት ሥም ሆነ እና በጉጉት ጠበቅኩኝ። ከዛ ስትጨርስ እንግሊዘኛ አምስግና ቀጥላ አመሰግናለሁበአማርኛ ቋንቋ  አለች። ሰውነቴን ወረረኝ። ብሄራዊነት እኮ ልዩ የሆነ ማግኔት አለው። ከቁጥጥር ውጭ ያደርጋል። ተነስቼ ቁሜ ነው ያጨበጨብኩት። ከዛ ደረጃ ሲወጣ ደግሞ ሁለተኛ ወጣች። የተወዳደረችበት ሙዚቃ እርእስSet Me Free.” ነው። ቅንብሩ ድርጁ እና ሥልጡን ነው።



ቅዳሜ ፋይናል ይኖራል። ጥሩ ደረጃ ይኖራታል ብዬ አስባለሁኝ። ልታሸንፍ ትችላለች ብዬ ተስፋ አደርጋለሁኝ።  ማን ያውቃል? እርግጥ አልባንያዊቷ አርቲስት በራሷ ቋንቋ በድንቅን የስቴጅ ቅንብር ሃሙስ ዕለቱን የሴሚ ፋይናል ውድድር አንደኛነት አጣናቃለች፤ ሌላም የሳበችኝ ቡልጋሪያዋ ወጣት ነበረች። የሆነ ሆኖ እኛይቱ አርቲስት ኤደን አለነ ካሸነፈች የመጀመሪያዋ ኢትዮ እስራኤላዊት ጥቁር ልትሆን ትችላለች። 

ዕድሉ ዕድል እንዳይምስላችሁ። 365 ቀናት ውስጥ 500 የሚዲያ ቀጠሮ ሊኖር ይችላል። የሽልማቱ፤ የተቀባይነቱ፤  ሆነ ሽልንጉም ዛቅ ያለ ነው። ከዛ በላይ ተጽዕኖ ፈጣሪነቱም ያን ያህል አንቱ ነው። አንድ ሰው ማውጣት ቀላል አይደለም።የልጅ እና የጢስ መወጫውየሚባለው እኮ ለዚህ ነው። ጣምራ ብሄራዊ ግዴታዋን እንደ ተወጣችም ታሪኳ ይገልጻል።



ሃሙስ 20.05.2021 ደግሞ ሲዊዘርላንድ ጨምሮ ሌሎች አገሮች ፉክክር አድርገዋል ሲዊዝ እንዲህ አይነት ፐርፎርማንስ አይቼ አላውቅም ነበር በኢሮቪዥን ውድድር በ2018 አላዬሁም እንጂ በተከታተልኳቸው ዘማናት ደከም ትል ነበር የኔዋ ገዳማዊቷሲዊዝሻ። “የቤትህ ቅናት በላኝ” ዓይነት ነበረብኝ። የሆነ ሆኖ ትናንት ከተወዳደሩት 17 አገሮች መካከል ሲዊዝ አልፋለች። ደስ ብሎኛል። ቆሜም አጨብጭቤያለሁኝ።

 

ድምጽ ልሰጥ ፈልጌ አሻም አለኝ ቴክንኒኩ መሰለኝ። ለፋይናሉም ቤተኛ ናት ገዳማዊቷ ደጓ ሲዊዝሻ። ይቅናት። አሜን! በጣም የሚገርም የደምጽ ቃና ያለው ወጣት በፈረንሳይኛ ነበር ያቀረበው። ልክ መንፈሳዊ ህይወት ውስጥ ያለ፤ የተመሰጠ፤ መንፈስን የሚያባበል ልስሉስ ድምጽ ነው ያዳመጥኩት ልክ እንደ ቡልጋሪየዋ ወጣት። ተስፋውም ሰፊ ነው ብዬ አስባለሁኝ።  Gjon's Tears - "Tout l'univers" ጉግል እንደሰጠኝ ትርጉሙ  "The whole universe" ነው። ብዙ ጊዜ አሸናፊወች በሰብዕዊ መብት ላይ ያተኩሩ ናቸው። እርግጥ ፖለቲካም አለበት። አሁን ራሺያ ዘንድሮ ደከም ያለ ነበር እንጂ የመድረክ ቅንብሩ ረቂቅ ነበር። ሁልጊዜ የማሸንፍ ዕድሉን ሲያጣ ግን አያለሁኝ። ከራሽያ ይልቅ ዩክሬን የተሻለ ዕድል አለው።



