የኔታዋ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኢትዮጵያዊ፤ አፍሪካዊ ግሎባላዊት ናት! የኔታዋ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዩንቨርስም ናት!

 

 

እንኳን ወደ ከበቡሽ ሚዲያ በሰላም መጡልኝ።

 

 በስመ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ። አሜን።

·       የኔታዋ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኢትዮጵያዊ፤ አፍሪካዊ ግሎባላዊት ናት!

·       የኔታዋ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዩንቨርስም ናት!

 

ዕለተ አርብ ማዕዶተ ኢትዮጵያ!

በከቡብሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና

በቢሆነኝ የተብራራ ብራ

በሰብለ ሕይወት አዝመራ

ለራህብ የሚራራ።

 

„የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል

እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“

(ምሳሌ 16 ቁጥር 9)

 


·       ዕለተ አርብ ማዕዶተ - ኢትዮጵያ!

 

የኔታዋ አርቶዶክስ ተዋህዶ አገረ ኢትዮጵያን በተፈጥሯዋ ልክ ያበጀች አንቱ ዓይነታ ሃይማኖት ናት። ዕውነት ከተደፈረ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የተፈጥሯዊነት በቅዱስ መንፈስም ናት። የሰውኛነት ውስጡ ናት። ይህቺ ቤተ-  ክርስትያን በጸበሏ ሁሉን በህመም የተንገላቱ ወገኖችን ሁሉ የፈወሰች። በፍቅር ያስተናገደች።

 የፍቅራዊነት ያጠጣች፤ የሰበከች ሐዋርያም ናት። በጸሎቷ ለሁሉ አጥር ቅጥር ሆነ የኖረች ያኖረች ህልውናም ናት። ዕውቀት አፍልቃ አጽድቃ ያሰበለች ፈርጥ ኃይማኖት ናት። የሥልጣኔም ብሩህ ጎዳናም ናት … ዝማሬዋ፤ ማህሌቷ፤ መልዕክተ ዮኋንሷ፤ ሀሁ ገበታዋ፤ አቡጊዳዋ ለሁሉ እኩል የህሊና መስኖ ሆኖ ሰብዕናን ገንብቷል። አንፆዋልም።

ቅድስቷ ቅድስናዋ በማለት ሳይሆን በተግባር ከብራ ያስከበረች የጽረ አርያም ቤተኛም ናት። ቅድስታችን ትምክህትን የናቀች በመከራ በቅላ፤ በመከራ ኖራ፤ መከራን ድል ያደረገች የድል ሁነኛ ተቋም፤ የችሎት ኮከብ አደባባይም ናት።

በቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ውስጥ ህፃፅ የለም። ግድፈት የለም። በዶግማ እና በቅኖናዋ ውስጥ ሳንክ የለም። ተዋህዶ ለትውልድ የፊደል ገበታ መቀረፆዋ ብቻ ሳይሆን እራሷም የፊደል ገበታ ናት። የዕውቀት ማማ የጥበብ፤ የዊዝድም መንበርም ናት። ቅድስቷ መንፈሷ ልዕልና በልቅና ነው።

ብጡልነቷ ህብራዊነት ነው። ቅድስቷ ውሎዋ ፈርኃ እግዚአብሔር ነው። ቅድስቷ ተመስጥዋ ተፈጥሯዊነት እና ሰዋዊነት ነው። ቅድስቷ ሰው አክብራ ተንስታ ሲያዋርዷት፤ ሲያቀሏት፤ ሲገላምጧት፤ ሲያንገላቷት ችላ ማስተማር የቻለች የችሎት አደባባይ ጸደይም ናት።

የተደሞ እናቷ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ፤ የዕድምታ ሚስጥሯ፤ የህይወት ጎዳናዋ ሁልጊዜም ፍትኃት፤ ምህረት፤ ሥርዬት፤ ርትህ፤ ሰላም ነው። ንባቧ፤ ትርጉሟ፤ ሚስጢሯ እዮራዊ ነው። አራራቷ፤ እዝሏ ግዕዟ ሰማያዊ ነው።

