ግልጽነት ገዳም በመግባቱ ቋቅ ነገሰ።

ግልጽነት ገዳም በመግባቱ ቋቅ ነገሠ።
"እናንተ የሰው ልጆች እስከ መቼ ድረስ 
     ልባችሁን ታክብዳላችሁ?"
ሐሰትንም ለምን ትሻላችሁ?" 
መዝሙር ፬ ምዕራፍ ፪ 
ከሥርጉተ©ሥላሴ
 15.10.2018 
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።


እኔ የሚገርመኝ ብሄራዊ የኢትዮጵያ ሰንደቅዓላማ የያዙት በአደባባይ ተረሽነው 1200 ነፍሶች ጦላይ ላይ ባለቤት፤ ጠያቂ ሁነኛ ድርጅት ሳይኖራቸው ፍዳቸውን እያዩ በሌላ በኩል ደግሞ የብሄራዊ ሰንደቅዓላማ ቀን ሰሞን ምክክር ውይይት ዲስኩር ይደመጣል። ይህን አጣጥሙ መጀመሪያ። እኔ አይደለም የምላችሁ ፋክት ነው የሚያፋጥጠው የጠ/ ሚር ጽ/ቤትን።

እኔ እኮ የማይጠቅመው ነገር እንደሚጠቅም ሁሉ እንዲቀጥል የሚፈቀደልት ምክንያት ነው የማይገባኝ። ትናንት የኤርትራው ፕሬዘዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ወደ ኢትዮጵያ ጎራ እንዳሉ አዳመጥን። ያዳመጥነውን አላምጠን መወጥ ይገባ ስለነበር እኔ አቶ ዳውድ ኢብሳ የኢትዮጵያን መንግሥት እያስደገደጉ ነው ብዬ ነው እማስበው ብዬ የጻፍኩትም ለዚህ ነው። አቶ ፍጹም አረጋ ደግሞ ይህን አስተባብለዋል በዓለም አቀፍ ሚዲያ ወጥተው።

ሆደ ሰፊነት ይሆን 5 ወጣቶችን በአደባባይ አስረሽኖ 1200 ባለቤት አልባዎችን ጦላይ ፍዳ እያስከፈለ፤ የጫት፤ የሺሻ፤ የቁማር፤ የዝርፊያ ፓርቲ ተፈጥሮ የተለጠፈላቸው፤ ጎንደር እና ወሎ ተነጥለው ከዛ የመጡ ወንጀሎኞች ማለትስ ምን ማለት ነው? አይገባንም ይህ? ልብም ህሊናም አለን።

ግልጽነት አዲስ ለውጥ አራማጆች መርህ ይሆናል ተብሎ ታውጆ እምናዬው እምንስማው ግን ድብቅነት እንደ ነገሠ ነው። ከስሜን አሜሪካ ከጠ/ ሚር ጉዞ መልስ ጀምሮ ያሉ ነገሮች በህልማችን ለምናምን ሰዎች ዕድምታውን እናውቀዋለን። ወንበሩ ባዶ ነው። 

ስለምን አልተገለጸም ማለት ህዝብን ለመረጋጋት ከሆነ የአባቶቻችን የእናቶቻችን ሌጋሲ እንዲቀጥል ስለሆነ ይሁን እንላለን። ሲበዛ ግን ማርም ይገለማል። በሆነው ሁሉ ነገር፤ በሚታዬው ነገር ሁሉ የሚደመጠው ማስተባባል ነው። ወጥ መረጃ የት ይገኝ?

እኔ ይህ ማስተባባያ የሚባለው የሰርክ ሲሆን ቋቅ እዬለኝ ነው። የአብይ መንፈስ ዕውነት ኢትዮጵያን እዬመራት ከሆነ አብዩን እናውቀዋለን እኮ። በመንፈሱ ብቃት ልክ የተደራጀ ስለመሆኑ። ዝርክርክ ነገሮች እንዲኖሩ የሚፈለገበት ምክንያትም ጠ/ ሚሩ አቅም አንሶኛል መምራት አልቻልኩም ብሎ ሪዛይን እንዲያደርግ ነው ብዬ አምናለሁኝ እኔ በግሌ። ለዚህ ደግሞ ሰዎች እዬተሰናዱ ነው። መርህ ባለው ሁኔታ ምዕራባውያኑ በሚቀበሉት መልክ። 

ምክንያቱም ከስሜን አሜሪካ መልስ ቅደመ ሁኔታዎች እንዳለ፤ እገታ እንደነበረ ስለማስብ። ህጋዊ በሆነ ሁኔታ ህዝብ ሳያውቅ ሌላ ሽግግር ማድረግ ያስፈልጋል ተብሎም ታምኖበታል ብዬ አስባለሁኝ። ህዝብ እራሱ ፈቅዶ ለቀቀ የሚለው ዕድምታ ለተተኪው ሰው የበለጠ አቅም እንዲያገኝ መሰናዶ እንዳለ ጠረን አለ ብዬም አምናለሁኝ። የራስ ተሰማ ናደው ሴራ እኮ ዘመን ተሻጋሪ ነው …  እዛው ነው ያለው ገመናው። ገመናው እሱ በእሱ ነው። 

አሁን እውነት አቶ ሃይለማርያም ደስአለኝ ወደው ነው እንዲለቁ የተደረገው? አይደለም። በፍጹም አይደለም። የለቀቁት በጫና ነው። ነገር ግን ተወዶ እንደለቀቁ ስለተደረገ ቀጣዩን ጠ/ ሚር አብይ አህመድን ካለምንም ቅድመ ሁኔታ የአፍሪካው ህብርት እና ምዕራቡ ዓለም ተቀበል። የዶር አብይ አህመድ በሳይንስ እና ቴኢክኖሎጂ ሚ/ር ሆነው መሥራታቸው፤ የራውንዳው ዓለም አቀፍ ግዳጅን መወጣት ታክሎ ሁሉም ተስማማበት።

ቀጣዩ ድራማም ይኸው መሰል ሁኔታዎች እንዲከውን ነው። ምዕራባውያን ጋር ትውውቁ ከሰሞናቱ እማናዬው የሹመት ትዕይንት ይገልጠዋል። ያን ጊዜ የካቲት እና መጋቢት ባለተቻለበት ሁኔታ ዕድሉ አምልጧል። አሁን የሚቻልበት ሁኔታ የኢህአዴግ ጉባኤ አመቻችቷል።
እውነት እንነጋገር ከተባለ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ አዳዲስ ኢትዮጵያን የመለወጥ ትልማቸው ላይ እዬሠሩ ነው ወይ? አይደለም። ታግተዋል። ስለሆነም ነው እኔ ሁልጊዜ አብይን ፍለጋ ላይ ነኝ እምለው።