 ዲታ አገሮች ጫን ያለ ገንዘባቸውን ከፍለው ለማጣሪያ ሳይቀርቡ በቀጥታ ለፋይናል ብቻ ይወዳደራሉ። 

በዚህ ውድድር አውስትራልያም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ተሳታፊ አገር ለመሆን ችሏል። ሁልጊዜ ለማጠሪያ ማለፍ ብቻ ሳየሆን ደረጃ ላይ የደረሰበት ጊዜም ነበር። የማክሰኞውን ማጣሪያውን ግን ማለፍ አልተቻለውም። ቻይና ዝግጅቱን በቀጥታ በቴሌቪዥን ያስተላልፈዋል። ይህ ተወዳጅ ፕሮግራም ለኢንተግሬሽን፤ ለኢንተግሪትም ዓይነተኛ የጥበብ ማዕዶት ነው።

አውዱ የጥበብም የባህልም አውራ ነው ማለት ይቻላል። የጥበብ ዓይነት በሙሉ በዬዘርፉ በሚባል ደረጃ በልዩ ሳቢ እና መሳጭ ቅንብር የሚቀርብበት፤ የዬዓመቱ የጥበብ ውህዳዊ ሥልጣኔ የሚታይበት ነው። በተለይ መድረክ ቅንብሩ ልዩ ፍጹም ልዩ ነው። ራሱን የቻለ የዕወቅት ማዕዶትም ነው።

የቀለማት ህብረት፤ ቃና፤ የተፈጥሮ ማራኪነት እና ሳቢነት ተዋህደው ሲቀርቡ ጉስቁልቁል ያለውን መንፈስ ይጠግናል። እኔ ሙዚቃ አድማጭ አይደለሁም። የተፈጥሮና የቤተ መቅደስ መዝሙር ነው የምወደው። የውቅያኖስ፤ የዝናብ፤ የወፍ’ ዋለን… ወዘተ … ይህኛው ግን የጥበብ ውቅያኖስ በአኃቲነት የዬዘመኑን ሥልጣኔያዊ ቀጣይ ጎዳና ስለሚያስተምረኝ፤ ስለሚተረጉምልኝ ነው እምከታተለው። ከሁሉ ነገር በላይ ግሎባል ትውልድ እና የተፈጥሯዊነት ምት አይበታለሁኝ።

ጨዋ ሰብዕና፤ ለሰባዐዊነት እና ለተፈጥሮ ተቆርቋሪነት፤ ሞድ፤ ዴኮሬሽን፤ የቪዲዮ ቅንብር ለዛ፤ የስቴጅ አደረጃጀት እና አመራር፤ የመብራት አስተዳደር እና ኮርድኔት፤ ጥልቅ የፈጣራ ጥበብ እድገት እና ሥልጣኔ ኢንተግሪቲም ፈክቶ እና አብቦ የሚቀርብበት ልዩ ተናፋቂ ዝግጅት ነው።

ከሁሉ የሚደንቀው እና አጓጊ ሁኔታው የመጨረሻው የፋይናል የድምጽ አሰጣጥ ሂደት ልብ አንጠልጣይነት ነው። ድምጹ ተወዳደሪን ከፍ እና ዝቅ ሲያደርገው ስታዩት ሌላ አርት ነው። አንደኛ የነበረውን 10ኛ ሲያደርገው፤ 12ኛ የነበረው ሦስተኛ ሲሆን ልብን ጨብጦ ይዞ ላይ እና ታች አይደረገ ሲያስደንሰው፤ ሲያስቧርቀው ምቱ …. ትርታው … ደውድው …. ጅረቱ ፏፏቴው …  

