To Toni Loba, Good Luck Wishes!
- · Toni Loba የፍቅር ጠይም ዕንቁ!
ሌላው
በሦስተኛ ደረጃ አሁን የፊታችን ሃሙስ እንደ አውሮፓወያኑ አቆጣጠር ግንቦት 24. 2018 ወደ 15ሺህ ተመልካች ታዳሚ በሚገኝበት
የጀርመን የ2018 የሞድ አሸናፊ Germeny Next Topmodel 2018 (GNTM) ውድድር በደም ሐረግ ዘሯ አፍሪካዊ ናይጀሪያዊቷ
በጀርመን ሽቶትጋርድ የምትኖረውን ቶኒ ትሆናለች ብዬ ነው እማስበው፤ ሦስት ተጨማሪ ተፈታኞችም አሉባት አንዷ እንደሷ ከጠይምነት
ወደ ዳማነት ያደላች ናት። ለነገሩ ጥርጣሬም የለኝም። ይህ ውድድር ለረጅም ጊዚያት ከቦታ ቦታ እዬተነቀሳቀሱ በጋራ በመኖር የሚካሄድ ሲሆን ወላጆች ሥራቸውን
በአግባቡ ስለማይሰሩ ፕሮጀክቱን ለሚመረቱ ለዓለም አቀፍ ሞዴሏ፤ የቴሌቪዠን ሞደሬተሯ፤ ለዳኛዋ ለወይዘሮ ሃይዲ ክሉም እና ለአጋር
ዳኞቻቸው እንዲሁም ለተሳታፊ የካሜራው ቲም ሁሉ ብዙ ፈተና በዬዘመኑ ይገጥማል።
ሰብዕናቸው ያልጠኑ ተወዳዳሪዎች
ከዘርኝነቱ ጋር ተዳምሮ ወይንም ከበታችነቱ ጋር ታክሎ ፈተናው በጣም ያዬለ ነው። ለዚህም ነው እኔ ወላጆች ልጆቻቸውን እንዴት ማሳደግ
አለባቸው፤ የልጆቻቸውን ራዕይ ለማሰካት ምን ላይ ቢያተኩሩ መልካም ይሆናል የሚለውን „ የተስፋ በርን“ እንድጽፍ የተገደድኩበት አብዩ ምክንያት። ልጆች የማይገኘውን ዕድላቸውን በሥነ - ምግባር አቅም
ማነስ፤ ወይንም ራስን ችሎ በመቆም አቅም መሳሳት፤ ወይንም በህሊና እንጻ ድህነት ምክንያት ወርቁን አጋጣሚ ያጡታል። እኔ ስለመጪው
ነገረ ዓለም ያስጨንቀኛል። ትውልድ በአግባቡ ካልተገነባ አህጉርም፤ ዓለምም፤ አገርም እንዳለ አይቆጠርም።
እኔ የማዬው ግድፈት በሠለጠነው
አለም ይሁን ባልሰለጠነው ዓለም በትውልድ አገነባብ ላይ ያለው ትጋት አንድ አቅጣጫ ብቻ የተከተለ እንጂ ህይወትን ተርጉሞ በዛ መልክ
በሁለመናነት በማነጽ ረገድ ዓለም ራሷ ብዙ ነገር ይቀራታል። የተነጠለ፤ ወይ የተዘነጠፈ፤ ወይ ቅርንጫፍ የሆነ የአኗኗር ስልትና
መንገድ ይዘው ነው ልጆች የሚያድጉት። ወላጆችም በዛ መልክ ስለመጡ ልጆቻቸውን አሟልተው የሁለገብ አቅም ባለቤት አድርገው አያሳድጓቸውም።
ቀደም ባሉት ዓመታት በዚኸው
የሞድ የተክለ ሰውነት ውድድር ኤርትራ፤ ብራዚል መሰል ዕድሉን አግኝተው ግን ሊጠቀሙበት አልቻሉም። የኤርትራዋ ውብ ወጣት በጣም
አግሬስብ ነበረች፤ የብራዚል ደግሞ አጋሮቿን ላለማዬት በጋዜጣ መጋረጃ የምትሰራ ነበረች አንድ ዓመት ላይ፤ ሌላ ዓመት ላይ ደግሞ