ይህ ሁሉ ቀውስ እኮ ታቅዶ ነው የሚከወነው። ቀውስ ፈጣሪው ይፋ አይሆንም። በህግ አይጠዬቅም። ሰው ተገድሎ ተዝቅዝቆ ተሰቅሎ የታዬው እኮ እንደ ድርጅት በኦህዴድ/ ኦዴፓ፤ እንደ መሪ በጠ/ ሚር አብይ አህመድ ዘመን ነው። ይህን መድፈር አልተቻለም። አጋሮ ላይ እኮ ከንቲባውን አስነስተው ሥርዓት አልበኞች ሲመሩ እንደ ነበር አድምጠናል። ይህም ማለት አጋሮ ላይም አቅም የለህም እንኳንስ ሌላው ላይ ነው።

ለመጀመሪያ ጊዜ አሜሪካ ኢንባሲ ለግማሽ ቀን ዝግ ነበር። ሰሞኑን ቤተ መንግሥት አካበቢ የነበሩ ተቋማት ለተወሰነ ሰዓት ዝግ ነበሩ በልዩ ሃይሉ  የአመጽ መንፈስ ምክንያት፤ ይህ ተቃሎ ተደመጠ ተንታኙም ያን ጊዜ አለዞ ገልጦ አሁን ሲያጋግለው አያለሁኝ።

የሆነ ሆኖ የመንግሥት ሆደ ሰፊነት መፈንቅለ መንፈስ ያደረገው ቡድን ይሁንታ እስኪሰጠው ድረስ ነው። ድንገተኛ ነገሮች ድንገተኛ መልስ ተሰጥው በኋላ ላይ የሚሰተካከሉትም በዚህ ምክንያት ነው።

ይህን ዕውነት የጠ/ሚር ጽ.ቤት አይደፍረውም ምክንያቱም የአብይ ካቢኔ ቅደመ ሁኔታ ላይ ስላለ። ዕውነቱን መቼውንም አይነግረንም። በተጻጻራሪው አብይን የደገፈው በገፍ ይታሰራል፤ አሳሩን ይከፍላል። የቁርሾ፤ የቂም፤ የቋሳ ማወራረጃ ሆኗል ንጹሃኑ ዜጋ።

የአብይ መንፈስ እሱን ለደገፉት ባለቤት ሊሆን ባለመቻሉ በአደባባይ ተረሽነዋል አዲስ አበባ ላይ ዜጎች። ይህም በዝምታ ውስጥ ነው ያለው። ይህ የሐምሌው የመንፈስ ኩዴታ ዕድምታ ነው። መሪውን እኔ አውቀዋለሁኝ። ቅናት ነው። 

ይህም ብቻ አይደለም ሆን ተብሎ ጠ/ ሚር አብይ በጠሩት የሙሁራን ስብሰባ ላይ ስለ አባይ ግድብ ተነስቷል። አባ ቅንዬ መልስ ሰጥተውበታል። ያን መልስ እንደሚሰጡ የሚያውቁ ሊሂቃኑ ናቸው ያ ጥያቄ እንዲነሳ ያስደረጉት። በጥቂት ቀናት ወስጥ ቆመስ ኢንጂነር ስመኛው አደባባይ ላይ ተገድለው ተገኝተዋል። ካሜራዎችም ቀድመው ተነስተዋል። ቀብር ክልክል ነበር። ወንጀሉንም ራሱ በግፍ ተገዳዩ ሆኗል። 

እስከ አሁን ድረስ በቆመስ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ አስተያዬት የሰጡት ሁሉ ተለቅመው እስር ቤት ይሆናሉ ብዬ አስባለሁኝ። በቆመስ ኢንጀነር ስመኛው ጉዳይ የአብይ መንፈስ ደፍሮ መናገር አይችልም። ለማናቸውም እንቅስቃሴ ትእዛዝ የሚቀበልበት ሃይል አለ ብዬ አስባለሁኝ። እጬጌው የቅናት ሹመኛ ናቸው ጠ/ ሚሩ። 

ያ ለአብይ የተሰጠው የድጋፍ ማዕበል መፈንቅል ስለተደረገበት እንዳሻው በተሰጠው ጸጋ እንዳይንቀሳቀስ እገዳ ተደርጎበታል። በዛ በፋፋ በሞቀ ሁኔታ ሳይበረድ ሽግግር ለማድረግ ነበር ሃሳቡ ሁሎቹም በፈጣሪ ጥበብ ከሸፉ። ራስ ተሰማ ናደው በትረ መንግሥቱን እይዛለሁ ብለው እቴጌ ጣይቱን ግዞት አስቀምጠው እሳቸው ሳይሰነበቱበት ተሰናበቱ። ቅብዕ ከፈጣሪ ፈቃድ ውጪ አይሆንም። ሁሉም መስሎት ነው።
  
አሁን ማን ያምናል „ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነው“ ባለው ሊሂቅ በሚራው ክልል ሰው ተገድሎ ተዘቅዝቆ ይሰቃላል ብሎ፤ አሁን ማን ያምናል አማራ እና ኦሮሞ አንድ ነን ያለው የጣና ኬኛ አብዮት ቀንበጦች አማርኛ ቋንቋ ተናገርክ ብለው ቡራዮ ላይ የጋሞ ወገኑን ሲጨፈጭፍ፤ ሲያሳድድ በአሰቃቂ ሁኔቴ ሲያፈናቅል?

