#ላይነት።
እንኳንም የምርጫ ሁነት ተጠናቀቀ። መታቀቡ #ሳንክ ላለመሆን ዝምታ የተፈቀደለት። ምርጫ ይገባል፤ ተመዝገቡ ዕድላችሁን አታፍሱ ሁሉም ነገር ከአገር ሉዓላዊነት በታች ስለሆነ። ምርጫችሁ ከተጠናቀቀ #ሙግቱን ይቀጥላል።
"ህግ ተላላፊወችን ጠላሁኝ።"
#ምዕራፍ ፲፱።
#ኦዬ።
በራስ የመተማመን አቅም ሲንጠራራ አይበጅም። ምን ታመጣላችሁን ያነግሳል።
በራስ የመተማመን አቅም ሲወርድም አይበጅም። "ለማኝ ነን፤ ለማኝ ጥገኛ ነው።
ጥገኛ ደግሞ ሉዓላዊነት የለውም። ደኃ ሉዓላዊ ሊሆን አይችልም" ወዘተ።
ያስከትል እና ኩርምት ጭምትር ያለ ሥነ - ልቦናን ይፈጥራል።
ሁለቱም ያልተመጣጠኑ፤ ልካቸውን ያልጠበቁ ናቸው። በልኩ መጥኖ ተግባራዊ
ማድረግ የባለቤቱ ኃላፊነት ነው። #መሪ ሲኮን ደግሞ ከባተሌው ዜጋ ይለያል።
የአመራሩ ተክለ - ሰውነት፤ በባህሬው ውስጣዊ ይዘት፤ በሥነ - ምግባሩ፤ በድርጊቱ፤ በሚያስተላልፋቸው
መሪ ንግግሮች፤ የሰብዕና አገነባብ፤ የሞራል እና የኤቲክስ ልክ፤ የታክቲክ እና የስትራቴጅ ውል፤
የማደራጀት፤ የማቀናጀት የማዋህድ እና የማስተባበር አቅም ቲም ሊደርነት፤ በሚወስዳቸው እርምጃወች የመሪነት ጥራት ይጠይቃል። ብቃት ከተፈጥሮ - ከጸጋ - ከአስተዳደግ - ከተመክሮ ከህዝብ ዕምቅ ዕንቁ አቅም ይገኛል - ከተፈቀደ።
#ኦሆ መሪነት።
አደብ እና ----መሪነት?
አቅል እና---- መሪነት?
አስተውሎት እና ----መሪነት?
አድማጭነት እና---- መሪነት?
ተጠያቂነት እና ----መሪነት?
ሁላዊነት እና ----መሪነት?
አቅርቦት እና--- መሪነት?
ዳኝነት እና ---መሪነት?
ታማኝነት እና ---መሪነት?
ትሁታዊነት እና ---መሪነት?
የንግግር ጥራት ጥንቁቁነት #ቁጥብነት እና መሪነት? መሪ ስሜቱን ገርቶ ከወቅት ገጠመኞች #አፈንግጦ ስንዴን መዝራት ሰብልንም ማፈስ ይገባዋል። መሪ ሁልጊዜ የሚናገር ከሆነ #አዘቦተኛ እና ከፖሊሲ የራቀ ይሆናል።
የመሪ ንግግር ተናፋቂ፤ አጭር፤ ግልጽ፤ ዲስፕሊንድ፤ ፖሊሲ አመንጪ መሆን ይኖርበታል። በየቀኑ አንድ መሪ የሚናገር ከሆነ ይሰለቻል ሞናትነስ ይሆናል፤ ፍሬዘሩም #ይራከሳል፤ ግድፈት ይበረክታል የሰማዩም የምድሩም ህግ መተላለፍ ሊያመጣ ይችላል።
በየለት ንግግር መፍትሄ አመንጪ ሳይሆን ችግር አመንጪ ይሆናል። ማይክራፎን ካሜራም እረፍት ይሻሉ።
በመሪነት ውስጥ ቢሮክራሲም ቁልፋ ጉዳይ ነው። የአጤው ወንበሩ ባዶውን ኤሉሄ ሊል አይገባም። በሌላ በኩል አጤ ወንበሩ የተቀማጭ ያለህ ብሎ አቤቱታ ሊያሰማ አይገባም። ቢሮክራሲ በስማ በለው ከሆነ #ህማማት ይሆናል ለአጤው ወንበር።
መሪ ከእኔ ከአልባሌዋ ሥርጉትሻ የአኗኗር፤ የአኳኋን፤ የራዕይ እና የግብ ፍላጎት ጋር የማይገናኝ ነው። መሪ እኮ #ላይነት። ከፈጣሪ በታች ማለት ነው። ይህም ላይነት ለአወንታዊ ይሁን ለአሉታዊው ቅብ'ው ከፈጣሪ ከአላህ ነው።
ድፍን ፰ዓመት በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ብቻ ይህን ያክል ዘመቻ???? ሌላው ደልቶት ስለምን ኦርቶተዋህዶ ትሳደዳለች? በአገሯ መሬት ስለምንስ #ተጠማኝ ትሆናለች??? ለምን? ይህን ያህል ጥቃት? ይህን ያክል የበቀል ክንውን አንድ የአገር መሪ እያለ፤ የዓለም ሎሬት የሆነ መሪ እያለ፤ የዓለም የሰላም አባት ተብሎ በግሎባል ደረጃ ዕውቅና የተሰጠው እያለ፤ የአገሪቱ የጦር፤ የደህንነት፤ የጸጥታ ሁሉ ጠቅላይ አዛዥ ሆኖ እያለ...