በቃ እንደ ታንቡር ተረራ ሆነ በአዬር የተሞላች ነበረች። ትዕቢቷ ዳር ደንበር አልነበረውም። አንዳንድ የኦስትርያ የጀርመን ተወዳደሪዎች
ደግሞ ከዘረኝነት ጋር የተያየዙ መቧደኖች በመፍጠር የህሊና ሽብር ይፈጥራሉ አብሱ በቡኒ ቀለማት ላይ፤ ከሁሉ በላይ ካሜራ እዬወደዳቸው
የሚመጡ ተወዳዳሪዎች በርካታ ሥራ ስለሚያገኙ፤ በአድማ የሚደርስባቸው መገለል ሌላው ፈተና ነው።
ከዚህ ጋር በተያያዘ ሌላም
ውድድር ላንሳ። ባለፈው ዓመት የጀርመን ኮከብ የሙዚቃ ዕድል ያገኜ አንድ የ16 ዓመት ታዳጊ ወጣት ሃበሻ ነበር። የድምጹ መክሊት
የሰማይ ሆኖ ግን ወላጆች ልጁን ሲያሳድጉ መኖርን ሳያስጀምሩ
ነበር። ስለሆነም ያን የመሰለ ዕድል ተንከባሎ ቀረ። ታዳጊ ወጣቱ በቀን ቢያንስ ወሳኔውን 6 ጊዜ ይቀይራል፤ እመለሳለሁ ይላል፤
ሊመለስ ነው ተብሎ የሽኝት መስናዶ ሲጀመር እቀጥላለሁ ይላል፤ ሊቀጥል ነው ተብሎ ሥራ ሲጀመር እሄዳለሁ ይላል፤ ጥዋት ተነሳ አትነሳ
መከራ ነበር። በጣም ብዙ ባለ ዕድሎችን ተሻምቶ ዕድሉን ካገኘ በኋዋላ መከራ።
·
ስለ እናትዬ
እና አቨይ ትንሽ።
እኛን እናታችን ስታሰድገን
እጃችሁን እጣታችሁን እዩት አወፋፈሩ፤ ቁመቱ፤ ቅርጹ ይለያያል። ግን እጅ ሆኖ መኖርን ይሰራል ትለናለች። መበላለጡን፤ በቅርጽና
በቁመት መለያዬቱ እጅን መዳፍ ከመሆን አይገድበውም፤ ስለዚህ አትቅኑ ትለን ነበር። አንዱ የበለጠ ሌላው ያነሰ ሊኖር እንደሚችል
እመኑ፤ በጋብቻ ላይም ግማሽ ሹረባ፤ አንድ ጆሮ ጉትቻ ያምራለን? ጉትቻዋን አውልቃ ሁሉ ታሳዬናለች፤ አሁን እኔ አምራለሁን በአንድ
ጆሮ ጉትቻ ብሄድ ጎንደር አበደች አይለኝንም? አንድን ብቻ ወገን ማቅረብ ግንጥል ጌጥ ነው። ዝምድና ተፈልጎ ነው አበልጅነት፤ ጉርበትና፤
ማህበርተኛነት የሚኮነው። ጋብቻም የሚፈለገው ለዝምድና ነው ትለን ነበር፤ ልጆቻችሁን የአባቶቻቸውን ሆነ የእናታቸውን ወገኖች እኩል
እንዲዩ እናንተ ማስተማር አለባችሁ። ሁሎችም ያስፈልጓቸዋል። ጌጥ ጌጥ የሚሆነው ሙሉ ሲሆን ነው ትለን ነበር፤
አሁን እኔ ሙሉ ዕድሜ ላይ
ነኝ። በዛ ዘመን ጨርቅ በጫማዋ ውስጥ ጨምራ አረማመድ ታስተምረኝ ነበር። ጎንደር ላይ። ስለሆነም በልጅነቴ ስጦታ ምን እናምጣለሽ
ሲሉኝ መስታውት እል ነበር። የሞድ መጋዝንም አሳድጄ አይ ነበር። አባቴ 7 ዓመቴ ላይ ጠረጴዛ ላይ አቁሞ መጽሐፍ እንዳነብ ያደርግ
ነበር። ያነበብኳቸውን እርእሶችን፤ ጸሐፊዎችን፤ የተጻፉበትን ዘመን፤ ጭብጦችን፤ የወደድኳቸውን አረፍተ ነገሮች እና ቃላትን፤ የአባባል