ሌላም ይታከል በተባባሩት መንግሥታ ድርጅት ጠ/ ሚር አብይ አህመድ እንዳይገኙ የተደረገበት ዋናው ምክንያት ምንድን ነው? ያ ልቅና፤  ዕውቅና መንፈሱን መፈንቅል ላደረገ „አቶ ሀ“ መሆን ይገባዋል ነው ፍቹ። የሰላም ፒስ ሽልማት ሎቢውስ የት ገባ? ስለምን የውሽማ ሞት ሆነ ቀረ? ለነገሩ ቀውስዩም እኮ እሱን ለማስቀረት ነው።

በሌላ በኩል በተገኘው አጋጣሚ የሐምሌን ዝምታ ከተገለጠች ጉድ ይፈላል ነው ስሜን አሜሪካ ላይ በድጋሚ እንደይገኙ የተደረገበት ምክንያት። ስለዚህ ሰንሰለቱ ዶር ወርቅነህ ገበዬሁ ጥብቅ አይደለም እና በፈለገው መልክ እሱን በዓይነ ቁራኛ የመጠበቅ አቅም የለውም ስለዚህ መሰረዝ አለበት ተብሎ ነው የተሰረዘው። 

ዓለም አቀፍ እውቅና አብይ እና መንፈሱ አይገባውም፤ ፍቅርም አይገባውም የሰጣችሁት ንፈጉት ነው ዘመቻው የመንፈስ መፈንቅል ያደረገው ሃይል የሚፈጥረው ህውከት፤ ማስተባባያው ዝርክርክነቱ ሁሉ ተልዕኮው ይህው ነው።  

እርግጥ ነው ጠ/ ሚር አብይ አህመድ አረብ አገር ነበሩ ግን  የኤርትራው መሪ እስከ ልጀቸው ነበሩ፤ አረቦችም በዚህ ጉዳይ እጃቸው አለበት ብዬ ነው እማምነው። ስለዚህ እንዲህ ሆነ ተብሎ ለመናገር አይችልም።

ጀርመን ላይ ጠ/ ሚር አብይ ይመጣሉ በማን ሰንሰለት ተጠርንፈው እንደሚሆን ይታያል። እኔ ጠ/ ሚር አብይ ታገቱ ብዬ በሳብኩበት ወቅት እስኪ ካናዳ ያሉ ወገኖች ግብዣ ያደርጉላቸው እና እሰከ ሙሉ ቤተሰቦቻቸው ከተፈቀደላቸው ብዬ ሁሉ ጽፌ ነበር።

ይህን ስንጥቅ የተፈጠረው ግንቦት መጨረሻ ነው። ያ የግንቦት መጨረሻ ክስተት አንድ አቋም ላይ አድርሷል። የሰኔ 16ቱ የግድያ ሙከራ እኮ ከግንቦቱ ዝግ ግንኙነት በኋዋለ የመጣ ነው። በዚህ ላይም ግልጽነት የለም። ማን እንዳደራጀው ግን የ ኢትዮጵያ መንግሥት አሳምሮ ያውቀዋል። ያ ከተገለጠ ... እህ። 

የግንቦት ክስተት ሐምሌ ላይ ስሜን አሜሪካ የታዬው የዲሲው ስብሰባ ደግሞ ሌላ ክረት እና ጡዘት አስጨምሯል። ወደ አገር መልስ ሲሆን የሐምሌው ዝምታ ክስተት ዕድምታው ይኸው ነው። የዚህ ሁሉ መከራ ሸክምም ያ ቀን የፈጠረው ነው። 

ቀድሜም ኤርትራ ሄጄ በነበርኩበት ወቅት አግኝቻቸዋለሁ ሄጄም አገኛቸዋለሁ አቶ ዳውድ ኢብሳን ብለው ነበር ጠ/ ሚሩ። ነገር ግን እሳቸው ያው በሐምሌው ዝምታ በተዘጋ ሁኔታ ቀርተው ዶር ወርቅነህ ገበዬሁ እና አቶ ለማ መገርሳ ሄደዋል። ሲሄዱ ዜና ነበር ሲመለሱ ደግሞ የውሽማ ሞት ነበር። ግልጽነት ገዳም ገባ። ቋቅም ነገሰ ይሏችኋዋል ይህው ነው። 

አሁን የአቶ ፍጹም አረጋ ማስተባባያ በስኳር ፓለቲካ የተሸበለለ ነው። የኤርትራው ፕ/ የመጡት ለአቶ ዳውድ ኢብሳ ትዕቢት አይደለም ነው የሚሉን። ስለምን የሻሸመኔው ገመና ግልጥ አልተደረገም? ስለምንስ  የቡራዬው ጭፍጭፋ ግልጥ አልሆነም? ስለምንስ የሰኔ 16ቱ ግድያ ሁኔታ በኦነግ ሥም ይለጣጠፋል? ኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት አስተዳደር አይደለም የሚባለው። እዛ እኮ ሶሪያ ሆኖ ነበር እኮ በነገረ ቡራዩ ሆነ በነገረ ነቀምት እንዲሁም በነገረ አጋሮ በተጨማሪም በነገረ ሻሸመኔ። ያን ያደራጀው አካል ያውቀዋል። ያን የመራው አካልም ያውቀዋል። ምንን ለማሳጣት ቢባል ቅኑን ጠ/ ሚር እና ካቢኔያቸውን። 

አሁን የኢትዮጵያ መንግሥት ከአቅሙ ከቁጥጥሩ ውጭ የሆነ ክልል እንዳለ ያውቀዋል። ከትግራይ ይልቅ ኦሮምያ። ለዚህ ነው ሦስት ምክትል አስተዳደሪ እና አዲስ ካቢኔ በአስቸኳይ ስብሰባ የተሰዬመው። ይህም ብቻ አይደለም የእነ ብጄ ከማል ገልቹ ምደባ ፍጥነቱም ይህንኑ ነው የሚነገረን። በቅርቡ እኮ ጉባኤም ተካሄዷል ምክርቤቱም አካላቱን መርጧል። ታዲያ ከመቼው ደግሞ ፉት ሳይደረቅ አዲስ አስቸኳይ ስብሰባ አስፈለገ?

ቀድሞ ነገር ኦዴፓ የእኔ የሚለው አባሉ፤ የጸጥታ ሃይሉ ምን ያህል ነው? ህዝቡ ለጊዜው እንተዎው። አቶ ዳውድ ኢብሳ ሲመጡ እኮ አብዛኞቹ ታዋቂዎቹ አንጋፋዎቹ የኦሮሞ ድርጅቶች ሊሂቃን አንድ ላይ ነበር የቆሙት። በመንፈስ ተዋህዱ ቢባል ይቀላል። መለያ አርማችን ይህ ነው ብለዋል የኦነግን። 

በዛ አቀባባል በመስከረም 5ቱ ማለት ነው የኦዴፓን ጨምሮ አንድም የሌላ የኦሮሞ ድርጅቶች ዓርማ አልታዬም። ኢትዮጵያ የተገለለችበት እና ምን ያህል እንደተጠላች ያዬንበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነበር። እራሱ ኢህአዴግ የሚባለው ግንባርም የተሰረዘበት ነበር። በሚሊዬነም አዳራሽ በአቶ ጃዋር መሃመድም። የባህርዳር አቀባባልም የኬኒያው መሪ ባህርዳር የገቡ ያህል ነበር የአቶ ጃዋር አቀባበል።