ህግ እና ሥርዓቷ ወጥ አህቲ ነው። ዛሬ ዕለተ አርብ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭም ቅዳሴ ቢኖር ምስባዕኳ አንድ አይነት ነው። ወጥ። ዝበት የለም። ይህ ሰው ሰራሽ እንዳይመስላችሁ። 

ማህሌቷ፤ ጸሎቷ፤ ስግዷቷ፤ ምህላዋ፤ ምናናዋ፤ ሱባኤዋ፤ ዝማሬዋ፤ አቋቋሟ፤ ድጓዋ፤ ንባቧ፤ ፆመ ድጓዋ፤ መጽሐፏ፤ ድርሳኗ፤ ታምራቷ፤ ገድላቷ፤ ትንቢቷ ሁሉ በመሆን የሰከኔ ጭምቶች ናቸው። የመንፈሳዊው ዓለም ብቻ ሳይሆን ጋህዳዊውን አለም ድልድይ ገንቢ ቢባል ተዋህዶ ዓይነታ ናት። አቮል ናት። መገሱም ናት ለህልውና አኗኗሪ ክስተት ሁሉ። ለሁሉም ሥርዓት ድንጋጌ ያላት ዴታ ናት የኔታዋ!

ቅድስቷ በገሃዳዊ የዕውቀት ዘርፍም ተፈጥሯዊ ሳይንስ በሉት ማህበራዊ ሳይንስ፤ ሃይማኖታዊ በሉት ዩንቨርስ ሁሉንም ታስተምራለች። ለሁሉም ድንጋጌ ድርሳናት ቀመር አላት። ሁሉንም የሃይማኖት አፈታት በትምህርቷ ውስጥ አካታ ታሳተምራለች። የእስያኑ ሳይቀር። ሊቅነቷ ቀንዲለነቷ የጸሐይ ብርኃን ያህል ሙሉነት ሁለንትናዊነት፤ ሁለገብነት ያለው ነው።

የአውሮፓ ስልጣኔ የተመሰረተው፤ የደመቀው፤ የሰከነው በእሷ የሚስጢር መድብል ነው። መጸሐፈ ፈውስ ይበቃል አይደለም ሌላው። ጊዜ በማጣት፤ ብክነት በመብዛቱ እንጂ የአውሮፓ የሽልማት አስኳል ምንጩ እኮ ይህችው በገዳ ወረራ እዬተረገጠች ባለችው ቅድስት ተዋህዶ ሚስጢራት ቀለም ያሸተ ነው።

ልዘርዝርህ ቢባል ቀለሙም ብራናውም አይችለውም። ቤተክርስትያናችን ቅብዕም አላት። ይህን መዳፈር ማቱ ከሰማይ ይዘንባል። ጠብቁት። ዬኔታዋ የመላዕክታን ሠራዊት አላት። በያንዳንዱ ነገር ሁሉ መላዕክታን ይረባሉ። መንፍስ ቅዱስ ተለይቷት አያውቅም።

የኔታዋ ቅድስት ተዋህዶ በበታችንት ስሜት ተሰቃይታ አታውቅም። ምን እንዳላት፤ ምን እንደምትችል፤ ምን እንደሚፈቀድላት፤ ምን ደግሞ እንደማይፈቅድላት ጠንቅቃ ታውቃለች። ጎዳናውን ቀያሽ መንፈስ ቅዱስ ነውና።

በሃይማኖት ዶግማ እና ቅኖና ሚዛን ወ/ሮ ሙፍርያት ካሜል ምንድን ናቸው? ወይንስ ወ/ሮ አዳነች አበቤ ማን ናቸው? ወይንስ አቶ ብናልፍ አንዷለም ከወዴት ናቸው? እነሱ ለዚልፏት፤ ቁምስቅሏን ሊያሳዮዋት ቀርቶ ከጫፏ ሊደርሱ ባልተገባ ነበር። ይህ የሆነው እኛ በመተኛታችን ብቻ ነው። እኛ በመስነፋችን ብቻ ነው። እኛ የቤት ሥራችን ባለመስራታችን ብቻ ነው። እኛ እራሳችን በመርሳታችን ብቻ ነው።