ዘይቤዎችን እንድመዘገብ ያደርግ ነበር። ለዚህም ነው ምጻዕተ እስራኤልን፤ ፍቅር እስከ መቃብርን፤ እና ፊያሜታን እያንዳንዳቸውን
15 ጊዜ ያነበብኳቸው። አንብቤ አልሰለችም ነበር።
ወላጆች በት/ ቤት ብቻ ሳይሆን
ቤታቸው ት/ ቤት እንዲሆን መትጋት አለባቸው። ማህበረሰብ በዚህ መልክ ነው የሚታነጸው። ከእኛ ቤት ቅናት አይታወቅም፤ አንግዳ አይጠላም
ስንሸኘው መንገድ ላይ ይነጋል፤ ከማንኛውም ሰው ጋር ተላምዶ መኖር አይከብደንም። ለጓደኛ ሰብዕና እንጂ ምንም መስፈርት የለንም።
ስጦታ መስጠት በሽሚያ ነው።
ስለዚህ ወላጆች ልጆች ሁለገብ
ዕውቀት እንዲኖራቸው፤ ቀናተኛ እንዳይሆኑ፤ ሰብዕናቸው ሙሉዑ እንዲሆን ቤት ውስጥ መስራት አለባቸው። ይህን ስለማይሰሩ የጋራ ኑሮ፤
በራስ የመተማመን ዝቅተኝነት፤ ሃላፊነትን የመወጣት ብቃት፤ የናረ ቁጠኝነት፤ ከልክ ያለፈ ትዕቢት፤ ዘረኝነት፤ ሌሎችን ለመጨቆን
መሻትን፤ የማይታይ የባህሪ ዓይነት የለም። ለሞድ ውድድር ሄደው ለነገሩ ውድድር ብቻ ሳይሆን ስልጠናም ነው ለዛ ወስነው ሄደው ግን
ራሱ ጸጉራቸውን ለማስተካከል በሽምግልና፤ በቁልምጫ ነው። ሺዎች ተወዳድረው ዕዱልን ሳያገኙ ይቀሩና፤ ዕድሉን ያገኙት ናቸው እንደዛ
የሚዘባነኑት። ይህን እምጽፈው በተለያዬ ሁኔታ ዕድል የሚያገኙ ልጆች በዕድል መጠቀምን እንዲያውቁ ወላጆችም በዚህ ዙሪያ ሥራ መሥራት
እንዳለባቸው ለማስገንዘብ ነው። ጉዳዬ ነው እንደዚህ ያሉ የትውልድ ቀረጻ መሰረታዊ አመክንዮዎች።
- · ቶኒና ተጋድሎዋ፤
በዚህ ዓመት የነበረውን የተደራጀ
የዘረኝነት ሰንሰለት በፍቅር፤ በችሎት፤ በበዛ ትዕግስት፤ በአሳታራቂነት ንጽህና አስማምታ ለመጨረሻው የፋይናል ውድድር የበቃችው
ቶኒሻ ናት። በጣም የሚገርመው አንድ ወጣት ሲወዳደር የራሱን ፓተንቶች መደበቅ አለበት። እሷ ሰብስባ ለሚጠሏት ሁሉ ታስተምራለች።
እንዴት መሰናዳት እንደሚገባቸው ሁለገብ መረጃ ትሰጣቸዋለች። ሌላው ደግሞ ቡድኑ ጥቁርና ነጭ በሚል የተደራጀ ሲሆን እሷ ከነጩ ከዳኛ
እና አማካሪ አቶ ሚኬኤል ቡድን ስትሆን ሆነ ለጥቁሮችም ለዳኛ እና አማካሪ ለአቶ ቶማስ ቡድን አባላትም ጭምር ነው ሁለመናዋን የምትሰጠው።
ሁለቱ ቡድኖች እንደ ቡድንም ውድድር አለባቸው። በዬቡድኑ ውስጥም እርስ በርስ ውድድር አለ። እሷ ግን ትህትናን፤ መከባበርን፤ ፈጣሪን
ስለመፍራት ብቻ ሳይሆን በራስ መተማመን፤ መድፈርን፤ የገጽ አቀራረብን፤ የመፍጠርን ጥበብን ሁሉን በግልጽ ትነግራቸዋለች። ሲከፋቸው