ራሱ አዲስ አባባ ላይ የደረሰው የኦሮሞ ልጆች ንብረት፤ የቋንቋ ት/ ቤት ውድመት እኔ እራሱ ይህ የአብይ መንፈስን መፈንቅል ያደረገው ሃይል እንደ ሃውዚን ያሰናዳው ነው የምለው። ይህን ጉዳት አበክረው ሲገልጹ የሚደመጡት አቶ በቀለ ገርባ ናቸው። በዛ ልፍ ሁሉ ብለዋል፤ የሚያሳዝነው በቀኝም በግራም ህዝቡ መጠጊያ ማጣቱ ነው።
ወዙን ጠብ አድርጎ የሚያደርገው ጥረት፤ ያደራጀው ተቋም ሃላፊነት የሚወስድለት በሌላው አካል ንብረቱ ይቃጠላል፤ የቋንቋ ት/ቤቱ ይወድማል፤ እሱም ራሱ ይሰዋል። 

እውነቱ አስኳሉ ነገር በኦሮሞ ሊሂቃን ዘንድ በራሱ በኦዴፓ የጠ/ ሚር አብይ አህመድ እና የአርበኛ አንዳርጋቸው የቤተ መንግሥት ግንኙነት አልተወደደም። ሃቁ ይሄ ነው። 

የሆኑት ነገሮች ሁሉ ከዚያ በኋዋላ ነው። ለምሳሌ ኖሮይ የሚኖሩ የፖለቲካ ሊሂቅ አርበኛ አቶ ኦኬሎ አኳያ ከደቡብ ሱዳን ነው የተጠለፉት። አርበኛ እንዳርጋቸው ደግሞ ከዬመን ነው። የጋንቤላ ሊሂቃን የአርበኛ አንዳርጋቸው ከጠ/ ሚር አብይ አህመድ ጋር ግንኙነት ስለደረጉ ተመሳሳይ ኬዝ ሆኖ ዶር ኦባንግ ኢትዮጵያ ሜቶ ወጥቶ ነው ደስታውን ነው የገለጸው። አቶ በቀለ ገርባን እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋንም እኩል ነው ዕውቅና የሰጠው ፕሮሞት ያደረገው እኩል ነው ድርጅቱ የአዲሲቱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ።

ለኦሮሞ ሊሂቃን ግን የእግር እሳት ነው የነበረው፤ ይህንም በተለያዬ ሁኔታ አቶ በቀለ ገርባ በጥዋቱ ተናግረውታል። የሳቸውን ያህል አቅም ያለው ሊሂቅ በባሳ ሁኔታ ሰቆቃ የደረሰበት ነፍሱንም እራሳቸው ያተረፉት አቶ አንዱአለም አራጌ እኩያ ሊሂቅ ነው - ከሙሉ ማስተዋል ጋራ። ግን ለምን ብሎ አልጠዬቀም? ከሳቸው ያልተናናሰ አካላቸውን ያጡም እስረኞች መሰል ህዝባዊ የምልዕት ሞገድ ያስነሱ መንፈሶች ሁሉም በቀና ነው የተቀበለው የአርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌ እና የጠ/ ሚር አብይ አህመድን ዝግ ግንኙነት። ለኦሮሞ ሊሂቃን ግን የተመቼ አልነበረም፤ እሳተ ጎመራም ይሕው ነው። የመፈንቅለ መንፈስ መከራም ይሕው ነው።

እንደ እኔ በውይይቱ ላይ ዶር ለማ መገርሳ ዋቆ ኑረው ቢሆን ኖሮ መልካም በሆነ ነበር። በፈለገው ሁኔታ ኢትዮጵያዊነትን ቢያነሱ ቢያሞግሱ ዶር ለማ መገርሳ የዶር አብይ አህመድን ያህል ለኦሮሞ ሊሂቃን የእግር እሳት አይሆኑም፤ ይህን ዶር መራራ ጉዲናም በቅኔያዊ ዘይቤያቸው ገልጸውታል „ለማ ፊቱ ኦሮሞ ይመስላል“ ብለውናል።

ለአረብ አገሮች ለኤርትራ መንግሥትም ቢሆን የማይመቹ ነገሮች እንዲኖሩ ሌላ የሎቢተግባርም ተከናውኗል። በሰላም ፋውንዴሽን ስብሰባ ላይ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ከተነናገሩት ውስጥ አጣሞ ሰበር ዜና አድርጎ በማሳጣት፤ የአሁን የግብጽ ፍንገጣም ይኸው ነው። ስለምን ለሚለው ቅኔን መፍታት ነው? ይህን ጉዳይ ቀደም ባሉ ጹሑፎቼም የችግሩ ምንጭ ብዬ እኔ በጥቅሉ ሳነሳሳው ባጅቻለሁኝ።

አብሶ የነገረ አንዳርጋቸው ያ ቅሬታ አድጎ ጎልምሶ ሄዶ መስከረም 4 / 5/6 እያለ እስከ ጥቅምት የውትድርና አመጽ ደረሰ። በጣም ጥሩ ያልሆነው ደግሞ አርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌ በኢትዮ ኤርትራ ሰላማዊ ግንኙነት ድርጅታቸው እንዳለበት የገለጹበት አግባብ በቀላሉ የታየ ግን ሰፊ የሆነ የፖለቲካ የባለቤትነት የቅሬታ ዕድምታን ያስከተለ ነው።

ባለቤት የሌላቸው አዲስ አበቤዎች የበቀል መቋደሻ የሆኑበትም ከዚህ አንጻርም ነው። ግንቦት ወር ምቹ አይደለም። ጎንደሬዎች በግንቦት ሠርግ አድርገው አያውቁም። በግንቦት የረባ ቤተሰባዊ ይሁን ማህበራዊ ትውፊት የለንም - ጎንደሬዎች። ለጎንደሬዎች ግንቦት እንደ ጀርመኖቹ ቁጥር 13 ዓይነት ነው።

የግንቦት 20 ጦስ ይኸው ይህን ሁሉ መከራ አሸከመን፤ ቤት ለእንግዳ ትልቁ ባህላችን እንሆ ተቀበረ። አትምጡብን ይደመጣል በስፋት። እግዚኦ ነው። የተገፉ የኦርቶዶክስ ተዋህዶን 9ኙን ሊቀ ሊቃውንታት፤ የእስልምና ሊሂቃን እቅፍ ድግፍ አድርጋ የተቀበለች አገር፤ ምርኮኛን አስደስታ የምትሸኝ አገር፤ ዜጎቿን ዋ! ድርሽ ትሉና እያለች ነው። ከዚህ በላይ ኮሶ መከራ ምን አለና?