·       የእኛ መተኛት፤

·       የእኛ ፍዘት፤

·       የእኛ መደንዘዝ፤

·       የእኛ ማንቀላፋት፤

·       የእኛ መስነፍ፤

·       የእኛ ዝልኝነት፤

·       እኛ እራሳችን መስራት ውርዴትን በዋንጫ እንድናወራርድ ተደርገናል።

·       ክብራችን አውልቀን ለበለሃሰብም ሸልመናል።  

የእኛ የቤት ሥራችን በቅጡ፤ በወጉ፤ በመክሊታችን ልክ አለመሥራት በኢትዮጵያዊነት ልክ ስትመዝኑት ቁልቁልነታችን፤ ዳጥነታችን ቁልጭ ብሎ ይታያል። ወደ ጥበባዊ መክሊታችን መመለስ ብቻ ነው ፍቱኑ ጎዳና!

የእኛ እራሳችን መርሳት ቅዱሱ ሥፍራ መንበረ ፓትርያርክ እንሆ በዬለቱ ተደፈረ! ተጨፈለቀ! ተጠቀጠቀ! ተዘለፈ! ቀድሞ ነገር ወ/ሮ ሙፍርያት ካሜል ይሁኑ ወ/ሮ አዳነች አበቤ ለዛ ቦታ ክብር ፈጽሞ አይመጥኑም። 

እራሱ በፆታቸው ሴት በመሆናቸው እንኳን ያን ግርማ ሞገስ ያለውም የፈጣሪን አደባባይ ሊደፍሩት ሊገቡበትም አይገባም ነበር። ሌላውን ትተን። ቅዱስ ሲኖዱሱ አሻም ሊለው ይገባል።

ይህ ማት ዘመን ውስጡ ለቄስ ነው። ሁሉም በውስጡ አንግቦት የሚሽከረከርበት የራሱ ቅምጥ ፍላጎት አለና። ዝም እምንለው ከዬትኛውም ሃይማኖት የምናከብራቸው ሰብዕናዎች ስላሉ ብቻ ሳይሆን የኔታዋ ቅድስት ኦርቶዶክስ የትኛውንም ሃይማኖት በ እኩል አይን እናይ ሰንድ በራስ መተማመንን መግባ ስላሳደገችን ነው። አማኝ ሁን ብላ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ከማንም ደጅ ቁማ አታውቅም።

እኛን ልጆቿን በመሆን ውስጥ መስከንን አስተምራ፤ መግባ ስላሳደገችን ብቻ ነው ታግሰን ያለነው። ከተዋህዶ ወገን እኔ ብቻ ነበርኩኝ በዛ የጨለማ ዘመን “እኔ ድምጻችን ነኝ” ብላ የወጣችው ሥርጉተ ሥላሴ ብቻ ነበረች። በደጉ ዘሃበሻ ዕልፍኝ ውስጥ ይገኛል። ሌላም እስከ ነጩ ቤተ - መንግሥት የደረሰው ስቅለት በኢትዮጵያ አጭር ፊልሜ “የድምጻችን ይሰማ ታጋዮችን” ለይቼ አልሰራሁም። የዛሬዎቹ የ አብይዝም ተሿሚወች፤ የቅርብ ቤተኞች ደግሞ እሷን ሊጣጠፉ ታጥቀው ተነስተዋል። ዘመን ጥሩ ነው ሁሉን አሳዬን።

የወ/ሮ ሙፍርያትን ሆነ የወት/ ብርቱካን ሚዲቅሳ መስመር እማዬው ከዚህ አንጻር ነው። ተዋህዶነት ምቾት አያስጠውም። ሹመቱም ሽላማቱም ለዳብል ተልዕኮ ነው። ትዕግሥት ሲያልቅ ፍቅር መሰደዱን፤ ፍቅርም ሲያልቅ ትዕግስት መሰደዱን ቢያውቁ ጥሩ ነው። ሲከር መበጠሱን፤ ሲሞላም መፍሰሱን።

 ከ“ብልጽግና” የክልል ጠጠሪዎች ውስጥ አንድም ዘረ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የለም። ይህ የአደባባይ ሃቅ ነው። በክርስትና ውስጥ እራሱ የራባ ሰው የለውም። አይደለም በኦርቶዶክስ ተዋህዶ። ቅድስት ተዋህዶ ከጨዋታ ውጭ ናት። ተዘርዛለች። ከዜግነትም ከአገራዊነትም።