የሚጠሏትን፤ ጥቁረነቷን ማዬት ለማይሹት ሁሉ፤ የሚዋጓቱን እቅፍ አድርጋ ታባብላለች። ለሁሉችም ለዕናባቸው ቅርብ ናት። ወጣቶቹ ረዘም
ላለ ጊዜ ከቤተሰብ ስለሚለዩ ናፍቆት ሲያጠቃቸው ቀርብ ብላ እያሻች ጭኗን አስደግፋ ታባብላቸዋለች። የቶኒ ልዩ ነው። ሁሉንም ሰጥቷታል።
ከፍቅር በላይ ናት። ከባድ ውድድር ሲኖርባቸው ሰብስባ ጸሎት አድርጋ በአሜን
ታሳርገዋለች። ፍጹም የሆነች የአፍሪካ ብርሃን ጥቁር ዕንቁ ናት።
ኢትዮጵያዊ ወጣቶች የማህበራዊ
ሚደያ ታታሪዎች አፍሪካዊነትን የምትውዱ ዕንቡጦች እባካችሁ ኢትዮጵያን እዬጻፋችሁ የምትችሉትን ያህል ድምጻችሁን ፍቅራችሁን ስጧት
- የእኛ ብትባል አታሳፍርም። የምትሰጧት ድጋፍ እንድታሸንፍ አቅም ይሆናለታል፤ ስለ አፍሪካም እንድታስብ የቤት ሥራ እግረ መነገዳችሁን
ትሰጧታላችሁ።
እንዴት ካለ ከተባረከ ፈጣሪን
ከሚፈራ ቤት እና መንፈስ እንዳደገች እጅግ ይገርመኛል። በሚሰጣት የቤት ሥራ ውስጥ ብቻ ሳይሆን የተፈጥሮም ልዩ መክሊት አላት።
ሁሉ ነገር ከእሷ ሲደርስ ያምርበታል። በፓን አፍረካኒዘም ስሜት አብሶ ጀርመን ያላችሁ የቡኒነት / የጠይምነት ፍቅረኞች ልትረዷት
ይገባል። የአፍሪካን ሥም ባልተጓደለ ሁኔታ በመልካም ምግባር እና ሙሉ ብቃት ወደፊት በዓለም አቀፍ ደረጃ ታስነሳለች ብዬ አስባለሁ።
በሷ ያለኝ ትምህክት ሆነ ተስፋ በጉልሁ ነው። ባታሸነፍም ጥላቻን ያሸነፈች ብርቅዬ አፍሪካዊት ወጣት ናት። የፍቅር ዕንቁ!
የእሷ ትልቁ ኮሊቲዋ ያገኘችውን ዕድል ዕውቅና መስጠቷ ነው። ያገኘቸውን ዕድል መንከባከቧ ነው። መነሻዋን ያወቀቸው መድርሻዋን
ያስገኝላታል። ዝቅ ብላ ዕድሏን አከበረችው። ለትንሿ ስጦታ ነገር ሁሉ ያላት አክብሮት እና አድናቆት እዮራዊ ነው። ታኮራለች። ሰብዕናዋ
የትም የማይገኝ ነው። ዕድሜዋ እኮ ገና 18 ነው። በዚህ ዕድሜ ነው የሚያገሏትን ሁሉ ወዳ እና አጽናኝ ሆና የምታዮዋት። ፈርጣም
ጠይሟ ዕንቁ አንድታሸንፍልኝ እኔም እጸልይላታለሁኝ። መልካም ዕድል የእኔ ውብ! Good Luck!
- · ክውና።
ሦስት ፈርጣማ የቡኒ ዕንቁ
ጠይማን ግንቦት ላይ በምድረ አውሮፓ እንደ ጠሐይ አበሩ። ሐሤት!
ጥቁርነት አዲስ ቀለም ነው!
የኔዎቹ ቅኖቹ ለነበረን የጠይማም
ደማማዊ ጊዜ ኑሩልኝ ልሸልም። መልካም ሰንበት።
·
የፎቶ ምንጭ
ከጉግል ጋላሪ።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