ከዛም የቀደመው አንድ ግንቦት ወር ላይ በደርግ ዘመን የመኮንኖች ኩዴታ ነበር፤ የደርግ ስንብትም መባቻ ነበር። የዚህ ሁሉ ቀውስ መነሻም በግንቦት ወር የተካሄደው የጠ/ሚር አብይ አህመድ እና የግንቦት 7 ከፍተኛ መሪ የአርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌ መፈታት ሳይሆን ከጠ/ ሚር አብይ አህመድ ጋር ያደረጉት ዝግ ስብሰባ ነው። 

ስሜን አሜሪካ የነበረውንም ዕውቅና ሁላችንም ያዬነው ነው። ያ ለኦሮሞ ሊሂቃን፤ ለአክቲቢስቶች የሚደላ አልነበረም። መሬቷን ከመርገጣቸው በፊት በተከታታይ ጥቃቶችን ፈጽመዋል። ያ በ100 ቀን የተከወነውን መንፈስን የባሰውን ዘምተውበት አውከውታል።

ከስሜን አሜሪካ መልስ ያለውን የዶር አብይ አህመድ ያ እንደ ፏፏቴ ነፍሳችን ይፈውስ የነበረው የሐሤት ብሥራትም ቀስ በቀስ እዬተሸበሸበ እንዲመጣ ገደብ የተጣለበት አመክንዮም ይኸው ነው። በመስቀል በዕል ተዳፍኖ እንዲከበር የተደረገውም የብሄራዊ ሰንድቅ ዓላማ ጸሐይ ማዬት ስላልተፈቀደ ነው እዮር እንጅባራ ላይ ፍርዱን ሰጠበት እንጂ።

 የአብዩ የመንፈስ ጸጋ ተገልጾ አያልቅም፤ ተጠግቦም አያበቃም፤ ቅንነቱም በሊሂቅ ደረጃ ጉልላት ነው። ትህትናው እና ርህርህናውም ቅድስና ነው። ግን ምን ይሆናል? በአያያዝ ግድፈት አጣናው … 

አሁን እኮ ለአደባባይ በዋሉ በቀደሙ መንፈሶች ዙሪያ ለዛውም ወጣ ገባ በሆነ ሁኔታ እንጂ በነበረው ያ የዳዊት አቅም ልክ አብይ ቢንቀሳቀስ የት በተደረሰ ነበር። 100/100 ይሆን ነበር። አሁን ከመቶ ቀናት ዕሴቶችም እዬቀነስን ነው። ይህን ተደራጅተው የራሴ የሚላቸው መንፈሶች እያጋዩት ነው በግራ በቀኝ።

አብይ ማለት እኮ ይህ ነው …

Ethiopia - Dr Abiy ፈረንጆቹን አሸማቆ መለሳቸዉ!!


ያን አንበሳ ዛሬ በተፈቀደለት ልክ ብቻ፤ በተሰራለት መስመር ብቻ እንዲንቀሳቀስ ተገዷል። ቀድሜ ስጽፍ እንደባጀሁት ይህ ሚስጢር መቸውንም ቢሆን አይወጣም። ልክ ትውልድ እንደማይተካቸው ጸሐፊ አቶ በዐሉ ግርማ፤ ሳይንቲስት ኢንጂነር ቅጣው፤ ጋዜጠኛ እና ጸሐፊ ጋሼ ሙሉጌታ ሉሌ። እኔ ሰሞኑን የካፒቴን ዮሖንስ ተስፋዬን ታሪክ ሳዳምጥ እንዲህ ጸሐፊ በዐሉ ግርማስ ገጠር ገብተው ይኖሩ ይሆን እላላሁኝ። በዘመነ አጤውም አርበኛ አብቹ ታሪክ እንዲህ ተዳፍኖ ነው የቀረው። ለምዶብናል።

ወደ አቶ ፍጹም አረጋ የአሁኑ ድንገት ደራሽ የፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ ማስተባባያ ስመጣ ከተጨባጩ ውጭ ነው እኔ የምለው። ኦህዴድ አለኝ የሚለው የጸጥታ ሃይል የእሱ ስለመሆኑ እርግጠኛ አይደለም ሚስጢሩ ይኸው ነው። ራሱ በኦህዴድ አመራር ውስጥ የእኔ የሚለውን መለዬትም ተስኖታል የጠ/ ሚር ቢሮ። 

ሁሉ የጃዋር መንፈስ ተገዢ ከሆነ ምን ማድረግ ይችላል? ስንቱ ተቀጥቶ? ስንቱ ታስሮ? ስንቱ ከስራ ተባሮ ይቻላል? ሁሉም ጠ/ ሚር መሆን ነው ህልሙ። አቶ አዲሱ አረጋ ቢያገኙ አይጠሉም፤ ቢያንስ የ አቶ ፍጹም አረጋን ቦታ። 

አቶ ጃዋር መሃመድ ቢያገኝ አይጠላም፤ ፕ/ ህዝቃኤል ጋቢሳ ቢታደሉት ማለፊያ ነው የሚሉት፤ አቶ በቀለ ገርባም ገና ከ እስር ሲወጡ ያለሙት ነው፤ አቶደ አውድ ኢብሳ በትልቁ ወዘተ … ሁሉም የአብዩን ወንበር ተመኝቷል። ከዛ ደግሞ ሸዌ/ አሪሰ/ ወለጌ/ ይቀጥላል በዚህም አያበቃም ሮቤ፤ ድሬ፤ ደንቢ፤ ነቀምት፤ በቆጂ፤ አንቦ ይቀጥላል … መከራው ማቆሚያ የለውም።

ኦዴፓ ወደ ራሱ ተመልሶ ከህውከትም እጁን ሰብስቦ ጤነኛ መንፈሶችን በማቀረብ ቅብዕ ለተፈቀደለት ለአብይ ካቢኔ ቢተጋ ነገን ማሳመር ይችላል - ለራሱ ታሪክ። ቢያንስ ኦዴፓ ያሉ የሥልጣን ጥመኞች  ለኦሮሞ እናት ለማህበረ ታደሉ መከራ ይሰቡ። 