·       ዕውነት።

https://www.youtube.com/watch?v=FmeGfeOaM_I

Ungerecht (injustice) neue

በድምጽ አልባዎቹ የኢትዮጵያ እናቶች ጉዳይ ከ10 ዓመት በላይ ስተጋ ክልል ክትር አልነበረኝም። ለዬትኛውም አገር፤ ለዬትኛውም አህጉራዊ፤ ለዬትኛውም ግሎባል ድርጅት ስጽፍ ዕንባ በኢትዮጵያ እንዲቆም ብቻ ነው የሠራሁት። የክልል፤ የዞግ፤ የሃይማኖት መቀረጣጠፍ በእኔ ህሊና ውስጥ ተፈጥሮ አያውቅም። ፈጽሞ። ወደፊትም አይፈቀደልትም። ጥሪዬ ይህ አይደለም። ከጥሪዬ የተዛነፍኩ ዕለት መኖሬን ፈጣሪ ይቀማኝ። ከሰውነት በላይ ምን ክብር አለና!

https://www.youtube.com/watch?v=5FcKNQPV1tI&t=171s

"የድምፃችን ይሰማ የስኬት ተመክሮ ዕድምታ እና የሥርጉተ ዕይታ።" (07.05.2019)

May 7, 2019

ማንም ሰው ለድምጻችን ይሰማ ንቅናቄ ለትውልድ መምህር ይሆን ዘንድ እንደዚህ አሳምሮ የሠራው የለም። ከእኔ ከሥርጉተ ሥላሴ በስተቀር። የትኛውንም ድርጅት፤ ተቋም፤ ንቅናቄ ተጋድሎ በጸጋዬ ራዲዮ እኩል ተሰርቶበታል። እኔ ያልደከምኩበት ዘርፍ የለም። አርኬቡ ገብቶ ማዬት ይቻላል።

እኛ እንዲህ ነን። እነሱ ግን አድራሻቸው የት እንደሆን እያዬን፤ እዬሰማን ነው። ነገም ብዙ ቁምነገር አለው እና እምናዬውን እናያለን። ከቅድስት ተዋህዶ መከራ፤ ጉስቁልና፤ ፍዳ፤ መገለል ጋር የቆመ ተቋም አላዬነም። አልሰማነም። 

እንዲያውም  በአጋጣሚው ሁሉ እሷን ከሥር ለመንቀል ለአርዮሱ የገዳ ወራራ መዶሻ በማቀብል ግን አይተናል፤ ሰምተናል። ዝምታችን ፍርኃት አይደለም። ዝምታችን ኢትዮጵያዊነታችን ስላከበርን ብቻ ሳይሆን የላይኛውን ስለምናከብር፤ ስለምንፈራም ነው።

በዚህ የመቃብር ሥፍራ ሦስት ዓመት ያላዬነው፤ ያልተደሎተብን ስውር ደባ፤ ሸር እና መከራ ትተን በምናዬው መከራ እንኳን ምን ያህል ታግሰን በማስተዋል ጎዳና ላይ እንዳለን ሰው ባይመሰክረው ፈጣሪ ያዬዋል፤ ይመዝናዋል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብነትነቷ ዕለታዊ አይደለም። ዝልቅ ነው። 

ዝልቅነት ደግሞ የመንፈስ ቅዱስ ነው። መንፈስ ቅዱስ አይያዝም፤ አይጨበጥም። አይፈርስም። አይደረመስም። ረቂቅ ነው። የኔታዋ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ረቂቅ ናት። ፍጽምናው ረቂቅነቷ ነው። ኢትዮጵያን መስጥራ የያዝበት ጥበቧም እዮራዊ ነው። ቢመርም፤ ቢያንገሸግሽም ዕውነቱ ይህ ነው።

ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አይደለም ዕምነት ላለለው ለኢአማያምን ወገኗም የህሊና ዕልፈኟ ክፍት ነው። የአብርኃሙ ቤት ናት እና። ደጀ ሰላሟ ለሁሉም የኔቢጤ የቸገረው፤ ብቻኛ ሁሉ ቤቱ፤ ጎጆው፤ ትዳሩ፤ ህልውናው ነው።

·       በዘመነ አብይዝም ተጨፈለቀች፤ ተጨፈጨፈችም!   

