ጠ/ ሚር ዶር አብይ ለልዩ ሃይሉ ትህትና መቀለባቸውን እደግፈዋለሁ።
መጋጋል ። „እግዚአብሄር የእውነት ዳኛ ነው፤ ሃይለኛም ታጋሽም ነው። ሁልጊዜ አይቆጣም“ ከሥርጉተ© ሥላሴ 13.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። በሰሞናቱ የልዩ ሃይል አመጥ ጉዳይ የሁለገብ ሊቀ ሊቃውነቱ ሻለቃ ዳዊት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አዳመጥኩት። ያው ሙያዊ ነው። እሳቸው ሉላዊ ዕውቀትም፤ ልዩ ተመክሮም ያላቸው ሊሂቅ እጬጌም ናቸው። በሌላ በኩል መጀመሪያ ላይ ከምንም ያልቆጠሩት ሁሉ አሁን ውይይቱ ሦስት ቀን ነበር ሲባል ማጋጋሉን ተያይዘውታል። መጀመሪያ ላይ ነው ጠረኑ ትክክል አለመሆኑን በርቀት ማዬት፤ ጠንከር ያለ ማሳሰቢያ ለመንግስት መስጠት። ቀደም ብሎ ጉዳዩን ማጥናት፤ መተንተን እና መረጃውን ከተለያዬ አቅጣጫ የመገምገም ምህንድስና ሊደረግበት ነበር የሚጋባው። ቀድሞ ነገር እንደዚህ ያለ ነገር ሲደመጥም ወዲያው ማብራሪያ መስጠትም የተገባ አይደለም። ችኮላ አያስፈልገውም። ተደሞ ያስፈልገዋል። ርጋታ እና ስክነትም ይጠይቃል። አሳድሮ አገላብጦ አይቶ ከስሜት ጋር ሳይስጠጉ፤ በራስ ፍላጎት ሳይቸነክሩ የጭብጡን ማንነት ብቻ በራሱ ማንነት ራሱን አስችሎ መመርመር ነበር የሚገባው። የሆነ ሆኖ እኔ አስተያዬቴን ዛሬ ልሰጥ የፈልግኩበት ምክንያት ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮወርጊስ ዕይታ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ የወሰዱት እርምጃ ትክክል አይደለም የሚሉትን ነው። እሳቸው ዘመን ጠገብ ባለሙያ ስለሆኑ እሳቸውን አሻቅቤ መተቸት አልችልም። ክህሎቱም ተመክሮውም ብልጹግ ነው በሲቢሉም ሆነ በወታደራዊ። መሬት ላይም ሰርተውበታል። ነገር ግን እኔ እንደ ሰው ጠ/ ሚር አብይ አህመድ የወሰዱት እርምጃ ትክክል ነው ብዬ ነው እማስበው ። ጠ/ ሚር አብይ አህመድ እያስተማሩ ያሉት የሃሳብ አቅም ከባዱን ተራራ ንዶ፤ ደልድሎ፤ ሸካራው...