ይህቺን ዕድል ካስመለጣት መከራው ለኦሮሞ ህዝብ የከፋ ነው የሚሆነው። ምክንያቱም በግራ በቀኝ እሳት እዬነደደ እያዬን ነውና። ማን የቱ ወዴት እንደሆነ ግራ ነው። አቅጣጫ የለሽ ጉዞ ለ አንድ ቦታ ባለው ቀዝቃዛ ጦርነት ምክንያት። 

ግን ዶር ለማ መገርሳ ከዬትኛው ወገን ናቸው? ጨዋታውን ካነሳሁት ከስሜን አሜሪካ መልስ የጋብቻ ቀለብት አስረው አይቻለሁኝ እንኳን ደስ አለዎት ስላልኩኝ አሁን ልበል። ሌላ ያልገባኝ ግን የ ዓመቱ የደግ ሰው ሽልማት ላይ የጠ/ ሚር አብይ አህመድ ያህል ጥበቃ ሲደረግላቸው አይቻለሁኝ። ይህን መሰል በዶር ገዱ አንዳርጋቸው አላዬሁኝም። እስቲ  በአደብ ይታይ ይህ ሊንክ።

2010 በጎ ሰው ሽልማት ልዩ ተሸላሚ ክቡር አቶ ለማ መገርሳ አስደናቂ ንግግር


መሳሪያ ኦነግን ያስታጠቀው ማን ነው? ባዶ እጁን ሲገባ እኛ አይተናልና? መንግሥትም እዬነገረን ነው። አብዩ እናጠቃለን ተብሎ የታለመው ሴራ ሁሉ ዙሮ ተመልሶ „ኦሮሞ አገር መምራት አይችልም“ የሚለውን ዕድምታ ቢያበለጽገው እንጂ አያደበዝዘውም። እኛም ምዕራባውያን ያሉት ዕውነት ነበር ለካ እያልን ነው። እኔ ግልጽ እና ቀጥተኛ ሴት ነኝ። ሌላም ሃይማኖታዊ ጣጣም አለ ምእራባውያኑ አብዝተው የሚፈሩት ድርድር ፈጽሞ የማያደርጉበት። 
  
ብቻ ነገረ የኦሮሞ ኢንፓዬር እስመልክቶ የኢትዮጵያ መንግሥት ለዚህም ይመስላል የውስጥ ውጥረቱን ለማስታገስ በላይ በላይ ሹምት በሹመት የኦሮሞ ልጅ እንዲሆን የሚፈለግበት ምክንያትም ይህው ነው። 

የምናዬው ሌላው ኢትዮጵያዊው ሊሂቅ ወደ ኤኮኖሚ እና ማህበራዊ ዘርፍ ይገፋል ቁልፍ የፖለቲካ ቦታዎች ለኦሮምያ ብቻ ያ ካልተቻል ምክትሉ ወይም ቃል አቀባዩ ለኦሮሞ ይህ እያዬን ያለነው ሃቅ ነው። እና ማስተባበያው ለእኔ ከልብ ጠብ የማይል የጢባ ጢቦ ጨዋታ ነው። 

ይህን ያመጣው ሰፊው ቀውስ ፈጣሪው ጉዳይ ደግሞ ሚዛኑን ያጣ  የእውቅና ጉሮ ወሸባዬ ነው።  የቄሮ እንቅስቃሴ እዛው አንቦ አካባቢ ነው የነበረው፤ ሰላሌ፤ ምንጃር፤ ደብረብርሃን፤ ገብሬጉራቻ እንኳን አላዬንም። አርሲ ባሌ ወለጋ ሐረር ከፋም አልነበረም። ግንጫ ላይ ተነሳ በዛው አቅጣጫ ቀጠለ፤ መዋቅርም መሬት ላይ የነበረ መሪም አልነበረውም። ያነሳውም በሳቢያ ደረጃ የሚታይ የአዲስ አባባ የማስተር ፕላን ጉዳይ ነው፤ ዕውቅናው ግን ሰማይ ጣሪያ የነካ ነበር። ከፈረንሳይ አብዮት በላይ ነበር ግምት የተሰጠው። እብጠቱም መታበዩም ምንጩ ይህው ነው። 

በሌላ በኩል የአማራ የህልውና የማንነት ጥያቄ ምክንያታዊ የነበረ፤ በቅጡ የተደራጀ፤ መሰረታዊ ብሄራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጥያቄዎችን ያነሳ፤ ለእያንዳንዱን ብሄራዊ ችግሮችን ዕውቅናን በክብር አጎናጸፈ የሎሎችንም የመብት ጥያቄን የጨረ ምክንያታዊ ነበር። ታዳፍኖ እንዲቀር ነው የተደረገው። ተጋድሎው በከፋ ሁኔታ መስዋዕትነቱን ከፈለ። ተጋድሎው ለፍሬ አበቃ ግን ዕውቅናው ተነፈገ። ሚዛን ያልጠበቀው መከራ ያመጣው አንዱን ይህው ነው። 

አማራ ቅን ነው። የዋህ ህዝብ ነው። የቄሮ ንጉሶች እነ አቶ ጃዋር መሃመድ አጤ በሆኑበት መንበር ላይ የአማራ አብዮት እጬጌዎች፤ የጀግኖች ጀግኖች ዝቅ ብለው ጥያቄዎችን እንዲያቀርቡ ተደርጓል። ገናም ቀን የሚሰጠው፤ ቀን የሚያስከበረው ሃቅ ይፈልቃል። አሁን ሁሉም እዬመረረው፤ እዬጎመዘዘው ቢሆንም የዘራውን እያጨደ እዬከመረ ነው። የጣና ኬኛ ሞገድ መንፈስ ያሰገኘው ገድል በማን የመንፈስ ፈቀድ ስለመሆኑ እዬታወቀ ተጠቀጠቀ። አልፎ ተርፎ መከራን የተቀበሉ ዜጎች ተዘልፈውበታል።  
  • ·      ኔ ሳስበው።  

የመንፈስ ኩዴታ ከስሜን አሜሪካ መልስ ተከናውኗል። የቀደመውን አዲስ መንፈስ ከመፈንቅለ መንፈሱ ጋር አዋዶ ለመቀጠል መከረኛው ጠ/ ሚር ፍዳቸውን እዬከፈሉ ነው። አውጠተው ቢናገሩት በቅጽበት በቤተሰባቸው ላይ የሚሆነው ይሆናል። 

አታስታውሱንም ውዶቼ እርእስ አስይዤ ጽፌበታለሁኝ በሐምሌው ዝምታ ሰሞን አንድ አለም አቀፍ የሴቶች ጉባኤ አዲስ አባባ ተካሂዶ ደልዳዋ ቀዳማዊ እምቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው እኮ አልተገኙም፤ የተገኙት የቀድሞዋ እሳቸውም ደልዳላ ናቸው ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ ነበሩ ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት።

እኔን የሚገባኝ አሁን ያለውን መሪ መንፈስ ቀስ አድርጎ የመግፋት መሰናዶ እያተደረገ መሆኑን ነው። ለዚህም አንዱ የአቶ ደመቀ መኮነን ራስን የማግለል ምህንድስና የነበረው። ያ ከሽፏል፤ በሌላ ሁኔታ ምን አልባትም በከፋ ሁኔታ እሰኪገለሉ ድረስ ቀን እዬተጠበቀ ነው …. 