·       የቦቲንግ አሰጣጥ ሥርዓት፤

·       ኦን ላይን በመደወል፤

·       የዬተሳታፊ አገሮች ዳኞች የሚሰጡት ድምጽ፤

·       በመጨረሻ አህጉራዊ ዳኞች የሚሰጡት ወሳኝ ይሆናል።

 

የእያንዳንዱ ተሳታፊ አገር ዳኛወች የወል ድምጽ፤ በቀጥታ የህዝብ ኦን ላይን ድምጽ፤ ድምጹን ደረጃውን መውጣት እና መውረድ ሲያዘፍን ይቆይ እና አህጉራዊ ዳኞች የሚሰጡት ድምጽ የመጨረሻ ሲሆን ያልተጠበቀ ውጤት ይመጣል።

እራሱ ራንክ ላይ ያሉትንም ያመሰቀቅለዋል። ከድምጹ የቅንብር የአርቱ ጠረን ልዩ ነው። ይጥማል። ቅንብሩ የዬአገሮች ጥረት እና ፉክክር መሳነዶው ሙሉዑም ልዩ ነው።

የዬአገሮች ታሪክም ከመቅረባቸው በፊት ዬተወዳዳሪወች ታሪክ ይነገራል። ለዚህ የኦስትርያው ORF Eins ባለውለታ ነው። እንሱን ነው እኔ በዬዘመኑ እምከታተለው። ከ5 ዓመት በፊት አሸናፊም ነበሩ። ግሎባሉን የናጠ ዋንጫ ነበር የወሰዱት። ታሪክን ባህልን ፈጠራን ዘርዝር አድርገው ያቀርባሉ:: 

ያለፉ ዓመታትን በምልሰት ያስቀኛሉ። አሁን አርመኖች አፍንጫቸው ትልቅ መሆኑን ያወቅኩት በእነሱ የአገሮችን የማህበረሰብ ባህል፤ ወግ እና ልማድ ሐረጋዊ ቅኝት ነው። ማወቅ ዩንቨርስቲ ብቻ አይደለም። ለፈቀደ ትምህርት ከሁሉም ቦታ ይገኛል። የምማርባቸው ተቋማት ይሁኑ ሰብዕናወቼ ለእኔ ክብሬም ክብረቶቼም ትርታዎቼም ናቸው

·       ተከታታይነት …

 

ባለመቻል 2019 አልተከታተልኩም። አስቀድሜ ፕሮግራም ይዤ ዬዬዘመኑን የኦስትራሽን፤ የጀርመን እና የሲዊዝን ተወዳዳሪወች ሂደታዊ ታሪክ እከታተልም ነበር። ዘንድሮም ያን ለማድረግ አልቻልኩም። ታሪኩን አላጠናሁትም። ያዬሁት ሴሚ ፋይናሉን የማክስኞ እና የሃሙስን ብቻ ነው። ስለዚህ መረጃዬ ሙሉ አይደለም። እናንተ ግን ሊንኩን ስለለጠፍኩኝ ሁሉንም መከታተል ትቸላላችሁ።

እኔ የትውልዱ ነገር ስለሚጨንቀኝ እንደዚህ ዓይነት ትውልዳዊ ጉዳዮችን በትጋት ነው እምከታተለው። ማሽን አምላኪ ትውልድ እዬተፈጠረ ነው። ቤተሰባዊ፤ ማህበራዊ፤ ብሄራዊ ዕሴቶች ዋጋ እያጡ እንዳይሄዱ ስጋት አለብኝ። ፍቅራዊነት ጥግ አጥቷል። ቤተሰባዊነት ዕሴቱ ቀንሷል።


