ልጥፎች

ከሜይ 18, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#በአናርኪዝም ውስጥ ተስፋም፤ ሰላምም ሊበቅል አይችልም። #ኢትዮጵያኒዝም እና #ህወሃት።

  • #በአናርኪዝም ውስጥ ተስፋም፤ ሰላምም ሊበቅል አይችልም።   "ህግ ተላላፊወችን ጠላሁኝ።"   #ምዕራፍ ፲፱።   #ጠብታ ።   እንዴት ናችሁ ማህበረ ቅንነት? ደህና ናችሁ ወይ? እጅግ አድካሚው፤ እጅግ አሰልቺው፤ እጅግም ግትሩ የዞግ የፖለቲካ ድርጅት ህወሃትን ተሸክማ የኖረች ኢትዮጵያ መጥኔ ለእሷ፤ ለትግራይ እናቶችም መጥኔ።   #የማይደመጥ የለ።   ህወሃት እና #ጠማዳ ድርጊቱን እያዳመጥኩ፤ እያዬሁም ነበር ያደኩት። ስለሆነም አንዲት ደቂቃ ለህወሃት ብኰሩና አቅም አፍስሼ አላውቅም። ተሰቃይተን ነው ያደግነው። ከአጋም የተጠጋ ቁልቋል ዘወትር ሲያለቅስ ይኖራል እንዲሉ።   ሰሜን ጎንደር ሙሉ ዘመኑን በህወሃት በጋመ የበቀል ወላፈን ሲንገረገብ ኖሯል። ይህ በስማ በለው ሳይሆን ኖሬበት፤ ህይወቱን ያዬሁበት ነው። ለረጅም ዓመታት በምድር የሚታዩ በደሎችን ፈጽሞ፤ ያ ሳያረካው ሲቀር ቅዳሜ ገብያን በስልጣን ዘመኑ አነደደ።    የክልሉን ወሰን በማንአለብኝነት ጥሶም ሰብዕናን ተዳፈረ። የህወሃት መራራ ስንብቱ በኢትዮጵያ መንበረ መንግሥቱ የተፈጸመው #ሐምሌ ፭ ነበር። ያን መሰል አዋራጅ ጥቃት ተሸክሞ መዝለቅ አልቻልንም። መቻልም ልክ አለው። ትዕግሥት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል። ፍቅርም ሲያልቅ ትዕግሥት ይሰደዳል።    ህወሃት ቢያውቅበት ለትግራይ ቅርቡ ጎንደር ነው። ሁለመናው ውህድ ነው። ሁለመናው ፌክ ያልሆነ ተፈጥሯዊ ነው። ጋብቻው፤ የሃይማኖቱ ሂደት፤ የመማር ማስተማሩ፤ የሊቃውንታት የመኖር ጥበብ ልዩ ነበር። ጎንደሬ አብዛኛው ሥሙ የኋንስ ነው። ይህ ደግሞ ፈቅዶ እና ወዶ የሚፈጽመው የጎንደሬ ንጥር ዕውነቱ ነው።   ሌላው እቴጌ ትግራይ በከፋት ቁጥር የቅርብ የልብ ...