ልጥፎች

ከሜይ 20, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ብፁዕ አቡነ መርቀርዬስ የሱባኤ ዕድምታ!

ምስል
  የሱባኤ አባትነት በቅድስና - ብጽዕና በብትህና በትህትና !            ከሥርጉተ ሥላሴ 12.09.2015 ( ሲዘርላንድ -  ዙሪክ )        „ቃሌን ስሙ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ፤ እናንተም ህዝብ ትሆኑኛላችሁ፣         መልካምም ይሆንላችሁ ዘንድ ባዘዝኋችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ ብዬ በዚህ       መንገድ አዘዝኋቸው“  (ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፰ ቁጥር ከ፳፫ እስከ ፳፬)             በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱሳን አሃዱ አምላክ አሜን! ሳይገባኝና ሳልመቸው፤ አሮጌውን ዓመት ሸኝተን የመንገድ ጠራጊውን የሰማዕቱን ቅዱስ ዮኋንስን ስንቀበል፤ በ 2007 ዓ.ም ከተከወኑት ድንቅ ተግባራት - ለእኔ፤ አውራ የሆነው የኢትዮዽያ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖታችን ደማቅነት በሚመለከት፤ የውስጤን መንፈስ ለመግለጽ መፍቀድ ግድ አለኝ። በውነቱ ቁንጮ የሆነ ብሄራዊነትን ያበራ፤ ለልዕልቴ ለኢትዮጵያ አለንልሽ ያለ፤ ዕንባዋን የተጋራ ጉልላት ተግባር ስለሆነ። እንዲህም ሆነ - የተግባር ቀጠሮ ሳይኖረን የሙያ አባቴና የሥራም አለቃዬ - ደወለልኝ።  ቃል ስጠብቅ ዘለግ አድርጎ በድምቀት „ ዎህ“ አለ። ትንፋሼን ሰብሰብ አድርጌ „ምነው በደህና?“ ስል በድንጋጤ ግን በልስሉስ ለዛ ጠዬቅኩት „ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን አቡነ መርቀርዮዎስ ፓ...