ግለኝነት፤ ክፉነት፤ ኢጎም እንዲሁ የዓለም ገዢ እንዳይሆኑ እሰጋለሁኝ። ስለሆነም እንደነዚህ መሰል መሰናዶወችን በትትርና እከተተላለሁኝ። ቀደም ባለው ጊዜ እንደዚህ ሳልደክም አልፎ አልፎም አውሮፓ ህብረትን ሁሉ በፍቅራዊነት፤ በሰዋዊ ቤተሰባዊነት፤ በተፈጥሯዊነት ቤተሰባዊነት ኢንተግሪቲ ጉዳይ አበክሬ እሞግት ነበር። ጥሩ እዬሰሩ ቢሆንም ፍቅራዊነት የትምህርት አካል እንዲሆን አጎተጉት ነበር። እነሱም መረጃም ይልኩልኝ ነበር።

·       ኦደዬንሱ …

Eurovision Song Contest ተወዳደሪዎች ይሁኑ ቲሙ ቤተሰባዊ ነው። ፍቅራዊ ነው። ፉክክሩ የ እህት እና የወንድም ዓይነት ነው። ይህ አህጉራዊ ሆኖ ማዬት ለ እኔ የተስፋ ማህደር ነው። የዛሬን አያድርገው እና ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ሲመጡ እንደዚህ ዓይነት ኃላፊነቶችን ይወጣሉ ብዬ አስቤ ነበር። በፓን አፍሪካንሲትነት። አፈረሱት እንዲያውም የቀደመውን።

የሆነ ሆኖ አርቲስት ኤደን አለነ ባቀረበችው ዝግጅት ጥሩ ተቀባይነት በኦዲዬንሱም በማግኜቷ ለዕለቱ ውድድር ሁለተኛ ነበረች።  ከሁሉ የሚደንቀው ስትጨርስ ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት የአቶ ሽመልስ አብዲሳን አማርኛ ቋንቋን ቁልቁል አድርገነዋል ሲሉ የላይኛው ደግሞ አውሮፓ ላይ ብርኃኑን ላከለት። 

እማትታገለውን ታግለህ አታሸንፍህም ይላቸዋል አማኑኤል አባቴ ለትዕቢተኛው አቶ ሽመለስ አብዲሳ እና ለአፍራሽ ቲማቸው። “አመሰግናለሁ” ብላ ነበር የጨረሰችው የእኔ ልዕልት። ድንቅ ነበር ያለኝ። በጣም! አማርኛ ቋንቋ ቅብዕም አለው። ይህ ጸጋው አልታወቀም። ይህ ጸጋው ዕውቅና አልተሰጠውም።

የልዕልቴ የኤደን አለነ ኮንፊደንሷ ሙሉ ሆኖ አግኝቸዋለሁኝ። ድንቀቴን ያፈለቀው ይህም ነው። ብዙ ዝግጅቶችን ስከታተል ወጣቶች ይህ ያንሳቸዋል። ቤተሰብ በዚህ ዙሪያ ያነሰ ተግባር ነው የሚከውነው። ለዚህም ነው እኔ “ርግብ በርን” ለወላጆች መጸሐፍ የጻፍኩት። ልጆች ኮንፌደንስ ብቻ ሳይሆን ቲም ወርክ ላይም በጣም ደካማ ናቸው። አብዛኞወቹ ወላጆች በትምህርት ላይ ብቻ ስለሚተኩር እንደዚህ ባሉ የሰብዕና ግንባታዎች ላይ የቤት ሥራቸው ደካማ ሆኖ ነው እማዬው እዚህ አውሮፓ ላይም።

