ልጥፎች

ከኦክቶበር 29, 2021 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የወሎ ፋኖ የመሪነት ቅብዕ ልቅና በልዕልና። የአማራን ህዝብ እምራለሁ ስትል ዲስፕሊኒን የመሸከም ብቃትህን አቅምህን ዕውቅ።

ምስል
አማራን እምራለሁ ብለህ ስትነሳ በምን አቅመህ ብሎ መጠዬቅ ይገባል። ይህን ጥያቄ መጠዬቃችን የተገባ የሚያደርገው የዚህ የወሎ ፋኖ የህሊና ልቅና በልዕልና ነው። ይህን የሚዲያውን አርቲ ቡርቲ፤ የኬክ ቆረሳ፤ የከረባት እና የገበርዲን እንድርቺ እንድርቺ የባጀብህን የኮሮጆ ውቂ ደብልቂ አስተውለህ እንዲህ ያለውን አንጀት አርስ ይትብኃል ስታደመጥ ህሊናህ ይፈወሳል። ገነትህ ከሰማይ ሳይሆን   ምድርም እንዳለ በተስፋ ትሰክናለህ። አልጠግበው አልኩኝ። ትንሽ ቦጨቅ ቦጨቅ እዬደረገ ለእንኮቶው ፖለቲከኛ ሁሉ ቢያድለው ተመኜሁኝ። ተጠምኖ ላገኜው ሚኒስተርነት እንድርቺ እንድርቺ ለሰነበተው ፌስተኛ ሁሉ ቢመርበት ተመኜሁ። ከዚህም ከዚያም በውዳሴ ከንቱ ተኮፍሶ ሲያምሰን ውሎ ለሚያደረው ዕብን ሁሉ ተቋም ነው። በቅናትም፤ በምቀኝነትም ትርምስምስ ሲተም ውሎ ለሚያድረውም። ኢትዮጵያዊነት እንዲያ አምሮበት ሲቀደስለት ድርሳኑ በሥህን - ሲዘከርለት በውስጥነት ሲከብር …. አዬ አማራዬ …. አብሮ ስለሚወድቀው፤ ደሙን ስለሚያፈወሰው እና ስለካህዲውም በሚዛናዊነት እንደምን እንደቀረበ ማስተዋሉና ችሎቱ ሚዛኑ በዚህ ደግሞ ቅና ማህብረ ከንቱ።