ልጥፎች

ከጁን 11, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#ተናፍቃችኋል። አቶ ኦባንግ ሜቶ የሰባዊ መብት ዓራት ዓይናማ ሞጋች። ዶር ኮንቴ ሙሳ ጭምት ፖለቲከኛ። ጋዜጠኛ ተመስገን ደስአለኝ ትጉህ ሞጋች ሃያሲ ጸሐፊ። ፖለቲከኛ አቶ ክንፋ አሰፋ አምደኛም።

  ለነፃነት ትግል ሊቀ - ትጉኃን የሆናችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ድምፃችሁ #ናፈቀኝ የት ይሆን   ያላችሁ? #ተናፍቃችኋል ።   • የመደመር መንግሥትን በግልባጩ ላንብበውን?   "ሥጋን እንጂ ነፍስን መግደል የማይችሉትን አትፍሯቸው።" (ማቴ ፲፡፳)   #ምዕራፍ ፲፱።   #እፍታ ።   መፈላለግ፤ መጠያዬቅ፤ መተሳሰብ ትውፊታችን ነው። ትውፊታችን ማስቀጠል ደግሞ ግዴታችን ነው። ለረጅም ጊዜ አቶ ኦባን ሜቶን አስመልክቶ ፌስቡኩኑም፤ ኤክስ አካውንቱንም ፈታትሼ የት ነህ የሚል ጥያቄ ሳቀርብ ነበር። ድምጹ ከለት ወደ ዕለት እዬራቀ ሲሄድም እንደ አንዲት ኢትዮጵያዊት እህት ሲጨንቀኝ ጭንቀቴን ተጋሩ ብዬ በፔጄ ላይ ስጽፍ ቆይቻለሁኝ። አሁን ከምርጫ በኋላ በአንድም በሌላም ላያቸው እችል ይሆን ብዬ አስቤ ነበር። ግን አላየኋቸውም። ስለሆነም በጸረ ህወሃት ትግል ትጉህ የነበሩ ወገኖቼን በጥልቀት አሰብኳቸው። #ቆጥረን ባንሰጥም።    1) አቶ ኦባንግ ሜቶ የሰባዊ መብት ዓራት ዓይናማ ሞጋች። 2) ዶር ኮንቴ ሙሳ ጭምት ፖለቲከኛ። 3) ጋዜጠኛ ተመስገን ደስአለኝ ትጉህ ሞጋች ሃያሲ ጸሐፊ። 4) ፖለቲከኛ አቶ ክንፋ አሰፋ አምደኛም።   አቤቱ አጤ "መደመር፤ የመደመር ትውልድ፤ የመደመር መንግሥት።" እነኝህን ሊቀ - ትጉኃን የአገር ልጆችን #ቀነሰ ወይንስ አከለ? አፋፋ ላይ አስቀመጠ ወይንስ አገተ? አጠነከረ ወይንስ #አቀበ ? አሰበለ ወይንስ አጠወለገ? የሚለውን አደባባይ ላይ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድን ልንጠይቃቸው፤ ልንሞግታቸው ይገባል ባይ ነኝ።    ጠቅላይ ሚኒስተሩም እንደ ቀደምት መሪወች "ላም እረኛ ምን አለ?" ብለው ጆሯቸውን ዘንበል አድርገው ሊያደምጡን፤ መልስም ሊሰጡን ይገ...