ዛሬ መስጊድ እንዲህ አልተደፈረም። መስጊድ እንዲህ አልተጠቀጠቀም። መስኪድ እንዲህ አልተጨፈለቀም። እጬጌው፤ ጉልላቱ የእስልምና አቨው እንዲህ ከፍ እና ዝቅ ተደርጎ አልተዋረደም። በእኛ በሙቶች ላይ ነው ይህ ሁሉ መዳፈር፤ ይህ ሁሉ ጥቅጠቃ፤ ይህ ሁሉ ዲስክርምኔሽ አይሎ የሚገኜው። 

እራሱ የምርጫ ቦርድ ሰፊ የሆነ ዲስክርምኔሽን እዬፈጸመ ነው። በፖለቲካው የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት የመሠረቷቸው ድርጅቶችን የሰረዘበት ዓይነተኛ ምክንያት ተዋህዶ ልጅነታቸው ነው። ምርጫ ቦርድ የሚሠራው ለፕሮቴስታንት ኢንፓዬር ነው። ሌላውም እንዲሁ።

ይህ ድፈረት በማንም ላይ እንዳይመስላችሁ በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያዊነት ላይ ነው። ብልኋ፤ አስተዋዮዋ፤ ሐዋራዊት ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አገር ብቻ አይደለችም ዩንቨርስም ናት። ልድገመው። ብልኋ፤ አስተዋዮዋ፤ ሐዋራዊት ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አገር ብቻ አይደለችም። ዩንቨርስም ናት! 

ይጎመዝዛል ለገዳ ወረራ፤ ለገዳ መስፋፋት፤ ለገዳ አስምሌሽን። ዕውነቱ ግን ይህ ነው። ዕውነት ንጥር ነው። የስሜን ፖለቲካ እንዳይነሳ ሆኖ በቦንብ የሚቀጠቀጥበት መሰረታዊ አምክንዮም ይህ ነው። መሠረቷ ያ ብሩክ ቀዬ ነውና።

የስሜን ፖለቲከኞች፤ የስሜን ሊቃናት፤ የስሜን ሊሂቃን፤ የስሜን አክቲቢስት፤ የስሜን ጋዜጠኛ፤ የስሜን ጦማርያን ደግሞ ሚስጥራቸውን ዘለው በረባው ባረባው ሲተራመሱ አንዲት ነገር አንጠልጥለው ሲቀጣቀጡ አያለሁኝ። መፍረስም፤ መደርመስም፤ መጨፍለቅም፤ መወረርም፤ የጫጉላ ሽርሽር ሆኖ ከዘለቀ ነገ ይታያል። ከዚህ ዘመን በላይ ዩንቨርስቲ የለም። ህሊና ላለው። ይበቃኛል ብሎ ገድሞ ለመኖር ለወሰነ ግን ይታዬዋል። ነገር ዓለሙ ሁሉ ፏ ፍንትው ብሎ።

·       እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ጅል አይደለሁም።

እኔ ጅል አይደለሁም። መጀመሪያ ላይ ጅል እምሆነው ቅንነት ስለለኝ ብቻ ነው። ቅንነቴን በገፍ ለግሼ ግን አልተኛም። እያንዳንዷን ነቁጥ እከታተላለሁኝ። ሲጋባኝ አቅም አለፈሰም። ባለፈውም ነገርም አልጸጸትም። 

እኔ በቦታዬ ነኝ። ዕውነት የጎደለበት ባመንኩት ነፍስ ነው። ዕውነት ነኝ ሲል በንጽህና፤ በድንግልና ይደገፋል ተቋም ይሁን ግለሰብ። ዕውነት ሲሸሽ ወይንም ሲያስረከርከው ወይንም ሲያጎሸው ደግሞ የእኔ ጉዳይ አይደለም። 

