ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ኢትዮጵያ #የጭቃ ምርጊት ወይንም ልስን አይደለችም። ኢትዮጵያ አፈጣጠሯ ይሁን ጸጋዋ #miracle ነው። የኢትዮጵያ ተክለ ማንነት #ከአዕምሮ በላይ ነው። #በመሰጠት የተሰጣት አገር። የምትመስጥም።

ኢትዮጵያ #የጭቃ ምርጊት ወይንም ልስን አይደለችም። ኢትዮጵያ አፈጣጠሯ ይሁን ጸጋዋ #miracle ነው።

የኢትዮጵያ ተክለ ማንነት #ከአዕምሮ በላይ ነው። #በመሰጠት የተሰጣት አገር። የምትመስጥም።
 
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
 
 May be an image of one or more people, people smiling and jewelry
#ምዕራፍ ፲፱።
 
ኢትዮጵያን አለማወቅ ብዙ ዋጋ አስከፍሏል። ወደፊትም ያስከፍላል።
ኢትዮጵያን አቅሎ ማየትም ፋንታዚው #ምራቅ ሆኖ እንዲቀር ትናንትም አድርጓል - ነገም።
ኢትዮጵያን #መተንበይ#መገመት፤ ማቀድ እና ግብ ማሳካት በእሷ ላይ እስተ ዛሬ አልተቻለም - ነገም።
ይመኟታል ሊገዟት፤ ሊጨቁኗት የተመኟት ግን ተሳክቶላቸው ትናንትም አያውቅም - ነገም።
ኢትዮጵያን ክዶም ይሁን በእሷ ላይ ደባ የሠራም አይበረክትም። #እርቃኑን ይቀራል።
 
ኢትዮጵያን ቱርኮች፤ ፖርቹጊዞች፤ ጣሊያኖች፤ እንግሊዞች ወጣ ገባ ቢሆንም ሌሎችም ተመኟት ግን ምኞቷታቸው አልተሳካም። መጨረሻ የውስጥ ኃይሎችን በመቅረብ፤ በመርዳት በማደራጀት የዞግ ፖለቲካን ከብክበው ቤተ - መንግሥት አስገቡ። ሌላም ሌላም ሁነት ተፈጠረ። ኢትዮጵያ ግን የአፍሪካ #አንከር ሆና፤ የዓለም ፬ኛ #ርዕሰ መዲና ሁና አለች። ዛሬ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ነገም ትኖራለች።
 
ፈላስፊት ኢትዮጵያ #የሚያኖራት ተመርቃ የተፈጠረችበት miracle ጸጋ አይደፈሬ አድርጓታል። ይህን የሚፈታ ቁልፍ ከማንም፤ ከየትም አይገኝም። ስለዚህም የየዘመኑ ሟርተኞች ያሰቡትን ትናንም አላሳኩም፤ ነገም አያሳኩም። ምንግዜም አይሳካም። "በፌድራሉ" እና በህወሃት ጦርነት በተካሄደ ጊዜ ከጥቂት አገሮች በስተቀር ብቻዋን ነበር ኢትዮጵያ የቆመችው። እንደ ታሰበው ተሳካ ወይ? እእ። 
 
ኢትዮጵያ የአንድ ጀንበር #ዳንቴል አይደለችም። ኢትዮጵያ ቀደምትነቷ ብቻ ሳይሆን በማንነቷ ውስጥ ያለ የማይነካ፤ የማይደፈርም ንጥረ ነገር ክብሯ፤ ማዕረጓ፤ ሞገሷ ተፈሪነቷም #ተደፋሪ አይደለም። ሙከራ ሊኖር ይችላል። ግን ለስኬት አይበቃም። እጃቸውን አራጠው የሚጠቁሙ ቢኖሩ ወዲያው ይሰበሰባሉ። ይህ በየዘመኑ በሚኖሩ የመንግሥት ሥርዓቶች ጥንካሬ ወይንም ብርታት ብቻ አይመስለኝም።
 
ኢትዮጵያ የማንነቷ አፈጣጠር ኦርጋኒክ ነው - ጥበብ ነው - ዊዝደምም ነው - ረቂቅም ነው - ኢትዮጵያ እንደ ጉልት ገብያ ወይንም እንደ ዘመናዊው ትልቅ ግሮሰሪ አቅም ያለው ሁሉ የሚሸምታት፤ የሚከዝናት፤ የሚያቀናት አገር አይደለችም። ይገርመኛል የመንግሥት ሚዲያወች ሳይቀር "ኑ አገራችን አብረን እንሥራ" የሚል #ቆባ ዕርስ ይዘው ሲወጡ። በኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ማንነት ነው እነሱን የፈጠራቸው፤ የሠራቸው። አሻቅበው ከሚናገሩ በልካቸው ቢሆኑ ጥሩ ነው። ጎንደሮች ባለቅኔወች ናቸው። ይህን መሰል ጉዳይ ሲገጥማቸው " ልክን ማወቅ ከልክ ያደርሳል" ይላሉ። 
 