#ላይነት።

  #ላይነት ።   እንኳንም የምርጫ ሁነት ተጠናቀቀ። መታቀቡ #ሳንክ ላለመሆን ዝምታ የተፈቀደለት። ምርጫ ይገባል፤ ተመዝገቡ ዕድላችሁን አታፍሱ ሁሉም ነገር ከአገር ሉዓላዊነት በታች ስለሆነ። ምርጫችሁ ከተጠናቀቀ #ሙግቱን ይቀጥላል።   "ህግ ተላላፊወችን ጠላሁኝ።"   #ምዕራፍ ፲፱።   ከምኔው #ማሰር #ናፈቃችሁ ? የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆችን ስለምን ተጣድፋችሁ አሰራችሁ???? ከምኔው አማንያንን #ማዋከብ #ቀናችሁ ይሆን?    "ለታምረኛ ድንቅ ህዝብ? ምን ልካሰው?" ለተባለ ህዝብ #ሃዘን #አጭቶ #ስጋት መላክ ምን ይባል ይሆን?   #ኦዬ ።   በራስ የመተማመን አቅም ሲንጠራራ አይበጅም። ምን ታመጣላችሁን ያነግሳል። በራስ የመተማመን አቅም ሲወርድም አይበጅም። "ለማኝ ነን፤ ለማኝ ጥገኛ ነው። ጥገኛ ደግሞ ሉዓላዊነት የለውም። ደኃ ሉዓላዊ ሊሆን አይችልም" ወዘተ። ያስከትል እና ኩርምት ጭምትር ያለ ሥነ - ልቦናን ይፈጥራል። ሁለቱም ያልተመጣጠኑ፤ ልካቸውን ያልጠበቁ ናቸው። በልኩ መጥኖ ተግባራዊ ማድረግ የባለቤቱ ኃላፊነት ነው። #መሪ ሲኮን ደግሞ ከባተሌው ዜጋ ይለያል። የአመራሩ ተክለ - ሰውነት፤ በባህሬው ውስጣዊ ይዘት፤ በሥነ - ምግባሩ፤ በድርጊቱ፤ በሚያስተላልፋቸው መሪ ንግግሮች፤ የሰብዕና አገነባብ፤ የሞራል እና የኤቲክስ ልክ፤ የታክቲክ እና የስትራቴጅ ውል፤ የማደራጀት፤ የማቀናጀት የማዋህድ እና የማስተባበር አቅም ቲም ሊደርነት፤ በሚወስዳቸው እርምጃወች የመሪነት ጥራት ይጠይቃል። ብቃት ከተፈጥሮ - ከጸጋ - ከአስተዳደግ - ከተመክሮ ከህዝብ ዕምቅ ዕንቁ አቅም ይገኛል - ከተፈቀደ።    #ኦሆ መሪነት።   አደብ እና ----መሪነት? ...

#ጥምዶ ለህወሃት፤ ጥምዶ ለአማራ ፖለቲካ ይበጃልን? #በጥምዶ ተጠቃሚውስ ማን ይሆን?

ምስል
  #ጥምዶ ለህወሃት፤ ጥምዶ ለአማራ ፖለቲካ ይበጃልን? #በጥምዶ ተጠቃሚውስ ማን ይሆን?   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።      #ምዕራፍ ፲፱።   በጥምዶ ውስጥ የነፃ ዓውጪ ግንባሮች እንዳሉበት አዳምጫለሁኝ። አማራ ጨቁኖኛል ያለ የነፃ አውጪ ግንባር ሁሉ ህወሃትን ጨምሮ "አማራ #አልጨቆነኝም " ብሎ ይሆናል ከአማራ ጋር ሊሠራ የሚችለው።    ይህን ካሉ የነፃ አውጪ ግንባራት ሁሉ #ይፈርሳሉ ። ተደራጀን ያሉበትን ጭብጥ በካዱበት ቅጽበት ህልውናቸው ይጠናቀቃል። ይፈጠማሉ። ማናቸውም የነፃ ዓውጪ ግንባራት ህልውናቸው አይቀጥልም። ይህ ዕውነት የት #ይሸሸግ ? በየትኛው የማቆያ ሩምስ ይቀመጥ? የትስ ይደበቅ? ፋክት ነው። ፋክት ተሸሽቶ ስኬት የለም።   በሌላ በኩል የአማራ ፖለቲካ ሥረ - መሠረቱ፤ #ዘሃ ግራው የህወሃት ይሁን እሱ የፈጠራቸው የነፃ ዓውጪ ግንባሮች በደሉኝ ነው አይደል? ህወሃት ህገ - መንግሥት ሳያጸድቅም ጫካ እያለም፤ መንበረ ሥልጣን ላይ እያለም ጨክኖብኛል። ተበቅሎኛል ነው።    ይህ አልተፈጸመብኝም ብሎ የአማራ ፖለቲካ ከህወሃት እና ከፈጠራቸው ጋር አብሮ መሥራት ሲጀምር እስከ ዛሬ የተደከመበት፤ የተለፋበት ዘመንም፤ አቅም፤ መዋለ መንፈስም፤ ሰማዕትነትም ሁሉ አድራሻ ቢስ ይሆናል። ለቀጣይ ትግልም እርሾ አልቦሽ ነው የሚኮነው። ሂደቱም ውሳኔውም፤ አስደንጋጭ ነው።    "አለባብሰው ቢያርሱት በአረም ይመለሱ ነው።" ዕድሉን ደግሞ ቢገኝ የህወሃት በቀሉም የሚቻል አይሆንም። ህወሃት ከመንበረ ሥልጣኑን ማን እንደ ነቀለው፤ በኋላም ተስፋውን ማን እንዳሳረረው ጠንቅቆ ያውቃል። ህወሃት እኮ አዛውንት ድርጅት ነው። ልምዱም ተመክሮም አለው። ...