1) ያለመቻል፤
2) የአመራር አቅም የማጣት ሁነት?
3) ወይ ኢትዮጵያ ሌላ መሪ አላት ወይን?
4) መሪው ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ችግሩን አላመኑበትም? አ
5)ጠቅላ ሚኒስተሩ የድርጊቱ ተባባሪ ናቸው---- ን? ከ ፭ቱ አንዱን መሆን ግድ ይሆናል።
ለነገሩ የየክልሉን የፓርላማ እጩወች አየሁት ውክልና የፖለቲካ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ #ልሙጥ ነው። ሚዛኑን ያልጠበቀ ካቢኔ ነገን እንደምን ሊያስተዳድር፤ ሊመራ ይችል ይሆን? በዚህ የቀንድ፤ የአህጉር፤ የዓለም ውጥረት መከራ የበዛበት ምንዱብ በቃኝ ካለ ኢትዮጵያስ የሚለው መልስ ያጣል?
#በዓውጅ፤ በነጋሪት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማንያን አገር ልቀቁ ብሎ ማወጅ እኮ ይቻላል።
ብልጽግናወች ይህን ለማድረግ ባለመብት ናችሁ። 60% የሚሆነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተመችታችሁኛል ብሎ ተሰልፎ መርጧል። በመረጠው ልክ መወሰን መብት ያለው ደግሞ ብልጽግና ነው። ያ ቢደረግ የተሻለ ነው። በዚህ ልክ የህዝብ ቁጥር የመቀነስ ፕሮጀክት በአማራ ህዝብ እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በትጋት ሲከወን እንሆ ፰ ዓመታት እንደ ቀልድ አለፋ።
"ቤተ - እግዚአብሄር ቢቃጠል እንሠራዋለን ይባላል።" እንደዛ የሚል ሞቶ አይቻለሁኝ። እስከ አሁን የተደራጄ አካል ሻሸመኔ ሄዷልን፤ ሰምታችኋልን? የፈጣሪ ቤት በድፍረት ሲነድ፤ ሲቃጠል፤ ሲንቀለቀል በግፍ ጸሐይ ብርኃኗን ሳትነፍግ ስትቀር ሁሉ በኢትዮጵያ ይገርመኛል።
ቃጠሎ መንፈሱ፤ ትውፊቱ፤ ቀደምትነቱ አብሮ #ይቃጠላል። አድህኖ ስዕላት፤ ንዋዬ ቅድሳት አብረው ነደዋል፤ ጭሰዋል።
ዝዋይ፤ ሻሸመኔ፤ አጣዬ የቀደምቱን ጠረን ወዝና ለዛ ማምጣት ፈጽሞ አይቻልም። እንኳንስ የእግዜሩ ዓውደ ምህረት። ከቀደምትነቷ፤ ከሚስጢሯ ከኢትዮጵያዊነቷ ጋር ነው ትግሉ።
የኦርቶዶክስ ሰፊ ማህበራዊ መሠረት ባላቸው ክልሎች፤ ከተሞች ሁሉ የፓርላማ ውክልና፤ የመደበኛ የአመራር መዋቅር አሉታዊ #ዴሞግራፊ ላይ መሆናችሁ ጠበብትነት አይጠይቅም። አደባባይ የተሰጣ ሃቅ ነው።
የውጭ ጠላት ቢመጣ ከዚህ በላይ ምን ይፈጽማል? ኢትዮጵያ ነው እየነደደች፤ እየጋዬች እየተነቀለች ያለችው??? ለምንድን ነው ጠቅላይ ሚር አብይ ዝዋይ፤ ሻሸመኔ፤ አርሲ ሽርካ በአካል ተገኝተው ህዝቡን ማጽናናት የማይደፍሩት? ውላቸው ከፈጣሪ -----------ወይንስ??? ማን እንዳይከፋባቸው ይሆን የሌላ አገር መሪ ሆነው በርቀት ይህን የመሰለ የፍጅት ትዕይንት፤ የዕንባ ጎርፍ፤ የጥቃት ናዳ #በማዶ በዝምታ የሚያዩት???? ይህ አልበቃ ብሎ ደግሞ------------ እስር? ስንቱ-------- ይሰደድ? የትስ ----------ይሰደድ??