ባለ ፋንታዚው እንጂ እንደ ሽንብራ ቂጣ የሚገለባበጥ። እናት አገር ኢትዮጵያማ በልኳ ደርበብ ብላ ተደላድላ ነው ያለችው፤ ሁለንትናዊቷ ኢትዮጵያ በተፈጠረችበት ልክ ሁሉንም ወጀበኛ የምትታዘበው። ታስቀናለች። ይቀኑባታልም። #ይመቀኟታልም። ኢትዮጵያ ከየትኛውም የሰብ አዕምሮም ይሁን ክህሎት አቅም በላይ ናት። 
 
የሚገርመኝ በእሷ ክብር ተገኝቶ፤ በእሷ ላይ ግርማ ታፍሶም ይዳፈሯታል። ግን ከሳት እንደገባ ፕላስቲክ ተሸብሽበው መጠጊያ ሲፈልጉ፤ ሲባዝኑም ይኖራሉ። 
 
ይገርመኛል አንዳንድ ጊዜ በቀን ተለክቶ፤ በወራት ተሰልቶ እንዲህም፤ እንዲያም ትሆናለች ሲባል። የማይቻል #አይቻልም። ሌላው ቀርቶ የህዝቧ ሥነ - ልቦናንም በቁሙ ማንበብ፤ በቁሙ መተርጎም፤ በቁሙ ማመሳጠር የሚቻል አይደለም። የተለየ ነገር አለን። በአገርም ቢኖር፤ ብንሰደድም። Miracle.
 
ህዝቧ በውስጡ፤ ከውስጡ ስክነትን የፈቀደ ነው። በዚህ ላይ ለሃይማኖት ያለው ውስጥነት ፈርኃ እግዚአብሔር፤ ፈራህ አላህ ሲታከል ከአዕምሮ በላይ ነው። የኢትዮጵያ ተክለ - ማንነቷ ከአዕምሮ በላይ ነው። በልኳ መሆን ያቃተው የፖለቲካ ሊቃናቶቿ ናቸው።
 
ኢትዮጵያዊ መሆን ከሚሰጠው ሐሤት በላይ ለእኔ የሚሆንልኝ ምንም ክስተት የለም። ተጠቅሜባት አይደለም። ግን የማንነቷ ግርማ እና ሞገስ በፈተናወቼ ሁሉ ሳስበው መጽናናትን ይልክልኛላ። እንኳንስ መኖሬ ማለፌንም ከዚህ ረቂቅ #መሰጠት ጋር ሳስበው ይጨንቀኛል።
ህሊናዊነት፤ ተደሟዊነት፤ አርምሟዊነት፤ ሱባያዊነት፤ ዱዋዊነት፤ ምህላዊነት፤ ጭምታዊነት፤ ብርክታዊነት፤ ሰዋዊነት፤ ዊዝደማዊት፤ ተፈጥሯዊነት፤ ሰዋዊነት፤ አህጉራዊነት፤ ሉዓላዊነት፤ ሰዋሰዊነት ሁሉም በልኩ ልኩን አግኝቶ ይመሳጠራል በኢትዮጵያኒዝም። 
 
ኢትዮጵያዊነት #አናባቢም ተነባቢም ነው ብዬ የፃፍኩት በ2013/14 ነበር።
 
ስንት ነፃ አውጪ ግንባር ተፈጠረ? ምን ያህል ጊዜስ ቆዬ? ኢትዮጵያ የምትከሰስበት ይሁን የምትወገዝበት ዘመናትስ ምን አተረፈ? ምንስ አከሰረ? የትኛው ለድል በቃ? የትኛውስ #ቁሞ ቀር ሆነ? ኢትዮጵያ ያለፈችበትን ዘመናት ምዕራፍ // በምዕራፍ ቢመረመር በአደብ ኢትዮጵ ማንም እንደ አሻው እንደ ሸክላ አፈር ጭቃ አብኩቶ ሊጋግራት የማይችል ስለመሆኑ ዕውነቱ ይነግረናል።
 
አጋጣሚ ተሳክቶ ሽርፍራፊ ፍላጎት ወይንም ምኞት ሊሳካ ይችል ይሆናል። በዘለቄታ ግን የማይሆን ነው። ኢትዮጵያ በጭቃ ምርጊት እንደ ተሰራ አንድ ዛኒጋባ ቤት ያሻው፤ ባሻው ሰዓት ነቃቅሎ #አበቃላት፤ ተደመደመ ሊላት የሚችላት አገር አይደለችም።
 
ትንግርቷ እናት አገር ኢትዮጵያ የትኛውም አገር ከየትኛውም አገር ጋር ይተባበር፤ የትኛውም ተቋም ከየትኛውም ተቋም ጋር ተዳብሎ ይሁን ተዋህዶ ይፈትናት ኢትዮጵያ ሁሉንም ዓውሎ፤ ወጀብ፤ ሱናሜ ተቋቁማ #ትቀጥላለች። ለምን? ኢትዮጵያ የአፈጣጠሯ ቁልፍ በማንም እጅ አይደለም እና። #Miracle.
 