የሆነ ሆኖ “አመሰግናለሁኝ” የ2021 Eurovision Song Contes ቤተኛ ሆኗል። ደስ ብሎኛል ከምል ሐሤት አግኝቻለሁ ብል ይሻላል። ደስታ ዕለታዊ፤ ቅጽበታዊ ሊሆን ይችላል። ሐሤት ግን ከደስታ በላይ ነው፤ ዘላቂ እና ሰማያዊ ነው። እናት ሐሤት ናት። ፈታሪ አላህ ሐሤት ነው።

ዝግጅቱ ከማክሰኞ ሜይ 18 2021 – ቅዳሜ፣ ሜይ 22 / 2021 ነው። ለፋይናል አምትችሉ ሰወች አደራ ስልክ እንድትደውሉ። በዕለቱ ስልኩ ይሰጣል ላይፍ ላይ የምትከታተሉ ከሆነ። በተለይ ሆላንድ ያላችሁ ብርቱዎች አደራ ትጋታችሁን ቀልቡት። 090105025xx አገር ከምንም ነገር በላይ ነው። ብሄራዊነት ከምንም ነገር በላይ ነው። ውስጣችን ተቋሙ አገራዊነት መሆኑ ነው ሰው ሰው ያሰኜን። አገር የፈጣሪ ሥጦታም ነው። አገር የሰው ልጅ ችሮታ አይደለም።

የሚሰጠው ጊዜ አጭር ስለሆነ ፍጥነት ይፈልጋል ለስልክ ደወሉ። Eurovision Song Contest የዘንድሮውን ሆነ አመሰራረቱን መረጃ የሚሰጡ ሊንኮችን ለጥፌያለሁኝ። እንግዲህ መከታተል ነው። እሷንም በሃሳብ፤ በጸሎት መደገፍ ይገባል። ፌስቡኳን ሊንክ ማድረግ፤ ላይክ ማድረግ፤ ሼር ማድረግ፤ ፎሎው ማድረግ ከአገር ልጅ የሚጠበቅ ይመስለኛል። በተለይ ወጣቶች ይህን ተግባር ብትወጡ ጥሩ ነው። የእናንተ ዘመን ወጣት ናት እና። ልትበረታታ ይገባል። ወላጆቿም የተባረኩ ናቸው። ለዚህ አብቀተዋታል። ሊመሰገኑም ይገባቸዋል። እሷም ታኮራለች። ሐሤት ትመግባለች። ልትመሰገን ይገባታል። 

·         https://www.facebook.com/edenaleneofficial

Eurovision Song Contest 2021

·         https://en.wikipedia.org/wiki/Eurovision_Song_Contest_2021

EUROVISION SONG CONTEST 2021

·         https://en.wikipedia.org/wiki/Eden_Alene

Eden Alene

·          https://www.youtube.com/watch?v=jRIHdPDt6ew

 

የእሷ 59.49 ላይ ይጀምራል።

Eurovision Song Contest 2021 - First Semi-Final - Live Stream

2,144,038 views

·         Eurovision Song Contest

https://de.wikipedia.org/wiki/Eurovision_Song_Contest

https://www.youtube.com/watch?v=9nss3FsrgJo

Eden Alene - Set Me Free - Official Music Video - Israel 🇮🇱 - Eurovision 2021

1,782,823 views

•Mar 26, 202

Eden Alene will represent Israel at the Eurovision Song Contest 2021 with the song Set Me Free.

Eden Alene

ኢትዮጵያ ቅዳሜ በ አውሮፓው የጥበብ ዕልፍኛ ማዕዶተኛ ናት። ተመስገን! ይህቺ የጥበብ ጣዝማ አገርን አሸንፎ መውጣት አይቻልም። ፈጽሞ። ፈጣሪ አላህ አለላት እና።

 


እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

20.05.2021

 

የእኔ ልዕልት አርቲስት ኤደን አለነ ሆይ! አማኑኤል ይርዳሽ። አሜን።

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!

አማርኛ ቋንቋ ጠላቶቹን በድርጊት የረታ ባለቅባዓ!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።