ቀጣዩ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ አልቻልኩም ብለው በፈቃዳቸው መልቀቅ ነው … የሚሊዬንም አዳራሽ የቅዱስ ዮሖንስ ዕድምታም ሌላ ነገር አይቻለሁኝ። በትዝብት ያልተደፈረበትን ምክንያት ብቻዬን አወጋግቼአለሁኝ። ሃቅን ውስብስብን ጥምልልም አድርጎ የያዘው አንድ ዕውነት አለ። ማስጠንቀቂያ በጥብቅ የተሰጠበት ሁኔታ። 

  • ጥምንምኑ ዕውነት።


ሰላማዊ ትግል የመረጠው ኦፌኮ እኮ ጊዜ አልፈጀበትም ከኦነግ ጋር ለስምምነት እጁን ሲዘረጋ፤ በአቀባበሉም ላይ የተገባው ዕውቅና አግኝቷል ኦፌኮ። ኦህዴድ የቀድመው ላቀረበው ጥሪም በጥንቃቄ ነበር ያለው ኦፌኮ ኦነግን ሲቀበል ግን በጥንቃቄ ሲል አልተደመጠም።

ኦህዴድን ያዬነው ነው አቶ ታዬ፤ አቶ አዲሱ፤ አክቲቢስት ገረሱ እንዲከደን የፈለጉትን ፍልስፍና ከልብ ሆነን ተከታትለናል። መድፈር አይችልም የአብይ ካቢኔ ኦዴፓን እራሱ። 

አሁን ማን ምን እንደሆን አይታወቅም። ማን ከማን ጋር እንደቆመ አይታወቅም። ደፍርሷል። እርግጥ ነው የጠ/ ሚር ቦታው እነሱ የፈቀዱት ሰው እስኪይዝላቸው ድረስ ከሳቸው እጅ እንዲወጣ አይፈልጉም። ያን ለማስተከካል ሌላ ትግል ስለሚጠይቅ። ለምሳሌ ወ/ሮ ሙፍርያት ቢይዙት ኖሮ ዳገት ይሆንባቸው ነበር። 

ጠ/ ሚር አብይ አህመድ የሚፈለጉት እንደ ማቆያ ነው። ይህ ቀን ጠብቁና ታዩታላችሁ። እንድ ጹሑፍ ጽፌያለሁኝ ገለጥ ለጥ ያለ "የልብ ህሊና በተከዘነው ሚስጢር ሲያወጋ" የሚል ይቆይ ብዬ ነው። መነሻዬ „የአብይ ካቢኔ የኦሮሞ ሥርዕዎ መንግሥት እያጠናከረ ነው“ የሚል ጹሑፍ ሳተናው ላይ ስላነበብበኩኝ እርእሱ ስላልተመቸኝ ነው አፍረጥርጬ መጻፍ ነው የፈልገኩት። እርእሱ የመፈንቅል መንፈስ ሃይሉ ተብሎ መስተካካል በሚል መጻፍ ስላለበት። ግን ይቆይ ብዬ እራሴው አስሬዋለሁኝ። 

እኔ መምራት አልቻልኩም ብለው ዶር አብይ አህመድ ቢለቁ ህውከቱ ሁሉ ተግ ይላል። ይህን በመስቀል እና በእሬቻ ባዕል ማዬት ችለናል። ትዕዛዝ ሰጪውን ማወቁ አይጠቅምም። ቁም ነገሩ ልብ ሰጥቶት ከልቡ ጋር መክሮ ይህን የሽግግር ጊዜ ላለማጥቆር ራሱን ቢያርም እና ኢጎውን ቢያስታግስ መልካም ነው። ሥም ከስብ ይሸታል እና። የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ አንድ ጊዜ ከተፋ አይመለሰም። 

  • ብልህነት። 

በተጨማሪ ለጠ/ ሚር ቢሮ እኔ እማሳስበው እንደ ሱማሌው አካሄድ ጋንቤላ ላይ የተዳፈነ ፈንጅ ስላለ አቶ አቦንግ ሜቶ እና አንድም ሊሂቅ /ዶር/ እንደታሰሩ አዳምጫለሁኝ እሳቸውን አስፈትቶ እንዲሁም አቶ ኦኬሎ አኳያን አክሎ አዲስ አመራር መፍጠር ቢቻል መልካም ነው። በዚህ ዙሪያ እርእስ ሰጥቼ ጽፌበታለሁኝ። ነባሮችን የጋንቤላ አመራሮች በቁም እስር በጥበቃ እስር ማቆዬት፤ 

አፋር ላይም ሌላ ፈንጅ ስላለ፤ ይህንንም አስቀድሜ ጽፌበታለሁኝ ለስላሳውን ዶር ኮንቴ ሙሳን እና ፍጹም ታታሪውን አቶ ገሃስ አህመድን ወደ ስልጣን ማምጣት እና ነባሮችን እንዲሁ በጥበቃ ሥር ማድረግ ይገባል። ሌላ ንደትም እዛ ዓይኑን አፍጥጦ እዬጠበቀ ስለሆነ። ይሄ የማስተባባያ ድሪቶ የትም አያደርስም። የሚፈይደውም ነገር የለም።

መንግሥት ናችሁ እና እንደ መንግሥት መሆን ግድ ይላል ያው አዲሱን አመራር ደግሞ ተፈጥሮ እስኪታይ ድረስ። በማህበራዊ ኑሮም አንድ ጉደለት እንዳይኖር ተብሎ ያዬነውን አይተናል። ህጋዊ መሰረት ለማስያዝ። ሰው መሪ ሲሆን የሚጠይቀው መስፈረትን በሚመለከት …. ዝምታ ቀለበት ይኑረው ብለን ነው ጭጭ ያልነው። 

