ማንዴላይዝም የጽናት የእርቅ እና የምህረት እሽታ ካሪክለም ነው።
ማንዴላይዝም የጽናት የእርቅ እና የምህረት እሽታ ካሪክለም ነው። • "ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌ ባለዕዳው አይቀበለውም" ሆነ እንጂ። #አገርኛ የመንፈስ ቴራፒ ነው። አገር የህይወት መንገድ ናት። ከቶስ #ሰው መሆናችን ያላግባባን ምን ያግባባን? " ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን። ክፋውን ነገር ተጸየፋት፤ ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ፤ በወንድማማች መዋደድ፤ እርስ በእርሳችሁ #ተዋደዱ ፤ እርስ በእርሳችሁ #ተከባበሩ ። ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ፤ በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ታገሱ፤ በጸሎት ጽኑ፤ ቅዱሳንን በሚያስፈልጋቸው እርዱ፤ #እንግዶችን ለመቀበል #ትጉ ። (ሮሜ ምዕራፍ ፲፪ ቁጥር ከ፱ - ፲፫።) ደቡብ አፍሪካ .... Religion in South Africa ... Religion in South Africa Wikipedia https://en.wikipedia.org › wiki › Relig... · "Religion in South Africa · Christianity (85.3%) · Traditional faiths (7.80%) · No religion (3.10%) · Islam (1.60%) · Hinduism (1.10%) · Others (1.10%)." #ምዕራፍ ፲፱። እኔ ከወንጌል ውስጥ የሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መልዕክታት ሁሉ ይመስጡኛል። ሮሜ ግን ይበልጥብኛል። ለመዝሙር የሚሆን ግጥምም ነበረኝ። የሆነ ሆኖ ዘመናችን ይቃኛል። ዛሬ ያለንበት ዘመን ከፊተኛው የፈተና ጊዜ ጋር እንደምን እንደሚገናኝ ያሳያል። የጎደለብንን፤ ያጎደልንበትን ሳስበው የሁሉም አሉታዊ መነሻ እና መድረሻ #የክፋ ሃሳብ ጽንት፤ ብቅለት፤ ስብለት ስለመሆኑ ያብራራልናል።...