እርገት ይሁን።
ትግሉም፤ ስልቱም፤ ሙግቱም፤ አቤቱታው መንገዱም ጥበቡም ጠፍቶን አይደለም። በዚህ ውስብስብ ዓለም ዓቀፍ የቀውስ፤ የጦርነት፤ ተለዋዋጭ የኃይል አሰላለፍ ሁኔታ የኢትዮጵያ ህዝብ አገር፤ መንግስት ይገባዋል የሚል የተጠና፤ በተደሞ የታሰበበት፤ በጥሞና የተቀመረ አደባዊ መሻት ስላለ በሚሆነው ነገር ሁሉ እራስን በመቅጣት ዝምታ እንዲነግሥ ተፈቀደለት።
መሻትን ለማስፈጸም ምንም ዓይነት ስትራቴጂ አያስፈልግም። አንድ ቀንጣ ነፍስ ንጹህ ልብ፤ ቅን ሰብዕና በሱባኤ ጥንካሬ ያለው ከሆነ የሚሊዮኖች ድምጽ የመሆን አቅሙ የፈጣሪ ስጦታ ይሆናል።
ያ ሁሉ ----ሰቆቃ፤ ያ ሁሉ ------መነቀል፤ ያ ሁሉ---- ፍጅት፤ ያ ሁሉ ----ዕንባ፤ ያ ሁሉ ተስፋ ----ማጣት፤ ያ ሁሉ -----የአጽናኝ እጦት፤ ያ ሁሉ -----የመንፈስ ነቀላ እና ተከላ፤ ያ ሁሉ ሁለገብ ------ጥቃት ሰው ለሆነ ሁሉ መሸከም የማይችለው የፈተና ጋራ ነው። ይህም አልበቃ ብሎ ዛሬም ሞት፤ ዛሬም መፈናቀል፤ ዛሬም መንደድ ዛሬም ካ -----------ቴና----- ሲከር ይበጠሳል ሲሞላም ይፈሳል። በዛ በጣም። ከረፋም።
የሥርጉትሻ ቀና ቤተኞች እንዴት አደራችሁ? እንደምን አረፈዳችሁልኝ? እንዴትስ ዋላችሁልኝ። የእስሩን ዜና ሰምቻለሁኝ። ፎቶ ሾፕ ወይ AI ሊሆን ይችላል ብዬ ነው ጨምቼ የቆየሁት። ህወሃት መንበሩን ሥልጣኑን ያጣው እኮ በግፍ እስር፤ በግፍ የጭካኔ ግድያ፤ በግፍ የገብያ ቃጠሎ፤ የሴት ሊቃናት የተሳትፎ አለመኖር የኢትዮጵያ እናቶች ዕንባ ሊገታ ባለመቻሉ ነበር።
ያነን ያስቀጠለው አቤቱ ብልጽግናም አሻም ናፍቆት ይሆናል ከቀን ቀን፤ ከወራት ወራት በሰብዓዊ መብት ጥቃት ላይ አደበ ቢስ ሆነ። ችግርን ትተን ከፍ ብለን በረናል አዳኝ ሞቶ አይደለም።
ሰው ሰው ሰው ሰብአዊነት ሰብአዊነት ነፃነት የሃይማኖት፤ ነፃነት የሃሳብ ለኢትዮጵያ ቢያንሳት እንጂ የሚበዛባት ጉዳይ አይደለም። አልነበረምም። የእዮሩ ውሳኔ ከመጣ ይከብዳል። መክበድን መናፈቅ አለመታደል ነው። የልቡ የደረሰለት ብልጽግና ይህን ያክል መከራን ለማስቀጠል መትጋት???
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
11/06/026.
ፍቅር ሲያልቅ ትዕግሥት ይሰደዳል።
ትዕግሥትም ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