እንዲያውም ማስተባባያው ሁሉም አልቆ እዛ ጥቅልል ብለው ወደ አገር የገቡትን ይሁን፤ ለውጥ እንመራለን የሚሉትን ሊሂቃኑን፤ የአብይን ካቢኔ በበላይነት የሚመራው ነገ በትረ መንግሥቱን እይዛለሁ ብሎ በ ግንባሩ ሊደፋ የሚጣደፈውም መንፈስም ቢሆን ሁሉንም ይዞ እንዳያሰምጥ እርምጃዎችን በተሎ በቶሎ ከሥር ከሥር መውሰድ ያስፈልጋል።

የሆነ ሆኖ አቶ ዳውድ ኢብሳ ለኤርትራ መንግሥትም ውለታ ስላለብኝ ዕውቅና ማሰጠት እፈልጋለሁኝም ባይ ናቸው። ይህን ግንቦት 7 ካናዳ ላይ በነበረው ስብሰባው ገልፆል። አቶ አውድ ኢብሳም ታዲያ ስለምን ይቅርባቸው?

በጣም እምደሰትብት የአማራ ታጠቂ ሃይሎች ከዚህ ትርምስ ራሳቸውን ማውጣታቸው ነው። የአማራ የተገለሉ የጦር መኮነንኖች ይሁኑ የተገለሉ የፖለቲካ ሊሂቃን፤ የተገለሉ ጋዜጠኞች፤ አክቲቢስቶች፤ ዕድሜያቸው ሳይደርስ ጡረታ የወጡት ሁሉ ወደ አገር የተመለሱ የአማራ ድርጅቶች፤ ሊሂቃን ከዚህ ሁሉ ንትርክ ውስጥ አለመሆናቸው ስከነታቸውን ዘመን እራሱ ይመስከረው። ትልቅ ነገር ነው።

ለውጡ መደገፍ ማለት ከእነዚህ ዓይነት የግል አሉታዊ ኢጎ ሱሰኝነት መውጣትም ማለት ነው። እዩኝ እዩኝ አይሉም። ድምጣቸውን አጥፈተው ተግባር ተኮር ትትርናቸውን ቀጥለዋል። 

ይህም ነው የአያት የቅድመ አያት ሌጋሲ ማስቀጠል ማለት ነው። ይህም ነው አገር ማበጀት ማለት። ይህም ነው የውሃ ልክነት ማለት፤ ይህም ነው ትውፊትን መጠበቅ የሃይማኖት ያህል ማተበኛ መሆን ማለት። ተመስገን!

ተደሞ ዕድምታ ቅኔ እንደ አቦው እና እመው። በዚህ ስክነት፤ በዚህ እርጋት፤ በዚህ ሥልጣኔ ልክ መጓዝ ለውጡን አቅም በፈቀደው ልክ መደገፍ፤ ነዋሪዎችን ዋስተናቸው እንዳይነጋ ሁሉም ዘብ መቆም፤ ህግ ማስጠበቅ ህግን ማክበር ይገባል።

ጉልህ የትርምሱ የቀዝቃዛው ጦርነት ፍልሚያ ያለው በኢትዮጵያ መንግሥት ጉልህ ዕውቅና ተሰጥቷቸው፤ በሚዲያውም በቂ አትኩሮት በተሰጣቸው ሁለት አካላት ማህል ነው። ሁለቱም ኤርትራ መንግሥት ጋር ቁርኝት የነበራቸው ናቸው። በዚህ መስክ የኤርትራ መንግሥት ሚናም ጉልህ ነው በማፍረስም ይሁን በመገንባትም። የአሁን ድርድር ይህው ነው። በርቀት የዶላራል አሞሌ የአረብ ኢምሬት አለ።

እኔ እንደሚረዳኝ ማስተባባያ አገር አያመራም፤ አገር የሚመራው በሃቅ ነው። እርግጥ ነው ግልጥ እንዳይሆኑ የሚፈለጉ ጉዳዮች ሊኖሩ ይችላሉ ለምሳሌ የሐምሌው ዝምታ። ያ ዝምታ እኮ ነው አሁን ከእውነት አገር ጋር እዬተፋገተ፤ እዬተሟገተ ያለው። እውነት ራሱ ማንነት አለውና።

በሌላ በኩል ግን ጎልተው በሚወጡ ጉዳዮች ላይ ዛሬ ማህበራዊ ሚዲያው አለ። የፈለገ ቢሸፋፈን፤ የፈለገ ቢታፈን ጭራው ከተገኜ ይራባል፤ ይሰፋል። ይህ ደግሞ የሉላዊ ዜጋው መብት ነው ህዝብን ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ እስካልወሰደ ድረስ።

እያንዳንዱ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ ጋዜጠኛ ነው። እያንዳንዱ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ ፎቶግራፈር ነው። ከዚህ ሂደት ጋር መጓዝ ግድ ይላል። ማጣጠሉ ምንም ጠቀሚ አይደለም። መከደኑም የሚበጅ አይደለም መሬት ላይ የበላይ የሆነው መንፈስ ማን እንደሆነ እዬታዬ ነው። የአብይ ንጹህ መንፈስ እዬተዳጠ ስለመሆኑ ለቀባሪው አረዱት ይሆናል። ይልቅ ገላጣውን ነገር መድፈሩ ነው የሚጠቅመው። 

የሆነ ሆኖ የጀርመኑ ጉዞ ሰንሰለቱን ይገልጠዋል። የአብይ መንፈስ አዳፍኖ እንዲይዘው የተፈለገው ፍንጩ ይገለጣል። የጉግሱ ሚስጢር ያለው ከዛ ጭብጥ ነው። አስሮ ማሰራት። አስሮ ማስመሰል።

የሰሞናቱም ሹም ሽር መሰናዶ ያው በዚያው ነው ሚስጢረ የሐምሌን ዝምታ ገለጥለጥ ያደርገዋል። ይብቃን ለዛሬው። እንደ ጎንደሮቹ „ልብ ያለው ሸብ“ ይሁን ብለናል። 

በቀጣዮቹ ጊዜያቶች አሁን ቤተ መንግሥትን እያሾረው ያለው፤ የበተ መንግሥት ጥመኛ መንፈስ ይታያል … ምን ሲያጣድፍ … ሹመት ያዳብርንም አስቀድመን መላክ ግን አስፈላጊ ይመስላል …

ልብ አለነ! ህሊናም አለን!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።