ሲሄድም ሲመጣም ዕውነት ከሆነ በጸዳ ህሊና ይሰተናገዳል። ዕውነት ጊዜያዊ አይደለም። ዕውነት የወረትም አይደለም። ዕውነት አስቸኳይም አይደለም። ዕውነት በተፈጥሮው ልክ የጨመተ - የሰከነ ነው። ትናንትም ዕውነት፤ ዛሬም ዕውነት፤ ነገም ዕውነት። የዕውነት ልጣጨ የለም። እውነት ቅርፊት የለውም። ዕውነት ቀጠሮው ለዕውነት ብቻ ነው።

ስለዚህ በተዋህዶ ውስጥ ያለው ዕውነት ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው። በተዋህዶ ውስጥ ያለው ንጥረ ነገር ሰውኛነት ብቻ ነው። ተዋህዶ ማንንም ተፎካክራ፤ በገንዘብ ገዝታ፤ በብልጭልጭ ነገር ማርካ አታውቅም። 

ተዋህዶ ለአምንያኑ መንፈስ እንጂ የብር ዳረንጎት ሰጥታ አታውቅም። በሌላ በኩል ተዋህዶ ብድር ሄዳ አታውቅም። ምን አጥታ? አላት! ተርፎም ይናኛል። ተዝቆ የማያልቅ መሆን አላት። በመሆን ተፈጥራ በመሆን የሰከነች ሃይማኖት ናት የኔታዋ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ። ኢትዮጵያም መሆን ናትና።

ለዚህ ነው ለሰከንድ የማንነት ቀውስ ትውር ብሎባት የማያውቀው። ተዋህዶ እራሷን ተብድራ፤ ተውሳ፤ ዱቤ ተቀብላበት አታውቅም። ተዋህዶ በጎቿን ብታሰማራ የሚተርፍ አንዳችም ነገር የለም። የኔታ ጎዳና ያዕቆብ አንድ ነገር ሲናገሩ ሰምቼያለሁ ከሰሞኑ “ተዋህዶ ፈርሳ አይደለም አገር መንደር አይኖርም” ብለዋል። ዕውነት ነው።

·       እኔስ እላለሁ … 

ተዋህዶ አገርም ብቻ ሳትሆን ዩንቨርስም ናት። ስለ ዩንቨርስ ተዋህዶ ኮርስ አላት፤ መጽሐፍ አላት፤ አንዱ የዕውቀት ዘርፏ ነው። ፋለስፋ ናት እኮ ተዋህዶ። ዘመንን የቀመረች አንቱ እኮ ናት ቅድስቷ! “ልክን ማወቅ ከልክ ያደርሳል” ይላሉ ጎንደሮች! መንጠራራት በልክ ሲሆን ጥሩ ነው።






·       እነ ትዕቢት ስንቁ አትንጠራሩ

ወ/ት ብርቱካን ሚዲቅሳ!

ወ/ሮ ሙፍርያት ካሜል!

የቁም እንቅሉፉ፤ ነቀዙ፤ ዝልኙ፤ አቶ ብናልፍ አንዱአለም!

ወ/ሮ አዳነች አበቤ! ቤተ …. መቅደሳችን በመዳፈር አታቆሽሹት! በውነቱ ደናግል አባቶቼ በእነኝህ ሰዎች ላይ ሁለት ሱባኤ ቢይዙ በጣም እጅግ በጣም እሻለሁኝ። ሊገሰፁ ይገባል እና። አውደ ምህረቱም ለመዳን ካልሆ ለመጫን፤ ማስፈራራት ሊፈቅድላቸው አይገባም።

 

·       አነ መንጠራራት …

 

እጃችሁን ከብሄራዊት፤ ከአህጉራዊቷ፤ ከሉዓላዊቷ፤ ከዩንቨርሷ ተዋህዶ አንሱ!

በዚህ የሚነሳው ሞገድ አይቻልም። ጉዟችሁ ወደዬት እንደሆን እያተከታተልኩት ነው። ኢንፓዬርነት ብዝኃትነትን ካስፈለጋት ከየኔታዋ ቅድስት ተዋህዶ በላይ ማንም ይለም። ግን ተዋህዶ መጫንን አትወደውም። ሰው እኩል ነው ብላ ታምናለች። ሰው ነፃነት ነው ብላ ታምናለች። ትዕግስቷ የበዛውም ለዚህም ነው።

 


ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

21/05/2021

ወስብሃት ለእግዚአብሔር

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።