ድካሙ የውርንጫ ድካም፤ ጥረቱም የእንቧይ ካብ፤ ተስፋውም በትነት ይወራረዳል። ምክንያት የሳይንቲስቷ ኢትዮጵያ አፈጣጠሯ እንዳትናድ ሆና የተፈጠረች አገር ናት። መዳጥም ይሁን መጨፍለቅ፤ መበወዝ ይሁን #ማስረክረክ አይቻልም።
 
ኢትዮጵያ ውሃ በቀጠነ ቁጥር #የምትፍረከረክ#የምትበረግግ#የምትንዘፈዘፍ አገር አይደለችም። ሁለመናዋ miracle ነው።
ማህበረ ቅንነት ቤተ - ሥርጉትሻ እንዴት ናችሁልኝ?
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
09/06/026.
 
ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነው።
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

ህሊናዊነት፤ ተደሟዊነት፤ አርምሟዊነት፤ ሱባያዊነት፤ ዱዋዊነት፤ ምህላዊነት፤ ጭምታዊነት፤ ብርክታዊነት፤ ሰዋዊነት፤ ዊዝደማዊት፤ ተፈጥሯዊነት፤ ሰዋዊነት፤ አህጉራዊነት፤ ሉዓላዊነት፤ ሰዋሰዊነት ሁሉም በልኩ ልኩን አግኝቶ ይመሳጠራል በኢትዮጵያኒዝም። ኢትዮጵያዊነት #አናባቢም ተነባቢም ነው ብዬ የፃፍኩት በ2013/14 ነበር።
ስንት ነፃ አውጪ ግንባር ተፈጠረ? ምን ያህል ጊዜስ ቆዬ? ኢትዮጵያ የምትከሰስበት ይሁን የምትወገዝበት ዘመናትስ ምን አተረፈ? ምንስ አከሰረ? የትኛው ለድል በቃ? የትኛውስ #ቁሞ ቀር ሆነ? ኢትዮጵያ ያለፈችበትን ዘመናት ምዕራፍ // በምዕራፍ ቢመረመር በአደብ ኢትዮጵ ማንም እንደ አሻው እንደ ሸክላ አፈር ጭቃ አብኩቶ ሊጋግራት የማይችል ስለመሆኑ ዕውነቱ ይነግረናል።
አጋጣሚ ተሳክቶ ሽርፍራፊ ፍላጎት ወይንም ምኞት ሊሳካ ይችል ይሆናል። በዘለቄታ ግን የማይሆን ነው። ኢትዮጵያ በጭቃ ምርጊት እንደ ተሰራ አንድ ዛኒጋባ ቤት ያሻው፤ ባሻው ሰዓት ነቃቅሎ #አበቃላት፤ ተደመደመ ሊላት የሚችላት አገር አይደለችም።
ትንግርቷ እናት አገር ኢትዮጵያ የትኛውም አገር ከየትኛውም አገር ጋር ይተባበር፤ የትኛውም ተቋም ከየትኛውም ተቋም ጋር ተዳብሎ ይሁን ተዋህዶ ይፈትናት ኢትዮጵያ ሁሉንም ዓውሎ፤ ወጀብ፤ ሱናሜ ተቋቁማ #ትቀጥላለች። ለምን? ኢትዮጵያ የአፈጣጠሯ ቁልፍ በማንም እጅ አይደለም እና። #Miracle.
ድካሙ የውርንጫ ድካም፤ ጥረቱም የእንቧይ ካብ፤ ተስፋውም በትነት ይወራረዳል። ምክንያት የሳይንቲስቷ ኢትዮጵያ አፈጣጠሯ እንዳትናድ ሆና የተፈጠረች አገር ናት። መዳጥም ይሁን መጨፍለቅ፤ መበወዝ ይሁን #ማስረክረክ አይቻልም።
ኢትዮጵያ ውሃ በቀጠነ ቁጥር #የምትፍረከረክ#የምትበረግግ#የምትንዘፈዘፍ አገር አይደለችም። ሁለመናዋ miracle ነው።
ማህበረ ቅንነት ቤተ - ሥርጉትሻ እንዴት ናችሁልኝ?
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
09/06/026.
ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነው።
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
See less

  • Reply
  • Hide
No insights to show
Ashenafi Hialu
‎ሰላም የሐገሬ ልጆች መልካም ቀና በጎ የደግነት ልብ ያላችሁ በተለይም ለመምህራን ክብር ያላችሁ በመምህር የተሻለ ቦታ የደረሳችሁ በተለይ በባህር ማዶ ያላችሁ ውድ ኢትዮጵያዊያን እንደ ሐገር አሁን ላይ…
See more

  • Reply
  • Hide

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።